Кабинет
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

ለአስተያየት ለጥያቄ በግል ለማውራት @abigezenige ይህን ይጠቀሙ። ሐምሌ 27/11 ዓ᎐ም

Юзернейм
@abizeeotc
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики11 450
Просмотров на пост, 7 дн.1 107−28,9% к пред. 7 дн.
ERR9,67 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
9 нояб. 2026 г.1 640
10 нояб. 2026 г.1 550
13 нояб. 2026 г.1 363
14 нояб. 2026 г.1 390
15 нояб. 2026 г.1 330
16 нояб. 2026 г.2 045
19 нояб. 2026 г.2 230
20 нояб. 2026 г.1 250
21 нояб. 2026 г.2 010
22 нояб. 2026 г.1 050
23 нояб. 2026 г.951
24 нояб. 2026 г.1 070
25 нояб. 2026 г.481

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры2,47 тыс.
    Пересылки—
    Реакции4
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры2,23 тыс.
    Пересылки—
    Реакции1
    Комментарии—
  3. 03

    አቤኔዘር እባላለሁ ያው አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ 🤗 ይህ ፎቶዬ 4ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ የተነሳሁት ነው። ከጀርባ ያለው ቆርቆሮ "እድገት ወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር የተጋለጡ ሕጻናት መርጃ ማኅበር" ጊቢ ነው። በዚህ ድርጅት ከ4ኛ ክፍል ጀምሮ ዩኒቨርስቲ ተምሬ እስካጠናቅቅ ድረስ ቆይታ አድርጌያለሁ። በቆይታዬም ከድርጅቱ የትምህርት ቁሳቁስ ያሟላልኝ እና የትምህርት ክፍያዎችን ይከፍልልኝ ነበር፥ እንዲሁም በበዓላት ወቅት አዳዲስ ልብሰና ጫማም ይሰጠናል፥ ከሰኞ እስከ አርብ ምሳ የተለያየ አይነት ምግብም ይመግበን ነበር፥ የመዝናኛ ቦታዎች ይወስደን ነበር፥ የሕክምና ወጪ ይሸፍናል በተለይ ለእኔ ጽድት ያሉ ክራንቾችን ከእንግሊዝ ሀገር ያስመጣልኝ ነበር። ያው በወቅቱ በዚያ ድርጅት ክራንች የሚያስፈልገኝ እኔ ብቻ ስለነበርኩ፤ የድርጅቱ ስፖንሰር አብዛኞቹ በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው። ድርጅቱ ከ300 በላይ ሕጻናትን አሁንም ድረስ ይዞ እየረዳ ይገኛል። የድርጅቱ አድራሻ አ/አ/ክ/ከ/ል/ወ/3 አብነት አካባቢ ይገኛል። ለአቤኔዘር ዘተዋሕዶ የመኪና ግዢ ቻሌንጅ እንደቀጠለ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ በቀጣይ ቀናት live በመግባት የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐግብር አከናውናለሁ። 3ሺ የአቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ ቤተሰብ 1ሺ ብር ቢያግዘኝ መኪና እገዛና ራሴንም ቤተሰቤንም ስራ እየሰራሁ ለማገዝ አስቤያለሁ። በአቅማችሁ ድጋፍ በማድረግ ከጎኔ መቆም ለምትፈልጉ፦ * የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000 510 909 635 * (Telebirr): [+251933143133] የባንክ አካውንት ስም: አቤኔዘር ገዛኸኝ ስሜ Abenezer Gezahegn Sime My name is Abenezer—yes, the one from the "Abenezer Ze-Tewahido" page! 🤗 This photo was taken when I was a 4th-grade student. The corrugated iron structure in the background belongs to the compound of "Idget" (Progress)—an association that supports children who have lost their parents or are facing hardship. I remained with this organization from the 4th grade all the way through to the completion of my university studies. During my time there, they provided all my educational materials and covered my tuition fees. They also gave us new clothes and shoes for holidays, provided various types of lunch from Monday to Friday, took us to recreational spots, and covered our medical expenses. In my case, they even imported high-quality crutches for me all the way from England—at the time, I was the only child in the organization who needed them. Most of the organization’s sponsors are foreign nationals living in England. To this day, the organization continues to support over 300 children. It is located in Addis Ababa, Sub-city 3 (Lideta), in the Abinet area. The fundraising challenge to purchase a vehicle for "Abenezer Ze-Tewahido" is still ongoing. God willing, I will host a live session in the coming days to continue the fundraising efforts. If the 3,000 members of the "Abenezer ZeTewahido" community could each contribute 1,000 Birr, I plan to purchase a vehicle. This would enable me to work and, in turn, support both myself and my family. For those who would like to stand by me by providing support according to your means: * Commercial Bank of Ethiopia (CBE): 1000 510 909 635 * Telebirr: 093 314 3133 Account Name: Abenezer Gezahegn Sime አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ @topfans

