Кабинет
ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ስለታሪካቸው፣ ሃይማኖታዊ ትርጉማቸው፣ አሣሣል መረጃ የሚያገኙበት ቦታ፡፡ A channel that discusses about icons of ethiopian orthodox tewahido church. Contact for questions @shihaile or [email protected] or www.ethioicons.wordpress.com

Юзернейм
@ethioicons
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики5 039
Просмотров на пост, 7 дн.—за 7 дней
ERR23,27 %в среднем за 30 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
28 окт. 2026 г.1 387
1 нояб. 2026 г.1 380
3 нояб. 2026 г.866
6 нояб. 2026 г.1 293
15 нояб. 2026 г.885

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры1,49 тыс.
    Пересылки—
    Реакции10
    Комментарии—
  2. 02

    1፤እግዚአብሔር፡የበቀል፡አምላክ፡ነው።የበቀል፡አምላክ፡ተገለጠ። 2፤የምድር፡ፈራጅ፡ሆይ፥ከፍ፡ከፍ፡በል፤ለትዕቢተኛዎች፡ፍዳቸውን፡ክፈላቸው። 3፤አቤቱ፥ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፧ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፡ይጓደዳሉ፧ 4፤ይከራከራሉ፥ዐመፃንም፡ይናገራሉ፤ዐመፃንም፡የሚያደርጉ፡ዅሉ፡ይናገራሉ። 5፤አቤቱ፥ሕዝብን፡አዋረዱ፥ርስትኽንም፡አስቸገሩ። 6፤ባልቴቲቱንና፡ድኻ፡አደጉን፡ገደሉ፥ስደተኛውንም፡ገደሉ። 7፤እግዚአብሔር፡አያይም፥የያዕቆብ፡አምላክ፡አያስተውልም፡አሉ። 8፤የሕዝብ፡ደንቈሮዎች፡ሆይ፥አስተውሉ፤ሰነፎችማ፡መቼ፡ይጠበባሉ፧ 9፤ዦሮን፡የተከለው፡አይሰማምን፧ዐይንን፡የሠራው፡አያይምን፧ 10፤አሕዛብንስ፡የሚገሥጸው፥ለሰውም፡ዕውቀት፡የሚያስተምረው፡ርሱ፡አይዘልፍምን፧ 11፤የሰዎች፡ዐሳብ፡ከንቱ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ያውቃል። 12-13፤ለኀጢአተኛ፡ጕድጓድ፡እስኪቈፈር፡ድረስ፡ከክፉዎች፡ዘመናት፡ይወገድ፡ዘንድ፥አቤቱ፥አንተ፡ የገሠጽኸው፡ሕግኽንም፡ያስተማርኸው፡ሰው፡ምስጉን፡ነው። 14፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አይጥልምና፥ርስቱንም፡አይተውምና። መዝሙር 93(94) :1-14

    Текст
    Просмотры1,44 тыс.
    Пересылки—
    Реакции12
    Комментарии—
  3. 03

    በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ ከተገደሉት መካከል እስካሁን የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን መገኘቱ ተሰማ። ከምእመናን በተጨማሪ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ወደ አካባቢው እየሄዱ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ( MK TV ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ የምእመናን ግድያ የጀመረው ከጥር 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዛሬም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ያሉ ምእመናን የዛሬውን ግድያ ከቀድሞው ጋር ወደ ኋላ መለስ ብለው ያስታውሳሉ። ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ ስሆን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸርካ ወረዳ እንደተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በእንዳቶ ቀበሌ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸሙን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቮዥን መረጃ አድርሰዋል። እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ታጣቂዎች በፈጸሙት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ይህንን ዜና እስከምንዘግብበት ጊዜ ድረስ ከሟቾች መካከል የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን በእንደቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡን አሳውቀዋል። የሟቾች ቁጥርም እንደሚያሻቅብ ተጠቁሟል።

