Кабинет
ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @B_promotor

Юзернейм
@ethio_mereja_news
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики44 879−30 за 1 день
Просмотров на пост, 7 дн.3 835за 7 дней
ERR8,54 %за 7 дней

Подписчики, 30 дней

28 нояб. – 29 нояб.−30 (−0,1%)

Показать таблицей
ДатаПодписчики
28 нояб. 2026 г.44 909
29 нояб. 2026 г.44 879

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
25 нояб. 2026 г.4 922
26 нояб. 2026 г.4 295
27 нояб. 2026 г.3 608
28 нояб. 2026 г.2 066

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    በመቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች 12 ስራ ጀመሩ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች መካከል 12ቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ግርማይ አስታወቁ። በመቐለ ከተማ 750 የሕዝብ ትራንስፖርት ታክሲዎች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው፣ ለነዚህ ታክሲዎች ቅድሚያ የነዳጅ አቅርቦት እንዲሰጣቸው በማድረግ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እና አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉን ገልፀዋል። የተወሰዱት እነዚህ እርምጃዎች በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲሁም የነዳጅ ስርጭትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ነዳጅ ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋሉን እና አለመዋሉን ለመለየትና ለመቆጣጠር እንዲያስችል፣ የነዳጅ ሽያጭ በቴሌብር ዲጂታል ግብይት ብቻ እንዲፈጸም መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በነዳጅ አቅርቦት ላይ ምንም ዓይነት መቆራረጥ ወይም እጥረት እንዳይፈጠር ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋይ ግርማይ ጨምረው ገልጸዋል።

    Фото
    Просмотры5,27 тыс.
    Пересылки—
    Реакции14
    Комментарии—
  2. 02

    አምስት ሴቶችን የገደለው ግለሰብ‼ ​በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ሽረ ከተማ፣ ቀደም ሲል በግድያ ወንጀል የ22 ዓመት እስራት ተፈርዶበት የነበረው የ54 ዓመቱ ተስፋይ ገብረዮሐንስ ከእስር ከወጣ በኋላ በ20 ቀናት ውስጥ አምስት ሴቶችን ገድሎ ፆታዊ ጥቃት መፈጸሙን ፖሊስ ገለጸ። ​የዞኑ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ እንዳስታወቁት፣ ተጠርጣሪው መስከረም 25/2019 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ከእስር ከወጣ በኋላ ከጥቅምት 19 እስከ ኅዳር 8 ባሉት ቀናት ውስጥ ቢላዋ፣ መጥረቢያና ድንጋይ በመጠቀም ወንጀሉን ፈጽሟል። ​በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈው በሻይ ቡና ንግድና በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ የነበሩት ዮርዳኖስ ሓጎስ፣ የሻለም ዘነበ፣ ገነት ደጀን፣ ሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር እና ወሰንየለሽ መኮንን ናቸው። በተጨማሪም ተጠርጣሪው የአንዷን ሟች የ5 ዓመት ሕፃን ልጅ ያገተ ሲሆን፣ ሕፃኗ ያለችበት ሁኔታ እስካሁን አልታወቀም። ​ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ውሎ ድርጊቱን ያመነ ሲሆን፣ የሕፃኗን አድራሻ የማፈላለግ ምርመራ ቀጥሏል። የትግራይ ባላደራ አስተዳደር የሴቶች ጉዳይ ቢሮም ድርጊቱን በማውገዝ በወንጀለኛው ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል። ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

    Текст
    Просмотры5,19 тыс.
    Пересылки—
    Реакции42
    Комментарии—
  3. 03

    እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ከክፉ ነገር ትከልለን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ትሙላልን🙏 መንገስተ ሰማያት መግቢያ ኪዳን አባቶቻችን የሃዘን ብዛት የእንባ ጎርፍ አይን ያጠፋል፣ ፊት ያንጣጣል፣ ልብ ይሰውራል አካልንም ያዝላል ይላሉ፡፡ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደቷ ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ድረስ አልቅሳለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ ሆና ከእርሱ ከተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ጸልያለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ይህም ታላቅ በዓል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እየተባለ በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን ይከበራል፡፡ ይህ ዕለት ድንቅ ተአምራትም ያደረገችበት ነው፡፡ ስምዖን የሚባል የአባታችን የቅዱስ አብርሃምን ታሪክ የሰማና እንደ እርሱ እንግዳ መቀበል የሚወድ ሰው ነበር፡፡ ጠላታችን ሰይጣንም እንግዳ መስሎ ወደ ቤቱ በመምጣት ልጅህን አርደህ አብላኝ አለው፡፡ እርሱም “አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው” በሚል እሳቤ ያለውን አደረገ፡፡ ሲያቀርብለትም ቅመስልኝ አለው፤ እሺ ብሎ ሲቀምስለት በዚያው ተዋሐደው፡፡ ከዚህ በኋላ በላኤ ከቤተሰቦቹ ጀምሮ “በላዔ ሰብእ” ወይም “ሰው በላው” እስኪባል ድረስ 78 ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ የቆሰለ ነዳይ አይቶ ሊበላው ሲቀርብ ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፡፡ ነዳዩ ግን ውሃ አጠጣኝ ሲል በሥላሴ፣ በቅዱሳን ሁሉ ስም ቢለምነው፤ አልሰማውም፡፡ በድንግል ማርያም ስም ሲለው በአእመሮው አቃጨለበትና “ምህረት እንደምታሰጥ በልጅነቴ ሰምቻለሁ” ብሎ ከያዘው ውሃ ጥቂት አጠጣው፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አጊኝቶ ሊበላው ሲል “አንተ ያ በላዔ የምትባል ነህ?” አለው፡፡ ለካ ይህ ነገር ተሰምቶብኛል ብሎ ወደ አንድ ዋሻ ሔዶ በጸጸት ሞቷል፡፡ የጨለማ መላዕክት ነፍሱን በጌታ ፊት ሲያቀርቧትም እመቤታችን “ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ” አለችው፡፡ ጌታችንም ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋና ፈጣሪውን የካደ እንዴት ይማራል አላት፤ እመቤታችንም በስሜ የተጠማውን አጠጥቷል ስትል ነፍሱን አስምራዋለች፡፡ እኛንም በቃል ኪዳኗ ታስምረን፣ አማላጅነቷም አይለየን፡፡ አሜን!!! ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

    Текст
    Просмотры5,08 тыс.
    Пересылки—
    Реакции25
    Комментарии—
  4. 04

    እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 #በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በግብጽ በስደቷ፣ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ከሙታን ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ለተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ጡዋፍ ዘቢብ መባእ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ እኛም ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከእመቤታችን ጋር ዕለቱን በየወሩ በ16ኛው ቀን በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ይህን ቃል ኪዳኗን ያመኑ፣ በእናትነት ፍቅሯ ከምልጃዋ በረከት የተካፈሉ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን ቅድስት ሆይ ለምኝንልን ይሏታል፡፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር ሳይበግራቸው በጸሎተው ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የእመቤታችን በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፡፡  ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

    Текст
    Просмотры5,02 тыс.
    Пересылки—
    Реакции30
    Комментарии—

Новые посты

#26504Текст

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!! ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Открыть в Telegram
Просмотры2 190−43%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч594
4 ч1 930
8 ч2 190
  1. Через 1 час594
  2. Через 6 часов1 930
  3. Всего сейчас2 190
#26503Фото
Просмотры2 010−48%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч559
4 ч1 780
8 ч2 010
  1. Через 1 час559
  2. Через 6 часов1 780
  3. Всего сейчас2 010
#26502Текст

የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ 59 የኩፍኝ ወረርሽኞች መከሰታቸውን ተከትሎ በሽታው በአደገኛ ሁኔታ እያገረሸ መምጣቱን አስጠነቀቀ ​የኩፍኝ በሽታ ዳግም ማገርሸት፤ የዓለም ጤና ድርጅት አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አወጣ ​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፣ ከፈረንጆቹ 2000 ወዲህ በኩፍኝ በሽታ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ91 በመቶ ቀንሶ 72 ሺህ ቢደርስም፣ አሁን ላይ በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዳግም እያገረሸ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም ዙሪያ 59 ከፍተኛ የኩፍኝ ወረርሽኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 9.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ​በተለይም ቀደም ሲል በሽታውን ሙሉ በሙሉ አጥፍተው የነበሩት አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ቦሊቪያ ይህንን እውቅናቸውን ማጣታቸውን ድርጅቱ በስጋት ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ፣ «ኩፍኝ ቸልተኝነትን አይታገስም፤ በሽታውን አጥፍተው የነበሩ ሀገራት ዛሬ ያንን ደረጃ እያጡ ነው» በማለት፣ እያንዳንዱ ሕፃን ሁለት ዙር ክትባት እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል። ​በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ የሕዝቡ በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም፣ እንዲሁም በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የክትባት ሽፋን በእጅጉ ማሽቆልቆል ለወረርሽኙ መስፋፋት ዋና ምክንያት ሆኗል። ለአብነትም በሞንቴኔግሮ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱት 13 በመቶ ብቻ ሲሆኑ፣ ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ (84 በመቶ) ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችና የሴራ ትንታኔዎች ወላጆች ልጆቻቸውን እንዳያስከትቡ እያደረጉ መሆኑን የጤና ተቋማት አስጠንቅቀዋል።

Открыть в Telegram
Просмотры2 140−44%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч901
7 ч2 140
  1. Через 1 час901
  2. Через 6 часов2 140
  3. Всего сейчас2 140
#26501Текст

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏 #ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!! በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል አብሳሬ ትስብዕት ነው፡፡ እመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ታላቁን የምሥራች ይዞ የደረሰው እርሱ ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሀዲስ ኪዳን ስሙ ተደጋግሞ በመጠቀሱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ነው፡፡ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚወልድ የዘመናትን የጸሎት ምላሽ ይዞ የመጣ፣ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ የሚያለቅሰውን የነቢዩ ዳንኤልን የጸሎት መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል። በዕምነታቸው የጸኑት ሦስቱ የባቢሎን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” አሉት፡፡ ወደ እቶን እሳት ተጣሉ፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው፡፡ ናቡከደነጾርም ተደንቆ በእሳቱ ላይ ሦስት ሰዎች ሰዎች ጥለን ነበር አሁን ግን አራት ሰዎች አያለሁ፤ የአራተኛውም መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ይህ የአምላክን መልክ ይመስላ የተባለው  ቅዱስ ገብርኤልን ገዳማውያን በመንፈሳዊ ውጊያቸው ሁሉ ይረዳቸዋል፡፡ የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንድንሆን በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ፡፡    ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Открыть в Telegram
Просмотры2 100−45%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч982
8 ч2 100
  1. Через 6 часов2 100
  2. Всего сейчас2 100
#26500Фото
Просмотры1 890−51%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч879
8 ч1 890
  1. Через 6 часов1 890
  2. Всего сейчас1 890
#26499Текст

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ነን በሚል ስም የንግድ ተቋማትን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ በቱሉ ዲምቱ ወረዳ በንግድ ቤቶች በመዞር ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል 100 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው በመግለጽ፣ ቅጣቱን ለመንግስት ከመክፈል ይልቅ ለእነሱ 50 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቅ ሲያጭበረብሩ እንደነበር ነው ቢሮው ያስታወቀው። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕግ ተገዢነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ፓርቲ ንጉሴ ግለሰቦቹ እውነተኛ ማንነታቸውን በመደበቅና ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ወንጀሉን ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ ምትኩ ጋዲሰ በሐሰተኛ ስም አየለ ጥላሁን፣ እንዲሁም አቶ ጌታሁን ደቻሳ በሐሰተኛ ስም አድማሱ ከበደ በሚል ማንነታቸውን በመቀየር የሐሰት መታወቂያ ተጠቅመው ሲያጭበረብሩ በንግዱ ማህበረሰብ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በአሁኑ ወቅትም በሕግ አግባብ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። በተጠርጣሪዎቹ እጅ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ ሐሰተኛ መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የመሬት ባለሙያ መሆናቸውን የሚገልጽ ሌላ ሐሰተኛ መታወቂያም መገኘቱን ገልጸዋል። ከዩኒፎርም ውጪ ቁጥጥር የሚያካሂዱ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ባርኮድ ያለው መታወቂያ የሚይዙ በመሆኑ፣ ግብር ከፋዮች መታወቂያቸውን በመጠየቅና ባርኮዱን በስልክ ስካን በማድረግ ትክክለኛ ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።

