Кабинет
Christ and Him Crucified

Christ and Him Crucified

As we navigate the journey of life together, let’s focus on pursuing truth, holiness, and godliness. Let's to gently confront sin, along with the influences of the world & the flesh. CORAM DEO.

Юзернейм
@christisallsufficient
Категория
Религия
Подписчики3 190
Просмотров на пост, 7 дн.265−53,9% к пред. 7 дн.
ERR8,29 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
6 нояб. 2026 г.837
9 нояб. 2026 г.637
10 нояб. 2026 г.756
11 нояб. 2026 г.710
12 нояб. 2026 г.636
13 нояб. 2026 г.495
14 нояб. 2026 г.634
15 нояб. 2026 г.618
17 нояб. 2026 г.514
18 нояб. 2026 г.699
19 нояб. 2026 г.497
20 нояб. 2026 г.426
22 нояб. 2026 г.355
23 нояб. 2026 г.278
26 нояб. 2026 г.45

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры837
    Пересылки—
    Реакции16
    Комментарии—
  2. 02

    ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈጠናቸው ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ ከእዛ ጉስቁልና ከመከራ ወጣ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች እርሷም እንደሰው . (1) . ዘመኗ ደረሰ እምባዋ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ ዛሬም ብንጠበው በመጠበቂያችን እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም . . . © ታደሰ እሽቴ @Christisallsufficient

    Аудио
    Просмотры756
    Пересылки—
    Реакции7
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры753
    Пересылки—
    Реакции11
    Комментарии—
  4. 04

    Wishing you a happy Sabbath and a meaningful communion. ጥሩ የግል የጸሎት፣ የንባብና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ ሊኖረን ይችላል። ይህ እጅግ ታላቅ መንፈሳዊ ባለጠግነት ነው፤ የማይተካም በረከት ነው። በእርግጥም እነዚህ የግል መንፈሳዊ ልምምዶች ለክርስቲያን ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ልምምዶች ከቤተክርስቲያን ሕብረት ተነጥለው ሲከናወኑ የሚያፈሩት ፍሬ ሊያንስ ይችላል። በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕብረት የሰጠውን ታላቅ ቦታና አስፈላጊነት እንመለከታለን። በረከቶችና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋቶች እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸው ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ብዙዎቹንም በቤተክርስቲያን ሕብረት ውስጥ እንድንለማመድ ወስኗል። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች «ጸድቃችኋል፣ ተመርጣችኋል፣ ቅዱሳን ናችሁ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፣ ተባርካችኋል፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ናችሁ» በማለት አማኞችን በብዙ ቁጥርና በሕብረት የሚገልጻቸው በአጋጣሚ አይደለም። ይህም የክርስቲያን ሕይወት በግለሰብ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በአንድ አካል ውስጥ የተሳሰረ የአማኞች ሕይወት መሆኑን ያሳያል። «እነሆ፥ ወንድሞች በአንድነት ተቀምጠው መኖር እንዴት መልካምና ያማረ ነው!» (መዝሙር 133፥1)። መንፈሳዊ ሕይወት ለብቻችን የምንኖረው ሕይወት አይደለም። በእርግጥ እያንዳንዳችን በግል በእምነት ወደ ክርስቶስ እንመጣለን፤ እያንዳንዱም በግል በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ከኃጢአትና ከሞት ያዳነን ለብቻችን ተነጥለን እንድንኖር ሳይሆን የክርስቶስ አካል አባላት እንድንሆን ነው። ስለዚህ የድነትን በረከቶች የምንለማመደውና በጸጋ የምናድገው በአማኞች ሕብረት ውስጥም ጭምር ነው። «እኛ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እያንዳንዳችንም ለእርስ በርሳችን አካላት ነን» (ሮሜ 12፥5)። ያለ ሕብረት ብቻችንን የምንኖረው መንፈሳዊ ሕይወት ከመንጋው ተለይቶ ብቻውን ከቀረ አንበሳ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። አንበሳ የአራዊት ንጉሥ ቢባልም፣ ከመንጋው ተለይቶ ብቻውን ሲቀር ለጥቃት ይበልጥ የተጋለጠ ይሆናል። በተመሳሳይም ክርስቲያን ከቤተክርስቲያን ሕብረት ራሱን ሲያገል፣ በመንፈሳዊ ትግሉ ውስጥ ብቻውን ይቀራል፤ የወንድሞችና የእህቶች ማበረታቻ፣ ምክር፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ድጋፍም ይጎድለዋል። ምክንያቱም «አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ባልንጀራው ያነሣዋል» (መክብብ 4፥10)። May God help us to grow in holy fellowship! @Christisallsufficient

