Кабинет
Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ

Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ

Media - ሚዲያ

Юзернейм
@wanawmedia
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики2 497−1 за 1 день
Просмотров на пост, 7 дн.343за 7 дней
ERR13,74 %за 7 дней

Подписчики, 30 дней

28 нояб. – 29 нояб.−1 (0%)

Показать таблицей
ДатаПодписчики
28 нояб. 2026 г.2 498
29 нояб. 2026 г.2 497

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
5 нояб. 2026 г.861
11 нояб. 2026 г.787
22 нояб. 2026 г.555
26 нояб. 2026 г.237

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    ያለደረሰኝ ሽያጭ ማከናወን (መገበያየት) በህግ የተከለከለና በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ነው በዚህ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ማድረጉ ይበረታታል ይሁንና ግን በነዚህ የወንጀል ተግባር የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ህግ የሚያስከብር አካል ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ሲያውል የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ትናንት በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የተመለከትነው ካለደረሰኝ ሽያጭ ከማከናወን ጋር በተያያዘ በወላይታ ሶዶ አንድ የምግብ ቤት ባለቤትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተወሰደው እርምጃ ከፀጥታ አካላት ስነምግባር ያፈነገጠ እና የተጠርጣሪዋን ሰብዓዊ መብትና፣ክብር በጣሰ መልኩ የተፈፀመ በመሆኑ ሊታረም ይገባል ከስነምግባር ባፈነገጠ መልኩ እና የተጠርጣሪዋን መብትና፣ክብር በጣሰ መልኩ ግለሰቧን መሬት ለመሬት በመጎተት ተግባር የተሳተፉ አካላት ላይ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል በቀጣይ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈጸም በየጊዜው የስነ ምግባር ስልጠናዎችን መስጠት ተገቢ ነው ለግብር ከፋዩ የንግዱ ማህበረሰብ በየጊዜው ያለደረሰኝ ሽያጭ ማከናወን (መገበያየት) በህግ የተከለከለና በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ማስገንዘብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው በተለይም እራሱ ግብር ከፋዩ የንግዱ ማህበረሰብ ወንጀልን እንዲከላከል በየጊዜው የጋራ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በተጨማሪም በንግድ ተቋማቸው በማቅናት በማነቃቃት፣ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ያስፈልጋል ከዚህ ባለፈ ህግ የሚጥሱ ነጋዴዎች በአግባቡ በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉ ለነገ የሚባል አደለም ነገር ግን ሰብዓዊ መብትን ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ በነገራችን ላይ በወላይታ ሶዶ በርካታ ወንጀልን የመከላከል ስራዎች በጠንካራ ፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ተከናውነዋል ይህ ይበረታታል ግን አልፎ አልፎ እንደዚህ አይነት የስነ ምግባር ጥሰቶች ሲፈጸሙ ደግሞ የተሰሩ በርካታ ወንጀል የመከላከል ስራዎችን ጥላሸት የሚቀባ ነውና ጥንቃቄ ቢደረግ ጥሩ ነው በተረፈ ሁላችንም በየአካባቢያችን ወንጀልን በጋራ እንከላከል የህግ የበላይነትን እናክብር፣እናስከብር ታሪክ አዱኛ ሰላም ለሀገራችን ይሁን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 25/2/2019

    Фото
    Просмотры861
    Пересылки—
    Реакции1
    Комментарии—
  2. 02

    "ካቢኔ ያላየው ውሳኔ ማን ወሰነው? "ጠ/ሚ አብይ "መጀመርያ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር አክሰስ ያሳጣውን ውሳኔ ማን ወሰነው? ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔውን ዶክመንት ብናገላብጥ የለም።ካቢኔው አያውቀውም። አይ የለም ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብንወስን ምክር ቤቱ አልነበረም፣ ምክር ቤት አያውቀውም ውሳኔውን። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ እንዳይሆን እንዳይባል እኛም ነበርን…። የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነው፣ ተወካዮቹ ያላዩት ቢያንስ ቢያንስ ካስፈፀመው ካቢኔ ያላየው ውሳኔ ማን ወሰነው? ማጣትን የሚያክል ነገር፣ ያጣንበት መንገድ ህጋዊነት ችግር እንዳለው ማሳያ፣ ተቋሞች አልገቡበትም፣ ካቢኔው አያውቀውም። አንድ ገፅ ወረቀት ማግኘት አልቻልንም። እንዴት እንዳጣነው የሚያስረዳን፣ ህዝብም የማያውቀው፣ ፓርላማ የማያውቀው፣ ካቢኔው የማያውቀው የኢትዮጵያ የቀይ ባህር አክሰስ ውሳኔ የሚያሳጣ ነገር የወሰነው ማነው የሚል ጥያቄ ማንሳት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል? ካለ ይነገረን፤ከሌለ ግን ይሄን ውሃ አንስቶ፣ እንደመድፋት አይደለም፣ የህልውና ጉዳይ ነው፣ ማን ወሰነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ምክር ቤት ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

    Фото
    Просмотры787
    Пересылки—
    Реакции1
    Комментарии—
  3. 03

    እንደ ወሎ ዳቦ ! አስወድደኝ አቦ❤ ደሴ፣ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም (አሚኮ ደሴ) የወሎ ዳቦ ቤት መገኛው በደሴ ከተማ እምብርት አረብ ገንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ዳቦ ቤቱ ከተመሰረተ ከ85 ዓመት በላይ ኾኖታል፡፡ በኢጣሊያ ዳግም ወረራ ወቅት በሦስት ከተሞች ማለትም በደሴ፣በአዲስ አበባና በአስመራ ከተተከሉ ዘመናዊ የዳቦ ማሽኖች መካከል አንዱ ነው የወሎ ዳቦ መጋገሪያ ማሽን፡፡ የዳቦ ቤቱን አመሠራረት በተመለከተ ታላላቅ አባቶች እንደሚናገሩት በ3 ከተሞች የተተከለው የዳቦ መጋገሪነያ ማሽን ጣሊያኖች ለወታደሮቻቸውና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲኾን በማሰብ የመሰረቱት ነው ይላሉ፡፡ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀላሉዲን አብዱ በአንድ ወቅት እንደገለፁት በጣሊያኖች ባለቤትነት ይተዳደር የነበረውን ዳቦ ቤት አረቦች ገዝተውት እንደነበርና በኋላም በ1935 ዓ.ም አያታቸው ሸህ እንድሪስ ኢብራሂም እንደገዙት ገልፀዋል። "የወሎ ዳቦ ቤት የሚል ስያሜ የሠጡትም እሳቸው መኾናቸው ይነገራል። በጣዕሙ፣ በይዘቱና በአመራረት ሂደቱ የተለየው የወሎ ዳቦ፤ከደሴ ከተማ ህዝብ ጋር 8 አስርት ዓመታትን የተሻገረ ወዳጅነት አለው። በርግጥ ዛሬም ድረስ እስከ ተወዳጅነቱ ሕያው ኾኖ የቆየ ዳቦ ስለመኾኑ ብዙዎች ይመሠክራሉ፡፡ አቶ ከበደ ወ/ሩፋኤል፣ ውቢት ባህሩ፣ ሻምበል ሀሽም ጀማል፣ እና ም/ሳጅን መስፍን ንጋቱ የተባሉ ታዋቂ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀድሞው የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ወሎ ኤፍ ኤም 87.9 ጋር በወሎ ዳቦ ቤት ትዝታዎች ዙሪያ ቆይታ ነበራቸው። የወሎ ዳቦ ምርጥና ተፈላጊ፤ጣእሙ የማይለዋወጥ፤ መጠኑ የማይቀያየር በሁሉም የእድሜ ክፍል ያሉ የሚወዱት መኾኑን ምስክርነት ሰጥተው ነበር። ከ2 እስከ 3 ቀን ቢቆይ የማይበላሽ፤ ከተለያዪ የምግቦች አይነቶች ጋር አብሮ የሚቀርብ፤ ያለ ማባያ ብቻውን በፍቅር የሚበላ ነውም ይላሉ። ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ደሴ የሚመጡ እንግዶች ‹‹ከደሴ ስትመጣ የወሎ ዳቦ ይዘህልኝ ና›› ተብለው የሚወስዱት አይነት ዳቦ እንደነበር ነው የሚያስታውሱት የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡ ለዚያም ይመስላል እንደወሎ ዳቦ! አስወድደኝ አቦ! የሚል ስንኝ የተቋጠረለት። ዛሬም ቢኾን ከጣሊያንና ከፈረንሳይ የሚመጡ አንዳንድ የውጭ ዜጎች ስለማሽኑ ስለሚሰሙና ጣዕሙን ስለሚወዱት ወደ ታሪካዊው ወሎ ዳቦ ቤት ገብተው ፎቶ ይነሳሉ። ማሽኑ በ24 ሰአት እስከ 45 ኩንታል የመጋገር አቅም አለው፡፡ ነገር ግን ባለው የግብዓት አቅርቦት ችግር አሁን ላይ በቀን ማምረት በሚገባው ልክ እየሠራ አይደለም። በወሎ ዳቦ ቤት ከ50 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሠራተኞች እንዳሉ ይነገራል። ወሎ ዳቦ ቤት ሁሉም በእኩል መስተንግዶ በሠልፍ የሚስተናገድበት፤ በውስን ሠዓት ብቻ ምርቱ የሚጠናቀቅ የሁሉም ቤት የከተማዋ ምልክትም ጭምር ነው፡፡ የወሎ ዳቦን ለማግኘት ረዥም ሠልፍ መጠበቅ ግድ ነው። በተለይ በፆም ወቅት የእግረኛ መንገድ ሁሉ በደንበኞች ሲያጨናነቅ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ የዳቦ ቤቱ መጋገሪያ ማሽን የቆየና ልዩ በመኾኑ የመለዋወጫ እቃ እንደልብ ማግኘት አይቻልም። በቀደመው ጊዜ የማሽን ብልሽት ሲገጥም አስመራ ላይ ጣሊያኖች ስለነበሩ መለዋወጫ ይገኝ ስለነበር በቀላሉ ጥገና ይሰራ ነበር። በ10 ሣንቲም 3 ዳቦ የሚገዛበት ታሪካዊው ወሎ ዳቦ ቤት፤ 110 ግራም ዳቦ 25 ሣንቲም ይሸጥበት ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ የወሎ ዳቦ ዋጋ በብዙ እጥፍ ቢጨምርም በአመራረት ሂደቱም ታሪኩን እንደጠበቀ ቀጥሏል። ✍️ጀማል ይማም

    Фото
    Просмотры555
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры252
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#2326Фото

Открыть в Telegram
Просмотры555+4%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#2323Фото

