የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፎርሙ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እዳ ጫና መቀነስ እና ጤናማ ማድረግ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በሪፎርሙ የኢትዮጵያን የእዳ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ዝቅ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተዋል። በዚህም ከታቀደው ጊዜ ቀድሞ የኢትዮጵያ እዳ ሁኔታ ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱንና ይህም የሪፎርሙ ትልቅ ስኬት መሆኑን አመልክተዋል። የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እና ተቋማት ከብክነት ወጥተው ወደ ትርፋማነት መሸጋገራቸው ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል።ENA
Открыть в TelegramПосты канала Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የዜጎችን እርካታ የሚያሳድግ ቀልጣፋ የዲጂታል አገልግሎት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዜጎችን እርካታና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና አስተማማኝ የማድረግ ሥራውን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በሚኒስቴሩ የዲጂታል አገልግሎቶች መቆራረጥ ምክንያት የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና አገልግሎቶቹን በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ለመመለስ ከዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የአገልግሎቶቹ መቆራረጥ ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ማዘመን ሥራ ጋር ተያይዞ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል። የሥርዓቱ የማዘመን ሥራ በአብዛኛው ተጠናቆ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶች ወደ ሥራ መመለሳቸውም ተመላክቷል። ቀሪ የማዘመን ሥራዎችንም በአፋጣኝ በማጠናቀቅ ሁሉንም አገልግሎቶች ወደ ሥራ ለማስገባት በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ቀሪ የማዘመን ሥራዎች በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁና አገልግሎቶቹም በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ሚኒስቴሩ በዲጂታል መንገድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የበለጠ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramየውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሂደትን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ፍትሐዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ የዘርፉን አሠራር ለማሻሻል፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍና ግልጽነትን ለማረጋገጥ በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ አሠራር መፍጠር ቁልፍ የትኩረት መስክ መሆኑ ተጠቁሟል። ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት አግኝተው ሕጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ዲጂታል አሠራሮችን ማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ የአሠራር መጓተትን ለመቀነስ፣ ተጠያቂነትን ለማሳደግና ዜጎች በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ በውይይቱ የጉዞ ወኪል ማህበራትና የቦርድ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegram‼️ ዜጎች በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል! ዜጎች በሐሰተኛ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል እንደሚያገናኙና ከሚኒስቴሩ ውክልና እንዳላቸው በመግለጽ ዜጎችን የሚያታልሉ ሕገወጥ አካላት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ተበራክተዋል። የሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሠራተኛ ስምሪት ዴስክ ኃላፊ አቶ በዛወርቅ ከተማ፣ በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስር ገፆች ዜጎችን ወደ ካናዳና ሌሎች ሀገራት ለሥራ እንልካለን በሚሉ አካላት ዜጎች ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረጉ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል። ኃላፊው እንዳስገነዘቡት፣ የሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎች በተለይም በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ የውጭ ሀገር የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀጥታ ከማመን ይልቅ የመረጃውን ትክክለኛነትና የሚያቀርበውን አካል ሕጋዊነት አስቀድመው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪቶች በሚኒስቴሩ ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ብቻ የሚከናወኑ መሆኑን ገልፀው ዜጎችም ከማንኛውም ኤጀንሲ ጋር ሂደቱን ከመጀመራቸው በፊት ሕጋዊ ፈቃድ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramበዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችሮችንለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ፣ የዜጎችን እንግልት ከመቀነስና ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ የሚነሱ ጥያቄዎች በዝርዝር ተመልክተዋል። በዘርፉ አሰራሮችን ለማዘመን የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም ማሻሻያ በሕግና በመመሪያ መሠረት መፈጸምና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ ተጠቁሟል። ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አስገንዝበው፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአሰራር ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ገልፀዋል። ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramእንኳን ለ119ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! መከላከያ ሠራዊታችን የሀገር ደኅንነት ጋሻ፣ የሕዝብ ኩራትና የሰላም ተስፋ ነው!
