እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሰለም በጤና አደረሳችሁ። ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ሲሆን “ጾመ ነቢያት›› የተባለበት ምክንያት ነቢያት ስለጾሙት ነው፡፡ ‹‹ነቢያት የጾሙት ስለምንድን ነው?›› ቢሉ ለአዳም የተሰጠውን ‹‹ዐምስት ሺህ ዐምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ›› የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፣ ከድንግል ማርያም ይወለዳል፣ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነጻ ያወጣዋል ብለው ነው፡፡ ‹‹ይህንን ጾም የትኞቹ ነቢያት ናቸው የጾሙት?›› ቢሉ ሊቀ ነቢያት ሙሴ 40 ቀን ጾሟል፡፡ ዘፀአ 34 ፥ 27 ነቢዩ ኤልያስም 40 ቀን ጾሟል፡፡ 1ኛ ነገ 19 ፥ 1 በተጨማሪም በተለያየ ዘመን የነበሩት ነቢዩ ዕዝራ፣ ነቢዩ ነህምያ፣ ነቢዩ ዳንኤል እንዲሁም ክቡር ዳዊት ጾመዋል፡፡ ‹‹ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል›› ብለው ከጾሙ፤ ክርስቶስ እርሱ ከሰማይ ወርዶ፣ ከድንግል ተወልዶ በመስቀል ተሰቅሎ ካዳነን በኋላ እኛ የሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ስለምን የነቢያትን ጾም እንጾማለን? ቢሉ እኛ የነቢያትን ጾም የምንጾመው እንደ ቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያልን ሳይሆን የቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያሉ የጾሙትን በማሰብ በመጾማችን ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ፣ በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ እንድናገኝበት ነው፡፡ ጾመ ነቢያት ከኅዳር 15 ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 29 ቀን (በዘመነ ዮሐንስ እስከ ታኅሣሥ 28 ቀን) ድረስ ለ44ቀናት (በዘመነ ዮሐንስ ለ43 ቀናት) ይጾማል፡፡ ከእነዚህም መካከል40 ቀናት ጾመ ነቢያት፣ 3 ቀናት ጾመ አብርሃም ሶርያዊ ሲሆኑ የቀረው 1 ቀን ደግሞ የገሃድ ጾም ነው (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 585፣ 586 ) ጾመ ነቢያትን ከኅዳር 15 ጀምሮ ሳይጾሙ የልደትን ዋዜማ ብቻ መጾም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አይደለም ፡፡ መልካም ጾምን ጾመን ብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና ለማክበር ያብቃን ።
Открыть в Telegram
"ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
@Dan12bot ለአስተያየትዎ ይህን ይጠቀሙ እናመሠግናለን
Новые посты
“ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” (ማቴ.26፡15)፡፡ ይሁዳ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! ክርስቶስ ያስተማረህ ይህ ነውን? “በመቀነታችሁ ወርቅ ወይም ብር ወይም መሐለቅ አትያዙ” ብሎ ጌታህ ከውስጥህ የንዋይ ፍቅርን አላራቀልህምን? (ማቴ.10፡9)፡፡ ብዙ ጊዜስ፡- “ቀኝ ፊትህን ለሚመታህ ግራ ፊትህን መልስለት” ብሎ አላስተማረህምን? (ማቴ.5፡39)፡፡ “ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፡፡” አቤት! እንደ ምን ያለ ዕብደት ነው?! ጌታህን አሳልፈህ የምትሰጠው ምን አጉድሎብህ ነው? መምህርህ ምን ጥቂት ወይም ብዙ በድሎህ ነው? በአጋንንት ላይ ሥልጣን ስለ ሰጠህ ነውን? ድውያነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስንም በትምህርት ማዳን ትችል ዘንድ ሥልጣን ስለ ሰጠህ ነውን? ለምጻሞችን እንድታነጻ ስላደረገህ ነውን? ሙታንን እንድታስነሣ ስላደረገህ ነውን? ወይስ ሞትን ስለ ገደለው ነውን? እነዚህን ኹሉ ለሰጠህ መልስህ አሳልፎ መስጠት ነውን? “ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፡፡” አቤት ዕብደት! አቤት ፍቅረ ንዋይ! ይሁዳ ይህን ኹሉ ክፋት እንዲያደርግ ያደረገው ፍቅረ ንዋይ ነውና፡፡ ይሁዳ የገዛ መምህሩን አሳልፎ እንዲሰጥ ያደረገው የገንዘብ መውደድ ነውና፡፡ የዚህ ክፋት ሥሩ ይኸው ነው፡፡ ከዲያብሎስም በላይ የከፋው ይኸው ነው - የገንዘብ ፍቅር! የገንዘብ ፍቅር ልብን ያነዝዛል፡፡ በገንዘብ ፍቅር የተያዙ ሰዎች ኹሉንም ይጠላሉ - ይሰጡት ዘንድ አይሹምና ድኻን ይጠላሉ፤ ይቀሙት ዘንድም ይሻሉና ባለጸጋን ይጠላሉ፡፡ ሌላውን ሰውስ ይቅርና ራሳቸውን እንዲጠሉ፣ ልባቸውን እንዲስቱ፣ ዕብዶችም እንዲኾኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህን ማወቅ መረዳት ትችሉ ዘንድም ይሁዳን ተመልከቱት፡- የጌታችን ደቀ መዝሙር የነበረውን፣ ጌታችን በዋለበት ይውል ባደረበትም ያድር የነበረውን፣ ከጌታችን ጋር አብሮ የበላውን፣ ጌታችን ድውያነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ሲያድን የተመለከተውን፣ ከራሱ ከጌታችን የተማረውንና የተገሠጸውን ይሁዳን ተመልከቱት! የነበረውን ኹሉ መንፈሳዊ ሀብት፣ ጸጋ ብቻ ሳይኾን ነፍሱንም እንዲያጣ ያደረገው የገንዘብ ፍቅር ነው! ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ገንዘብን መውደድ የክፋት ኹሉ ሥር ነው” ያለውም ለዚህ ነው (1ኛ ጢሞ.6፡10)፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች )
Открыть в Telegram#ጉልባን ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡ (ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002)
Открыть в Telegramንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት። በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ። የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስተያናት ታነፁለት። እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ።
