Forwarded from Qualitymovbot
ነፃ internet 🌐ተመልሷል ለመጠቀም ከስር ያለውን free internet የሚለውን ነክታቹ join በማለት መጠቀም ትችላላቹ
Open in Telegram
🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹 ➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1 Since 2011 E.C.
By publication day
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 31, 2026 | 5,460 |
| Nov 26, 2026 | 32 |
Forwarded from Qualitymovbot
ነፃ internet 🌐ተመልሷል ለመጠቀም ከስር ያለውን free internet የሚለውን ነክታቹ join በማለት መጠቀም ትችላላቹ
Open in TelegramForwarded from Qualitymovbot
🔥 በየቀኑ የተለያዩ ምርጥ ምርጥ ቀመሮች ማግኘት ከፈለጋቹ ተቀላቀሉን Win ማረግ ከፈለጉ 🔥 👇👇👇👇 https://t.me/+yPYuSN6dJJc0OGE0 https://t.me/+yPYuSN6dJJc0OGE0 https://t.me/+yPYuSN6dJJc0OGE0
Open in TelegramForwarded from ሳሎዳ ትሬዲንግ ️
📌 እስማርት ካቢኔት ሎክ ☎️ ለማዘዝ +251914855557 ☎️ Facebook: https://www.facebook.com/salodatrading Instagram: https://www.instagram.com/saloda_trading Telegram: https://t.me/saloda_trading Tiktok: https://www.tiktok.com/@salodatrading
Open in TelegramForwarded from ሳሎዳ ትሬዲንግ ️
🏡✨ ቤትዎን የቅንጦት መልክ ለማላበስ እየፈለጉ ነው? 🤩 SALODA TRADING ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የUV Board የግድግዳና የወለል ፓነሎች ያቀርብልዎታል! ✅ ዘመናዊና ማራኪ ዲዛይን ✅ ውብና የተለያዩ የቀለም አማራጮች ✅ ለማጽዳት ቀላል ✅ ውሃን የሚቋቋም ገጽታ ✅ ለቤትዎና ለንግድ ቦታዎ ተስማሚ 📏 መጠን፦ 1220 × 2440 ሚሜ 📐 ውፍረት፦ 3 ሚሜ 📍 አድራሻችን፦ ፒያሳ፣ ጎጋን ህንፃ፣ የመሬት ወለል D38 📞 ለትዕዛዝና ለተጨማሪ መረጃ ፦ 09 14 85 55 57 ✨ SALODA TRADING ጥራት ያለው እቃ፣ ውበት ያለው ቤት! #SalodaTrading #UVBoard #የቤትውበት #ዘመናዊዲዛይን #የግንባታእቃዎች #AddisAbaba
Open in TelegramForwarded from ሳሎዳ ትሬዲንግ ️
📌 በተለያዩ የከለር አማራጮች ያገኛሉ። ፍፁም ጥንቅቅ ላለ ሥራ " ላንተ 🫵 “ስራዎት ያቅልሉ " ሳሎዳ ትሬዲንግ ☎️.... ይደውሉ ይዘዙን... ☎️ @Salodatrading Contact us:-📞 +251914855557 💬 ማንኛዉም የዕቃ ዋጋ ለማወቅ @Salodatrading @Salodatrading
