Кабинет
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

Юзернейм
@ethiobooks
Категория
Книги
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики10 305
Просмотров на пост, 7 дн.688−36,2% к пред. 7 дн.
ERR6,68 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
14 нояб. 2026 г.1 237
16 нояб. 2026 г.984
18 нояб. 2026 г.935
20 нояб. 2026 г.914
21 нояб. 2026 г.856
23 нояб. 2026 г.623
24 нояб. 2026 г.516
25 нояб. 2026 г.363

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры1,26 тыс.
    Пересылки—
    Реакции4
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры1,23 тыс.
    Пересылки—
    Реакции4
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры1,22 тыс.
    Пересылки—
    Реакции5
    Комментарии—
  4. 04

    «ኦ... ያ_ _» ━•✦•━ ✍ ሕይወት እምሻው ' አፍላ ፍቅራቸውን እንደሚያጣጥሙ ወጣት ፍቅረኛሞች እጅ ለእጅ ተያይዘን ከምንወደው ካፌ እየወጣን ነበር፤ ላብ ያጠመቃቸው ጣቶቻችን ተሳስረው። ወደ ዋናው መንገድ ለመድረስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀሩን ግን በድንገት እጇን ከእጄ መንጭቃ አላቀቀችና፣ «እኔ እኮ አላምንም... ያ ያፌት አይደል እንዴ?!» አለች። ያፌት። የቀድሞ ፍቅረኛዋ። ከእኔ በፊት የነበረው ፍቅረኛዋ። በሄድንበት የሚከተለን፣ ከመሃከላችን የማይጠፋው ረዥም ጥላ። ከእኔ ጋር ዘጠኝ ወር በፍቅር ስንቆይ ከአፏ ልትነጥለው ግን አልቻለችም። ስሙን በሰበብ በአስባቡ ታነሳለች። 'ያፌት እንዲህ ብሎ።' 'ያፌት እንዲህ አድርጎ።' 'ያፌት ቢሆን እንዲህ ይል ነበር።' 'ያፌት ቢጠየቅ እንዲህ ያደርግ ነበር።' እኔ እና እሷ ባለንበት ቦታ ሁሉ፣ አብረን በምናሳልፋቸው ቅጽበቶች መሃከል ስሙ ዝቅ ተደርጎ እንደተከፈተ ለስላሳ ሙዚቃ ያጅበናል። ሳይጋበዝ አብሮን ይቀመጣል። አንድ ሆኖ  እንደ ብዙ ሰው ይከበናል። ነገር ግን እኔ ቀናተኛና በራሱ የማይተማመን ወንድ ስላልሆንኩ አይቼ እንዳላየ፣ ገብቶኝ እንዳልገባኝ አልፋታለሁ።             ☆    ☆    ☆ አንድ ጊዜ፣ በስሜት እየተወዘወዝኩ ረዥምና የሚያምር አንገቷን ከላይ እስከ ታች እየሳምኳት፣ «ኦ... ያ_ _» ስትለኝ ልቤ ለአፍታ ምት አቆመ። ደርቄ ቀረሁ። የሁኔታዬን መቀያየር ስትረዳ የሚርበተበቱ ከንፈሮቿን ወደ ከንፈሮቼ አስጠጋችና ትኩስ ትንፋሽዋን በመቀዝቀዝ ላይ ካለ ትንፋሼ ጋር  እየደባለቀች ሳቅ ብላ፣ «... ያ...ያበደ ነው...እንዳታቆም...»  አለችኝ። ልትል የነበረውን እያወቅኩ እንዳላወቅኩ መስዬ ይሄንንም አለፍኳት።             ☆    ☆    ☆ አሁን፣ በማላየው ገመድ ይጎትታት ይመስል ወደፊት፣ ወደ እርሱ ተንደረደረች። «አቦ ባላየኝ!» አለች ልትደርስበት እየተጣደፈች።  «ያየኝ ይመስልሃል? ካየኝ በጣም ይደብራል አይደል…? ማለቴ ከሌላ ወንድ ጋር ሲያገኘኝ?» ቃላቶቿ እርስ በርስ እስኪደራረቡ ፈጥና እየተናገረች ፈጥና ስትራመድ እኔም በዚያው ፍጥነት ከኋላዋ ተከተልኳት። ልትደረስበት ግን አልቻለችም። ያን ጊዜ ነው በድንገት፣ «ያፌት! አንተ ያፌት!» ብላ ጮኻ የጠራችው። እኔ ቆምኩ። በድንጋጤ። እሷ ሮጠች። ወደ እርሱ። ጥሪዋን ሰምቶ ዞር ሲል እንዳያት ፈገግ አለና፣ «እኔ እኮ አላምንም... ኮኪ?» ብሎ ፊቱን አዙሮ ወደ እሷ መምጣት ጀመረ። ተቃቀፉ። በኃይል። ተሳሳቁ። በጣም። የሁለቱም ፊት በድንገት የበራ መሰለ። በተለይ የእሷ። እኔ ግን ከናካቴው፣ ከነመፈጠሬም ተረሳሁ። እኔን በማያካትት የናፍቆትና የትዝታ ቅጽበት በሰከንዶች ከሚኖሩት አምባ ተደመሰስኩ። አይቼባት በማላውቀው መንገድ ተሽኮረመመች። እንደ ሆነ ነገር አደረጋት። ድምጿ እየሰለለና እየቀጠነ፣ አነጋገሯ ከዚህ በፊት በማላውቀው አኳኋን እየተሞላቀቀ ታዋራው ጀመር። ብዙ ደቂቃዎች እንዲህ ካለፉ በኋላ መኖሬን በድንገት እንዳስታወሰች ሁሉ ቁጣዬን እየታገልኩ ፈንጠር ብዬ በቆምኩበት መልከት አድርጋኝ፣ «በቃ ደውልልኝና እንገናኝ... አንጠፋፋ... ስልኬ ከጠፋብህ ያዘው... ያንተ ነገር ይሄኔ ደልተኸዋል» አለችው። ያፌት ስልክ ቁጥሯን ለመቀበል ጉጉት ያደረበት አይመስልም። ዓይኖቹ ከትከሻዋ ባሻገር እኔን ይመለከታሉ። እሷ ግን አላስተዋለችም። ዓይኗን በጨው አጥባ መቃበጡ ጊዜ አልሰጣትም።             ☆    ☆    ☆ ይህ በሆነ በሳምንቱ አንድ የጋራ ጓደኛችን ከያፌት ጋር "ገላኒ ኮፊ" እንዳያቸው ግራ በመጋባት ነገረኝ። ይህንን ግን ማለፍ አልቻልኩም። ያንኑ ዕለት ማታ ስንገናኝ አነሳሁባት። «ካንተ ጋር ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ልነግረው እኮ ነው ያገኘሁት» አለችኝ ፈርጠም ብላ። ሳቅ ታገለኝ። «በአሁን የፍቅር ሕይወታቸው ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ለቀድሞ ፍቅረኛቸው ደስተኛ ነኝ ማለት አይጠበቅባቸውም... ያውም በቀጠሮ» አልኳት። «ባክህ አንተ ደሞ... የሌለብህን ቅናት ዛሬ አትጀምር!» አለችኝ ባለማፈር። ረጅም ትንፋሽ ወሰድኩና ትኩር ብዬ ካየኋት በኋላ ለራሴም ባልገባኝ መንገድ ተረጋግቼ፣ «ኮኪ... አንድ ውለታ ዋይልኝ?» እልኳት። «የምን ውለታ?» «ለወደፊቱ ከአዲሱ ፍቅረኛሽ ጋር ሆነሽ መንገድ ላይ ብታዩኝ በሩቁ እጅሽን አውለብልበሽ ሰላም በይኝ እንጂ ሮጠሽ እንዳታቅፊኝ... እንደውም ጭራሽ ሰላም አትበዪኝ... ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ኑሮሽን ቀጥይ... እሺ?» አልኳት። ግራ እንደገባት ሁሉ ፊቷን አኮሳትራ፣ «ማለት... ምንድነው ምታወራው?...» ብላ ጠየቀችኝ። «የማወራውማ ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ የቀድሞ ፍቅረኛሽ ስለመሆኔ ነው!» ብዬ መለስኩላትና ለበላነውና ለጠጣነው የሚበቃ ገንዘብ ጠረጴዛው ላይ ትቼና ከወንበሬ ተነስቼ ወደ ሬስቶራንቱ በር አመራሁ። 'ያፌት' 'ያፌት' ማለት የሚወደው አንደበቷም ሆነ መቼም የእኔ ሆኖ የማያውቀው ውብ ገላዋ ስላልተከተሉኝ ደስ አለኝ። ━━━━━━━━ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

    Превью ссылки
    Просмотры1,12 тыс.
    Пересылки—
    Реакции8
    Комментарии—