Открыть в Telegram#ኅዳር_25 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕት (ፒሉፓዴር) አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አምስት በዚች ቀን የስሙ ትርጓሜ መርቆሬዎስ የሆነ ፒሉፓዴር በሰማዕትነት አረፈ። መርቆሬዎስም ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው በሁለተኛ ትርጓሜ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው። የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት በሉት። ሁለተኛም አባቱን ሊበሉት ፈለጉ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው፤ ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለአለ አትንኩት አላቸው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው። በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መጥተው ሰገዱለት። በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ። አብረውትም ወደ መንደር ገቡ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት። የውሻ መልክ ያላቸውም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ። የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሉ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት። እናቱንም ታቦት አሏት። ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት። የውሻ መልክ ያላቸው ግን የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ። ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው ንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው። ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ። ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የውሻ አርአያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር። ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር። ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ። ንጉሡም ከጦር ሠራዊት ጋር የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርአያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ ያመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ። በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው፤ ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ። ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ። ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በተመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም። ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ። ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሙና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከሀገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች። ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ። የውሻ መልኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል። ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ። የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነቱ ወጣ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት። ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም። በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ። ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ አንደሆነ አወቀችው። እርሱ ግን አላወቃትም። በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው። እርሱም አባቱ ነው። በተቀመጠ ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ። የመርቆሬዎስም እናት መጥታ ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆነች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው እጅግም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ። ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው። ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልብ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ። ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ። እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት። እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ። እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ። ቅዱስ መርቆሬዎስም እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ አለው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የእግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አስበው። ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት ለምን የፈጣሪህን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ አለው። ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባበረ አስረዱት። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው። በመዘግየቱም አድንቆ ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልመጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው። እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።