    Фото
    Просмотры2,01 тыс.
    Пересылки—
    Реакции16
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры1,64 тыс.
    Пересылки—
    Реакции5
    Комментарии—

Новые посты

#5963Текст

የእግዚአብሔርን መልስ ለማግኘት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል ማለት ነው፡፡ ከዛ በኋላ ችግራችንን ያስወግዳል የሰማይ አባታችን፡፡ 7• ሰባተኛ ስለዘለዓለም ሕይወት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል፡– ስለምን ይወሰዳል? ስለዘለዓለም ሕይወት፡፡ የዘለዓለም ሕይወት አለህ ማለት ደግሞ ይሄ አጥፊው መንፈስ በሕይወትህ ውስጥ ስፍራ የለውም፡፡ አንተ የዘለዓለም እንጂ የግዜዎች አይደለህም፡፡ ዛሬ በየግዜውራሳችንን እያገለባበጥን፤ ኑሯችንን ሲገለባበጥ፣ ጠባያችንን ሲገለባበጥ፣ ህሊናችንን ሲገለባበጥ፣ አመላችን ሲገለባበጥ፡፡ እንዴት ነው? እየተገለባበጥን እስከ መቸ ነው? ራሳችንን ለማግኘት ለምን አልቻልንም? ሊቆይ የሚችለው ለምን ማግኘት አልቻልንም? የዘለዓለም ሕይወት ከውስጥህ ሲወጣ፤ የሚጠብቅህ ነገር ቢኖር እንዲሁ ትርኪ ሚርኪ የሆነ የመንደር ኑሮ ነው፡፡ የመንደር ኑሮ፤ የግዜ ኑሮ፤ የሰዓት ኑሮ፡፡ ግዜዎች ሲወድቁ አብረህ ትወድቃለህ፤ ግዜዎች ሲጠፉ አብረህ ትጠፋለህ፤ ግዜዎች ሲያርፉ አብረህ ታርፋለህ፤ ግዜዎች ሲሰደዱ አብረህ ትሰደዳለህ፡፡ እንዴት ይሆናል ይሄ? ክርስትያኖች በሰማይ አምላክ ዘንድ ባለ በዘለዓለማዊ ሕይወት መያዝ አለባቸው፡፡ እና ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት ቅዱስ ቁርባን ይወሰዳል ማለት ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አስጀምሮ ላስፈጸመን የሰማዩ አባት ልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው አሜን። የእግዚአብሔር ምኅረት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ "የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 16: ፥20)። መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን። አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

Открыть в Telegram
Просмотры451−66%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#5962Текст

የቅዱስ ቁርባን 7 ጥቅሞች 1. አንደኛ ኃጢያትን ለማስተሰረይ፡– ኃጢያት ተሰረየ ማለት ካንተና ከልጆችህ፤ ከቤትና ከኑሮህ፤ ከታሪክህና ከዘመንህ ሁሉ ተወገደ ማለት ነው፡፡ ኃጢያት ተሰረየ ማለት በሚቀጥለው ዘመን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳትና እንቅፋት ቆመ ማለት ነው፡፡ የዲያብሎስ ሽምቅ ውግያና ስልቱ ሁሉ በሕይወትህ ያዘጋጀው መዝገብ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ 2. ሁለተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ለሕይወታችን አስፈላጊነት፡– ሁለተኛ እና በጣም ትልቁ በሕይወታችን ውስጥ ፍቅር እንዲኖር የክርስቶስ ሥጋና ደም ያስፈልገናል፡፡ ፍቅር እንዲኖር፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚል ቃል በዮሐንስ መልዕክት ላይ ታገኛለችሁ፡፡ እግዚአብሔር ምንድ ነው? ፍቅር ነው፡፡ ታድያ ከእርሱ ጋር እርቅ ሳናደርግ፤ በሰውነታችን ውስጥ ስፍራ ሳይይዝ፤ በባህሪያችን ውስጥ ሳይገባ፤ በሚስጥረ መለኮት የሰጠው ሥጋና ደሙን ሳንቀበል አሁን ከዚህ ትውልድ ፍቅር ይጠበቃል ወይ? እንዴት ይሆናል? እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ሲጠፋ የክርስቶስ ሥጋና ደም ያስፈልገናል፡፡ እንዲህ ብለን ወደሱ እንጠጋለን "አቤቱ ጌታ ሆይ ፍቅር ከህይወቴ ጠፍቷል፡፡" እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ንቁ የሚለው በዚህም ጭምር ላይ ነው፡፡ ከቤተሰብህ ፍቅር ሲጠፋ <ጌታ ሆይ ፍቅር ሁነኝ> ማለት አለብህ፡፡ "በውስጤ ውስጥ እደር ባህርያቴን ለውጠው፤ ሰማያዊ የሆነ ስጦታህን አካፍለኝ፤ የቸርነትህ ጸጋ ከኔ ጋር ይሁን፤ ሁሉ ግዜ በሃሳብህ ባርከኝ፤ ፍቅርህ ከሁሉ በላይ የሕይወቴ ፈር ይሁን" ብለህ ቅዱስ ቁርባን ስትወስድ ፍቅሩን ይመልስልሃል፡፡ በፍቅርህ ውስጥ ጠላት የሆነውን ኃይል ከሕይወትህ ያስወግደዋል፡፡ በዚህ ግዜ እንግዲህ ለአገርህም፣፡ለወገንህም፣ ለህዝብህም፣ ለጎረቤትህም፣ ለጠባይህም፣ ለቤትህም፣ ለገንዘብህም ፍቅር ትሆናለህ ማለት ነው፡፡ ገንዘብ አንተ አፍቅረኸው ሳይሆን ገንዘብ አንተን አፍቅሮ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ ኑሮ አንተ አፍቅረኸው ሳይሆን ኑሮ አንተን አፍቅሮ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ እንጀራ አንተ ወደኸው ሳይሆን እንጀራው አንተን ወዶ ወደ አንተ ይመጣል፡፡ ግዜ አንተ ወደኸው፤ አንተ አቅደኸው ሳይሆን ግዜው አንተን ለመርዳት ወደ አንተ ይመጣል፡፡ በእያንዳንዱ ግንኝነቶችም ውስጥ ሰማያዊ ፍቅር እስካለህ ድረስ ተፈጥሮዎች ያገለግሉሃል፡፡ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ 3. ሦስተኛ ቅዱስ ቁርባን የሚያስፈልገን ሰውነታችን ሲከብደን ነው፡– ሰውነት ሲከብድ፤ መጫን ሲጀምር፤ ውስጣዊ ህይወትህ መረጋጋት ሲያቅተው በዚህ ጊዜ ማቴዎስ ወንጌል ላይ የተናገረው ቃል ትዝ ሊለን ይገባል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 11 መጨረሻው ላይ እንዲህ ይላል ‹‹እናንተ ሸክም የከበዳችሁ ወደኔ ኑ››፡፡ ምን የከበዳችሁ? ሸክም፡፡ የግዜ ሸክም፣ የኑሮ ሸክም፣ የትውልድ ሸክም፣ የዓመታትን ሸክም፡፡ ስንት ዓመታቶች አልፈው፤ ዛሬ እየከበደን እየከበደን የመጣውን ሸክማችንን ማን ይቻለው? እኛ ነን የምችለው? ምድሪቱ ነች የምትችለው? ኑሯችን ነው የሚችለው? ገንዘባችን ነው የሚችለው? ማን ነው የሚችለው?