Кабинет
ራዕየ ማርያም ✝

ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

Юзернейм
@raiye_mariyam
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики1 176
Просмотров на пост, 7 дн.—за 7 дней
ERR17,20 %в среднем за 30 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
28 окт. 2026 г.192
30 окт. 2026 г.234
3 нояб. 2026 г.202
4 нояб. 2026 г.202
6 нояб. 2026 г.157

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры244
    Пересылки—
    Реакции2
    Комментарии—
  2. 02

    #_የንስሐና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ! ❤ #_በጎሮ_ኪዳነ_ምህረት_ቤተ_ክርስቲያን! ❤ #_እሑድ_ጥቅምት_22_ጠዋት_2_ሰዓት! ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም #_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ! "ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25 "የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም" ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ❤ #_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን? ❤ #_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን? #_የነፍስ_ጉዳይ_ነውና_ሳትቸኩሉ_በደንብ_አንብቡት! ተወዳጆች ሆይ በተአምረኛዋ በጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እሑድ ጥቅምት 22 የንስሐ፣ የቄደር ጥሞቀት እና የጠበል ጥምቀት መርሃ ግብር አዘጋጅተናል። ስለዚህ እሑድ ጥቅምት 22 ጠዋት 2 ሰዓት ከቅዳሴ መልስ በተአምረኛዋ በጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የንስሐ እና የቄደር ጥምቀት እንዲሁም የመደበኛ የጠበል ጥምቀት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ፣ ጠበል ተጠመቁ። የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር። ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣ ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣ ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን። ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል። በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል። ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ሰኔ 7 ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ። የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ። የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም። የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። ስለዚህ እሑድ ጥቅምት 22 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ። ❤ #_ማሳሰቢያ :- ሴቶች ቀለል ያለ የመጠመቅያ ልብስ ልበሱ ወይም ያዙ! ❤ ወንዶችም ቀለል ያለ መጠመቂያ ወይም ቱታ ልበሱ ወይም