ክርስትና በእሁድ የምንለብሰው የኃይማኖት ልብስ፣ በአፋችን የምንደግመው የእምነት ቃል ወይም በሰዎች ፊት የምናሳየው መንፈሳዊ ማንነት ብቻ አይደለም። ክርስትና በየዕለቱ በምንኖረው ሕይወት የሚገለጥ እውነት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ «ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ነገር ግን በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ» (ሮሜ 12፥2) በማለት የክርስቲያን ሕይወት ከዓለም አስተሳሰብ፣ ከዓለም እሴቶችና ከዓለም የሕይወት አቀራረብ የተለየ መኾን እንዳለበት ያስተምረናል። እምነታችን ከአፋችን ብቻ ሳይኾን ከሕይወታችንም መነበብ አለበት። በንግግራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በተግባራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሥራችን ዓለምን እየመሰልን፣ በግንኙነታችን ዓለምን እየመሰልን፣ በሐቀኝነት፣ በፍትሕ፣ በይቅርታና በፍቅር ላይ የዓለምን አመለካከት እየተከተልን ከኾነ፣ በአፋችን ክርስቲያን መኾናችንን ብናውጅ እንኳን ሕይወታችን የሚያሳየው ሌላ ነገር ነው። ያዕቆብ 2፥17 እምነት ከሥራ ውጭ ከኾነች ሙታ እንደኾነች ይነግረናል። ሰዎች ከእኛ የሚያዩት የክርስቶስን ባሕርይ ካልኾነ፣ የምንሰብከው ወንጌል በሕይወታችን ውስጥ ምን ያኽል ሥራ እየሠራ ነው? ዓለም በሐሰት፣ በራስ ወዳድነት፣ በቂም፣ በስግብግብነት፣ በጥላቻና በሥጋዊ ፍላጎት ላይ ቢመሠረት እኛ ግን በእውነት፣ በፍቅር፣ በትሕትና፣ በቅድስናና በፍትሕ መራመድ አለብን። ክርስቶስ በማቴዎስ 5፥16 «መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ» ብርሃናችን በሰዎች ፊት እንዲበራ አዝዞናል። ይኽ ማለት በሰዎች ፊት ለመታየት መልካም ሥራ መሥራት ሳይሆን፣ ሕይወታችን እግዚአብሔርን እንዲያከብር መኖር ማለት ነው። ክርስትና የተለየ አስተሳሰብ ብቻ ሳይኾን የተለየ አኗኗር ነው። ስለዚኽ የምንለውን ብቻ ሳይሆን የምንኖረውንም ሕይወት እንመርምር። በቤታችን፣ በሥራ ቦታችን፣ በንግዳችን፣ በማኅበራዊ ግንኙነታችን፣ በምንጽፈው ነገር፣ በምንናገረው ቃል፣ በምንወስነው ውሳኔና በምንፈጽመው ተግባር ሁሉ ክርስቶስ ይታይ። ከእኛ ጋር የሚገናኝ ሰው የዓለምን ክፋት ሳይሆን የክርስቶስን ባሕርይ እንዲያይ እንኑር። ዓለም እኛን ወደ ራሷ እንድትቀይር አንፈቀድ፤ እኛ ግን በክርስቶስ ተለውጠን ለዓለም ብርሃንና ጨው እንሁን። “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” ሮሜ 12:1-2 NASV
Открыть в TelegramПосты канала Christ and Him Crucified
Christianity will humble you in every direction when you grow under the authority of the scriptures. Christianity is truly beautiful!
Открыть в TelegramWhen God gives you a chance to repent, that's one of the best calls you could ever receive. If you skip this calling, you risk your life and despise His mercy. There will come a time when you will miss this calling.
Открыть в Telegramክርስቲያን አልወልድም ከወለድሁም አንድ ነው እምወልደው እያለ ይሽኮረመማል! እስልምና በ2035 ክርስትናን በልጦ በዓለም ትልቁ ሃይማኖት ይሆናል እየተባለ ነው! እስልምና ታላቁ ሃይማኖት በ2035 የሚሆነው የእስልምናን መሰረታዊ አስተምህሮ በአለም በመስበክ ወይም እንደ ከዚህ በፊቱ በጂሃድ ጦርነት አይደለም፤ ይልቁን ብዙ ልጆች የመውለድ ዝንባሌ ስላላቸው ነው ይለናል የፒው የምርምር ማዕከል ትንበያ! ዛሬ ቀንህን የምታከብረው ክርስቲያን ወንድ ሆይ ተነስተህ የቃልኪዳን ምስትህን ፈልግ፤ የቃልኪዳን ምስትህን እንዳገኘህ ብዙ የቃልኪዳን ማህበር አባል የሚሆኑ ልጆችን ውለድ!