በእርግጥ ተናገሩ ብንባል የፈጠረን አምላክ ይችልልናል ነው የምንለው፡፡ በእውነታና በሕይወት ውስጥ ባለው ትርጉም ውስጥ ግን የሚታይ ምላሽ የለንም፡፡ ስለዚህ በሸለቆ ውስጥ ሆነን ሰማያዊ ነገር አልታይ አለን፡፡ ሲከብደን ቅዱስ ቁርባን ያስፈልገናል፡፡ ምን ማለት ነው እንግዲህ? ሸክም ማራቅያ ነው ማለት ነው፡፡ 4. አራተኛ በረከት ከሕይወታችን ሲጠፋ፡– በረከት ከሕይወታችን ሲጠፋ የበረከት አምላክ ሕይወታችንና ኑሯችን ውስጥ እንዲኖር ቅዱስ ቁርባን ያስፈልገናል፡፡ በረከት ከምናችን ሲጠፋ? ከህይወታችን፣ ከኑሯችንና ከቤተሰባችን ሲጠፋ፡፡ ያኔ አንድ ነገር ገብተዋል ማለት ነው፡፡ የበረከት ጠላት በዙሪያችን አለ ማለት ነው፡፡ እንኪያሳ በበረከት ጎዳና ውስጥ እንጀራን ለብዙ ሺ ህዝብ የመገበ አምላክ ለኛም ሊሰጠን እንደሚችል ልቦናችን ማሳመን መቻል አለብን፡፡ ስለዚህ "ጌታ ሆይ አንተ የበረከት ንጉሥ ነህ የጎደለውን በረከቴ አንተ ሙላልኝ፤ የበረከት ጠላትን ኃይል አርቅልኝ" ብለን እሱ ተማፅነን ቅዱስ ቁርባን ስንወስድ በረከታችን ይመለሳል፡፡ 5• አምስተኛ መልካምና ጥሩ ዘር ለማግኘት፡– መልካም ትውልድ ለማፍራት ቅዱስ ቁርባን ያስፈልጋል፡፡ መልካም ትውልድ፤ የእግዚአብሔር የሆነ ትውልድ፤ የሰማይ አምላክ የሆነ ትውልድ፡፡ ዛሬ በአብዛኛው ከዚህ መንፈሳዊ በረከት ርቆ የተወለደው ቃልቻ ሆነ፤ ጠንቋይ ሆነ፤ መተተኛ ሆነ፡፡ ከዛም ደግሞ አልፎ ተርፎ እንዲሁም የተወለደው የመተተኞች፣ የአስማተኞች መንፈስ መኖርያ ሆነ፤ የዛርና የውቃቤ መጫወቻ ሆነ፤ የክፉ ባህርይና የክፉ ጠባይ መጫወቻ ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ከቤተሰብ መንፈሳዊ ትከሻ አንፃር ያለው ጉዳት ነው፡፡ አብዛኛው ወላጅ እያወረስን ያለው ሰማያዊ ነገርን ሳይሆን፤ ሰማያዊ ስጦታ ሳይሆን፤ ክፉውን ነው የምናወርሰው፡፡ ይህንን ውርስ ለመከላከል ለልጆች ቅዱስ ቁርባን ሊወሰድላቸው ይገባል፡፡ በሁለት አይነት መንገድ፦ ♦ አንደኛ ከመወለዳቸው በፊት ቤተሰቦች ቅዱስ ቁርባን ለሚወለዱት ገና ለሚፀነሱት አስበው ቅዱስ ቁርባን መውሰድ አለባቸው፡፡ ☞ ክፉ መንፈስ አብሯቸው ከማኅጸን ጀምሮ እንዳይወለድ ♦ሁለተኛ ከተወለዱ በኋላ ለልጆቻቸው ቅዱስ ቁርባን መውሰድ የሕይወት መርሃቸው ማድረግ አለባቸው፡፡ ☞ ሕይወታቸውን ከማለዳው ክርስቶስ እንዲመራው። 6• ስድስተኛ ቅዱስ ቁርባን የሚወሰደው የእግዚአብሔርን መልስ ስንፈልግ ፡- ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ስትጀምሩ በፍጹም ከሰው ልጅ ጠባይና ባህሪይ ጋር አትስማሙም፡፡ ስለዚህ ብቸኝነት ይሰማቹሃል፡፡ በዚህ ግዜ "ጌታ ሆይ ዓለሙ ከኔ ሸሽተዋል አንተ ከእኔ ጋር ሁን" ማለት እንጀምራለን፡፡ ልክ በዚህ ወቅት የሕይወት ደስታ እና እርካታ አንድ ሺህ ሰው ከከበበን ይልቅ ለብቻችን ከክርስቶስ ጋር የምንኖረው ኑሮ ያረካል፡፡ ያ አንድ ሺህ ሰው ቢከብህ እየተቸ፤ በጎሪጥ አፉን እያጣመመ፤ ዓይኑን እያጨነቆረ ነው የሚያይህ፡፡ እግዚአብሔር ግን በብቸኝነት ውስጥ ብርሃን ይሰጥሃል፡፡ ይሄ ነው የሱ ልዩ ሞገስ፡፡ መልሱንም በራእይ ወይም በህልም ስንጠብቅ ተገቢ በሆነ ጊዜና ሰዓት እግዚአብሔር ይሰጠናል፡፡ ውስጣችን መቀደስ ሲጀምር ከውጪ ያለውን እግዚአብሔር መሪ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እያሱ ህዝቡን ሲመራ፤ በመጽሐፈ እያሱ ምዕራፍ አንድ ላይ አንድ ታላቅ ድምፅ እንሰማለን እንዲህ ሲል ‹‹በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፡፡›› በቃ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ የሚለውን ድምፅ የሰማው ማን ነው? እያሱ ነው፡፡ የእስራኤልን ህዝብ ወደ ምድረ ርስት ለመውሰድ በሚያደርገው ጉዞ ውስ፤ የርስት ባለቤቶች እንዲሆኑ ለማድረግ ባደረገው ጉዞ ውስጥ፤ ማንም አይቋቋምህም የሚለውን ድምፅ በሕይወቱ ውስጥ እግዚአብሔር ሰጠው፡፡ እኛ የምንወርሰው ነገር አሁን ምን አለ?፡፡ በመሠረቱ እኮ የእግዚአብሔር ህዝብ መስጠት እንጂ፤ እየሰጠ የሚሄድ እንጂ እያጣ፤ እየደኸየ የሚሄድ አይደለም፡፡ እኛ ግን እያጣን፤ እየደኸየን መጣን፡፡ ውስጣችን መጀመርያ እግዚአብሔርን አጣ፡፡ ከዛ በኋላ በዓለም ላይ ባለው ነገር ላይ ምንም ባለቤትነትን አጣን፡፡ ለማንኛውም ነገር ቅጥረኞች ሆንን፡፡ ከሁሉም ደግሞ የሚገርመው እንጀራ በባህሪው ከነክፋቱ፤ ከነተንኮሉ፤ ከነምቀኝነቱ ገዛን፡፡ እግዚአብሔር የሌለበት ስፍራ እንዲህ ይሆናል፡፡ እና ሲከብደን፣ ሲጫነን፤ በአከባቢ፣ በጎረቤት፣ በሀገር ሁሉ ላይ ችግሮች ሲመጡ፤

