Кабинет
Gumaa Saaqqataa

Gumaa Saaqqataa

Юзернейм
@gumaaoro
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики40 858
Просмотров на пост, 7 дн.3 825за 7 дней
ERR9,36 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
25 нояб. 2026 г.5 271
27 нояб. 2026 г.4 105
28 нояб. 2026 г.1 687

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    ከሽራሮ ከተማ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። ባድመ። ከሽረ እንዳስላሴ ከተማ ወደ ሽራሮ ከተማ የሚጓዝ ሰው ዓዲ ዳዕሮ፣ ዓዲ ነብርኢድ እና ዓዲ ሃገራይ ከተሞችን አቋርጦ ማለፍ አለበት። ከሽራሮ ከተማ ወደ ባድመ ከተማ ለመሄድ ደግሞ ዋዕላ ንህቢ፣ ገዛ ተጋሩ፣ ሰምበል፣ ደንበ መንጉል እና ደንበ ገዳሙ ይጠብቁሃል። * ወደ ባድመ ከተማ ስንገባ በመግቢያው ላይ የሚቀበሉን የሻዕቢያን ወረራ ለመመከት በቢያራ፣ በገዛ ገረላሰ፣ በጎቦ ጨጓር፣ በፅብራ፣ በጎቦ ቡምበት፣ በዓዲ ሃኪም፣ በፀሊም ቀላይ እና በሌሎችም ስፍራዎች የወራሪውን የሻእቢያን ወረራ ለመመከት በጀግንነት ሲዋጉ የተሰው ጀግኖች ኢትዮጵያውያን መቃብሮች በምትመለከቱት መልኩ እንደ ንቁ ወታደር በሰልፍ ተሰትረው ይገኛሉ። በእርግጥም ባድመ መሬት ብቻ አይደለችም በዚያ ያለን አፈር ብቻ አይደለም ። በባድመ የእልፍ ወንድሞቻችን ደም ፈሶበታል ፣ ቁጥር የማይገልጻቸው ወጣቶች አጥንት በዚያ አርፏል። ባድመ ለቁጥር በማይታክቱ ጀግኖች አጥንት የታጠረች በደማቸው ተለውሶ የታጠረ ሀቅ ነው።የባድመ መሬት አፈርና ሳር ብቻ የተሸከመ አይደለም፤ የጀግኖች ደምና አጥንት ጭምር እንጂ። ክብር ለሰማእታት!

    Фото
    Просмотры5,82 тыс.
    Пересылки—
    Реакции61
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры5,78 тыс.
    Пересылки—
    Реакции73
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры5,54 тыс.
    Пересылки—
    Реакции71
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры5,34 тыс.
    Пересылки—
    Реакции24
    Комментарии—

Новые посты

#10452Видео
Просмотры419−89%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч235
3 ч419
  1. Через 1 час235
  2. Всего сейчас419
#10451Видео
Просмотры1 660−57%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч1 270
4 ч1 530
7 ч1 660
  1. Через 6 часов1 660
  2. Всего сейчас1 660
#10450Текст

