• የፍቅር ዓይነቶች • "Types of Love" ━━━🧡━━━ Colors of Love በተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1973 በታተመው መጽሐፉ J. A. Lee ስለ ስድስቱ የፍቅር ዓይነቶች ለንባብ አብቅቷል። 1. Eros Love፡ ኤሮስ ብዙውን ጊዜ የጾታ ፍቅር ወይም በአካል እርስ በርስ የሚፈላለጉ ሰዎች መካከል ሊቀሰቀስ የሚችለውን ስሜት ለመግለጽ የምንጠቀመበት ቃል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቃሉ የግሪክ ፍቅር አምላክ ስም ሆኖ ያገለግልም ነበር። ኤሮቲክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ስርወ-መሰረቱ ይህ እንደሆነ ልብ ይሏል። ይህ የፍቅር ዓይነት ሮማንቲክና ስሜታዊ የሆነ ፍቅር ሲሆን ለሕይወታችን በጣም አስፈላጊ የሆነ የፍቅር ዓይነት ነው። ይኽኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርጽና ቁንጅና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች ናቸው። 2. Ludus Love፡ ይኽ ቁርጠኝነት የማይታይበት በእንግሊዘኛው Game-playing or Uncommitted Love የሚሉት ሲሆን፤ የዚህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ሰዎች ዓላማቸው አንድ ብቻ ነው፣ ይኸውም የግል ፍላጎታቸውን ማስከበር ብቻ ነው። 3. Storge Love፡ ይኽ ቀስ በቀስ እየጠነከረ የሚመጣ የረጅም ጊዜ ግንኙነት ውጤት ነው። በዚህ ዓይነት ፍቅር የተጠመዱ ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን በጋራ ማሳለፍ ይወዳሉ። 4. Pragma Love፡ የዚህ ዓይነት ፍቅር ጣራና መሰረቱ “የጋራ ጥቅምና መመሳሰል” የሚሉት ቃላት ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ ፍቅር ስሜታዊ አይደለም። ምክኒያቱም እነዚህ ፍቅረኛሞች የሚመሩት በሎጂክ ነውና። ብዙ ሰዎች በሥራ ቦታ አብረዋቸው ከሚውሉ ሰዎች ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚጀሚሩትም ለዚሁ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ እሷ የተማረች ከሆነ የምትመርጠው የተማረ ወንድን ነው። ወንዱም እንደዚሁ። 5. Mania Love፡ ይኽ ዓይነቱ ደግሞ በጣም አስቸጋሪና “እሱን/እሷን ካላገኘሁ እሞታለሁ” የሚያሰኝ ሲሆን በእንግሊዘኛው Obsessive or Possessive Love የሚባለው ነው። ለምሳሌ፦ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ይኽ ዓይነቱ ፍቅር ነው። 6. Agape Love፡ ይኽ ዓይነቱ ፍቅር መተሳሰብ የተሞላበት፣ ከመቀበል ይልቅ መስጠት ላይ የሚያደላ፣ ወንድማዊ የሆነና ከራስ ወዳድነት የፀዳ ነው። እንደዚህ ዓይነቱን ፍቅር ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ፦ ማዘር ቴሬዛ ለተቸገሩ ሰዎች ያሳዩት የነበረው ፍቅር ይኽን ዓይነቱን ፍቅር ነበር። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ወንዶች በአመዛኙ Ludus የተሰኘውን የፍቅር ዓይነት የሚያሳዩ ሲሆን ሴቶች ደግሞ Storge እና Pragma በተሰኙት የፍቅር ዓይነቶች ይያዛሉ። ━━━━━━━━━━━━ ምንጭ ➢ ድረ-ገጽ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Open in Telegram
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 14, 2026 | 1,237 |
| Nov 16, 2026 | 984 |
| Nov 18, 2026 | 935 |
| Nov 20, 2026 | 914 |
| Nov 21, 2026 | 856 |
| Nov 23, 2026 | 623 |
| Nov 24, 2026 | 516 |
| Nov 25, 2026 | 363 |
Most viewed this month
- 01Views1.26KForwards—Reactions4Comments—
- 02Views1.23KForwards—Reactions4Comments—
- 03Views1.22KForwards—Reactions5Comments—
- 04Views1.12KForwards—Reactions8Comments—
Latest posts
💬 ❝የፍቅር ቦታው ልብ ነው፤ ልብ ደግሞ ንፁህ ወርቅ ነው።❞ ሼህ ሙዛፊር 💬 ❝ፍቅር ማለት ሰዎች ነገሮች ሲሳኩላቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የገቡ እንዲመስላቸው የሚያደርግ ጊዜያዊ እብደት ነው።❞ አምብሮይስ ቢርስ 💬 ❝የሰው ልጅ የፍቅር ውሃ እየጠጣ ባይለመልም ኖሮ በአዳም ዘመን ደርቆ በረገፈ ነበር።❞ ዊልያም ጀምስ 💬 ❝ፍቅር፣ በተለይም ከቆንጆ ሴት ጋር የሚያከንፍ ፍቅር፣ "ወርቅ አልፈልግም፣ አልማዝ ካልሆነ በስተቀር" የሚባልበት የሰው ልጆች ራስ ማታለያና ከንቱ ድካም ነው።❞ ኦስካር ዋይልድ 💬 ❝ለማንኛውም የሰው ልጅ የምግባር በሽታ ጠንካራው መድኃኒት ፍቅር ብቻ ነው።❞ ራማያና 💬 ❝አንድ ወንድ አንዲት ሴት ሲያፈቅርና ያቺም ሴት ያን ወንድ ስታፈቅር፣ መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው በጎጇቸው እየኖሩ የደስታ መዝሙራቸውን ያንቆረቁራሉ።❞ ብራህማ 💬 ❝ፍቅር ማለት ሁለት አካል በአንድ ነፍስ ውስጥ ሲታቀፍ ነው።❞ ፕሌቶ 💬 ❝ፍቅረኞች ዓለምን ረስተው ዓለማቸውን የሚቀጩ ይመስላቸዋል እንጂ፤ ዓለም ምን ያህል እንደምትረሳቸው አይታወቃቸውም።❞ ማቲው አርኖልድ 💬 💬 ጥቅሶች @ethiobooks
Open in Telegramፍቅርና ፍቅረኞች ━━•✦•━━ ✍ መስፍን ሀብተማርያም ' በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አንድ አስደናቂ ነገር ፖላንድ ውስጥ እንደተፈፀመ "ሪደርስ ዳይጀስት" በተባለው መጽሔት ላይ ሰፍሮ ተመልክቻለሁ። የናዚ ጀርመን አምባገነንነት በሰፈነባት አውሮፓ ብዙ ሰዎች በየጊዜው ከአሰቃቂ እስር ቤቶች እየተወሰዱ ይረሸኑ ነበር። እና በአንድ ወቅት ከሁለት መቶ የማያንሱ እስረኞች እንዲወጡ ይታዘዙና ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ትተው ሌሎቹን ሊገድሉ ተዘጋጁ። የሚጠበቀው የኮሎኔሉ ትዕዛዝ ብቻ ነበር። ኮሎኔሉ ትዕዛዝ ሊሰጥ ሲል አንድ ኮሳሳ ሽማግሌ «እባክህ ኮሎኔል! ፍቀድልኝና ለአንዲት ደቂቃ ልናገር!» ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጠየቁ። «በል ፈጠን በል ተፈቅዶልሃል!» አላቸው ኮሎኔሉ። «ያንን ወጣት ተመልከተው» አሉ አዛውንቱ «በአንድ እስር ቤት ለሁለት ዓመት ኖረናል። ሚስቱን እንደሚያፈቅር ሌት ከቀን ይነግረኝ ነበር። ሙሽርነቱን ገና ጠግቦ ሳይጨርስ ነበር የታሰረው። ስለዚህ ዘወትር ሚስቱን እያነሳ ያለቅሳል፤ ይብሰለሰላል። ምግቡን እንኳን አጣጥሞ በልቶ አያውቅም። ፈገግታ ከረሳ ቆይቷል። ስለዚህ አሁን እንድትፈቅድልኝ የምጠይቅህ ... እኔ ሞቴን የምጠብቅ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴንና ልጆቼን ቀብሬያለሁ። እባክህ በሱ ምትክ እኔ ልገደል። እሱን ግን አንድ ቀን ሚስቱን ለማግኘት በቅቶ ፍቅሩን እንዲጨርስ እድል ስጠው።» በዚህ አነጋገር ኮሎኔሉ ልቡ ተነክቶ እንባ ተናነቀውና ሊረሸኑ የተወሰነባቸውን ሁሉንም ምሕረት አደረገላቸው። ፍቅር የሚሉት ነገር ይሄን ያስደርጋል? ወደ ሌላ አጋጣሚ ደግሞ እንለፍ። አንድ ሰውዬ ነበረ። ይሄ ሰው ሳይቤሪያ አምስት ዓመታት ታስሮ በሕይወት መቆየቱ ያስገረማቸው የሶቪየት ባለስልጣኖች «ሌሎች የእስር ቤት ጓደኞችህ በበረዶ እየተሰቃዩ ሲሞቱ አንተ እንዴት ተቋቋምከው?» ሲሉ ጠየቁት። «ሚስቴን ሁልጊዜ ስለማስብ ብርዱ እምብዛም አይሰማኝም!» በማለት ነበር እርሱም ምስጢሩን የገለፀላቸው። ... ❝ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው፣ ከድንጋይ ይከብዳል ለተሸከመው ሰው።❞ ከተባለለት ወዲያ ኃይለኝነቱ መች ይጠየቃል። >>> ━━━━━━━━━━━ 📔 እፍታ - ቅፅ 1 (44 ትረካዎች) 📄 197 - 198 🗓 1991 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Open in Telegram