    Фото
    Просмотры1,44 тыс.
    Пересылки—
    Реакции9
    Комментарии—
  4. 04

    እንኳን ለጥበበኛ፣ ሠዓሊ፣ ወንጌላዊ፣ ሐዋርያ፣ ሐኪምና ሰማዕት ቅዱስ ሉቃስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ። ቅዱሳት ሥዕላት በሐዲስ ኪዳን ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ለማሰየት አብነት የምናደርገው የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል የሣለልን የቅዱስ ገብርኤልና የቅድስት ኤልሳቤጥን ምስጋና የጻፈልን የእመቤታችንን ጸሎት የመዘገበልን መከራና ስደቷን የጻፈልን የቅዱሳን ሴቶች አገልግሎትን በክርስቶስ ፊት ምን እንደነበረ የነገረን ድንቅ ሐዋርያ የቅዱሳን ሐዋርያት ተጋድሎ የጻፈልን አባት ዛሬ መታሰቢያው ጥቅምት 22 ነው። የቻላችሁ ለየነቢጤ እንዳቅማችሁ በቅዱስ ሉቃስ እያላችሁ በመዘከር አስቡት በምልጃው እንዲረዳችሁ። በዘመናችን የተረሳው ሐዋርያና ወንጌላዊ በጣም ከሚያሳዝኑኛና ከሚያስቆጩኝ ነገሮች አንዱ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ውለታ ከዋሉት ቅዱሳን መካከል ዘመናት በየአራት ዓመቱ የሚቆጠርለት ይህ አባት አንድ ደብር በስሙ ለማግኘት ከባድ መሆኑ። ዛሬ በዓሉ ሆኖ እንኳ ብዙዎቻችን እርሱን በዕለተ ቀኑ መርሳታችን ያስቆጫል። እስቲ የምታውቁ ካላችሁ ታቦቱ በድርብ እንኳ የሚገኝበት ቦታ አሳውቁኝ። ከሌለ እስቲ ምን ብናደርግ ጥሩ ይመስላችኋል።

    Фото
    Просмотры1,38 тыс.
    Пересылки—
    Реакции24
    Комментарии—

Новые посты

#1090Фото
Просмотры885−25%к среднему
Пересылки—
Реакции52
Комментарии—
#1089Текст

1፤እግዚአብሔር፡የበቀል፡አምላክ፡ነው።የበቀል፡አምላክ፡ተገለጠ። 2፤የምድር፡ፈራጅ፡ሆይ፥ከፍ፡ከፍ፡በል፤ለትዕቢተኛዎች፡ፍዳቸውን፡ክፈላቸው። 3፤አቤቱ፥ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፧ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፡ይጓደዳሉ፧ 4፤ይከራከራሉ፥ዐመፃንም፡ይናገራሉ፤ዐመፃንም፡የሚያደርጉ፡ዅሉ፡ይናገራሉ። 5፤አቤቱ፥ሕዝብን፡አዋረዱ፥ርስትኽንም፡አስቸገሩ። 6፤ባልቴቲቱንና፡ድኻ፡አደጉን፡ገደሉ፥ስደተኛውንም፡ገደሉ። 7፤እግዚአብሔር፡አያይም፥የያዕቆብ፡አምላክ፡አያስተውልም፡አሉ። 8፤የሕዝብ፡ደንቈሮዎች፡ሆይ፥አስተውሉ፤ሰነፎችማ፡መቼ፡ይጠበባሉ፧ 9፤ዦሮን፡የተከለው፡አይሰማምን፧ዐይንን፡የሠራው፡አያይምን፧ 10፤አሕዛብንስ፡የሚገሥጸው፥ለሰውም፡ዕውቀት፡የሚያስተምረው፡ርሱ፡አይዘልፍምን፧ 11፤የሰዎች፡ዐሳብ፡ከንቱ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ያውቃል። 12-13፤ለኀጢአተኛ፡ጕድጓድ፡እስኪቈፈር፡ድረስ፡ከክፉዎች፡ዘመናት፡ይወገድ፡ዘንድ፥አቤቱ፥አንተ፡ የገሠጽኸው፡ሕግኽንም፡ያስተማርኸው፡ሰው፡ምስጉን፡ነው። 14፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አይጥልምና፥ርስቱንም፡አይተውምና። መዝሙር 93(94) :1-14

Открыть в Telegram
Просмотры1 440+23%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#1088Фото

በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ ከተገደሉት መካከል እስካሁን የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን መገኘቱ ተሰማ። ከምእመናን በተጨማሪ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ወደ አካባቢው እየሄዱ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ( MK TV ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ የምእመናን ግድያ የጀመረው ከጥር 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዛሬም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ያሉ ምእመናን የዛሬውን ግድያ ከቀድሞው ጋር ወደ ኋላ መለስ ብለው ያስታውሳሉ። ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ ስሆን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸርካ ወረዳ እንደተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በእንዳቶ ቀበሌ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸሙን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቮዥን መረጃ አድርሰዋል። እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ታጣቂዎች በፈጸሙት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ይህንን ዜና እስከምንዘግብበት ጊዜ ድረስ ከሟቾች መካከል የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን በእንደቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡን አሳውቀዋል። የሟቾች ቁጥርም እንደሚያሻቅብ ተጠቁሟል።