Открыть в Telegram
Просмотры382−71%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#5961Фото
Просмотры610−54%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#5960Текст

ማታ ፆም ስንይዝ በልተን ያስተረፍነውን ስጋ ወጥ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እህቴ አሙቃ ልተበላው ስትል ተገጣጠምን ምን እየሆንሽ ነው ልበላው ነዋ ፆም ገብቷልኮ ያምሻል??ስላት እህቴ መልሳ ሳቅ ብላ ይህ ምግብ ማታ በክብር ተበልቷል ዛሬ አንድ ለሊት በማደሩ ግን ማንም ሰው ቢቀርብለት አይበላውም ምክንያቱ ደሞ ፆም ነው!!ፆም አንድም የትላንት ምግባችንን ብቻ ሳይሆን የትላንት የማይመጥኑንን የተሳሳቱ የጎደፉ ማንነታችንን ጭምር መተው ማለት ነው!!ቀድሞውንም የምትለኝን ለማየት እንጂ ልበላው አልነበረም አስተውል ፆም ሲገባ የፆም ምግብ እንዳለ ከቤት ይወጣል የምግብ እቃ የሆነ ሁሉ ይታጠባል ይህንን ወደ እራሳችን ስንቀይረው በሀጥያት የደከመች ስጋችን ሀጥያቶቿን ልክ እንደ ፆም ምግብ አውጥታ ታስወግዳለች ያልታጠበ ሰሀን እንደማይበላበት ሁሉ እኛም ቀድመን በንሰሐ ታጥበን እንቀርባለን በል እኔ እቃውን እስካጣጥብ ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ ቤተክርስትያን እንሄዳለን አለቺኝ ልወቅሳት የተነሳሁትን በሚስጥር ቋጥራ አስተምራ መለሰቺኝ ፆም ገብቷል እኛ ከህጉ እንዳንወጣ እግዚአብሔር ይርዳን

