ክርስትና በእሁድ የምንለብሰው የኃይማኖት ልብስ፣ በአፋችን የምንደግመው የእምነት ቃል ወይም በሰዎች ፊት የምናሳየው መንፈሳዊ ማንነት ብቻ አይደለም። ክርስትና በየዕለቱ በምንኖረው ሕይወት የሚገለጥ እውነት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ «ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ነገር ግን በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ» (ሮሜ 12፥2) በማለት የክርስቲያን ሕይወት ከዓለም አስተሳሰብ፣ ከዓለም እሴቶችና ከዓለም የሕይወት አቀራረብ የተለየ መኾን እንዳለበት ያስተምረናል። እምነታችን ከአፋችን ብቻ ሳይኾን ከሕይወታችንም መነበብ አለበት። በንግግራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በተግባራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሥራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በግንኙነታችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሐቀኝነት፣ በፍትሕ፣ በይቅርታና በፍቅር ላይ የዓለምን አመለካከት እየተከተልን ከኾነ፣ በአፋችን ክርስቲያን መኾናችንን ብናውጅ እንኳን ሕይወታችን የሚያሳየው ሌላ ነገር ነው። ያዕቆብ 2፥17 እምነት ከሥራ ውጭ ከኾነች ሙታ እንደኾነች ይነግረናል። ሰዎች ከእኛ የሚያዩት የክርስቶስን ባሕርይ ካልኾነ፣ የምንሰብከው ወንጌል በሕይወታችን ውስጥ ምን ያኽል ሥራ እየሠራ ነው? ዓለም በሐሰት፣ በራስ ወዳድነት፣ በቂም፣ በስግብግብነት፣ በጥላቻና በሥጋዊ ፍላጎት ላይ ቢመሠረት እኛ ግን በእውነት፣ በፍቅር፣ በትሕትና፣ በቅድስናና በፍትሕ መራመድ አለብን። ክርስቶስ በማቴዎስ 5፥16 «መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ» ብርሃናችን በሰዎች ፊት እንዲበራ አዝዞናል። ይኽ ማለት በሰዎች ፊት ለመታየት መልካም ሥራ መሥራት ሳይሆን፣ ሕይወታችን እግዚአብሔርን እንዲያከብር መኖር ማለት ነው። ክርስትና የተለየ አስተሳሰብ ብቻ ሳይኾን የተለየ አኗኗር ነው። ስለዚኽ የምንለውን ብቻ ሳይሆን የምንኖረውንም ሕይወት እንመርምር። በቤታችን፣ በሥራ ቦታችን፣ በንግዳችን፣ በማኅበራዊ ግንኙነታችን፣ በምንጽፈው ነገር፣ በምንናገረው ቃል፣ በምንወስነው ውሳኔና በምንፈጽመው ተግባር ሁሉ ክርስቶስ ይታይ። ከእኛ ጋር የሚገናኝ ሰው የዓለምን ክፋት ሳይሆን የክርስቶስን ባሕርይ እንዲያይ እንኑር። ዓለም እኛን ወደ ራሷ እንድትቀይር አንፈቀድ፤ እኛ ግን በክርስቶስ ተለውጠን ለዓለም ብርሃንና ጨው እንሁን። “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” ሮሜ 12:1-2 NASV
Open in Telegram
Christ and Him Crucified
As we navigate the journey of life together, let’s focus on pursuing truth, holiness, and godliness. Let's to gently confront sin, along with the influences of the world & the flesh. CORAM DEO.
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 6, 2026 | 837 |
| Nov 9, 2026 | 637 |
| Nov 10, 2026 | 756 |
| Nov 11, 2026 | 710 |
| Nov 12, 2026 | 636 |
| Nov 13, 2026 | 495 |
| Nov 14, 2026 | 634 |
| Nov 15, 2026 | 618 |
| Nov 17, 2026 | 514 |
| Nov 18, 2026 | 699 |
| Nov 19, 2026 | 497 |
| Nov 20, 2026 | 426 |
| Nov 22, 2026 | 355 |
| Nov 23, 2026 | 278 |
| Nov 26, 2026 | 45 |
Most viewed this month
- 01Views837Forwards—Reactions16Comments—
- 02Views756Forwards—Reactions7Comments—
- 03Views753Forwards—Reactions11Comments—
- 04Views708Forwards—Reactions11Comments—
Latest posts
Christianity will humble you in every direction when you grow under the authority of the scriptures. Christianity is truly beautiful!