Open in Telegram . ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️ 💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞 #ክፍል_5 ...🖊ለመጀመሪያ ጊዜ ዎክ ካደረግን በኋላ ማክሰኞ የኔ እና የኢክራም ዉድ ቀን ሆነች። ማክሰኞ ኢክራም ከሀይማኖታዊ ትምህርት ነፃ የምትሆንበት ቀን ነዉ። ሌሎቹን ቀናት ጁምዓን ሳይጨምር መስጂድ ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን ትማራለች። ሁሌም ማክሰኞ አስር ሰዓት ላይ ተገናኝተን እስከ አስራሁለት ሰአት ድረስ አብረን እናሳልፋለን። አስራሁለት ሰዓት ሲሞላ እናቷ ከስራ ስለምትመጣ ወደ ቤቷ እሸኛታለሁ። እናቷ ከስራ አርፍዳ የምትመጣ ቀን ኢክሩ እስከ አንድ ሰአት ድረስ ከኔ ጋር አርፍዳ ወደ ቤቷ ትገባለች። ከኔ ከተለየች በኋላ ወደ ቤቷ ስትገባ እናቷ እስከምትመጣ ድረስ ብቻዋን ቤት ዉስጥ እንደምትቀመጥ ሳስበዉ ለሷ እኔ እታመማለሁ። ከብቸኝነት በላይ ህመም የለም። የሚያዳምጠን ሰዉ ከማጣት በላይ ስቃይ አይኖርም። . አንድ ቀን ከኢክሩ ጋር ሁሌም ወደምንቀመጥበት ከሰፈራችን ትንሽ ዝቅ ብሎ ወዳለዉ ሰፊ የሳር ሜዳ ሄድን። ሜዳዉ ላይ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች አሉ። ከሜዳዉ ራቅ ብሎ ደግሞ ልክ እንደኛ የአካባቢዉን ከሰዉ አይን የራቀ መሆን ፈልገዉ የመጡ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ሁሌም እንደምናደርገዉ ከክቡ የድንጋይ ቋጥኝ አጠገብ ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን። ኢክሩ ድብር ብሏታል። ቀስ ብዬ "ኢክሩዬ ስለምን እያሰብሽ ነዉ?" አልኳት። እንባ እየተናነቃት "ፈዊ እናቴ ላይ ሸክም እንደሆንኩባት እየተሰማኝ ነዉ።" አለችኝ። እየሳቅኩ "ኢክሩዬ እናት ላይ እንዴት ሸክም ይኮናል? እናቶቻችን እኮ ሁሌም እኛን ለመንከባከብ አይታክቱም።" አልኳት። አንገቷን በአሉታ እየነቀነቀች እንዳልተረዳኋት ገልፃልኝ ማብራራቷን ቀጠለች። "ፈዊ እናቴ በጣም ወጣት ናት። አንድ ላይ ብታየን እህትማማቾች እንጂ እናት እና ልጅ አንመስልህም። እሷ የማታገባዉ ባል ጠፍቶ አይደለም ግን እኔን ከእንጀራ አባት ጋር ማኖር ከብዷት ነዉ። እራስ ወዳድ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፣ በእናቴ መቅለጥ ነዉ እየፈካሁ ያለሁት።" ንግግሯ በእንባ መታጀብ ጀምሯል። ወይኔ ሰዉ ሲያለቅስም እንዲህ ያምራል? ወንድነቴን አደብ አስገዝቼ በለቅሶ የታጀበ ንግግሯን ማዳመጤን ቀጠልኩ። "ፈዊ እኔ ባገባ እኮ ማማ ያለስጋት አግብታ መኖር ትችል ነበር። ግን እኔ አሁንም እንደ ልጅ እየተጨማለቅኩ የሷን ህይወት እየቀማኋት ነዉ።" ብላ እንባዋን መጥረግ ጀመረች። አሁን የኢክራምን ዉበት ያየ በዚህ ሁሉ ችግር ዉስጥ እየተፈተነች ያለች ይመስለዋል? በፍፁም አይመስለዉም። ኢክሩ ከተረጋጋች በኋላ ጭንቀቷን እንድትረሳዉ ብዬ ስላሳለፍነዉ የፍቅር ታሪክ እንድንጨዋወት ጠየቅኳት። እሷ ከዚህ በፊት ብዙ ያፈቅሯት የነበሩ ልጆች የነበሩ ቢሆንም የሚነገር የፍቅር ታሪክ እንደሌላት ነገረችኝ። እኔ በልጅነቴ ስላፈቀርኳት መርየም ስለምትባል ልጅ አጫወትኳት። ታሪኩን ከነገርኳት በኋላ "ኢክሩዬ ለመርየም ካደረግኳቸዉ ነገሮች ዉስጥ የቱ እንደሚገርመኝ ታዉቂያለሽ?" አልኳት። እንድቀጥልላት ምልክት ሰጠችኝ "ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነዉ። አንድ ቀን ናቲ የሚባል ጓደኛችን አስተማሪ ገርፎት ክፍል ዉስጥ እየተንሰቀሰቀ ያለቅሳል። መርየም እና ጓደኛዋ ናቲን ሲያባብሉት አየሁ። መርየም አይዞህ እያለች ስትንከባከበዉ ሳይ ናቲን መሆን ተመኘሁ። በቀጣዩ ክፍለጊዜ ሰበብ ፈልጌ ከአስተማሪ ጋር ተጣላሁ። ግን አስተማሪዋ አልገረፈችኝም። ተቆጥታኝ አለፈችኝ። እኔ ግን አላማዬ የመርየምን ማፅናኛ ማግኘት ስለነበር ተንሰቅስቄ አለቀስኩ።" ኢክራም ሳቅ እያፈናት "እና መርየም አባበለችህ?" አለችኝ። "ባክህ ዝም በል" አለችኝ ስላት ኢክሩ እንባዋ ከአይኗ እስኪፈስ ድረስ እየተንከተከተች ሳቀች። ኢክሩ ስትስቅ በጣም ታምራለች። በዛ ላይ ደግሞ ሳቋን ሊያጅቡ እንባዎቿ ከዉብ አይኖቿ ሲፈሱ በጣም ለየት ያለ ዉበት አላት። ኢክሩን እንደዛ ቀን ስትስቅ አይቻት አላዉቅም። ሌላም እንደዚህ የሚያስቅ ታሪክ በኖረኝ እና ነግሬያት እንዲህ ስትፍለቀለቅ ባየኋት ብዬ ተመኘሁ። . ከኢክራም ጋር ወንድሟ ሆኜ ሀዘኗን እየተካፈልኳት እና ጭንቀቴን እያማከርኳት ለሁለት ወር ቆየን። አንድ ቀን እንደለመድነዉ ተገናኝተን ተጨዋዉተን ከተለያየን በኋላ ኢክሩ ፌስቡክ ላይ የሚያስደነግጥ መልዕክት ላከችልኝ። "ፈዊ የእኔ እና አንተ ሁሌ መገናኘት ጥቅሙ አልታይሽ ብሎኛል። ቢቀርብን የሚሻል ይመስለኛል።" ይላል መልዕክቷ!! ግራ ገባኝ ኢክሩ ከኔ ጋር ስትሆን ሁሌም ደስተኛ ነበረች። ዛሬ ምን ተገኘና በቃኸኝ አለችኝ? ዉስጤ ተረበሸ። እኔ ሳዉቅ ለሷ ጥሩ ወንድም ነበርኩ። ቢሆንም አልተበሳጨሁባትም በአካል አግኝቼ ላዋራት ወሰንኩ። ደወልኩላት እንደተለመደዉ እየተፍለቀለቀች አናገረችኝ። ላናግራት እንደምፈልግ ነግሬያት በነጋታዉ ሰፈራችን ዉስጥ ያለዉ ቤተ መፅሀፍ ለመገናኘት ተቀጣጠርን። . በነገራችን ላይ የኛ ሰፈሩ ቤተ መፅሀፍ ማንበቢያ ከሚባል ይልቅ የወንድና ሴቶች መቀጣጠሪያ ቢባል የሚገልፀዉ ይመስለኛል። ለማንበብ ከሚመጣዉ ሰዉ በቁጥር የማያንሱ ቤተ መፅሀፍ ተቀጣጥረዉ የሚገናኙ ጥንዶች አሉ። የሰዉ ልጅ ለአንድ አላማ የተለያዩ ቦታዎች ይሄዳል አላልኳችሁም ነበር? ይኸዉ ቤተ መፅሀፍ እንኳ አልተረፈም። መጣበሻ ሆኗል። እኔና ኢክሩ ቤተ መፅሀፍ የተቀጣጠርነዉ እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን የምወስድበት ጊዜ ስለተቃረበ እና በንባብ ተጠምጄ ስለነበር ነዉ። በነጋታዉ ኢክሩ ደዉላ ከቤተ መፅሀፉ እንድወጣ ነገረችኝ። ስወጣ በር ላይ ቆማለች። የቤተ መፅሀፉ አጥር ላይ ወዳለዉ መቀመጫ ሄደን ስለላከችልኝ መልዕክት ማብራሪያ እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት። "ፈዊ መገናኘታችን ትርጉሙ አልገባኝም። በስልክ ከተደዋወልን የሚበቃ ይመስለኛል።" አለችኝ። ስታወራ ይብቃን ሳይሆን እንቀጥል የምትል ነዉ የምትመስለዉ። ትኩር ብዬ ተመለከትኳት ፣ በረዥሙ ተነፈስኩና "ኢክሩዬ አብሬሽ በወንድምነት ያሳለፍኩት ጊዜ በጣም ደስ ይል ነበር። አንቺ በቃኝ ካልሽ ግን ዉሳኔሽን አከብራለሁ።" ብዬ እስከ ቤቷ ድረስ እንደተለመደዉ ሸኝቼ ተሰናበትኳት። ከዚህ ቀን ጀምሬ ኢክራም ጋር መደወል አቆምኩ። በሰዓቱ ለፈተና እየተዘገጃጀሁ የነበረ መሆኑ ብዙም ስለ ኢክራም እንዳላስብ ረዳኝ። ሰዉ መለማመጥ አልወድም። ኢክራም ከበቃት በቅቷታል አለቀ። ደግሞ ምንም የተለየ ነገር አልነበረንም። ግን የእኔ እና እሷ የመገናኛ ዉድ ቀን ማክሰኞን በጉጉት ትናፍቅ የነበረችዉ ኢክራም ይብቃን ያለችበት ምክንያት ምንድነዉ? ኢክሩ ልታገባ ነዉ? ፍቅረኛ ልትይዝ ነዉ? ለምን? ምክንያት እንዳለዉ ገብቶኛል። ግን ምን እንደሆነ አላዉቅም። #ይቀጥላል... https://t.me/+kahGvq58K6k5ZTU0 ✎ ክፍል ስድስት (6) ይቀጥላል❤️🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ። ┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄
Open in TelegramForwarded from ሳሎዳ ትሬዲንግ ️
📌 4 in 1 positioning ruler ☎️ ለማዘዝ +251914855557 ☎️ Facebook: https://www.facebook.com/salodatrading Instagram: https://www.instagram.com/saloda_trading Telegram: https://t.me/saloda_trading Tiktok: https://www.tiktok.com/@salodatrading
Open in Telegram. ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️ 💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞 #ክፍል_4 ...🖊የኢክራምን ስልክ የሪም እድሜ ይርዘምና ምንም ሳልለፋ አገኘሁት። በነጋታዉ ኢክራምን ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ላወራት ደወልኩ። ስታወራ ደስ ትላለች። አዳማጭ ብቻ ሆና አታስጨንቅም። አስራስድስት ደቂቃ አወራን ፣ ከማላዉቃት ሴት ጋር ያዉም ለመጀመሪያ ጊዜ እያወራን ይህን ሁላ ደቂቃ ማናገሬ ገርሞኛል። በሁለተኛዉ ቀን ደዉዬ ስናወራ "ኢክሩ ግን ትኮሪያለሽ አይደል?" አልኳት። "ምነዉ? ምናጠፋሁ?" አለችኝ ግራ እየተጋባች። "አንቺ መች ታስታዉሺኛለሽ፣ ኧረ አንቺም ፈልጊኝ!!" አልኳት። ሁሉም ነገር እኮ በአንድ ወገን በኩል ብቻ ሲሆን ያስጠላል። ሰጥቶ እንደመቀበል የሚያስደስት ነገር የለም። አንዳንዶች ሁሌ እንድትሰጧቸዉ ብቻ ይፈልጋሉ። እነሱ ግን በምላሹ ምንም አይሰጧችሁም። ይሄ የወዳጅነት ትስስርን ይነቀንቃል። እኔም እኔ ብቻ ስደዉል እኔ ብቻ ፈላጊ እንደሆንኩ ስለተሰማኝ ነዉ እንዲህ ያልኳት። ኢክሩ እየተቅለሰለሰች "ኧረ አልኮራም፣ እደዉላለሁ ችግር የለዉም ፈዉዛኔ!!" አለችኝ። ከዚህ ቀን ጀምሮ በተራ መደዋወል ጀመርን። እኔ ዛሬ ከደወልኩ እሷ ነገ ትደዉላለች። በስልክ በምናወራበት ሰአት ስለሷ አንዳንድ ነገሮችን አወቅኩ። አባቷ በህይወት የለም። ወንድምም ሆነ እህት የላትም። ከእናቷ ጋር ብቻቸዉን ነዉ የሚኖሩት። ብቸኛ ወዳጇ ፊልም ነዉ። ሲደብራት ተከታታይ ፊልሞችን ዲሽ ላይ ትከታተላለች። ፊልም ነዉ ያሳደጋት። ፊልም እያየች አድጋ ነዉ እኔም ላይ ቆንጆ ፊልም የሰራችብኝ!! ያየችዉን ነዉ የተገበረችብኝ!! . ኢክራም ታሪኳን ስትነግረኝ ምናልባት በህይወቷ ዉስጥ ያጣችዉን ወንድሟን ሆኜ ብቸኝነቷን ላስረሳት አሰብኩ። የጅንጀና ሙዴ ሁሉ ተጦለበ። በቃ ንፁህ ወንድሟ ለመሆን አለምኩ። አንድ ቀን ማታ ላይ ኡስማን ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ወደ ሰፈር እየገባን ስሟን ሳልነግረዉ ታሪኳን አጫወትኩትና ከኔ ይልቅ እሱ ሴት መንከባከብ ስለሚችል እንደዉም ባስተዋዉቃቸዉና እሱ ቢንከባከባት ደስ እንደሚለኝ ነገርኩት። ኡስማን ደግሞ በጣም የምወደዉ መስጂድ የተዋወቅኩት ጓደኛዬ ነዉ። ታሪኳን ከነገርኩት በኋላ እሱም ልቡ ተነክቶ "ፈዉዛኔ እቺን ምርጥ ሀብታም ፈልጎ አሁኑኑ መዳር ነዉ!!" አለኝ። በሰፊዉ እንደምናወራበት ተነጋግረን ከኡስማን ጋር ተለያየን። ከዛ በኋላ ግን ከኡስማን ጋር ስለሷ አዉርቼ አላዉቅም። ኡስማን ወንድ ነዉ ግን እዉነት ለመናገር ለሴት ከንፈሯ ሲያምር ምናምን እንደምንለዉ ፀጉሩ፣ መልኩ በአጠቃላይ የሚያምር ልጅ ነዉ። በጣም ደግሞ ተግባቢ ነዉ። በጣም ብዙ ሴቶች የሚመኙት ወንድ ነዉ። ኢክሩን እንዲንከባከባት ያሰብኩት ከዚህ በፊት ካለዉ ልምድ ተነስቼ ነበር። ዉስጤ ላይ ያደረዉ የወንድምነት መንፈስ ከኔ ሴት በመንከባከብ ለተሻለ ወንድ አሳልፎ እስከመስጠት ወስዶኝ ነበር። የፈጣሪ ጥበብ ግን ይገርማል ትናንተ ስለማላዉቃት አንድ ሴት ዛሬ ከማንም በላይ የምጨነቅ ፍጡር እንድሆን አደረገኝ። . ከኢክራም ጋር ግንኙነታችን ከስልክ በአካል ወደመገናኘት ሊያድግ ቀን ቆረጥን። አርብ ዕለት ማታ አንድ ሰአት ላይ ሰፈራችን በሚገኘዉ አስፓልት ላይ ዎክ ለማድረግ ተቀጣጠርን። ከሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመገናኘት ስትቀጣጠሩ የሆነ የሚጨንቅ ነገር አለዉ። ልጅቷ ተጫዋች ናት ወይስ አንገቷን ከማነቃነቅ ዉጪ ምንም የማታወራ ልጉም የሚለዉ ያስጨንቃል። እኔ ግን አንድ ቀን ታክሲ ዉስጥ ስላገኘኋት ነዉ መሰለኝ ብዙም አልተጨነቅኩም። ይልቁንስ ስለዉበቷ ነዉ የማስበዉ ፣ ስትሽኮረመም በአይነህሊናዬ ይታየኛል። ከዛም በስልክ ያወራነዉ ታሪኳ ትዝ ይለኝና ስሜቴን አፍነዋለሁ። ከሴት ጋር ተቀጣጥሮ የመንዘላዘል ልምድ የለኝም። አሁን ግን መንዘላዘልም በሉት ምን ከኢክራም ጋር ለመገናኘት ተቀጣጥሬያለሁ። . ጁምዓ ደረሰ!! ማታ ላይ ኢክራም ከሪም ጋር ሆና የተቀጣጠርንበት ቦታ ላይ ተገናኘን። እኔ ግን ግራ የሚገባኝ ሴቶች ለምንድነዉ የመጀመሪያ ቀን ስትቀጥሯቸዉ ከጓደኛቸዉ ጋር የሚመጡት? እኔ ግን ስገምት ደህንነት የሚሰማቸዉ አይመስለኝም። ምናልባት ወንዱ አደብ ከሌለዉ ስርዓት ለማስያዝ አሊያም አብሮ ለመጮህም ሊሆን ይችላል ሁለት ሆነዉ የሚመጡት። ኢክራም ቤት ስትመለስ ሪም ጋር ነበርኩ ለማለት አቅዳ ነዉ በድፍረት በማታ ያገኘችኝ። ከዛ ቀን በኋላ እስክንለያይ ድረስ በዛ ሰዓት አግኝቼያት አላዉቅም። እስከምሽቱ ሁለት ሰዓት ያመሸነዉ የዛኔ ብቻ ነዉ። ኢክራምን ገና ከሩቅ ሳያት ልቤ "የምን ወንድምነት ነዉ? እያት እስኪ ያስችልሀል?" እያለ ሞገተኝ። ልቤን አደብ አስገዝቼ እነ ኢክራምን ተቀላቀልኳቸዉ። ሁለቱም የለበሱት ሺቲ ነዉ። ኢክራም ከላይ ጃኬት ደርባለች። በጅልባብ ስላልመጣች ጌታዬን አመሰገንኩ። ሺቲ እና ድሪያ ልዩነቱ ምን እንደሆነ አላዉቅም። የልብሱ ስም ሺቲ እንደሚባል ኋላ ላይ ነዉ ኢክሩ ራሷ የነገረችኝ። ንፋሱ የለበሰችዉን ሺቲ ገላዋ ላይ ሲለጥፈዉ የሰዉነቷ ቅርፅ ወለል ብሎ ታየኝ። መጠነኛ መቀመጫ አላት ፣ ወገቧ ከመቀመጫዋ እጅጉን ቀጥኖ ስምንት ቁጥር ሰርቷል። ንፋስን ቅርጿን እንዳይ ስፖንሰር ስላደረገኝ ከልብ አመሰገንኩ። ወዲያዉ ሪም ተሰናብታን ሄደች። እኔና ኢክሩ ብቻ ፣ ማታ ላይ ፣የመንገድ መብራት ባስጌጠዉ ዉብ ጎዳና ላይ አብረን ቀረን። ግን አልተፈራራንም አንዳንችን በአንዳችን መኖር ምቾት ተሰምቶናል። ምናልባት በህይወቴ እስከዛሬ ካደረግኳቸዉ ዎኮች ዉስጥ የህይወቴን ልዩ ታሪክ የመሰረተዉ ዎክ ይሄ ይመስለኛል። "ኢክራም" አልኳት መንገድ መንገዱን እያየሁ። "አቤት ፈዉዛን" አለችኝ አንገቷን ወደኔ አዙራ። "ባለፈዉ ታክሲ ዉስጥ ስንገናኝ ጅልባብ ነበር የለበስሽዉ ዛሬ እንዴት አወለቅሽዉ?" አልኳት። ፈገግ አለች እና እጆቿን እያፋጨች "ጅልባብ ሀይማኖታዊ ልብስ ነዉ!! እስልምና ደግሞ በጋብቻ ካልተሳሰርኩት ወንድ አሊያም ዘመዴ ካልሆነ ሰዉ ጋር እንዲህ እንድሆን አይፈቅድም። በአጭሩ የሀይማኖት ልብስ ለብሼ እምነቴ የከለከለኝን ነገር ላለማድረግ ብዬ ነዉ!! ሀይማኖታችንን ላለማሰደብ!!" አለችኝ። በመልሷ በጣም ደስ ተሰኘሁኝ። እኔም ለጅልባቧ እና ለሀይማኖቷ ባላት ክብር አደነቅኳት። ፈገግ ብዬ "ሁሌም እኔን ስታገኚኝ ጅልባብ ባትለብሺ ደስ ይለኛል።" አልኳት። "ይኸዉ ልክ እንደዚህ በሺቲ እመጣለሁ።" አለችኝ አንገቷን በሀፍረት እየሰበረች በልቤ በጣም ሳቅኩ ፣ ደስ አለኝ!! በሺቲ እመጣለሁ ስላለችኝ አይደለም። ግን በንግግሯ ዉስጥ ከዚህ በኋላም እንገናኛለን የሚል መልዕክት ነበር። "ኢክሩ ባለፈዉ ግን ለምንድን ነበር ታክሲ ዉስጥ እያየሽኝ የሳቅሽዉ?" አልኳት ትልቅ ነገር እንዳስታወሰ ሰዉ ወደሷ እየዞርኩ "እንዴ ፈዉዛኔ ታክሲዉ ዉስጥ ስትቃለድ የነበረዉ እኮ ከሴቶች ጋር ነበር። እኔ ደግሞ በጣም ኮስታራ ስለምትመስለኝ ሴት የምታናግር ራሱ አይመስለኝም ነበር።" አለችኝ ልክ እንደባለፈዉ እየሳቀች ብዙዎች የሚታሰቡት እነሱ እንደሆኑት አይደለም። ተመልካቹ እንደሚስላቸዉ ነዉ። እንደኔ እኮ ተጫዋች የለም ግን ኮስታራ መሰልኳት። ይገርማል!! . ሁለት ሰአት ሊሆን ሲል ከኢክሩ ጋር ተለያየን። ቤቷን ስለማላዉቀዉ እስከቤቷ አልሸኘኋትም። የሰፈራችን መስጂድ ጋር ስንደርስ አዛን እያለ ነበር። አዛን ማለት ሁሌም ከመስጂድ የሚሰማዉ "አላሁአክበር" የሚለዉ የስግደት ሰዓት መድረሱን መጠቆሚያ ድምፅ ነዉ። እሷ በቅያሱ ታጥፋ ሄደች እኔ መስጂድ ገባሁ። መስጂዱ አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዳያዩን ሁለታችን
Open in Telegram. ♥️●●●#ነጠብጣብ●●●♥️ 💞#እውነተኛ_እና አስተማሪ_ታሪክ💞 #ክፍል_3 ...🖊ሰዉ የራሱ መልካም ጎን እንዳለዉ ሁሉ ደካማ ጎንም ይኖረዋል። ገና ለገና ዛሬ ተለያየን ተብሎ የሰዉን ስም አተላ መቀባት አግባብ ነዉ ብዬ አላምንም። ኢክሩ አብረን እያለን ለኔ መልካም ነበረች። . አስተናጋጇ ፊቴ መጥታ ቆመች ፈገግ ብላ "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" አለችኝ። ስሟ ረሂማ ነዉ። ከኢክራም ጋር እዚህ ቤት ስንመላለስ ሁሌም የምታስተናግደን እሷ ነበረች። "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" ያለችኝ ወተት በሳፊ ስለምጠጣ መሆኑ አንዱ ምክንያቱ ነዉ። ሰሞኑን ግን ይሄን ቃል የምትጠቀመዉ ብቻዬን ስለምመጣ ነዉ። ያዉ ወተት ሳፊ ሲሆን ያለቡና ብቻዉን አይደል የሚቀርበዉ። ጨዋታዋ ደስ ስለሚለኝ ምንም ጥሩ ስሜት ላይ ባልሆንም ፈገግ ብዬ "ወዬ ረሂማ ኮካ" አልኳት። ሳቋ ወዲያዉ ወዲያዉ ቡፍ ስለሚል ነዉ ኮካ የምላት። "ከወተት ሌላ ምትፈልገዉ ነገር አለ?" አለችኝ። ምን እንደምጠጣ በደንብ ታዉቃለች። "ወተት ብቻ አምጭልኝ ኮካዬ" አልኳት እየሳቅኩ። ምላሷን አዉጥታብኝ ወተቱን ልታመጣ ሄደች። በነገራችን ላይ ከአስተናጋጆች ጋር እንደዚህ ያለ ወዳጃዊ ግንኙነት መመስረት ደስ ይለኛል። ካፌ ብቻ ሳይሆን የትም ስሄድ ፊቴን ከመከስከስ ይልቅ ፈታ ብዬ እየተጫወትኩ ከሰዎቹ ጋር መግባባት ያስደስተኛል። ተጫዋችማ ነበርኩ ኢክሩ ያደረገችኝ ነገር የሆነ አዚማም አደረገኝ እንጂ!! ከኢክሩ ጋር የተዋወቅንበት መንገድ ትንሽ ለየት ይላል። ፈጣሪ እራሱ ተዋወቁ ብሎ ሜዳዉንም ፈረሱንም እንካችሁ እንደማለት ነበር ያመቻቸልን። ከኢክሩ ጋር እንዴት እንደተዋወቅን በደንብ አስታዉሳለሁ!! አዎ በደንብ!! ቀኑ ጁምዓ(አርብ) ቀን ነበር!!ከኢክራም ጋር የተገናኘነዉ የዛሬ ሁለት ዓመት እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን ለመዉሰድ ስዘጋጅ ፣ እሷ ደግሞ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ስትዘጋጅ ነበር። ይህቺን ዉብ ፈጣሪ ሲያንቀለቅል ታክሲ ዉስጥ ይዞልኝ መጣ። ታክሲዉ ዉስጥ ብቻም አይደለም!! ከታክሲዉም እኔ የተቀመጥኩበት የመጨረሻዉ ወንበር ላይ በመካከላችን አንድ ሰዉ ብቻ እስከሚኖር ድረስ አቀራርቦ አስቀመጠልኝ። በመካከላችን አንድ ሰዉ መኖሩ ፈጣሪ "አንተም የድርሻህን ያህል ጣር እንጂ" ሊለኝ ያደረገዉ ነበር የመሰለኝ። እኔም እሷም ከትምህርት ቤት እየተመለስን ነበር። እሷ የምትማርበት ትምህርት ቤት እኔ ከአራተኛ ክፍል እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩበት ትምህርት ቤት ነዉ። የለበሰችዉን ዩኒፎርም ስመለከት በትምህርት ቤቱ ያሳለፍኩት ትዝታ ወለል ብሎ ይታየኝ ጀመር። ታክሲዉ ዉስጥ የሷን አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች ነበሩ። ከነሱ ጋር የመምህራንን ስም እና ባህሪ እየነገርኳቸዉ ስንሳሳቅ እሷም እየሰረቀች ስታየኝ ተመለከትኩ። ጥሎብኝ ሴት ቀድማ ሳታናግረኝ አላዋራም። ለራሴ ዋጋ ስለምሰጥ ነዉ መሰለኝ ለማንም መርከስ አልፈልግም። የዛን ቀን ግን እየተሽኮረመመች ስትመለከተኝ ሳይ ወዲያዉ ፊቴን ወደሷ አዙሬ እርግጠኛነት በተሞላበት ስሜት "አንቺ የሆነ ቦታ ታዉቂኛለሽ።" አልኳት። እሷም አሁንም ከሳቋ ጋር እየታገለች በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ። በሁለታችን መካከል የነበረችዉ ልጅ "በሉ ልውጣላችሁ" ብላ ከታክሲዉ ወረደች። የመዉረጃ ቦታዋ ደርሶ ይሁን የወረደችዉ አሊያም የኛን የማዉራት ፍላጎት ተረድታ አላወቅኩም። ብቻ ለትዉዉቃችን አስተዋፅዖ አበርክታለች። ግን ምናለ ልጅቷ ከመካከላችን ባልወጣች እና እኔና ኢክሩ ሳንተዋወቅ በቀረን። ከነዉበቷም ከነፈገግታዋም ስብራቴ መሆኗ ላይቀር ምናለ ባላወቅኳት። ልጅቷ ከመካከላችን እንደወጣች ኢክራምን የት እንደምታዉቀኝ ጠየቅኳት። መስጂድ የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ መድረክ ስመራ እንደምታዉቀኝ ነገረችኝ። . በትርፍ ሰዓቴ መስጂድ ዉስጥ የስነ ፅሁፍ ስራዎችን እሰራለሁ። በእስልምና ሀይማኖት መሰረት የወንዶች መስገጃ ቦታ እና የሴቶች መስገጃ ቦታ የተለያየ ቦታ ላይ ነዉ የሚሆነዉ። እኔ ኢክራምን ከዛ ቀን በፊት አላዉቃትም ነበር። መስጂድ ነዉ የማዉቅህ ስትለኝ ወዲያዉ አደብ ያዝኩ!! የተከበረ ቦታ ላይ ታዉቄማ እዚህ አልረክስም አልኩ በልቤ። ግን