Открыть в Telegram
Просмотры1 440+23%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#1086Текст

Переслано из ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

አሰኮ ወረዳ የኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ አርሲ ዞንሌላኛው ወረዳ ነው። በዚህ ወረዳ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በታጣቂ ኃይሎች ሕይወታቸው እንዳለፈ የተረጋገጠው  12 ምእመናን ናቸው። 22). ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይህ በእንዲህ  እንዳለ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጥቃት  ደርሶባቸው  ሥርዓተ ቀብራቸው ከተፈጸመ ወረዳዎች መካከል ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ እና በሽርካ ወረዳ ይጠቀሳሉ፡- ሀ) በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ የተፈጸመ ጥቃት ቦታ ተጂ ወልቂጤ ቀበሌ ሰሆን 5 ሰዎች ታግተው ከተያዙት መካከል የሁለቱ 2 ሰዎች ሕይወት በአክራሪዎች እንዲያልፍ ተደርጓል። እነዚህ ሁለት መእመናን በበረዶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ለ) በሽርካ ወረዳ የተፈጸመ ጥቃት ሚታና ዋጂ ቀበሌ ይባላል አሰቃቂው ድርጊትየተፈጸመበት። አስክሬናቸው ተጥሎ የተገኘበት ደግሞ በሚታና ጋዶ ቀበሌ ሲሆን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑት ሁለት ወንድማማች ወጣቶች ከገዛ መኖሪያ ቤታቸው በኃይል ተወስደው ተገለዋል። እነዚህ የቤተሰብ አባላት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ምበጋዶ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንበአንድ መቃብር ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ሐ) በአሰኮ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት  8 ምእመናን ተገለዋል። 23) ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ቄስ ዐባይነህ በምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚታናጋዶ ቀበሌ የጋዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ነበሩ። ካህኑ በእርሻ ማሳ ላይ እንዳሉ ከበሬያቸው ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደው ተጣሉ። ሥርዐተ ቀብራቸውም  ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ምሲያገለግሉበት በነበረው ጋዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። 24) ሰኔ 17ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በሐሮ አሌ ቀበሌ ልዩ ስሙላፍቶታ በሚባል አከባቢ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ አባወራ ሥራ ላይ እያለ በአክራሪዎቹ  በገጀራ እና ጥይት በመደብደብ  መገደሉ  ተነግሯል። 25) ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ሬኤ አርባ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጨድድ ወደላ በሚባል ቦታ ላይ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ለእሑድ አጥቢያ አክራሪ ታጣቂዎቹ አንድ ሰው ገድለው 3 ሰው አግተው ወስዱ። ሟቹም በግብርና ሥራ የሚተዳደር ነበር። 26) ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ጉና ወረዳ ረኤ አርባ ቀበሌ ጦሴ በሚባል ቦታ  ሰኔ 24 ቀን ለ25 አጥቢያ  ሁለት ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ። አንዱ መምህር በጥይት ተመቶ  ሆስፒታል ለሕክምና እርዳታ ተልኳል።  ሦስት ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ በዚሁ ዕለት ታግተው ተወስደዋል። 27) ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ዞን ጉና ወረዳ ሬኤ አርባ ቀበሌየአካባቢው ታዋቂ ገበሬ እና የሬኤ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ ኀላፊን ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ  6፡00 ሰዓትበተኛበት ታጣቂዎች በ10 ጥይት ገድለውት  የወንድሙን ሚስት ከነ ልጆቿዋ አግተው ወስዷቸው። እንዲሁም የካህኑን እና የሌሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከብቶች በሙሉ ወሰዱ። 28) ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ሐምሌ 22ቀን 2018ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካወረዳ ጃዊ ዋጬ ቀበሌ የዘጠኝ ኦርቶዶክሳውያንመኖሪያ ቤቶች በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎችተቃጠሉ። ከተቃጠሉት  ቤቶች  መካከል  የአራት ቤቶች ቆርቆሮ እና የሚፈልጉትን ንብረት አፈራርሰው  ወሰዱ። 29) ነሐሴ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ ልዩ ስሙመልከምያ መንደር ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለነሐሴ 3 ቀን  አጥብያ የ70 ዓመት አዛውንት እና ባለቤታቸውን እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩበመግደል 17 ከብቶቻቸውንም  ዘርፈው ወሰዱ። 30) ነሐሴ 15 ቅን 2018 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ነሐሴ 15 ቀን 2018ዓ.ምዐርብ ለቅዳሜ አጥቢያ በመጪቱ ቀበሌ “በቀቅሳ “ በሚባል አካባቢ በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከአንድ ቤተሰብ  ሦስት ኦርቶዶክሳውያን ታርደው  ተገደሉ። የዚህ ሰቆቃና ግፍ ዋናው መልእክት ብዙ ግልጽ ማሳያዎች ቢኖሩትም የሰው ልጅ ሕይወት እና ክብር ከማናቸውም የፖለቲካ ትርፍ በላይ ሊከበር ይገባል።መንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላት ሕግን የማስከበር ፣ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ እና አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረብ ታሪካዊ እና ሕገመንግሥታዊ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።