Открыть в Telegram
Просмотры3 760−2%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
13 ч2 780
25 ч3 760
  1. Через 24 часа3 760
  2. Всего сейчас3 760
#26498Текст

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን🙏 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏 የራማው ልዑል፣ መጋቤ ሐዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡ ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡    ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

Открыть в Telegram
Просмотры3 640−5%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
13 ч2 650
25 ч3 640
  1. Через 24 часа3 640
  2. Всего сейчас3 640
#26497Фото
Просмотры3 180−17%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
13 ч2 310
25 ч3 180
  1. Через 24 часа3 180
  2. Всего сейчас3 180
#26496Фото

በሰው አንጎል ውስጥ የሚቀበረው ማይክሮ ቺፕ ወሳኝ የሙከራ ፈቃድ አገኘ‼️ በኢሎን መስክ የሚመራው ኒውራሊንክ  የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ በሰው ልጅ አንጎል ውስጥ የሚገጠም ቺፕ ወሳኝ ክሊኒካዊ ሙከራ እንዲያደርግ ከአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር  ፈቃድ ማግኘቱ ተገለጸ። ኩባንያው ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ «ሊንክ» (LINK) ተብሎ የተሰየመው ይህ ሙከራ በአሜሪካ ውስጥ በአንጎል ለሚቀበሩ መሣሪያዎች የተፈቀደ የመጀመሪያው ወሳኝ የምርምር ምዕራፍ መሆኑን አስታውቋል። ይህ አዲስ ሙከራ የሚያተኩረው «ኤ.ኤል.ኤስ» (ALS) በተባለ ከባድ የነርቭ ሕመም ምክንያት ሰውነታቸው በሽባነት በተያዘ አዋቂ ታካሚዎች ላይ መሆኑ ተመላክቷል። ተሳታፊዎቹ በአንጎላቸው ውስጥ በሚገጠመው ቺፕ አማካኝነት ሃሳባቸውን ብቻ በመጠቀም ኮምፒውተሮችንና ሌሎች ዲጂታል መሣሪያዎችን ምን ያህል በብቃት ማዘዝ እንደሚችሉ እንደሚገመገም በኩባንያው ተብራርቷል። የአሁኑ ፈቃድ ቀደም ሲል በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በእንግሊዝ ከ30 በላይ በሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች ላይ በተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራዎች በተገኙ ውጤቶች ላይ የተመሠረተ መሆኑ ተነግሯል። በቀደሙት ሙከራዎች ተሳታፊዎቹ ቺፑን በመጠቀም መልዕክት መላክ፣ ትምህርታቸውን መከታተል እና የቪዲዮ ጌሞችን መጫወት መቻላቸውን ኒውራሊንክ ገልጿል። ሆኖም የተሰጠው ፈቃድ ቺፑን ለገበያ ለማቅረብ ሳይሆን ለምርምር ዓላማ ብቻ የሚውል መሆኑን ተቆጣጣሪው አካልና ዘገባዎች ጠቁመዋል። በዚህ ወሳኝ ሙከራ የሚገኘው የመሣሪያው ደህንነትና ውጤታማነት ማረጋገጫ ኩባንያው ወደፊት ቴክኖሎጂውን በስፋት ለሕክምና አገልግሎት ለማቅረብ ለሚያስገባው ማመልከቻ እንደ መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል ታውቋል።

Открыть в Telegram
Просмотры3 740−2%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—
#26495Текст

የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ታላቁ አለቃ ቅዱስ  ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

Открыть в Telegram
Просмотры3 860+1%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—

Все посты

Связи