Открыть в Telegramየወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ ተጠቆመ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ላይ ተወያየ። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሚድ ዱላ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት በመሆኑ፣ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት ከ38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቀው በተያዘው በጀት ዓመትም ከ40 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት መታቀዱን አብራርተዋል። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ አስመልክቶ በተካሄደው በውይይት የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅሞችን በአግባቡ ለመጠቀምና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። ዘገባው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramየሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጋራ ኃላፊነትና የተቀናጀ አሠራር ያስፈልጋል ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትን የጋራ ርብርብን የሚጠይቅ ሀገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው የሥራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን የሥራ ተሳትፎ ከማሳደግና የሰው ኃይልን አቅም ከመጠቀም ባለፈ፣ የሀገራዊ ምርታማነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ዘርፉ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደር መካከል የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸምና የጋራ ተጠያቂነት መኖር እንደሚገባ አመልክተዋል። የዘርፉ አመራሮች በመድረኩ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በግልጽነት በመገምገም፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥና ለታዩ ክፍተቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማስፈጸም እንደሚሠሩ ይጠበቃል። በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramየሠራተኞችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ የኮንፌዴሬሽኑ ሚና ወሳኝ ነው — ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ኮንፌዴሬሽኑ ባለፉት ዓመታት የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ሥራዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኮንፌዴሬሽኑ የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነትን በማስጠበቅ፣ የሠራተኛና የአሠሪ ግንኙነትን በማጠናከር እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሰላምን በማስፈን ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት ኮንፌዴሬሽኑን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እንደሚሠራም አመልክተዋል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ካሳሁን ፎሎን ጨምሮ የኮንፌዴሬሽኑ አመራሮች ተሳትፈዋል። ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽ/ቤትንና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ እንቅስቃሴን ጎበኙ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽ/ቤትንና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የዘርፉን አጠቃላይ ሥራዎች በመመልከት ለዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይበልጥ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ ከተካሄደው ውይይት በኋላ የተከናወነ ነው። በጉብኝቱ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የሁለቱን ቢሮዎች የሥራ እንቅስቃሴ፣ የአፈጻጸም ሂደትና ከተልዕኮዎቻቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በአካል ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramየዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የዜጎችን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማሳደግ ተቋማዊ የመፈጸም አቅም ማጠናከር፣ የአሠራር ጥራትን ማሻሻልና የአፈጻጸም ክፍተቶችን መፍታት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ። ክብርት ሰላማዊት ይህን የገለጹት ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮች ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎችና ዴስክ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተወያዩበት መድረክ ላይ ነው። በውይይቱ በዘርፉ እስካሁን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ቀርበዋል፡፡ ክብርት ሰላማዊት፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ የመንግሥት ዋና ትኩረት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህን ግብ ለማሳካት ተቋሚ የመፈጸም አቅምና የአሠራር ጥራት ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዘርፉ ያሉ ጥንካሬዎችን በመለየት ጥሩ አፈጻጸሞችን ማጠናከርና ማስቀጠል፣ እንዲሁም ያሉ ክፍተቶችንና ማነቆዎችን ከመሠረታቸው በመፍታት ውጤታማና ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramበዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚኒስትር ዴዔታዎች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት 1. ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት 2. ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እና 3.ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሹመዋልአሕመድ መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ! #የመደመርመንግሥት
Открыть в Telegramየተገኙ ውጤቶችን አልቆ ማስቀጠል፣ ውስንነቶችን ማረምና ዘርፉን ወደተሻለ ውጤት ማሸጋገር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ክቡር አቶ አወሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቀድሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአዲሱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር አቶ አወሉ አብዲ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡ በሥራ ርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባለፉት አምስት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው፣ በመደመር እሳቤ መሠረት በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን አልቆ ማስቀጠል፣ ያሉ ውስንነቶችን ማረምና ዘርፉን ወደተሻለ ውጤት ማሸጋገር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀገራዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ሚና ያለው ተቋም መሆኑን የገለፁት ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በ2050 እውን ልታደርገው ያቀስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት የአንበሳ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ የሰው ኃይል የሁሉም የልማት ዘርፎች መሠረት መሆኑን አመላክተው፣ የዘርፎች ውጤታማነት እንዲጨምር የሰው ኃይልን በአግባቡ መምራት፣ ከሥራ ገበያው ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ክህሎት ማልማትና ግልጽና ፍትሃዊ የሥራ ስምሪት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሂደቶች በግልጽነት እንደሚተገበሩ ገልጸው፣ እሴት የሚፈጥሩ ቴክኖሎጂዎችን ማልማትና ያሉትን ቴክኖሎጂዎች በተሻለ መንገድ መጠቀም ለሀገራዊ የግብ ስኬት መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ውጤታማ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለማረጋገጥ ትኩረት እንደሚሰጥም ነው ክቡር ሚኒስትሩ የገለፁት። በይፋዊ የሥራ ርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ክቡር ሚኒስትሩ ከቀረበላቸው ገለፃ በተጨማሪ ተቋሙን ተዘዋውረው ጎብንተዋል፡፡ መስከረም 30/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር!
Открыть в Telegramክቡር አቶ አወሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት ክቡር አቶ አወሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ትናንት በሙሉ ድምፅ ማጽደቁ ይታወሳል። ረቂቅ አዋጁም አዋጅ ቁጥር 1440/2019 ዓ.ም. ሆኖ ጸድቋል። ክቡር አቶ አወሉ አብዲ በአዲሱ የኃላፊነት ዘመናቸው ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን። #የመደመርመንግሥት
Открыть в Telegramመልካም የሥራ ዘመን! ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን እንደ አዲስ ከማቋቋም ጀምሮ የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች በመቅረጽና በመምራት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ዘርፍ ክህሎት የተላበሱ፣ ብቁና ተወዳዳዳሪ ዜጎች ማፍሪያ ብሎም የዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት ምስጋናችን የላቀ ነው። በመደመር መንግሥት ምስረታ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው በመሰየምዎ የተሰማንን ደስታ እየገለጽን፤ አዲሱ የሥራ ኃላፊነት ዘመንዎ እጅግ ስኬታማ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Открыть в Telegramጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
Открыть в Telegram