Open in TelegramWhen God gives you a chance to repent, that's one of the best calls you could ever receive. If you skip this calling, you risk your life and despise His mercy. There will come a time when you will miss this calling.
Open in Telegramክርስቲያን አልወልድም ከወለድሁም አንድ ነው እምወልደው እያለ ይሽኮረመማል! እስልምና በ2035 ክርስትናን በልጦ በዓለም ትልቁ ሃይማኖት ይሆናል እየተባለ ነው! እስልምና ታላቁ ሃይማኖት በ2035 የሚሆነው የእስልምናን መሰረታዊ አስተምህሮ በአለም በመስበክ ወይም እንደ ከዚህ በፊቱ በጂሃድ ጦርነት አይደለም፤ ይልቁን ብዙ ልጆች የመውለድ ዝንባሌ ስላላቸው ነው ይለናል የፒው የምርምር ማዕከል ትንበያ! ዛሬ ቀንህን የምታከብረው ክርስቲያን ወንድ ሆይ ተነስተህ የቃልኪዳን ምስትህን ፈልግ፤ የቃልኪዳን ምስትህን እንዳገኘህ ብዙ የቃልኪዳን ማህበር አባል የሚሆኑ ልጆችን ውለድ!
Open in TelegramDear unmarried Christian sisters, cherish your purity and remain untouched until marriage. Remember, you are meant to be someone's future wife.
Open in TelegramIf you happen to be around Hawassa and are seeking a Church that boldly shares the Word of God, you might consider visiting this church. https://lolechurch.et/
Open in Telegram<ቤተክርስቲያን ከላከችልን ወደ 40 ሺህ ብር ፈርቅ ይዘናል። ብዙም ባይሆን በቂ ነው።> ይህን ዛሬ ጠዋት የሆነ ዕቃ ለመግዛት ወደ አንድ ሱቅ ጎራ ባልኩበት የሰማሁት አስደንጋጭ ነገር ነው። ቤተክርስቲያን እምነቷን ጥላ ዕቃ እንዲገዛ ብላ የላከቻቸው ሰዎች (probably they seems like a Church leaders) እንዲህ መሆናቸው የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ያለችበትን የጽድቅና የሞራል ወድቀት ምን ያኽል እንደወረደ ይነግረናል። እነዚህ ሰዎች ለእኔ ከይሁዳ በምንም አይለዩም። ጌታን በአካል ቢያገኙ ያለጥርጥር ለገንዘብ ይለውጡታል። ደሞ ሻጩን 'ጌታ አንተን ይባርክህ' ማለታቸው በቁጣም ብሆን ፈገግ እንድል አደረገኝ። 🙂 እንግዲህ በልባቸው ላይ የነገሰው ጌታ (ገንዘብ) 'ይባርክህ' ማለታቸው ይመስላል። መሐረነ
Open in TelegramConnections
Similar channels
Dakwah Psychology@dakwahpsychologyReligion3.19K
آلّشآعرهً آلــــّعــلّويِـــه آلّمٌوسويِــــۿ@alweyaamosaweyarrrr2626Religion3.19K
ТОТРЕНГЦАЛ@totrengzalReligion3.19K
Hanafiy Fakulteti 🇺🇿 🇯🇴@hanafiyfakultetiReligion3.19K
ASTU ECSF@astuecsfReligion3.2K
إطمئنانّ.@feei3Religion3.2K
Евгений Куценко@evgenkutsenkoReligion3.18K
•مأویٰ القَلب•@konje8Religion3.2K