ክፍል ሁለት ስጋ እንዳገኘ ጉንዳን በብርጌድ ሁለት ምሽግ ላይ የሻእቢያ እግረኛው ሀይል ሲርመሰመስ ከጎን እና ከጀርባ የተጠመዱት የጠላት ከባድ መሳሪያዎች ላንቃቸውን ከፍተው የቅንቡላ ዝናብን ማውረድ የጀመሩት የኛን ምሽግ ትተው ከጀርባ ካለው የክፍለ ጦሩ ኮማንድ ፖስት (በወቅቱ ክፍለ ጦሯን የሚመራው ሌ/ጄ አበባው ኮማንድ ፖስት)ን በ130ሚሜ መድፍ በመቀጥቀጥ እረፍት አሳጡት።ቀድሞ ከላይ ያለውን የአመራሩን ሚና ሽባ በማድረግ ትእዛዝ እንዳይሰጥ ማድረጋቸው ነበር። ከምሽጉ ውጪ ሰብሰብ ብሎ ዳማ ሚጫወተው ፣ ልብሱን ሲያጥብ፣ ገላውን ሲለቃለቅ የነበረው ሁሉ በተከሰተው የተኩስ ውርጅብኝ መካከል አንዳንዱ በውስጥ ሱሪ ብቻ ከነ አረፋው ትጥቁን ይዞ ወደ ምሽጉ ሲንደረደር በቅጽበት ውስጥ ምሽጉን ሻእቢያ ይዞበታል።በግራ በቀኝ በሁሉም አቅጣጫ ምሽጎቹ በጠላት ተይዘዋል ። ወዴት አቅጣጫ መተኮስ እንዳለባቸው ፣ ትእዛዝ ከማን እንደሚቀበሉ የማይታወቅበት ወዴት መተኮስ እንዳለበት እና ጠላትን ከወገን ለመለየት የቸገረ ሁኔታ። በድንገተኝነት ምሽጉን የተነጠቀው ጦር አዛዥ ኮሎኔል ናቃቸው በባዶ እግር ወደ ማዘዣ ምሽጉ ሲንደረደር ኦፕሬተሩ እና የተወሰኑ ወታደሮች ምሽጋቸውን ላለማስደፈር በጭፍን የሚንደረደረውን የሻእቢያ ሀይል በጨበጣ ጭምር ይዘው እየወደቁ ነው። ውግያ መከፈቱን ሪፖርት የደረሳቸው ጀነራል ጻድቃን ከአዲሀገራይ ተነስተው አዲ አምሃራይ ላይ ኮማንድ ፖስታቸውን በማቋቋም በቀጥታ ለኮሎኔል ናቃቸው ቆምጨጭ ያለ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። በፍጥነት ምሽጉን እንዲያስመልስ። ለአንድ ሰአት ያህል በጭስ መካከል ቅልጥ ያለውም ተኩሱ እና ፍንዳታውን ለተመለከተ "ህይወት ከዚህ መካከል ይተርፋል ወይ?" የሚያስብል እና ምናልባትም በ ምትሀት ከሆነ የሚያስብል ነው። ግጥሚያው ከ ሰባት የሻእቢያ ክፍለጦሮች ጋር ነው። የሻእቢያ አንድ ክፍለጦር ከሁዋላው የሚከተለው አንድ ብርጌድ ድጋፍ ሰጪ ሀይል አለው ። ጠቅላላው የሻእቢያ ክፍለጦሮች ውስጥ ያሉት ብርጌዶች ሲሰሉ 28 የጠላት ብርጌድ ለአንዲት የኢትዮጵያ ብርጌድ ነው የገጠሙት ። የተወሰኑ ሀይሎቹን ማሰባሰብ የቻለው ኮሎኔል ናቃቸው እንደ አንድ ተዋጊ ክላሽንኮቩን ወደ ተያዘባቸው ምሽግ ደግኖ ሲተኩስ በአቅራቢያው ያለው ከፊቱ ቀድሞ ለመውደቅ እየተንደረደሩ በድንገተኝነት በተቀሙት ምሽግ ላይ እነሱም በቅጽበታዊነት በወሰዱት እርምጃ የተወሰኑ ምሽጎቻቸውን ማስለቀቅ ቻሉ። ለብርጌድ ሁለት እንድትደርስ መመሪያ የተሰጣት በ30 ኪ/ሜ ርቀት (ቢያራ) ስልጠና ላይ የነበረችው እና በኮሎኔል (ፊ/ማ) ብርሃኑ ጁላ የምትመራው 22ኛ ክ/ጦር ስትሆን በወቅቱ ሰራዊቱን በፍጥነት ወደ ምሽግ ለማስጠጋት አንድም መኪና