Открыть в TelegramDear unmarried Christian sisters, cherish your purity and remain untouched until marriage. Remember, you are meant to be someone's future wife.
Открыть в TelegramIf you happen to be around Hawassa and are seeking a Church that boldly shares the Word of God, you might consider visiting this church. https://lolechurch.et/
Открыть в Telegram<ቤተክርስቲያን ከላከችልን ወደ 40 ሺህ ብር ፈርቅ ይዘናል። ብዙም ባይሆን በቂ ነው።> ይህን ዛሬ ጠዋት የሆነ ዕቃ ለመግዛት ወደ አንድ ሱቅ ጎራ ባልኩበት የሰማሁት አስደንጋጭ ነገር ነው። ቤተክርስቲያን እምነቷን ጥላ ዕቃ እንዲገዛ ብላ የላከቻቸው ሰዎች (probably they seems like a Church leaders) እንዲህ መሆናቸው የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ያለችበትን የጽድቅና የሞራል ወድቀት ምን ያኽል እንደወረደ ይነግረናል። እነዚህ ሰዎች ለእኔ ከይሁዳ በምንም አይለዩም። ጌታን በአካል ቢያገኙ ያለጥርጥር ለገንዘብ ይለውጡታል። ደሞ ሻጩን 'ጌታ አንተን ይባርክህ' ማለታቸው በቁጣም ብሆን ፈገግ እንድል አደረገኝ። 🙂 እንግዲህ በልባቸው ላይ የነገሰው ጌታ (ገንዘብ) 'ይባርክህ' ማለታቸው ይመስላል። መሐረነ
Открыть в Telegramክርስትናችን እሁድ ጠዋት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን፣ ዝማሬ ዘምረን፣ ጸሎት አድርገንና ቃሉን ሰምተን እሁድ አመሻሽ ላይ የሚያበቃ ከሆነ፣ የምንኖረውን እምነት በቁም ነገር መመርመር ይገባናል። በአምልኮ ወቅት ቅዱሳን መስለን በዕለት ተዕለት ኑሮአችን ግን በሐሰት፣ በማታለል፣ በግፍና በራስ ወዳድነት የምንመላለስ ከሆነ፣ በአፋችን የምንመሰክረው እምነት ከሕይወታችን ጋር ተቃራኒ ሆኗል ማለት ነው። በጉባኤ የምናነሳው እጅ በሰዎች ላይ የሚያሴር፣ የምንዘምረው አፍ በሐሜትና በስድብ የሚጠመድ ከሆነ የእምነታችንን እውነተኛነት መጠየቅ አለብን። ክርስትና የእሁድ ሥነ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሕይወት መንገድ ነው። ስለዚህ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ የምንኖረው ኑሮ የእምነታችን ምስክር መሆን አለበት። በሥራ ቦታ ታማኝና ታታሪ ነን? የሰዎችን እምነት እንጠብቃለን? በንግድ፣ በገንዘብ ጉዳይና በግል ግንኙነቶቻችን በቅንነት እንመላለሳለን? ወይስ በቤተ ክርስቲያን የምንሰብከውን በሕይወታችን ማሳየት ተስኖናል? ክርስቶስ የእሁድ አምልኳችን ጌታ ብቻ ሳይሆን የሕይወታችን ሁሉ ጌታ ነው። እምነታችንን በጉባኤ ተሳትፎአችን ብቻ ሳይሆን በምንኖረው ኑሮ፣ በምንፈጽመው ተግባርና በምናሳየው ሰብአዊነት መመዘን ይገባል። ስለዚህ ጥያቄው እሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄድን ወይስ አልሄድንም የሚለው ብቻ አይደለም፤ በየዕለቱ በምንኖረው ሕይወት ክርስቶስን እያከበርን ነውን? ከወዴት ነን? @Christisallsufficient
Открыть в TelegramYou cannot truly worship God without the true Church, and you won't receive life apart from the Church. Have a blessed Sabbath everyone!!
