👏 #ዶክተር_እጹብ_ስንታየሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው የሕክምና ዶክተሮች መካከል ዶክተር እጹብ ስንታየሁ 3.86 ከ4.00 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በሜዳሊያ ተመርቃለች። ዶክተር እጹብ የተማሪነት ጉዞዋን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቋ የልፋቷን ዋጋ ያገኘችበት እና ትልቅ ደስታ የተሰማት አጋጣሚ መሆኑን ገልጻለች። " 3.86 በሕይወቴ ትልቅ ትርጉም ፈጥሮ ሕይወት ለማዳን አዘጋጅቶኛል " ያለችው ዶክተር እጹብ፣ የትምህርት ጉዞዋ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተለያዩ ፈተናዎች የታጀበ ቢሆንም በዚያው ወቅት ብዙ ዕውቀትና ልምድ ማግኘት እንደቻለች ተናግራለች። " የሕክምና ሙያ የሰውን ሕይወት በማዳን ፣ በማከምና በማገልገል ላይ የተመሠረተ ነው " ያለች ሲሆን ከዚህ በኋላ ሕዝብን በማገልገልና የሀገርን አደራ በመወጣት ለሙያው ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች። Via Bahir Dar University @thikvahethiopia.paid
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 25 |
| 3 ч | 69 |
- Через 1 час25
- Всего сейчас69