ባለመኖሩ ሰላሳ ኪሎሜትሩን በሩጫ ተያይዘውታል። የሻእቢያ ሀይል በቁጥር አንድ በመቶ በሚያስብል ደረጃ በሚታኮስባት በእያንዳንዷ ሰከንድ የ2ኛ ብርጌድ አባላት የህይወት መስዋእትነት እየከፈሉ ነበር። በጠላት ከበባ ውስጥ የወደቀችው ብርጌድ 9ሰአት ሲሆን የቀራቸውን የሰው ሀይል በመያዝ ሰብረው እንዲወጡ ትእዛዝ ተላለፈ። ብርጌድ ሁለት ተኩስ ሲከፈትባት የሰው ሀይሏ ቁጥር 850 ነበር። አመሻሽ ላይ ከኮሎኔል ናቃቸው የጠላትን የተኩስ ቀለበት ሰብረው ለመውጣት የቻሉት በቁጥር አንድ መቶ ሀምሳ የማይሞሉ ነበሩ። ለሊት ላይ ደግሞ ሌላ ግርምትን የሚፈጥር ታሪክ ተከሰተ ። የዚህችው የብርጌድ ሁለት አካል የሆነች እና መ/አ ታደሰ (ካልተሳሳትኩ የቀድሞ ሰራዊት ይመስለኛል) የሚመራት የሻምበል ሀይል ቀደም ብላ ሙሉ በሙሉ በጠላት እንደተደመሰሰች ነበር ሪፖርት የተደረገው። ሙሉ በሙሉ በጠላት ከበባ ውስጥ መውደቃቸውን የተረዳው መ/አ ታደሰ ጨለማውን ተገን በማድረግ ከከበባ ለመውጣት ለሚመራው ሀይል አንድ መመሪያ አስተላልፏል። " ማንም ቢያናግራቹ መልስ የምሰጠው እኔ ብቻ ነኝ" በማለት በጨለማው ውስጥ ከሻእቢያ ጦር ጎን ተሰልፈው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ሰፈረበት ለሊቱን ጉዞ ጀምረዋል። ሻእቢያዎች በጨለማው ውስጥ ከሌላኛው ጎናቸው አንድ መስመር ሰርተው የሚጓዙትን በመ/አ ታደሰ የሚመራው ጦር የራሳቸው ሀይል እንደሆነ ነበር የሚያስቡት ። ለሊቱ ከጨለማው እየተላቀቀ ባለበት ሰአትም ግራ ቀኝ የሚጓዘው ሀይል መስመሩን ይዞ ወደፊት እያመሩ ነው። ከአስር ሜትር ርቀት ላይ ካለው የሻእቢያ ወታደሮች አዛዥ መካከል አንዱ ድንገት ወዲህ ጠጋ በማለት ጥያቄ አነሳ በትግርኛ "ስንተኛ ናቹ" የሚል ነበር ጥያቄው። መ/አ ታደሰ ቀደም ብሎ "ጥያቄ ብትጠየቁ ከእኔ በቀር ማንም መልስ እንዳይሰጥ " ነበር ያላቸው።(ታደሰ ረጅም አመታት አልጌና እና ናቅፋ ላይ የኖረ ፣ የየአከባቢውን ቋንቋ አጠቃቀምም ጠንቅቆ የሚረዳ ነበር። ከወዲያ በኩል " እነማን ናቹህ" ለሚለው ጥያቄው መ/አ ታደሰ ምላሽ ከመስጠቱ በፊት አንድ የትግራይ ተወላጅ አፉ እንዳመጣለት መልስ ሰጠ "ሻለቃ ሰለስተ" "ሶስተኛ ሻለቃ" ማለቱ ነበር ። በ ቅጽበት ከማዶ ያሉትን የሻእቢያ ሰራዊት አይኖች እንደፈጠጡ እጆቻቸውን በመሳሪያቸው ቃታ አውለው ተኩስ ከፈቱ ። በህወሀት አጠራር ሻለቃን "ሻለቃ " በማለት የሚጠራ ሲሆን ሻእቢያ ደግሞ "ሻለቃን" ለመጥራት " ቦጦሎኒ" በማለት ነው የሚጠሩት። ሙሉ በሙሉ መደምሰሷ ሪፖርት የተላለፈባት በመ/አ ታደሰ የምትመራው የሻምበል ጦር ከሻእቢያ ሀይል ጋር ተታኩሳ የገጠማትን ገደል በመሻገር እናት ክፍሏን ስትቀላቀል ከሀያ የማይበልጡትን በመስዋእትነት ከፍላ ነበር።