ያዙ! #_ነገ_ንስሐ_ለመግባት_የምትመጡ_ይሄንን_ተጠቀሙ! #_የንስሐ_መግቢያ_የኃጢአት_ዝርዝር! #_ንስሐ_ስትገቡ_ይሄንን_ተጠቀሙ! "ሂድ ራስህን ለካህን አሳይ" ማቴ 8፥4 ❤ ተወዳጆች ሆይ ይሄ የንስሐ መግቢያ የኃጢአት ዝርዝር የተዘጋጀው በቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም ሲሆን የተዘጋጀበትም ምክንያት በአገልግሎቱ በአብዛኛው ለቄደር እና ለንስሐ የሚመጡትን ምዕመናን ምን ተብሎ ንስሐ እንደሚገባ ለማሳወቅ ነው። ❤ ሁለተኛው አንድ ኃጢአት ዙርያ ጥምጥም አድርጎ ከመናገር በቀጥታ የሰሩትን ኃጢአት ብቻ በአጭሩ እንዲናገሩ ከማሰብ ነው! ሦስተኛው ብዙዎች ንስሐ ሲገቡ ኃጢአታቸውን እየረሱ ስለሚቸገሩና፤ ንስሐ ከገቡ በኋላ የረሱትን ኃጢአት እያስታወሱ እንዳይቸገሩ ነው። 1. ከእግዚአብሔር ውጭ ሌላ ባዕድ አምልኮ አምልክያለሁ ፣ ለባዕድ አምልኮ ሰግጃለሁ! 2. የእግዚአብሔርን እና የቅዱሳንን ስም በከንቱ ጠርቻለሁ ፣ በነሱ ስም በሐሰት ምያለሁ፣ በእነሱ ስም ዋሽቻለሁ! 3. የሰንበትን ቀን አላከበርኩም፣ ሰንበትን ሽርያለሁ! 4. አባቴን፣ እናቴን፣ ቤተሰቦቼን እንዲሁም ሰዎችን አላከበርኩም ፣ ተሳድብያለሁ! 5. ሰውን ገድያለሁ፣ ሰውን አስገድያለሁ! 6. ውርጃ ፈጽምያለሁ ወይም ጽንስ አጨናግፍያለሁ። ጽንስ ለማጨናገፍ በገንዘቤ፣ በሐሳቤ ተባብርያለሁ! 7. ዝሙት ፈጽምያለሁ! ከተለያዩ ሰዎች ጋር ዝሙት ፈጽምያለሁ! 8. ገንዘብ፣ ዕቃ፣ ንብረት ወዘተ ሰርቄያለሁ! 9. በሐሰት መስክርያለሁ! 10. የባልንጀራዬን እና የሰዎችን ገንዘብ ተመኝቻለሁ! 11. ባልንጀራዬን እና ጠላቴን እንደ ራሴ አልወደድኩም! 12. አባቴን፣ እናቴን፣ ወንድሞቼን፣ እህቶቼን፣ እንዲሁም ሰዎችን ተቆጥቻለሁ 13. ሴቶችን ለዝሙት ተመኝቻለሁ! 14. ወንዶችን ለዝሙት ተመኝቻለሁ! 15. ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቴን/ባሌን ፈታሁ! 16. ያለ ዝሙት ምክንያት የፈታውን/የፈታችውን አገባሁ! 17. በሐሰት ምያለሁ፣ ዋሽቻለሁ! 18. ክፉውን በክፉ ተቃውምያለሁ! 19. ለተራበ አላበላሁም፣ ለተጠማ አላጠጣሁም፣ እንግዳ አልተቀበልኩም፣ ለታረዘ አላለበስኩም፣ የታመመን አልጠየኩም፣ የታሰረን አላስፈታሁም፣ የሞተ አልቀበርኩም! 20. ኩል ተኳልኩ ፣ ከንፈሬን ፊቴን ምናምቴ ተቀብቻለሁ! 21. ጸጉሬን ተቀልምያለሁ፣ ሌላ ጸጉር ቀጥያለሁ፣ቅንድቤን ተቀንድብያለሁ! 22. ራሴን የሚያራቁት/ዝሙት የሚያነሳሳ/ ልብስ ለብሻለሁ! 23. ጉቦ ሰጠሁ ጉቦ ተቀበልኩ፣ የሰው አደራ በልቻለሁ፣ ተበድሬ አልመለስኩም፣ ከሌባ ጋር ገንዘብ ተካፍያለሁ! 24. ጾም ሻርኩ ፣ ረቡዕ እና አርብ የፍስክ በላሁ! 25. ከሃይማኖቴ ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ፈጸምኩ! 26. በልጅነት እና ካደኩ በኋላ ግብረ ሰዶም ፈጸምኩ! 27. ከእንስሳት ጋር ግንኙነት አደረኩ! 28. በልጅነት መሬትን ወስቤያለሁ! 29. ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜያለሁ! 30. ቅዱስ ቁርባን ተቀብዬ በዝሙት ወደኩ፣ በግለ ወሲብ ወደኩ! 31. በቅዱስ ቁርባን አግብቼ በባሌ/በሚስቴ ላይ ዘሙቻለሁ! 32. ኢ- ሩካቤ ፈጽሜያለሁ (ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ፈጽሜያለሁ) 33. የአሕዛብን ምግብ በልቻለሁ! 34. ኦርቶዶክስ ሆኜ ወደ ሌላ እምነት ገብቼ ተመልሻለሁ! 35. ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ገብሬያለሁ፣ የተገበረውን መስዋዕት በልቻለሁ! 36. ጠንቋይ ቤት ሄጃለሁ፣ አውደ ነገሥት አስገልጫለሁ፣ ስለ ራሴ ጠንቋይና ጠይቅያለሁ፣ ዛር አንጋሽ ጋር ሄጃለሁ! 37. ግለ ወሲብ ፈጽሜያለሁ! 38. የወር አበባ ላይ ሆኜ ግንኙነት አድርግያለሁ ! 39. የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት አደረኩ! 40. ጫት ቅምያለሁ! መጠጥ ጠጥቼ ሰክርያለሁ! 41. ሲጋራ፣ ሺሻ፣ ጋንጃ፣ ሀሺሽ ተጠቅሜያለሁ! 42. ህልመ ሌሊት መቶኝ ቤተክርስቲያን ገባሁ ፣ ጸበል ተጠመቅሁ ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበልኩ! 43. የወር አበባ ላይ ሆኜ ቤተክርስቲያን ገባሁ ፣ ጸበል ተጠመቅሁ ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበልኩ 44. በጸሎት፣ በቅዳሴ ጊዜ አውርቻለሁ፣ ስቅያለሁ! 45. በእግዚአብሔር እና በቅዱሳን ስም ቃል ኪዳን ገብቼ አፍርሻለሁ! 46. የዝሙት ፊልም አይቻለሁ! የዝሙት ምስል ተመልክቻለሁ፣ 47. የግብረ ሰዶም ፊልም፣ የግብረ ሰዶም ምስል አይቻለሁ! 48. ዘፈን ዘፍኛለሁ ዘፈን ሰምቻለሁ ዳንስ አይቻለሁ፣ ደንሻለሁ! 49. በጾም፣ በግዝት እንዲሁም በበዓላት ጊዜ ሩካቤ ሥጋ ፈጽምያለሁ! 50. በቤተ ክርስቲያን ነክ ነገሮች ላይ ቀልጃለሁ! 51. ካህን ገዝቶኝ አፍርሻለሁ፣ ንስሐ ገብቼ ከእንደገ በኃጢአት ወድቅያለው፣ የተሰጠኝን የንስሐ ቀኖና አልጨረስኩም! 52. ፓትሪያሪኩን፣ ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ መነኮሳትን፣ ባህታውያንን፣ ካህናትን፣ ዲያቆናትን፣ መምህራንን አምቻለሁ፣ ተሳድብያለሁ! 53. ከሰው ጋር ተጣልቻለሁ፣ ይቅርታ እናእርቅን እምቢ ብያለሁ! 54. እራሴን ላጠፋ አስብያለሁ ፣ እራሴን ለማጥፋት በተግባር ሞክርያለሁ! 55. የእግዚአብሔርን ገንዘብ ወስጃለሁ/አስራት በኩራት አላወጣሁም/ 56. ሰው ደብድቤ ጎዶቻለሁ፣ ልጆቼን ያለ ጥፋታቸው መትቼ ጎድቻለሁ፣ የሰውን ልጅ መትቼ ጎድቻለሁ! 57. ወፍ፣ ድመት፣ ውሻ ወዘተ እንስሳትን ገድያለሁ! 58. የሰው ገንዘብ ክጃለሁ፣ የካድኩትን ገንዘብ አልመለስኩት! 59. ቅዱስ ቁርባን ተቀብዬ እለቱን ምራቄን ተፍቻለሁ፣ ቆርቤ ተሳድብያለሁ፣ ሰው አምቻለሁ! 60. ዲቁናዬን ቅስናዬን፣ ምንኩስናዬን በዝሙት አፍርሻለሁ! 61. ወልጄ ልጄን ክጅላሁ! 62. ሰው ላይ መተት አስመትቻለሁ፣ የሰው እድል በመተት ወስጃለሁ፣ በጥላ ወጊ ሰው አስገድያለሁ፣ የስልብና መተት ተጠቅያለሁ! 63. ሚስቴን በመስተፋቅር አግብቻለሁ፣ ባሌን በመስተፋቅር አግብቻለሁ፣ ሚስቴን ወይም ባሌን ላለመፍታት መስተዋድድ መስተፋቅር አስደርግያለሁ! 64. በሐሊዮ፣ በነቢብ እና በገቢር ወይም በሐሳብ፣ በንግግር እና በተግባር የሠራሁትን ኃጢአት፤ እኔ የረሳሁትን እግዚአብሔር የሚያውቀውን ይቅር ይበለኝ! ❤ #_የቦታው_አድራሻ_እና_የትራንስፖርት_መምጫው ፦ ❤ ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፓልቱ አጠገብ በስተ ግራ በኩል ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች። ❤ ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍራችሁ፣ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከመገናኛ 113 ቁጥር ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከፒያሳ ከእሳት አደጋው ዝቅ ብሎ ኮዬ ፈጬ በሚለው 131 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያኑ ጋር ይወርዳሉ! ❤ ከሜክሲኮ ሸበሌ ጋር 29 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያና ትገኛለች! ❤ ከሲኤምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፖልቱ ጫፍ ትገኛለች! ❤ ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ሳትደርሱ ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በስተቀኝ አስፖልቱ ዳር ትገኛለች፡፡ ጥቅምት 20-2-2019 ዓ.ም