Открыть в Telegram
Просмотры1 150−2%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#1085Текст

Переслано из ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

የ2018 ዓ.ም የኦርቶዶክሳውያኑን ግድያ በዝርዝር ስንመለከት፡- 1] መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ሮቤ ወረዳ እንዴቶ 01 ቀበሌ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 4 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሁለት ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ ሌላ አንድ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በምሥራቅ  አርሲ ከሚፈጸመው ግድያ  ባሻገር በተደጋጋሚ ጊዜ የምእመናን   ቤት  እየተነጠለ  ጉዳት  ሲደርስባቸው  ይስተዋላል። ከመስከረም 5ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮም በሽርካ ወረዳ በሚታና ጋዶ ቀበሌ 118 የምእመናን ቤቶች እየተለየ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 2) ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ጉና ወረዳ የመጀመሪያው ጥቃት የደረሰው ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ ነበር።  ጥቃቱ የደረሰበት ቀን 12 በመሆኑ «የቅዱስ የሚካኤል» ዕለትን ለማክበር በአንድ ቤት ውስጥ በተሰበሰቡ ስድስት  ምእመናን ላይ ነው። ምእመናኑ ከተሰበሰቡበት መኖሪያ ቤት ወደ ጫካ ከተወሰዱ በኋላ የመገደላቸው ዜና ተሰማ። 3)  ጥቅምት  13  ቀን 2018 ዓ.ም ጥቅምት 13 ቀን ለ14 አጥቢያ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ታጣቂዎች ወደ ኦርቶዶክሳውያኑ መኖሪያ ቤት በኃይል ሰብረው በመግባት እያንገላቱዋቸው«ተረአሊ» ወደሚባል ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ወሰዷቸው። በተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃትም በአጠቃላይ 14 ምእመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።ዕድሜያቸውም ከ2 ዓመት ሕፃን እስከ 76 ዓመትአዛውንት እንደሚደርሱ የአካባቢው የዐይን እማኞች ያስረዳሉ። 4 ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ከፍተኛ  ጥቃት  ከሚፈጸምባቸው  ወረዳዎች  መካከል ሽርካ  በቀዳሚነት  ይጠቀሳል በሽርካ ወረዳ በሄላ ዘምባባ ቀበሌ ብቻ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዘምባባ አርሴማ በተፈጸመ  ግድያ  3 ምእመናን ሕይወታቸውን  አጥተዋል፡፡   5)    ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 5 ምእመናን ተገለዋል።  እነዚህ  ኦርቶዶክሳውያን  በሃይማኖታቸው  ምክንያት  የገደሉ  ሲሆን የአንድ ቤተሰብ አባላትም  ናቸው።ሁለት ወንድማማቾችና ሁለት እኅትማማቾች፡፡   6) ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ  አርሲ የሚገኙ  ወረዳዎች  እንደ  ማንኛውም የሀገራችን  ክፍሎች  አብዛኞቸቹ በአርሶ አደርነት  የሚተዳዱሩ ናቸው ።  ታዲያ በዞኑ መርቲ ወረዳ ጋዶ ቀበሌ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት የእርሻ ሥራቸውን አጠናቀው ምሳቸውን ለመብላት  አረፍ  ያሉ 5 ኦርቶዶክሳያን  በማሳቸው  ውስጥ በታጠቂዎች በተከፈተባቸው የተኩስ እሩምታ ተገድለዋል፡፡  7)  ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በታጣቂዎችበተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት  የምእመናን መኖሪያ ቤትበእሳት ወድሞ 2 ክርስቲያኖች ሕይወታቸው አልፏል። 8) ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ  ከሚገኙ ወረዳዎች  መካከል በአሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ ልዩ ስሙ «ጠለታ ገብርኤል» በተባለ ቦታ ታጣቂ ኃይሎች በግብርና ሥራ ላይ በነበሩ 3 ምእመናን ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ጥቃቱየተፈጸመው ተጎጂዎቹ በአውድማ ላይ ሆነው እህል እየወቁ በነበረበት ወቅት በመሆኑ የታጠቁት ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያኑን ያለምንም ርኅራኄ በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል። 9) ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ አባት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በመኖሪያ  ቤታቸው ሳሉ  የታጠቁ ኃይሎች በሰነዘሩት ድንገተኛ ጥቃት የተገደሉት ደግሞ በመርቲ ወረዳ ፈረቀሳ ጃዊ በሚባል ቦታ ነው።   