Открыть в TelegramWishing you a happy Sabbath and a meaningful communion. ጥሩ የግል የጸሎት፣ የንባብና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ ሊኖረን ይችላል። ይህ እጅግ ታላቅ መንፈሳዊ ባለጠግነት ነው፤ የማይተካም በረከት ነው። በእርግጥም እነዚህ የግል መንፈሳዊ ልምምዶች ለክርስቲያን ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ልምምዶች ከቤተክርስቲያን ሕብረት ተነጥለው ሲከናወኑ የሚያፈሩት ፍሬ ሊያንስ ይችላል። በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕብረት የሰጠውን ታላቅ ቦታና አስፈላጊነት እንመለከታለን። በረከቶችና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋቶች እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸው ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ብዙዎቹንም በቤተክርስቲያን ሕብረት ውስጥ እንድንለማመድ ወስኗል። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች «ጸድቃችኋል፣ ተመርጣችኋል፣ ቅዱሳን ናችሁ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፣ ተባርካችኋል፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ናችሁ» በማለት አማኞችን በብዙ ቁጥርና በሕብረት የሚገልጻቸው በአጋጣሚ አይደለም። ይህም የክርስቲያን ሕይወት በግለሰብ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በአንድ አካል ውስጥ የተሳሰረ የአማኞች ሕይወት መሆኑን ያሳያል። «እነሆ፥ ወንድሞች በአንድነት ተቀምጠው መኖር እንዴት መልካምና ያማረ ነው!» (መዝሙር 133፥1)። መንፈሳዊ ሕይወት ለብቻችን የምንኖረው ሕይወት አይደለም። በእርግጥ እያንዳንዳችን በግል በእምነት ወደ ክርስቶስ እንመጣለን፤ እያንዳንዱም በግል በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ከኃጢአትና ከሞት ያዳነን ለብቻችን ተነጥለን እንድንኖር ሳይሆን የክርስቶስ አካል አባላት እንድንሆን ነው። ስለዚህ የድነትን በረከቶች የምንለማመደውና በጸጋ የምናድገው በአማኞች ሕብረት ውስጥም ጭምር ነው። «እኛ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እያንዳንዳችንም ለእርስ በርሳችን አካላት ነን» (ሮሜ 12፥5)። ያለ ሕብረት ብቻችንን የምንኖረው መንፈሳዊ ሕይወት ከመንጋው ተለይቶ ብቻውን ከቀረ አንበሳ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። አንበሳ የአራዊት ንጉሥ ቢባልም፣ ከመንጋው ተለይቶ ብቻውን ሲቀር ለጥቃት ይበልጥ የተጋለጠ ይሆናል። በተመሳሳይም ክርስቲያን ከቤተክርስቲያን ሕብረት ራሱን ሲያገል፣ በመንፈሳዊ ትግሉ ውስጥ ብቻውን ይቀራል፤ የወንድሞችና የእህቶች ማበረታቻ፣ ምክር፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ድጋፍም ይጎድለዋል። ምክንያቱም «አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ባልንጀራው ያነሣዋል» (መክብብ 4፥10)። May God help us to grow in holy fellowship! @Christisallsufficient
Открыть в Telegramከሙላታችን ከምንሰጠው ይልቅ ከጉድለታችን የምንካፈለው ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ የበለጠ ዋጋ ያለው ይመስለኛል። ምክንያቱም ሰው ከተረፈው መስጠት ብዙም መሥዋዕትነትን አይጠይቅም፤ በተለይም ስግብግብ ካልሆነ በስተቀር ያለው ሰው ለሌላው መካፈሉ አይከብደውም። ነገር ግን ከራሳችን ፍላጎት እና ከጉድለታችን መካከል ቆርሰን ለሌላው ስንሰጥ፣ ይህ የልባችንን ፍቅር፣ የእምነታችንን እውነተኛነትና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መታመን ይገልጣል። ስለዚህ የልግስና ዋጋ በሰጠነው ነገር መጠን ብቻ ሳይሆን፣ በሰጠንበት ልብና በሠዋነው ነገር ይመዘናል። ከመሥጠት (ከመቆረስ) ጋራ ተያይዞ ያለው ነገር በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ ተዘግቦልን የምናየው ሰዎች ከጉድለታቸው ሲቆረሱ የተስተዋለበት ቦታ ላይ ነው። ጌታችንም በማርቆስ ወንጌል ላይ አንዲት መበለት ከጉድለቷ ስትቆረስ አይቶ “...እውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት ሙዳየ መባ ውስጥ ሌሎቹ ከጨመሩት የበለጠ አስገባች። እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።” (ማርቆስ 12:43-44 NASV) ያለው። ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም በሁለተኛው የቆሮንቶስ መልእክቱ ተመሳሳይ ነገር ስጽፍ እንመለከታለን፦ “ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔር በመቄዶንያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት የሰጠውን ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን። የደረሰባቸው መከራ ጽኑ ቢሆንም ደስታቸው ግን የላቀ ነበር፤ ድኽነታቸው ብርቱ ቢሆንም ልግስናቸው ግን የበዛ ነበር። እንደ ዐቅማቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከዐቅማቸው በላይ በፈቃዳቸው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁ። እነርሱም ቅዱሳንን ለመርዳት በሚደረገው አገልግሎት ለመሳተፍ ዕድል ያገኙ ዘንድ አጥብቀው ይለምኑን ነበር። እኛ ከጠበቅነው በላይ፣ በመጀመሪያ ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፤ ቀጥለውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለእኛ ሰጡ። ስለዚህ ቲቶ፣ በእናንተ መካከል ቀደም ሲል የጀመረውን የልግስና ሥራ ከፍጻሜ እንዲያደርስ ለምነነው ነበር። እናንተም በሁሉ ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በዕውቀት፣ በፍጹም ትጋትና ለእኛም ባላችሁ ፍቅር ልቃችሁ እንደ ተገኛችሁ፣ በዚህም የቸርነት ሥራ ልቃችሁ እንድትገኙ ዐደራ እንላችኋለን።” (2 ቆሮንቶስ 8:1-7 NASV) ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት የስጦታችን ዋጋ በምንሰጠው መጠን ሳይሆን በምንሰጥበት ልብ፣ በመሥዋዕትነታችንና በእምነታችን ይመዘናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የእጃችንን ስጦታ ብቻ ሳይሆን የልባችንን መሥዋዕትነት ይመለከታል። እውነተኛ ልግስናም ከትርፍ የሚፈስ ሳይሆን ከፍቅር የሚመነጭ፣ ከድህነት መካከልም ቢሆን እግዚአብሔርን ከማመን የሚፈልቅ ነው። ይህም ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ከእኛ የተረፈንን ብቻ ሳይሆን እርሱን ከሁሉ በላይ እንደምንወድና እንደምንታመንበት የሚመሰክር የሕይወት መሥዋዕትነት ነው። በመጨረሻም እግዚአብሔር የሚያከብረው የሰጠነውን ብዛት ሳይሆን በፍቅር የተሞላውን ልባችንን ነው። @Christisallsufficient
Открыть в TelegramThe Church should not make its pastor either poor or rich. If he ends up rich or poor, the Church will take the responsibility. ቤተክርስቲያን ፓስተሯን (መጋቢዋን) ድሃም ሆነ ባለጸጋ ልታደርገው አይገባም። እርሱ ባለጸጋ ወይም ድሃ ከኾነ፣ ኃላፊነቱ የቤተክርስቲያኗ ይኾናል።
Открыть в TelegramDon't allow yourself to become proud of anything in this world. Christ alone should be the source of our everlasting pride. There is nothing in this world that can compare to Him. “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። ” ወደ ገላትያ ሰዎች 6:14 አማ54
Открыть в TelegramПереслано из Christ and Him Crucified
ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈጠናቸው ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ ከእዛ ጉስቁልና ከመከራ ወጣ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች እርሷም እንደሰው . (1) . ዘመኗ ደረሰ እምባዋ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ ዛሬም ብንጠበው በመጠበቂያችን እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም . . . © ታደሰ እሽቴ @Christisallsufficient
Открыть в TelegramWhat pleases God is not just a bunch of your theological knowledge. In fact, what really pleases God is your practical life, which is the byproduct of your tiny biblical (theological) knowledge that gradually grows.
Открыть в Telegram“እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል? አካሄዱ የቀና፣ ጽድቅን የሚያደርግ፤ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤ በምላሱ የማይሸነግል፤ በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ ወዳጁን የማያማ፤ ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤ ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣ በንጹሓን ላይ ጕቦ የማይቀበል። እነዚህን የሚያደርግ፣ ከቶ አይናወጥም።” መዝሙር 15:1-5 NASV @Christisallsufficient
Открыть в Telegram