    Текст
    Просмотры225
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры222
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры202
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—

Новые посты

#6136Текст
Просмотры2020%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#6133Фото

Переслано из ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры244+21%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#6132Текст

Просмотры225+11%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#6129Фото

Переслано из ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры186−8%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#6128Текст

Переслано из ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_እንደ_አቡነ_ሺኖዳ_ሱባኤ_ባትገቡልንም_ለምን_ዝም_አላችሁ? የአንድ ቄስ ሚስት ታገተች ብለው ሱባኤ ገቡ! የእኛ ሲገደሉ ዝም! በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በታህሳስ 2004 ዓ.ም ዋፋ ኮንስታንቲን /Wafaa Constantine/ የተባለች የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ሚስት ከቤቷ መጥፋቷ በመላው ግብጽ ታወቀ። ይልቁንም በግብጽ ክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ቁጣን ቀሰቀሰ። ይህቺ የቄስ ሚስት የታገተችው የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስን በሚቃወሙ አክራሪዎች ነበር። ይህን ጉዳይ በወቅቱ የነበሩት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሰሙ። አቡነ ሺኖዳ የቄሱ ሚስት መታገቷን እንዳወቁ በቀጥታ የቅዱስ ቢሾይ ገዳም ገብተው ስለ ቄሱ ሚስት ስለ ዋፋ ኮንስታንቲን ወደ እግዚአብሔር ሱባኤ ገቡላት። በጾም በጸሎትም እግዚአብሔርን ጠየቁላት። አቡነ ሺኖዳ ሱባኤ የገቡት ለሁለት ነገር ነው። አንደኛ የታገተችው የቄሱ ሚስት እንድትለቀቅና በሰላም በሕይወቷ ወደ ቤቷ አንድትመለስ ነው። ሁለተኛ ከመንግስት መፍትሔ አንዲገኝ እና የሚታሰሩት የሚታገቱት ክርስቲያኖች እንዲለቀቁ ነው። ይህ የአቡነ ሺኖዳ ድርጊት በግብጽና በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ በወቅቱ ትልቅ መነጋገሪያ ነበር። በመጨረሻም የቄሱ ሚስት ዋፋ ኮንስታንቲን ከታገተችበት መፈታቷን ወደ ቤቷ መመለሷን አቡነ ሺኖዳ ሰሙ። እሳቸውም ሱባኤ ከገቡበት ከቅዱስ ቢሾይ ገዳም ወጥተው ወደ መንበራቸው ተመለሱ። ይህ ከአቡነ ሺኖዳ ለአንድ የቄስ ሚስት የተከፈለ የሱባኤ ዋጋ ነው! የእኛ አባቶች ሆይ! ከሕፃናት ከወጣት እስከ አዛውንት ያሉት ኦርቶዶክሳውያን በአሩሲ ሲገደሉ፤ እንደ አቡነ ሺኖዳ ገዳም ሄዳችሁ ሱባኤ ይዛችሁ ወደ እግዚአብሔር መጮህ ቢያቅታችሁ፣ እንዴት ባላችሁበት ሆናችሁ መጮህ አቃታችሁ? ይህ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ደሙ ሲፈስ እናንተ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንባ ማፍሰስ አቃታችሁ? መነኮሰ ሞተ ነው! አስቀድሞ የሞተ እንዴት ሞትን ይፈራል? ወይስ እኛ አስቀድመን ሞተናል ለሚሞተው አያገባንም ብላችሁ ነው? የኦርቶዶክሳውያንን ግድያ መንግስት ባያስቆመውም እግዚአብሔር እንዲያስቆመው ምህላ ማወጅ ለምን አቃታችሁ? አቡነ ሺኖዳ የቄስ ሚስት ታገተች ብለው ሱባኤ ገቡ። እናንተ ኦርቶዶክሳዊው ተገደለ፤ ደሙ በግፍ ፈሰሰ ብላችሁ ሱባኤና ምህላ መያዝና ማወጅ ለምን አቃታችሁ? በጎቹ ምዕመናን በተኮላ ሲበሉ ሲገደሉ፤ እናንተ የበጎቹ እረኞች ምነውሳ ዝም አላችሁ? መቼ ነው ከሐዘን መግለጫ ወጥታችሁ ለበጎቹ ወደ እግዚአብሔር የምትጮሁት? በእውነት የአቡነ ሺኖዳ ድርጊት ምን ያስተምረናል? የአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ ይቀጥላል የእናንም ዝምታና የሐዘን መግለጫ ይቀጥላል .... ጥቅምት 18-2-2019 ዓ.ም