ወዲያዉ የጓደኛዬ የአዩብ ፍቅረኛ ሪም ትዝ አለችኝ እና ታዉቃት ከሆነ ብዬ ጠየቅኳት። በጣም የቅርብ ጓደኛዋ እንደሆነች ነገረችኝ። ለማንኛዉም ከሷ ጋር የሚተዋወቁ ከሆነ የእኔ እና የእሷ ነገር እንዳለቀለት አሰብኩ። አዩብ እና ሪም ሲኮራረፉ ሁሌም እኔ ነበርኩ የማስታርቃቸዉ። ሪም ቀርባ ሳታዉቀኝ በጣም ትጠላኝ ነበር። ስንቀራረብ ግን በጣም ወደደችኝ። አዩቤ ደግሞ ቁጡ ስለሆነ ሲጣሉ ለማረጋጋት ግዴታ እኔ መግባት አለብኝ። ስለፍቅር ህይወት እኮ ምንም አላዉቅም ግን እንደ ቀበሌ ሹም በባዶ ገብቼ እለምድባቸዉ ነበር። ኢክራም ስሜን እንደምታዉቀዉ ብገምትም ለወጉ ያክል ፈገግ ብዬ "እንተዋወቅ ፈዉዛን እባላለሁ" አልኳት። አይኖቿን በሀፍረት ሰበር እያደረገች "ኢክራም እባላለሁ" አለችኝ። የመዉረጃ ቦታዋ ከኔ ትንሽ ይቀድም ስለነበር ቀድማኝ ወረደች። የዛን ቀን ከለበሰችዉ ዩኒፎርም ላይ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳ ነበር። ጅልባብ ማለት በአብዛኛዉ ሙስሊም ሴቶች የሚያዘወትሩት እጅንና ፊትን ብቻ የሚያሳይ ሰፊ ልብስ ነዉ። ከወረደች በኋላ ስልኳን እንዳልተቀበልኳት አስታወስኩ። ኩራቴ ተናንቆኝ ነዉ? ለምን ስልኳን አልተቀበልኳትም? አዎን ገባኝ የሪም ጓደኛ ነኝ ስላለችኝ ነዉ ስልኳን ያልተቀበልኳት። የሪም ጓደኛ ከሆነች እኔና ሪም በጣም ስለምንግባባ ስልኳን በቀላሉ ማግኘት እንደምችል ስላሰብኩ ነዉ ዝም ያልኳት። . የዛን ቀን ታክሲ ዉስጥ ኢክራምን ሳወራት የነበራት አይነአፋርነት አሁን ላሉት አይንአዉጣ ሴቶች እና ለአሁን እሷነቷም ጭምር ቢታደል ይበቃ ነበር። የሆነ ከአይናፋርነትም ቀልብ የሚገዛ አይናፋርነት አለ እኮ የእዉነት!! የተመጠነ በዉስጡ ትህትናን እና አክብሮትን ያዘለ አይናፋርነት!! ከተለያየን በኋላ ቤት ገብቼ አረፍ አልኩ። ግን አሁንም የማስበዉ ዛሬ ታክሲ ዉስጥ ስለተዋወቅኳት ቆንጆ ልጅ ነበር። አይናፋርነቷ ፣ ፈገግታዋ ሁሉ ትዝ እያለኝ ብቻዬን ፈገግ አልኩ። ወዲያዉ ራሴን አረጋጋሁት ምንድነዉ ስለማላዉቃት ሴት ማሰብ? በሰዓቱ እኔ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ሀይማኖታዊ መድረኮችን መርቼ ከወረድኩ በኋላ በራሱ የሴቶቹ የፌስቡክ እና የስልክ መልዕክቶች ፈተና ነበር የሚሆኑብኝ። አንዳንዴ ፍላጎታችን ተመሳሳይ ሆኖ ግን የፍላጎታችንን ለማግኘት የተለያየ ቦታ እንሄዳለን። አንዳንድ ሴቶች ሀይማኖታዊ መድረኮች ላይ የሚታዩ ወንዶችን ለመጥበስ በየዝግጅቶቹ ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ እኮ ሁላችንም የመጥበስ መልዕክተኞች ሆነናል። በየትምህርት ቤቱ በየሄድንበት ሁሉ!! ሀይማኖት ቦታ ላይ ያለዉ አጠገቡ ያለችዉን ይጠብሳል ወይ ትጠብሰዋለች። ይሄ ደግሞ ሁሉም ሀይማኖት ላይ ያስተዋልኩት ሀቅ ነዉ። እኔም ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ገጥመዉኛል ግን ፊት አልሰጠኋቸዉም። በየጊዜዉ የማላዉቃቸዉ ሴቶች ልብ የሚያቀልጡ መልዕክቶችን ፌስቡክ ላይ ይልኩልኛል። እኔ ግን ብዙም ግድ አይሰጠኝም ነበር። ታዲያ ቆይ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነዉ ስለማላዉቃት ሴት የማስበዉ? ገርሞኛል። ቀልቤን ስርዓት ማስያዝ አለብኝ።
Open in Telegram