Кабинет
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

FDRE, Ministry of Labor and Skills Official Telegram Channel

Юзернейм
@fdre_mols
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики19 992
Просмотров на пост, 7 дн.1 600за 7 дней
ERR8,00 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
28 окт. 2026 г.10 500
1 нояб. 2026 г.9 150
3 нояб. 2026 г.9 380
8 нояб. 2026 г.6 550
26 нояб. 2026 г.1 600

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры10,5 тыс.
    Пересылки—
    Реакции56
    Комментарии—
  2. 02

    የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሂደትን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ፍትሐዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ የዘርፉን አሠራር ለማሻሻል፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍና ግልጽነትን ለማረጋገጥ በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ አሠራር መፍጠር ቁልፍ የትኩረት መስክ መሆኑ ተጠቁሟል። ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት አግኝተው ሕጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ዲጂታል አሠራሮችን ማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ የአሠራር መጓተትን ለመቀነስ፣ ተጠያቂነትን ለማሳደግና ዜጎች በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ በውይይቱ የጉዞ ወኪል ማህበራትና የቦርድ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

    Фото
    Просмотры9,38 тыс.
    Пересылки—
    Реакции76
    Комментарии—
  3. 03

    ‼️ ዜጎች በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል! ዜጎች በሐሰተኛ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል እንደሚያገናኙና ከሚኒስቴሩ ውክልና እንዳላቸው በመግለጽ ዜጎችን የሚያታልሉ ሕገወጥ አካላት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ተበራክተዋል። የሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሠራተኛ ስምሪት ዴስክ ኃላፊ አቶ በዛወርቅ ከተማ፣ በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስር ገፆች ዜጎችን ወደ ካናዳና ሌሎች ሀገራት ለሥራ እንልካለን በሚሉ አካላት ዜጎች ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረጉ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል። ኃላፊው እንዳስገነዘቡት፣ የሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎች በተለይም በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ የውጭ ሀገር የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀጥታ ከማመን ይልቅ የመረጃውን ትክክለኛነትና የሚያቀርበውን አካል ሕጋዊነት አስቀድመው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪቶች በሚኒስቴሩ ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ብቻ የሚከናወኑ መሆኑን ገልፀው ዜጎችም ከማንኛውም ኤጀንሲ ጋር ሂደቱን ከመጀመራቸው በፊት ሕጋዊ ፈቃድ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

    Фото
    Просмотры9,15 тыс.
    Пересылки—
    Реакции72
    Комментарии—
  4. 04

    የዜጎችን እርካታ የሚያሳድግ ቀልጣፋ የዲጂታል አገልግሎት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዜጎችን እርካታና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና አስተማማኝ የማድረግ ሥራውን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በሚኒስቴሩ የዲጂታል አገልግሎቶች መቆራረጥ ምክንያት የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና አገልግሎቶቹን በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ለመመለስ ከዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የአገልግሎቶቹ መቆራረጥ ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ማዘመን ሥራ ጋር ተያይዞ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል። የሥርዓቱ የማዘመን ሥራ በአብዛኛው ተጠናቆ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶች ወደ ሥራ መመለሳቸውም ተመላክቷል። ቀሪ የማዘመን ሥራዎችንም በአፋጣኝ በማጠናቀቅ ሁሉንም አገልግሎቶች ወደ ሥራ ለማስገባት በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ቀሪ የማዘመን ሥራዎች በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁና አገልግሎቶቹም በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ሚኒስቴሩ በዲጂታል መንገድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የበለጠ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

    Фото
    Просмотры6,55 тыс.
    Пересылки—
    Реакции68
    Комментарии—

Новые посты

#487Фото

የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፎርሙ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እዳ ጫና መቀነስ እና ጤናማ ማድረግ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በሪፎርሙ የኢትዮጵያን የእዳ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ዝቅ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተዋል። በዚህም ከታቀደው ጊዜ ቀድሞ የኢትዮጵያ እዳ ሁኔታ ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱንና ይህም የሪፎርሙ ትልቅ ስኬት መሆኑን አመልክተዋል። የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እና ተቋማት ከብክነት ወጥተው ወደ ትርፋማነት መሸጋገራቸው ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል።ENA

Открыть в Telegram
Просмотры1 600−78%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#486Фото

የዜጎችን እርካታ የሚያሳድግ ቀልጣፋ የዲጂታል አገልግሎት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዜጎችን እርካታና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና አስተማማኝ የማድረግ ሥራውን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በሚኒስቴሩ የዲጂታል አገልግሎቶች መቆራረጥ ምክንያት የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና አገልግሎቶቹን በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ለመመለስ ከዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የአገልግሎቶቹ መቆራረጥ ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ማዘመን ሥራ ጋር ተያይዞ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል። የሥርዓቱ የማዘመን ሥራ በአብዛኛው ተጠናቆ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶች ወደ ሥራ መመለሳቸውም ተመላክቷል። ቀሪ የማዘመን ሥራዎችንም በአፋጣኝ በማጠናቀቅ ሁሉንም አገልግሎቶች ወደ ሥራ ለማስገባት በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ቀሪ የማዘመን ሥራዎች በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁና አገልግሎቶቹም በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ሚኒስቴሩ በዲጂታል መንገድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የበለጠ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры6 550−12%к среднему
Пересылки—
Реакции68
Комментарии—
#485Фото