Открыть в Telegram"መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡ "እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡ ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Открыть в Telegramእግዚአብሔር ለምን ይቆጣናል? እግዚአብሔር የሚቆጣን ስለ ራሱ ክብር ብሎ አይደለም፡፡ ብንሰድበውም ብንክደውም እንኳን የሚቆጣን ስለ ሰደብነው ወይም ስለ ካድነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ ስለ ካድነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ እኛ ስለ ሰደብነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ ይልቁንም እንዲህ በማድረጋችን የምንጎዳው እኛው ነን፡፡ በመኾኑም የሚቀጣን ለእኛ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ ነው፡፡ የሚቆነጥጠን ለእኛ ካለው ወደርየለሽ ጠብቆቱ የተነሣ ነው፡፡ እርሱን እየናቅነውና እየራቅነው ስንሔድ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን ስንሔድ እንዳንጎዳ ሽቶ ነው፡፡ ብርሃንን የሚጠላ ሰው ብርሃኑን ሊጎዳው አይችልም፤ በጨለማ ውስጥ በመቀመጡ ራሱን ይጎዳል እንጂ፤ በራሱ ላይ የጉዳት ዓይነትን ይከምራል እንጂ፡፡ እኛም እግዚአብሔርን ብንጠላው በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ምንም ነገር አናጎድልም፤ ምረረ ገሃነምን በራሳችን ላይ እንፈርዳለን እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በእኛ እይታ እጅግ ክፉ የሚመስሉ ነገሮች በእኛ ላይ ሲያመጣ እኛን ከመበቀል አንጻር አይደለም፤ ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ እንጂ፡፡ ሐኪሞች አእምሮአቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡዋቸው አይከፋቸውም፡፡ በዚህ አኩርፈውም መድኃኒት ማድረጋቸውን አያቆሙም፡፡ ሕሙማኑ ለዚህ በሽታ የዳረጋቸውን በሽታ ይፈውሱላቸው ዘንድ ይተጋሉ እንጂ፡፡ የሕሙማኑን ችግር እንጂ የእነርሱ መሰደብ አያሳስባቸውም፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም የሚቆነጥጠን ስለ ሠራነው ኃጢአት አይደለም፤ ኃጢአት ሕመም ነውና ከሕመማችን እንድንፈወስ ሽቶ እንጂ፡፡ ቸር አባት ሆይ! ይህ ከአእምሮ የሚያልፍና የዚህ ዓለም ቋንቋ ሊገልፀው የማይችለው ፍቅርህና ጠብቆትህ ዘወትር እናስበው ዘንድ፣ አስበንም በተግባር እንኖረው ዘንድ አእምሮውን ማስተዋሉን ስጠን፡፡ ለዚህ ግሩም ፍቅርህ ያልተገባንና የዕውቀት ግምጃ ቤት ብቻ ኾነን እንዳንቀር ብርታቱን አድለን፡፡ አሜን!
Открыть в Telegram#ፍልሰታ_ለማርያም ፍልሰታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት ( የተነሣችበት ) ቀን ማለት ነው ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም ከጨለማው ዓለም ወደ ብርሃናማው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው ፡፡ ‹‹ ፍልሰታ ለማርያም ›› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ ፍልሰታ › ማለት ደግሞ ‹ ፈለሰ › ከሚል ግሥ የተገኘ ነው ፍልሰት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን መሻገርን ( መፍለስን ) ያመለክታል ። የእመቤታችንን ሥጋ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር መፍለሱን ፤ አንድም ከጌቴሴማኒ ወደ መንግሥተ ሰማያት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ‹‹ ማርያም በክብር በምስጋና ወደ ሰማያት ፈለሰች ( ተነሣች ዐረገች ) ሠራዊተ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ሊቀበሏት ወረዱ የጌታዬ እናቱ እመቤቴ እልሻለሁ ! አባቷ ዳዊት መሰንቆው ይዞ ሙሴም መጎናጸፊያውን ተሸክሞ ወደ እርሷ መጡ ጴጥሮስና ጳውሎስ ሐዋርያት ሥጋዋን በወርቅ ማዕጠንት አጠኑ ፣ ሱራፌል ኪሩቤል ክንፎቻቸውን በእርሷ ላይ ዘረጉ ፤ ብርሃን ከሰማያት ፣ የክብር መብረቅም ( ክርስቶስ ) ከደመናት ወረደ ። ›› በማለት ሊቁ ዕርገቷን ያበሥረናል :: እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀመጠ አላወቁም ነበርና ፤ እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው ። ይኸውም ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው ስለዚህ ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት ፣ ትንሣኤና ዕርገት የሚዘከርበት ፤ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው ፡፡ ምእመናንም በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ ፣ ያስቀድሳሉ ፤ ይቈርባሉ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው ? ካልን ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐሥራት አገር በመኾኗና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ ፣ ጥሬ እየቆረጠሙ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል ። ስለሆነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቁረብ በጋራ በፍቅር ፣ በሰላም ያሳልፉታል ፡፡
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ቴዎፍሎሳውያን ሚዲያ | Theophilusian Media@tekletewoflosРелигия1,01 тыс.
🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹@ychanutРелигия1,01 тыс.
ኡመተ ረሱል@smithhkРелигия1,07 тыс.- አል-ፈታዋ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን@fetawa_mohammedzainzhРелигия1,09 тыс.
S H E K A Y I N A H@shekayinahРелигия1,1 тыс.
𓆩 ѕαуяαη 𓆪@al_khuld2Религия1,1 тыс.
የአዲስ ኪዳን ካህናት@iyesusgetanwРелигия1,15 тыс.
ራዕየ ማርያም ✝@raiye_mariyamРелигия1,18 тыс.