Открыть в Telegram
Просмотры1 920−50%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч1 570
5 ч1 800
7 ч1 920
  1. Через 6 часов1 920
  2. Всего сейчас1 920
#10449Текст

ክፍል አንድ.... 1990 ዓ.ም. የኤርትራ ጦር ባድመን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በአካባቢው እጅግ ጠንካራ እና ጥልቅ የኮንክሪት ምሽጎችን ገንብቶ ነበር። ይህን ምሽጉን "አለም አቀፍ ወታደራዊ ጠበብቶች " በማለት የገለጿቸው የኢራቅ እና የአረብ ወታደራዊ ጀነራሎች ሳይቀሩ ስለጎበኙት ምሽግ እና ጥንካሬ ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ባድመን ለመያዝ ብትሞክር ኤርትራ ምሽጉን ሳታስደፍር ለመቶ ዓመት ያህል ያዋጋታል (አይደፈርም)" የሚልን ምስክርነትን ሰጡ። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና አደራዳሪዎች ኤርትራ ሠራዊቷን ከባድመ እንድታስወጣ ጥሪ ባቀረቡበት እለት ምሽት ላይ በትእቢት የሰከረው ኢሳያስ አፈወርቂ ለአለም ቁርጥ የሆነ ምላሽ ሰጠ "ባድመ መሬታችን ነው ለኛ ባድመን መልቀቅ ማለት ፀሐይ በምዕራብ ወጥታ በምሥራቅ እንደመግባት (እንደመጥለቅ) ነው» የሚል። የካቲት 1991 ዓ.ም.... ስልጠናውን አጠናቆ ባድመ ግምባር የደረሰው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ውግያ ሲገባ " ባድመን መልቀቅ ማለት ፀሐይ በምዕራብ ወጥታ በምሥራቅ እንደመጥለቅ ነው" ለሚለው ፉከራ የተሰጠ ምፀታዊ ምላሽ ይሆን ዘንድ የወታደራዊው ዘመቻ ስያሜ «ኦፕሬሽን ፀሐይ ግባት» (Operation Sunset) የሚል ነበር። ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 19 ቀን 1991 ዓ.ም ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀናት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውግያ ያ ለመቶ አመት ያዋጋል ተብሎ ብዙ የተዘመረለት ፣ በነጮች ምስክርነት የተሰጠለት ረጅም የኮንክሪት ምሽግ ሙሉ በሙሉ ተንዶ የካቲት 19 ቀን 1991 ዓ.ም ባድመንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ዋለ። ባድመን መልቀቅ ለ ኢሳያስ አፈወርቂ እንቅልፍ የሚያሳጣ ነበር ። ያን ሽንፈቱን የሚደልዝለት ሌላ ከባድ ስልትን በመጠቀም መልሶ ባድመን ለመቆጣጠር ቀን አስልተው ተንቀሳቀሱ ። በወቅቱ መላው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ስልጠና እንዲገባ የተደረገበት እና ከጀነራሎች ጀምሮ እስከ መስመራዊ መኮንኖች ድረስ ያሉት በባለፈው ውግያዎች የነበሯቸውን ጥሩም ይሁን ደካማ ጎኖች ላይ ጠንካራ ግምገማ ላይ ያሉበት ወቅት ነበር። በወቅቱ የኤርትራ ሰራዊት የሚጠቀምባቸው ማንኛውም አይነት ወታደራዊ መገናኛ ሬድዮኖች ዝግ እንዲሆኑ በመደረጋቸው በኢትዮጵያ ወገን ሁኔታዎችን ለመከታተል እጅግ አሰሰቸጋሪ ነበር። ግምቦት 2/1991 በዚያች እለት ኢትዮጵያ አለኝ የምትላቸው ወታደራዊ አመራሮች ከምሽጉ በ70k/m ርቀት ላይ ከምትገኘው አዲሀገራይ ላይ በጀነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይ አመካይነት ተሰብስበው የአመራር ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን ማንኛውንም አይነት ዋጋ ይሁይ ተከፍሎ ባድመን መልሶ እንዲይዝ ከኢሳያስ አፈወርቂ ትእዛዝ የወረደለት ሰራዊት በውግያው ግምባር ደርሷል። በኢትዮጵያ ሰራዊት በኩል ከባድመ ከተማ አቅራቢያ ላይ ምሽግ ይዞ የሚገኘው ሰራዊት በምስሉ ላይ በሚታየው ኮሎኔል ናቃቸው ጫቅሌ በምትመራው የ31ኛ ክ/ጦር አካል የሆነችው 2ኛ ብርጌድ ናት። ሻእቢያ በዚህ በኩል ለማጥቃት የመረጠበት ምክንያት በጠላት እና በእኛ ሰራዊት መካከል ያለው ርቀት ትልቁ ሶስት መቶ ሜትር ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ እስከ ሰላሳ ሜትር የተቀራረቡ ምሽጎች ሲሆኑ ከሁለቱም ወገን ሲጠራሩ ስለሚሰማ ጥበቃ ተረኛው ማን እንደሆነ በስም ጭምር ከሁለቱም ወገን እስከማወቅ ተደራርሰዋል። የሻእቢያ እቅድም በዚያች ቅርበት ባለባት መሬት በኩል የኢትዮጵያን ሰራዊት በማዘናጋት ሮጦ ምሽግ ውስጥ መግባት እንችላለን " የሚልን እምነት ሰንቀዋል። በወቅቱ የ31ኛ ክ/ጦር አካል ከሆነችው ብርጌድ2 አቅራቢያ ያሉት የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሁለት ክፍለጦሮች (31ኛ እና 33ኛ) ሲሆኑ ሁለቱም ምሽግ ላይ በመሆናቸው አንደኛው ለሌላኛው ለመድረስ ምሽጋቸውን መልቀቅ ስለሚሆንባቸው ሌላን ለማዳን በማይችሉበት አቋም ላይ የተሰለፉ ሲሆን በቅርበት ሰራዊት አለ ከተባለ ከባድመ 30ኪ/ሜ ርቀት በቢያራ ስልጠና ላይ የምትገኘው በእነ (በወቅቱ ኮሎኔል ) የዛሬው ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የምትመራው 22ኛ ክ/ጦር ናት። ባድመ ምሽግ ላይ በምትገኘው የ 31ኛ ክ/ጦር አካል በሆነችው ብርጌድ ሁለት ላይ ሻእቢያ ያዘመተችው ጦር 525ኛ በማለት የሚጠሩት ኮማንዶ ክፍለጦር (ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንደተገነጠለች አሜሪካ የአፍሪካን ቀንድ ሰላም ያስከብሩልኛል በማለት ለተከታታይ አመታት ለሻእቢያ ወታደሮች የሬንጀርስ ክማንዶ ስልጠና ስትሰጥ የቆየች ሲሆን ይህ 525ኛ የተባለው ኮማንዶ ክ/ጦርን ጨምሮ ሌሎች ስድስት ክፍለጦሮች አንዲት ብርጌድ በያዘችው መሬት ላይ ሲያሰማሩ በኢትዮጵያ በኩል "ኦፕሬሽን ፀሐይ ግባት" በማለት ባድመን ለያዘበት ምላሽ ለመስጠት በባድመ በኩል የተሰለፈው የሻእቢያ ሰባት ክፍለጦር ሰራዊት ከላይ የለበሰው ቲሸርት "ሰኑይ ባድመ" የሚል ነበር ( እርግጠኛ ሆነው ሰኞ ዕለት ባድመን እንቆጣጠራለን ነበር ያሉት) ለማለት ነዉ። ሰኔ 3 /1991 ከጠዋቱ 11 ሰአት .... ልክ በዚህች እለት (ሰኔ 3/1990) ይህችው በኮሎኔል ናቃቸው ስትመራ የነበረችው ክፍለጦር ከአንድ አመት በፊት እርዲ ማቲዎስ ላይ በሻእቢያ ተከባ ሙሉ በሙሉ እስከ መበታተን ብትደርስም በኮሎኔሉ ብቁ አመራር ከከበባ በመላቀቅ ዛሬ ላይ የደረሱ ሲሆን ከአመት በፊት የህይወት ዋጋ የከፈሉ ጓዶቻቸውን ለመዘከር ሻማ አብርተው ሻይ በማፍላት እየተጨዋወቱ ሲሆን ኮሎኔል ናቃቸው ከተጠራቀመው የበርሜል ውሀ በጀሪካን ይዞ ወደ ገላ መታጠቢያው በማምራት ልብሱን አውልቆ ውሀ በላዩ እያፈሰሰ ባለበት ነበር በዚያች አንዲት ብርጌድ በተሰለፈችበት በጠባቧ መሬት ላይ የጠላት ሰባት ክ/ጦር ጥይት በላ መውረድ የጀመረው.። ይቀጥላል....