"ካቢኔ ያላየው ውሳኔ ማን ወሰነው? "ጠ/ሚ አብይ "መጀመርያ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር አክሰስ ያሳጣውን ውሳኔ ማን ወሰነው? ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔውን ዶክመንት ብናገላብጥ የለም።ካቢኔው አያውቀውም። አይ የለም ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብንወስን ምክር ቤቱ አልነበረም፣ ምክር ቤት አያውቀውም ውሳኔውን። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ እንዳይሆን እንዳይባል እኛም ነበርን…። የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነው፣ ተወካዮቹ ያላዩት ቢያንስ ቢያንስ ካስፈፀመው ካቢኔ ያላየው ውሳኔ ማን ወሰነው? ማጣትን የሚያክል ነገር፣ ያጣንበት መንገድ ህጋዊነት ችግር እንዳለው ማሳያ፣ ተቋሞች አልገቡበትም፣ ካቢኔው አያውቀውም። አንድ ገፅ ወረቀት ማግኘት አልቻልንም። እንዴት እንዳጣነው የሚያስረዳን፣ ህዝብም የማያውቀው፣ ፓርላማ የማያውቀው፣ ካቢኔው የማያውቀው የኢትዮጵያ የቀይ ባህር አክሰስ ውሳኔ የሚያሳጣ ነገር የወሰነው ማነው የሚል ጥያቄ ማንሳት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል? ካለ ይነገረን፤ከሌለ ግን ይሄን ውሃ አንስቶ፣ እንደመድፋት አይደለም፣ የህልውና ጉዳይ ነው፣ ማን ወሰነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ምክር ቤት ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

Открыть в Telegram
Просмотры787+47%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#2320Фото

ያለደረሰኝ ሽያጭ ማከናወን (መገበያየት) በህግ የተከለከለና በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ነው በዚህ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ማድረጉ ይበረታታል ይሁንና ግን በነዚህ የወንጀል ተግባር የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ህግ የሚያስከብር አካል ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ሲያውል የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ትናንት በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የተመለከትነው ካለደረሰኝ ሽያጭ ከማከናወን ጋር በተያያዘ በወላይታ ሶዶ አንድ የምግብ ቤት ባለቤትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተወሰደው እርምጃ ከፀጥታ አካላት ስነምግባር ያፈነገጠ እና የተጠርጣሪዋን ሰብዓዊ መብትና፣ክብር በጣሰ መልኩ የተፈፀመ በመሆኑ ሊታረም ይገባል ከስነምግባር ባፈነገጠ መልኩ እና የተጠርጣሪዋን መብትና፣ክብር በጣሰ መልኩ ግለሰቧን መሬት ለመሬት በመጎተት ተግባር የተሳተፉ አካላት ላይ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል በቀጣይ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈጸም በየጊዜው የስነ ምግባር ስልጠናዎችን መስጠት ተገቢ ነው ለግብር ከፋዩ የንግዱ ማህበረሰብ በየጊዜው ያለደረሰኝ ሽያጭ ማከናወን (መገበያየት) በህግ የተከለከለና በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ማስገንዘብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው በተለይም እራሱ ግብር ከፋዩ የንግዱ ማህበረሰብ ወንጀልን እንዲከላከል በየጊዜው የጋራ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በተጨማሪም በንግድ ተቋማቸው በማቅናት በማነቃቃት፣ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ያስፈልጋል ከዚህ ባለፈ ህግ የሚጥሱ ነጋዴዎች በአግባቡ በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉ ለነገ የሚባል አደለም ነገር ግን ሰብዓዊ መብትን ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ በነገራችን ላይ በወላይታ ሶዶ በርካታ ወንጀልን የመከላከል ስራዎች በጠንካራ ፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ተከናውነዋል ይህ ይበረታታል ግን አልፎ አልፎ እንደዚህ አይነት የስነ ምግባር ጥሰቶች ሲፈጸሙ ደግሞ የተሰሩ በርካታ ወንጀል የመከላከል ስራዎችን ጥላሸት የሚቀባ ነውና ጥንቃቄ ቢደረግ ጥሩ ነው በተረፈ ሁላችንም በየአካባቢያችን ወንጀልን በጋራ እንከላከል የህግ የበላይነትን እናክብር፣እናስከብር ታሪክ አዱኛ ሰላም ለሀገራችን ይሁን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 25/2/2019

Открыть в Telegram
Просмотры861+61%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#2319Фото
Просмотры1 100+105%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#2316Фото
Просмотры1 450+171%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#2315Фото
Просмотры1 100+105%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#2314Фото
Просмотры1 340+150%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—

Все посты

Связи