10)  ታኅሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ መጭቱ ጎቶ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሀተታ በሚባል አካባቢ ታኅሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የ60 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ታርደው ተገድለዋል። 11) የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በመርቲ ወረዳ ፈረቀሳ በተባለ ቦታ 4 ምእመናንየተገደሉት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።  ከ10 በላይ የሚሆኑ የአባወራ ቤቶችም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። 12) የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሽርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር የካቲት 19 ቀንለ20 አጥቢያ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በተፈጸመ  የንጹሐን  ጭፍጨፋ አንድ ካህን ፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንዶች በድምሩ 21 ወገኖቻች ሕይወት አልፏል። 13) የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ሽርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ከቀኑ 9 እስከ 10 ሰዓት ገደማ በዚሁ ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 8 ሰዎችተገድለዋል። “አምስት ሰዎች ደግሞ ታግተው” መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ምእመን ገልጸዋል። 14) የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈጸመው ጥቃት ቀኑ እሑድ ምሽት ነበር። ቦታውምሽርካ ወረዳ በዚሁ አካባቢ ተጨማሪ 2 አዛውንት ወንድማማቾች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በአሰቃቂ  ሁኔታ ተገድለዋል። 15) መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ የ67 ዓመት ግለሰብ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ሊነጋጋ ሲል በታጣቂዎች ተገደሉ።ታጣቂዎቹ እኝህ አባት ከመግደላቸው በተጨማሪ ከ6 በላይ ከብቶችን ነድተው መውሰዳቸው ታውቋል። 16) መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም የ80 ዓመት የዕድሜ  ባለጸጋ ናቸው ። ነዋሪነታቸውም  በመርቲ ወረዳ ከቢሮ ኮኛቀበሌ ነው። እኒህ አዛውንት መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ምሊነጋጋ  ሲል በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው  ጥቃት  ሞተዋል።  17) መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ የሚፈጸመው ጥቃት ከአዛውንት  አልፎ ሕጻናት ፣ ወጣቶችንን እና ሴቶችን ጭምር ነው ለዚህ ማሳያ ደግሞ በአሰኮ ወረዳ ዲማ አሰኮ በተባለ  አካባቢ የተፈጸመው ግድና የአካል ጉዳት ነው። የ80 ዓመት አዛውንት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ልጃቸውም  የአካል ጉዳት ደርሶበታል። የእኝህ  አረጋዊ አባት የሚለየውም  ከገደሏቸው በኋላ አንገታቸውን ገዝግዘው ሆዳቸውን ቀደው ጥለው  በመሄድ ለአስክሬናቸው  ጭምር ክብር ነፍገዋቸዋል። 18) ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ የጄና መብሩቁ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት አንድ አባወራ ቀን በሥራ የደከመ ሰውነታቸውን ለማሳረፍ  ሲጠብቁ የዋሉትን  ከብቶች  ወደ ማደሪያቸው  ካስገቡ በኋላ ምሽት 1:00 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች ከ2 ወንድሞቻቸው ጋር ከመኖሪያ ቤታቸው ወሰዷቸው። በዚያው ምሽት ከ2 ወንድሞቻቸው ጋር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በጫካ ውስጥ በመሣሪያ ተረሽነው ተገደሉ። አስከሬናቸውም በማግስቱ ሚያዝያ 13 ቀን ጠዋት ተገኝቶ ተቀበሩ። 19)   ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌከቀኑ 10:00 ሰዓት ወደ መስክ የተሰማሩ ከብቶቻቸውን ለማየት በወጡበት ቅጽበት የ80 ዓመት አዛውንቱ እና ለሥራ ፍለጋ ከሲዳማ ክልል የመጣው ወጣት በአክራሪ ታጣቂዎችመገደላቸው ተሰማ። የእነዚህ ምእመናን ሥርዓተ ቀብራቸው ሚያዝያ 19 ቀን በቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። 20) ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአሰኮ ወረዳ የአንዲትቀበሌ ነዋሪ ምእመን ተገደለ። እንደ እርሱ ሁሉ በተለያዩ አጋጠሚ ተገለው መረጃው የማይነገርላቸው በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አሉ። 21) ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