Новые посты

#8954Превью ссылки

• የፍቅር ዓይነቶች • "Types of Love" ━━━🧡━━━ Colors of Love በተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1973 በታተመው መጽሐፉ J. A. Lee ስለ ስድስቱ የፍቅር ዓይነቶች ለንባብ አብቅቷል። 1. Eros Love፡ ኤሮስ ብዙውን ጊዜ የጾታ ፍቅር ወይም በአካል እርስ በርስ የሚፈላለጉ ሰዎች መካከል ሊቀሰቀስ የሚችለውን ስሜት ለመግለጽ የምንጠቀመበት ቃል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቃሉ የግሪክ ፍቅር አምላክ ስም ሆኖ ያገለግልም ነበር። ኤሮቲክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ስርወ-መሰረቱ ይህ እንደሆነ ልብ ይሏል። ይህ የፍቅር ዓይነት ሮማንቲክና ስሜታዊ የሆነ ፍቅር ሲሆን ለሕይወታችን በጣም አስፈላጊ የሆነ የፍቅር ዓይነት ነው። ይኽኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርጽና ቁንጅና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች ናቸው። 2. Ludus Love፡ ይኽ ቁርጠኝነት የማይታይበት በእንግሊዘኛው Game-playing or Uncommitted Love የሚሉት ሲሆን፤ የዚህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ሰዎች ዓላማቸው አንድ ብቻ ነው፣ ይኸውም የግል ፍላጎታቸውን ማስከበር ብቻ ነው። 3. Storge Love፡ ይኽ ቀስ በቀስ እየጠነከረ የሚመጣ የረጅም ጊዜ ግንኙነት ውጤት ነው። በዚህ ዓይነት ፍቅር የተጠመዱ ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን በጋራ ማሳለፍ ይወዳሉ። 4. Pragma Love፡ የዚህ ዓይነት ፍቅር ጣራና መሰረቱ “የጋራ ጥቅምና መመሳሰል” የሚሉት ቃላት ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ ፍቅር ስሜታዊ አይደለም። ምክኒያቱም እነዚህ ፍቅረኛሞች የሚመሩት በሎጂክ ነውና። ብዙ ሰዎች በሥራ ቦታ አብረዋቸው ከሚውሉ ሰዎች ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚጀሚሩትም ለዚሁ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ እሷ የተማረች ከሆነ የምትመርጠው የተማረ ወንድን ነው። ወንዱም እንደዚሁ። 5. Mania Love፡ ይኽ ዓይነቱ ደግሞ በጣም አስቸጋሪና “እሱን/እሷን ካላገኘሁ እሞታለሁ” የሚያሰኝ ሲሆን በእንግሊዘኛው Obsessive or Possessive Love የሚባለው ነው። ለምሳሌ፦ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ይኽ ዓይነቱ ፍቅር ነው። 6. Agape Love፡ ይኽ ዓይነቱ ፍቅር መተሳሰብ የተሞላበት፣ ከመቀበል ይልቅ መስጠት ላይ የሚያደላ፣ ወንድማዊ የሆነና ከራስ ወዳድነት የፀዳ ነው። እንደዚህ ዓይነቱን ፍቅር ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ፦ ማዘር ቴሬዛ ለተቸገሩ ሰዎች ያሳዩት የነበረው ፍቅር ይኽን ዓይነቱን ፍቅር ነበር። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ወንዶች በአመዛኙ Ludus የተሰኘውን የፍቅር ዓይነት የሚያሳዩ ሲሆን ሴቶች ደግሞ Storge እና Pragma በተሰኙት የፍቅር ዓይነቶች ይያዛሉ። ━━━━━━━━━━━━ ምንጭ ➢ ድረ-ገጽ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

Открыть в Telegram
Просмотры376−55%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#8952Фото

💬 ❝የፍቅር ቦታው ልብ ነው፤ ልብ ደግሞ ንፁህ ወርቅ ነው።❞ ሼህ ሙዛፊር 💬 ❝ፍቅር ማለት ሰዎች ነገሮች ሲሳኩላቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የገቡ እንዲመስላቸው የሚያደርግ ጊዜያዊ እብደት ነው።❞ አምብሮይስ ቢርስ 💬 ❝የሰው ልጅ የፍቅር ውሃ እየጠጣ ባይለመልም ኖሮ በአዳም ዘመን ደርቆ በረገፈ ነበር።❞ ዊልያም ጀምስ 💬 ❝ፍቅር፣ በተለይም ከቆንጆ ሴት ጋር የሚያከንፍ ፍቅር፣ "ወርቅ አልፈልግም፣ አልማዝ ካልሆነ በስተቀር" የሚባልበት የሰው ልጆች ራስ ማታለያና ከንቱ ድካም ነው።❞ ኦስካር ዋይልድ 💬 ❝ለማንኛውም የሰው ልጅ የምግባር በሽታ ጠንካራው መድኃኒት ፍቅር ብቻ ነው።❞ ራማያና 💬 ❝አንድ ወንድ አንዲት ሴት ሲያፈቅርና ያቺም ሴት ያን ወንድ ስታፈቅር፣ መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው በጎጇቸው እየኖሩ የደስታ መዝሙራቸውን ያንቆረቁራሉ።❞ ብራህማ 💬 ❝ፍቅር ማለት ሁለት አካል በአንድ ነፍስ ውስጥ ሲታቀፍ ነው።❞ ፕሌቶ 💬 ❝ፍቅረኞች ዓለምን ረስተው ዓለማቸውን የሚቀጩ ይመስላቸዋል እንጂ፤ ዓለም ምን ያህል እንደምትረሳቸው አይታወቃቸውም።❞ ማቲው አርኖልድ 💬 💬 ጥቅሶች @ethiobooks