    Текст
    Просмотры708
    Пересылки—
    Реакции11
    Комментарии—

Новые посты

#3698Текст

ክርስትና በእሁድ የምንለብሰው የኃይማኖት ልብስ፣ በአፋችን የምንደግመው የእምነት ቃል ወይም በሰዎች ፊት የምናሳየው መንፈሳዊ ማንነት ብቻ አይደለም። ክርስትና በየዕለቱ በምንኖረው ሕይወት የሚገለጥ እውነት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ «ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ነገር ግን በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ» (ሮሜ 12፥2) በማለት የክርስቲያን ሕይወት ከዓለም አስተሳሰብ፣ ከዓለም እሴቶችና ከዓለም የሕይወት አቀራረብ የተለየ መኾን እንዳለበት ያስተምረናል። እምነታችን ከአፋችን ብቻ ሳይኾን ከሕይወታችንም መነበብ አለበት። በንግግራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በተግባራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሥራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በግንኙነታችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሐቀኝነት፣ በፍትሕ፣ በይቅርታና በፍቅር ላይ የዓለምን አመለካከት እየተከተልን ከኾነ፣ በአፋችን ክርስቲያን መኾናችንን ብናውጅ እንኳን ሕይወታችን የሚያሳየው ሌላ ነገር ነው። ያዕቆብ 2፥17 እምነት ከሥራ ውጭ ከኾነች ሙታ እንደኾነች ይነግረናል። ሰዎች ከእኛ የሚያዩት የክርስቶስን ባሕርይ ካልኾነ፣ የምንሰብከው ወንጌል በሕይወታችን ውስጥ ምን ያኽል ሥራ እየሠራ ነው? ዓለም በሐሰት፣ በራስ ወዳድነት፣ በቂም፣ በስግብግብነት፣ በጥላቻና በሥጋዊ ፍላጎት ላይ ቢመሠረት እኛ ግን በእውነት፣ በፍቅር፣ በትሕትና፣ በቅድስናና በፍትሕ መራመድ አለብን። ክርስቶስ በማቴዎስ 5፥16 «መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ» ብርሃናችን በሰዎች ፊት እንዲበራ አዝዞናል። ይኽ ማለት በሰዎች ፊት ለመታየት መልካም ሥራ መሥራት ሳይሆን፣ ሕይወታችን እግዚአብሔርን እንዲያከብር መኖር ማለት ነው። ክርስትና የተለየ አስተሳሰብ ብቻ ሳይኾን የተለየ አኗኗር ነው። ስለዚኽ የምንለውን ብቻ ሳይሆን የምንኖረውንም ሕይወት እንመርምር። በቤታችን፣ በሥራ ቦታችን፣ በንግዳችን፣ በማኅበራዊ ግንኙነታችን፣ በምንጽፈው ነገር፣ በምንናገረው ቃል፣ በምንወስነው ውሳኔና በምንፈጽመው ተግባር ሁሉ ክርስቶስ ይታይ። ከእኛ ጋር የሚገናኝ ሰው የዓለምን ክፋት ሳይሆን የክርስቶስን ባሕርይ እንዲያይ እንኑር። ዓለም እኛን ወደ ራሷ እንድትቀይር አንፈቀድ፤ እኛ ግን በክርስቶስ ተለውጠን ለዓለም ብርሃንና ጨው እንሁን። “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” ሮሜ 12:1-2 NASV

Открыть в Telegram
Просмотры71−86%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#3693Текст
Просмотры375−27%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#3689Текст
Просмотры699+37%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—

Все посты

Связи