Открыть в Telegram
Просмотры859−35%к среднему
Пересылки—
Реакции28
Комментарии—
#5959Текст
Просмотры1 280−3%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5955Фото

አቤኔዘር እባላለሁ ያው አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ 🤗 ይህ ፎቶዬ 4ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ የተነሳሁት ነው። ከጀርባ ያለው ቆርቆሮ "እድገት ወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር የተጋለጡ ሕጻናት መርጃ ማኅበር" ጊቢ ነው። በዚህ ድርጅት ከ4ኛ ክፍል ጀምሮ ዩኒቨርስቲ ተምሬ እስካጠናቅቅ ድረስ ቆይታ አድርጌያለሁ። በቆይታዬም ከድርጅቱ የትምህርት ቁሳቁስ ያሟላልኝ እና የትምህርት ክፍያዎችን ይከፍልልኝ ነበር፥ እንዲሁም በበዓላት ወቅት አዳዲስ ልብሰና ጫማም ይሰጠናል፥ ከሰኞ እስከ አርብ ምሳ የተለያየ አይነት ምግብም ይመግበን ነበር፥ የመዝናኛ ቦታዎች ይወስደን ነበር፥ የሕክምና ወጪ ይሸፍናል በተለይ ለእኔ ጽድት ያሉ ክራንቾችን ከእንግሊዝ ሀገር ያስመጣልኝ ነበር። ያው በወቅቱ በዚያ ድርጅት ክራንች የሚያስፈልገኝ እኔ ብቻ ስለነበርኩ፤ የድርጅቱ ስፖንሰር አብዛኞቹ በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው። ድርጅቱ ከ300 በላይ ሕጻናትን አሁንም ድረስ ይዞ እየረዳ ይገኛል። የድርጅቱ አድራሻ አ/አ/ክ/ከ/ል/ወ/3 አብነት አካባቢ ይገኛል። ለአቤኔዘር ዘተዋሕዶ የመኪና ግዢ ቻሌንጅ እንደቀጠለ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ በቀጣይ ቀናት live በመግባት የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐግብር አከናውናለሁ። 3ሺ የአቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ ቤተሰብ 1ሺ ብር ቢያግዘኝ መኪና እገዛና ራሴንም ቤተሰቤንም ስራ እየሰራሁ ለማገዝ አስቤያለሁ። በአቅማችሁ ድጋፍ በማድረግ ከጎኔ መቆም ለምትፈልጉ፦ * የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000 510 909 635 * (Telebirr): [+251933143133] የባንክ አካውንት ስም: አቤኔዘር ገዛኸኝ ስሜ Abenezer Gezahegn Sime My name is Abenezer—yes, the one from the "Abenezer Ze-Tewahido" page! 🤗 This photo was taken when I was a 4th-grade student. The corrugated iron structure in the background belongs to the compound of "Idget" (Progress)—an association that supports children who have lost their parents or are facing hardship. I remained with this organization from the 4th grade all the way through to the completion of my university studies. During my time there, they provided all my educational materials and covered my tuition fees. They also gave us new clothes and shoes for holidays, provided various types of lunch from Monday to Friday, took us to recreational spots, and covered our medical expenses. In my case, they even imported high-quality crutches for me all the way from England—at the time, I was the only child in the organization who needed them. Most of the organization’s sponsors are foreign nationals living in England. To this day, the organization continues to support over 300 children. It is located in Addis Ababa, Sub-city 3 (Lideta), in the Abinet area. The fundraising challenge to purchase a vehicle for "Abenezer Ze-Tewahido" is still ongoing. God willing, I will host a live session in the coming days to continue the fundraising efforts. If the 3,000 members of the "Abenezer ZeTewahido" community could each contribute 1,000 Birr, I plan to purchase a vehicle. This would enable me to work and, in turn, support both myself and my family. For those who would like to stand by me by providing support according to your means: * Commercial Bank of Ethiopia (CBE): 1000 510 909 635 * Telebirr: 093 314 3133 Account Name: Abenezer Gezahegn Sime አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ @topfans

Открыть в Telegram
Просмотры2 010+52%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—

Все посты

Связи