Открыть в Telegram
Просмотры738−37%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#1080Фото

Переслано из ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ይህ ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ ጥናትን መሰረት ያደረገ ዘገባ ነው! በአርሲ ያለችው ቤተ ክርስቲያን አምና በ2018 ዓ.ም ብቻ ስንት ልጆቿን አጣች? ስንት ልጆቿን ተጎዳች? ታሪክ የራሱ የሆነ የማይናወጥ ማኅደር አለው የትኛውንም ክስተት መዝግቦ ያስቀምጣል። ከእነዚህም መካከል የምርጫ ሰሞን እና የመንግሥትለውጥ ሂደቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በአክራሪ ኀይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በንጹሐን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸሙት ዘግናኝ ጥቃቶች የዓለምአቀፍ የዜና ምንጮችና የተቋማት ትኩረት የሳቡ ሃቅናቸው። ይህ አሰቃቂ እውነታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ የዜጎችን ሰብአዊ መብትና የመኖሪያ ዋስትና ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።ለአብነት ያህል ብናነሳ በ2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ዞን በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው የሰቆቃ ታሪክ በኀዘን የሚዘከር ሌላው የጭካኔ ምዕራፍ ሆኗል። በአካባቢው የተከናወኑት ሁነቶች ስልታዊ የሆነ አሰቃቂ የንጹሐን ግድያ፣ ማፈናቀል እና ንብረት ማውደም መልክ ይዘው እንመለከታለን።ምእመናን በእምነታቸው ብቻ ቤታቸው ውስጥ ታርደዋል፣ በጥይትም ተደብድበው  ተገድለዋል። ለዘመናት ያፈሩት ንብረታቸው ተዘርፏል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ንዋያተ ቅዱሳት  ተዘርፈውና  ጉዳት  ደርሶባቸው  ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። 

Открыть в Telegram
Просмотры709−40%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#1075Фото

እንኳን ለጥበበኛ፣ ሠዓሊ፣ ወንጌላዊ፣ ሐዋርያ፣ ሐኪምና ሰማዕት ቅዱስ ሉቃስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ። ቅዱሳት ሥዕላት በሐዲስ ኪዳን ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ለማሰየት አብነት የምናደርገው የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል የሣለልን የቅዱስ ገብርኤልና የቅድስት ኤልሳቤጥን ምስጋና የጻፈልን የእመቤታችንን ጸሎት የመዘገበልን መከራና ስደቷን የጻፈልን የቅዱሳን ሴቶች አገልግሎትን በክርስቶስ ፊት ምን እንደነበረ የነገረን ድንቅ ሐዋርያ የቅዱሳን ሐዋርያት ተጋድሎ የጻፈልን አባት ዛሬ መታሰቢያው ጥቅምት 22 ነው። የቻላችሁ ለየነቢጤ እንዳቅማችሁ በቅዱስ ሉቃስ እያላችሁ በመዘከር አስቡት በምልጃው እንዲረዳችሁ። በዘመናችን የተረሳው ሐዋርያና ወንጌላዊ በጣም ከሚያሳዝኑኛና ከሚያስቆጩኝ ነገሮች አንዱ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ውለታ ከዋሉት ቅዱሳን መካከል ዘመናት በየአራት ዓመቱ የሚቆጠርለት ይህ አባት አንድ ደብር በስሙ ለማግኘት ከባድ መሆኑ። ዛሬ በዓሉ ሆኖ እንኳ ብዙዎቻችን እርሱን በዕለተ ቀኑ መርሳታችን ያስቆጫል። እስቲ የምታውቁ ካላችሁ ታቦቱ በድርብ እንኳ የሚገኝበት ቦታ አሳውቁኝ። ከሌለ እስቲ ምን ብናደርግ ጥሩ ይመስላችኋል።

Открыть в Telegram
Просмотры1 380+18%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#1074Текст
Просмотры1 490+27%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#1073Текст
Просмотры1 370+17%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—

Все посты

Связи