Открыть в Telegram
Просмотры554−33%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#8950Превью ссылки

ፍቅርና ፍቅረኞች ━━•✦•━━ ✍ መስፍን ሀብተማርያም ' በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አንድ አስደናቂ ነገር ፖላንድ ውስጥ እንደተፈፀመ "ሪደርስ ዳይጀስት" በተባለው መጽሔት ላይ ሰፍሮ ተመልክቻለሁ። የናዚ ጀርመን አምባገነንነት በሰፈነባት አውሮፓ ብዙ ሰዎች በየጊዜው ከአሰቃቂ እስር ቤቶች እየተወሰዱ ይረሸኑ ነበር። እና በአንድ ወቅት ከሁለት መቶ የማያንሱ እስረኞች እንዲወጡ ይታዘዙና ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ትተው ሌሎቹን ሊገድሉ ተዘጋጁ። የሚጠበቀው የኮሎኔሉ ትዕዛዝ ብቻ ነበር። ኮሎኔሉ ትዕዛዝ ሊሰጥ ሲል አንድ ኮሳሳ ሽማግሌ «እባክህ ኮሎኔል! ፍቀድልኝና ለአንዲት ደቂቃ ልናገር!» ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጠየቁ። «በል ፈጠን በል ተፈቅዶልሃል!» አላቸው ኮሎኔሉ። «ያንን ወጣት ተመልከተው» አሉ አዛውንቱ «በአንድ እስር ቤት ለሁለት ዓመት ኖረናል። ሚስቱን እንደሚያፈቅር ሌት ከቀን ይነግረኝ ነበር። ሙሽርነቱን ገና ጠግቦ ሳይጨርስ ነበር የታሰረው። ስለዚህ ዘወትር ሚስቱን እያነሳ ያለቅሳል፤ ይብሰለሰላል። ምግቡን እንኳን አጣጥሞ በልቶ አያውቅም። ፈገግታ ከረሳ ቆይቷል። ስለዚህ አሁን እንድትፈቅድልኝ የምጠይቅህ ... እኔ ሞቴን የምጠብቅ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴንና ልጆቼን ቀብሬያለሁ። እባክህ በሱ ምትክ እኔ ልገደል። እሱን ግን አንድ ቀን ሚስቱን ለማግኘት በቅቶ ፍቅሩን እንዲጨርስ እድል ስጠው።» በዚህ አነጋገር ኮሎኔሉ ልቡ ተነክቶ እንባ ተናነቀውና ሊረሸኑ የተወሰነባቸውን ሁሉንም ምሕረት አደረገላቸው። ፍቅር የሚሉት ነገር ይሄን ያስደርጋል? ወደ ሌላ አጋጣሚ ደግሞ እንለፍ። አንድ ሰውዬ ነበረ። ይሄ ሰው ሳይቤሪያ አምስት ዓመታት ታስሮ በሕይወት መቆየቱ ያስገረማቸው የሶቪየት ባለስልጣኖች «ሌሎች የእስር ቤት ጓደኞችህ በበረዶ እየተሰቃዩ ሲሞቱ አንተ እንዴት ተቋቋምከው?» ሲሉ ጠየቁት። «ሚስቴን ሁልጊዜ ስለማስብ ብርዱ እምብዛም አይሰማኝም!» በማለት ነበር እርሱም ምስጢሩን የገለፀላቸው። ...  ❝ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው፣ ከድንጋይ ይከብዳል ለተሸከመው ሰው።❞ ከተባለለት ወዲያ ኃይለኝነቱ መች ይጠየቃል። >>> ━━━━━━━━━━━  📔 እፍታ - ቅፅ 1 (44 ትረካዎች) 📄 197 - 198 🗓 1991 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

Открыть в Telegram
Просмотры664−20%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—

Все посты

Связи