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሂደትን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ፍትሐዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ የዘርፉን አሠራር ለማሻሻል፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍና ግልጽነትን ለማረጋገጥ በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ አሠራር መፍጠር ቁልፍ የትኩረት መስክ መሆኑ ተጠቁሟል። ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት አግኝተው ሕጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ዲጂታል አሠራሮችን ማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ የአሠራር መጓተትን ለመቀነስ፣ ተጠያቂነትን ለማሳደግና ዜጎች በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ በውይይቱ የጉዞ ወኪል ማህበራትና የቦርድ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры9 380+26%к среднему
Пересылки—
Реакции76
Комментарии—
#484Фото

‼️ ዜጎች በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል! ዜጎች በሐሰተኛ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል እንደሚያገናኙና ከሚኒስቴሩ ውክልና እንዳላቸው በመግለጽ ዜጎችን የሚያታልሉ ሕገወጥ አካላት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ተበራክተዋል። የሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሠራተኛ ስምሪት ዴስክ ኃላፊ አቶ በዛወርቅ ከተማ፣ በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስር ገፆች ዜጎችን ወደ ካናዳና ሌሎች ሀገራት ለሥራ እንልካለን በሚሉ አካላት ዜጎች ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረጉ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል። ኃላፊው እንዳስገነዘቡት፣ የሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎች በተለይም በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ የውጭ ሀገር የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀጥታ ከማመን ይልቅ የመረጃውን ትክክለኛነትና የሚያቀርበውን አካል ሕጋዊነት አስቀድመው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪቶች በሚኒስቴሩ ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ብቻ የሚከናወኑ መሆኑን ገልፀው ዜጎችም ከማንኛውም ኤጀንሲ ጋር ሂደቱን ከመጀመራቸው በፊት ሕጋዊ ፈቃድ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры9 150+23%к среднему
Пересылки—
Реакции72
Комментарии—
#483Фото

በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችሮችንለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  ከሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ፣ የዜጎችን እንግልት ከመቀነስና  ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ የሚነሱ ጥያቄዎች በዝርዝር ተመልክተዋል። በዘርፉ አሰራሮችን ለማዘመን የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም ማሻሻያ በሕግና በመመሪያ መሠረት መፈጸምና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ ተጠቁሟል። ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አስገንዝበው፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአሰራር ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ገልፀዋል። ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры10 500+41%к среднему
Пересылки—
Реакции56
Комментарии—
#481Фото

የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ ተጠቆመ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ላይ ተወያየ። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሚድ ዱላ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት በመሆኑ፣ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት ከ38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቀው በተያዘው በጀት ዓመትም ከ40 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት መታቀዱን አብራርተዋል። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ አስመልክቶ በተካሄደው በውይይት የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅሞችን በአግባቡ ለመጠቀምና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። ዘገባው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры10 700+44%к среднему
Пересылки—
Реакции49
Комментарии—
#480Фото

የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጋራ ኃላፊነትና የተቀናጀ አሠራር ያስፈልጋል ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትን የጋራ ርብርብን የሚጠይቅ ሀገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው የሥራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን የሥራ ተሳትፎ ከማሳደግና የሰው ኃይልን አቅም ከመጠቀም ባለፈ፣ የሀገራዊ ምርታማነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ዘርፉ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደር መካከል የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸምና የጋራ ተጠያቂነት መኖር እንደሚገባ አመልክተዋል። የዘርፉ አመራሮች በመድረኩ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በግልጽነት በመገምገም፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥና ለታዩ ክፍተቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማስፈጸም እንደሚሠሩ ይጠበቃል። በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры10 400+40%к среднему
Пересылки—
Реакции37
Комментарии—
#479Фото

የሠራተኞችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ የኮንፌዴሬሽኑ ሚና ወሳኝ ነው — ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ኮንፌዴሬሽኑ ባለፉት ዓመታት የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ሥራዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኮንፌዴሬሽኑ የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነትን በማስጠበቅ፣ የሠራተኛና የአሠሪ ግንኙነትን በማጠናከር እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሰላምን በማስፈን ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት ኮንፌዴሬሽኑን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እንደሚሠራም አመልክተዋል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ካሳሁን ፎሎን ጨምሮ የኮንፌዴሬሽኑ አመራሮች ተሳትፈዋል። ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!

Открыть в Telegram
Просмотры10 000+34%к среднему
Пересылки—
Реакции41
Комментарии—
#478Фото
Просмотры12 300+65%к среднему
Пересылки—
Реакции52
Комментарии—

Все посты

Связи