Открыть в Telegram
Просмотры2 490−35%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
4 ч2 350
7 ч2 490
  1. Через 6 часов2 490
  2. Всего сейчас2 490
#10448Фото
Просмотры2 380−38%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
4 ч2 250
7 ч2 380
  1. Через 6 часов2 380
  2. Всего сейчас2 380
#10447Видео
Просмотры4 170+9%к среднему
Пересылки—
Реакции51
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
11 ч2 450
28 ч4 170
  1. Через 24 часа4 170
  2. Всего сейчас4 170
#10445Фото
Просмотры4 040+6%к среднему
Пересылки—
Реакции77
Комментарии—
#10438Фото

ከሽራሮ ከተማ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። ባድመ። ከሽረ እንዳስላሴ ከተማ ወደ ሽራሮ ከተማ የሚጓዝ ሰው ዓዲ ዳዕሮ፣ ዓዲ ነብርኢድ እና ዓዲ ሃገራይ ከተሞችን አቋርጦ ማለፍ አለበት። ከሽራሮ ከተማ ወደ ባድመ ከተማ ለመሄድ ደግሞ ዋዕላ ንህቢ፣ ገዛ ተጋሩ፣ ሰምበል፣ ደንበ መንጉል እና ደንበ ገዳሙ ይጠብቁሃል። * ወደ ባድመ ከተማ ስንገባ በመግቢያው ላይ የሚቀበሉን የሻዕቢያን ወረራ ለመመከት በቢያራ፣ በገዛ ገረላሰ፣ በጎቦ ጨጓር፣ በፅብራ፣ በጎቦ ቡምበት፣ በዓዲ ሃኪም፣ በፀሊም ቀላይ እና በሌሎችም ስፍራዎች የወራሪውን የሻእቢያን ወረራ ለመመከት በጀግንነት ሲዋጉ የተሰው ጀግኖች ኢትዮጵያውያን መቃብሮች በምትመለከቱት መልኩ እንደ ንቁ ወታደር በሰልፍ ተሰትረው ይገኛሉ። በእርግጥም ባድመ መሬት ብቻ አይደለችም በዚያ ያለን አፈር ብቻ አይደለም ። በባድመ የእልፍ ወንድሞቻችን ደም ፈሶበታል ፣ ቁጥር የማይገልጻቸው ወጣቶች አጥንት በዚያ አርፏል። ባድመ ለቁጥር በማይታክቱ ጀግኖች አጥንት የታጠረች በደማቸው ተለውሶ የታጠረ ሀቅ ነው።የባድመ መሬት አፈርና ሳር ብቻ የተሸከመ አይደለም፤ የጀግኖች ደምና አጥንት ጭምር እንጂ። ክብር ለሰማእታት!

Открыть в Telegram
Просмотры5 820+52%к среднему
Пересылки—
Реакции61
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
52 ч5 310
70 ч5 820
  1. Всего сейчас5 820
#10437Видео
Просмотры5 020+31%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
54 ч4 630
71 ч5 020
  1. Всего сейчас5 020

Все посты

Связи