Открыть в Telegram
Просмотры199−2%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6126Фото

Переслано из ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры298+47%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#6125Текст

Переслано из ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_አርሲ_የደም_ኩርሲ! ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም! አርሲ የደም ኩርሲ ከሆነች ሰነባበተች! ኩርሲ ማለት መቀመጫ ማለት ነው። አርሲ ያሉት ኦርቶዶክሳውያን የሞት መቀመጫ ከሆኑ ቆዩ። ሞታቸው እንደዘበት የሚረሳበት ሆነ! በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያኖች ሁለት ፈተና ገጥማቸው ነበር። አንደኛው ገዳያቸው በወቅቱ የነገበሩት አላውያን ነገሥታቱ ስለነበሩ ቢጮሁም ሊደርሱላቸው አልቻሉም። ለእነሱ ከመድረስ ደማቸውን ማፍሰስ ሆነ ሥራቸው። ሁለተኛው ይደርሱላቸዋል የተባሉት ባለ መንበሮቹ ጳጳሳቱ፣ ሱኖዶሱ በወቅቱ የነበረው መዋቅር፣ ለነገሥታቱ የሚያድር ስለነበር፤ ሊደርሱላቸው ሞታቸውን ሊያስቆሙላቸው አልቻሉም። እየሆነ ያለው ይኸው ነው! እኛ ማድረግ ያለብን ጭኸታችንን ወደ ቤተ ክህነቱ ሳይሆን ወደ ሰማይ ቤቱ ነው። ወደ ጳጳሳትና ወደ ሲኖዶስ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ደማቸውን የሚያቆመው ስለ ዓለሙ የደማው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሞታቸውን የሚያቆመው ስለ ዓለሙ የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በአርሲ ክርስቲያኖች ሞት ጉዳይ ብዙዎቻችሁ ስለ እውነት ጮኻችሁ ግን ሰሚ ታጣ! ወደ ሰማይ አምላክ በምህላ እንጩህ! እላይ ካሉት መፍትሔ መጠበቅ እራስን ማስናቅ ነው! ምክንያቱም የክርስቲያኖቹን ሞት ከናቁ መፍትሔ መጠበቁ መፍትሔ ስለማይሆን! አንድ አባት "የሐዘን መግለጫ፣ ሰዉ እንዳይንጫጫ" አሉ! አዎ ባላዘነ ልብ አንድ ወረቀት በማንበብ፣ ሞታቸውን በግድ ያስረሱያል! ግን ሰማዕታቱ የሚረሱ ሰይሆን የሚታወሱ ናቸው! #_አርሲ_እስከ_መቼ_የደም_ኩርሲ? ቤተሰባችሁን በሃይማኖታቸው ምክንያት በሞት ላጣችሁ፣ እግዚአብሔር መጽናያቱን ይስጣችሁ! "ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፣ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን" ሮሜ 8፥36 ጥቅምት 9-2-2018 ዓ.ም!

Открыть в Telegram
Просмотры280+38%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—

Все посты

Связи