Account

THIQAH

ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia (ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው። ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።

Username
@thiqaheth
Subscribers9,120
Avg views per post, 7d2,038last 7 days
ERR22.34%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 24, 20262,697
Nov 27, 20262,120
Nov 28, 20261,653

Most viewed this month

  1. 01

    የሶማሊያ አየርመንገድ ከ35 አመት በኋላ በረራ ሊጀምር ነው። አየርመንገዱ በመጪው ወር ታህሳስ 10/2026 በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል። የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር ሞሐመድ ፋራህ ኑህ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በረራው እንደሚጀምር አረጋግጠዋል። ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ አየርመንገዱ እንደ አዲስ በረራ መጀመሩን በማስመልከት ሰፊ መርሃግብር መዘጋጀቱን አብራርተዋል። የሶማሊያ አየር መንገድ በረራ ያቆመው በ1991 ማዕከላዊ መንግስት መፍረሱን ተከትሎ ነበር። ሶማሊያ ይህን የአቪየሺን አገልግሎት ለማስጀመር በ2025 ሁለት የኤርባስ ኤ-320 አዛ ነበር። የሶማሊያ ሲቪል አቪየሺን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄነራል አህመድ ሞአሊን ሀሰን ቀደም ሲል በሰጡት አስተያየት በረራው ይጀምራል ተብሎ የታሰበው በባለፈው መስከረም ወር ነበር። አየር መንገዱ አገልግሎት በድጋሚ ይጀምራል ቢባልም የመጀመሪያው በረራ ወዴት እንደሚደረግ እና የትኬት ዋጋን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ የለም። በ1964 ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተው የሶማሊያ አየር መንገድ (Somali Air) በ1991 በይፋ ስራ እስካቆመቀት ጊዜ ድረስ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ በረራዎችን ሲያከናውን ነበር። #hiiraanonline @EyobTikuye @ThiqahEth

    Photo
    Views2.83K
    Forwards—
    Reactions17
    Comments—
  2. 02
    Views2.68K
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—
  3. 03
    Views2.58K
    Forwards—
    Reactions2
    Comments—
  4. 04
    Views2.2K
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—

Latest posts

#7616Photo

#ኮሬ "ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም ብቻ 11 ንጹሐን ሲገደሉ፣ 23 ተጎድተዋል፤ ከ200 በላይ እንስሳት ተዘርፈዋል" - ወረዳው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሶሮ ባርጉዳና ገላና ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የ "ሸኔ" ታጣቂዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ፣ ጎርካ ወረዳ በመግባት ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም ብቻ 11 ንጹሐን ሲገደሉ፣ 23 ተጎድተዋል ሲል ጎርካ ወረዳ ነግሮናል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አቶ መልካሙ አስፋው እንዳሉን፤ 12 ሺሕ 182 ሰዎች ከወረዳው ጀሎና ዶርባዴ ቀበሌዎች ተፈናቅለዋል፤ 215 እንስሳት ተዘርፈዋል፤ ለምርት የደረሰ በቆሎ፣ አደንጓሬ፣ የሙዝ እና የቡና ተክሎች ወድመዋል። ህዝቡ ለንግድ የሚንቀሳቀስበት ከኮሬ ዞን በምዕራብ ጉጂ አድርጎ ወደ ዲላ የሚወስደው የፌዴራል መንገድ በጸጥታ ችግር ለ11 ዓመት በመዘጋቱ ነጋዴዎች ዲላ የሚጓዙት፣ ቡርጂን፣ ኮንሶን፣ ጋርዱላን፣ ጋሞን፣ ወላይታን ዞረው ስለሚዞሩ ትራንስፖርቱ በሺሕ ብር የሚቆጠር ጭማሪ እንዳለው አስረድተዋል። የምርት ዋጋ ንሯል፤ ለአብነትም ሌላ ቦታ 40 ብር የሚሸጠው ሳሙና እነርሱ ጋር በሦስት እጥፍ መጨመሩን፣ የጸጥታው ችግር ኑሮው እንዲቃወስ ማድረጉን ተናግረዋል። "ችግሩ በሰላም አማራጭ እንዲፈታ ነው የምፈልገው፤ ግን የሰላም አማራጩ በኔ ፍላጎት ብቻ አይሆንም። ለሰላም አማራጭ ምቹ ሁኔታ የለም" ብለዋል። በሁለቱ የጉጂ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች "የፈለገውን እያደረገ ያለው ሸኔ" በመሆኑ፣ ከስፍራው መንግስት ጋር ተወያይቶ ችግሩን መፍታት እንዳልተቻለ ገልጸዋል። "በኦሮሚያ ክልል በኩል በህዝቡ ውስጥ እየኖረ ያለው ታጣቂ ቀጠናውን እንዲለቅ ከማድረግ አንጻር አይቶ መተው በተጨባጭ ይተስተዋላል" ብለዋል። ዋናው መንግስት ጣልቃ ይግባ ተብሏል። @EyobTikuye  @ThiqahEth

Open in Telegram
Views1,320−35%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#7614Photo
Views1,310−36%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#7613Photo
Views1,710−16%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#7611Photo

"ፋኖ" ለቢቢሲ ምን አለ? የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) "ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እና ልምድ ባላቸው ተቋማት" የሚመራ፤ "አፈጻጸሙንም የሚከታተሉት" ድርድር ከመንግሥት ጋር እንዲደረግ ጥያቄ የሚቀርብ ከሆነ "ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ" መሆኑን ቃል አቀባይ አስረስ ማረ ነገሩኝ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። "መንግስት የድርድር ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ" ከሆነ፣ የሚያቀርቧቸውን "ስልቶች በሰነድ" ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በሰሞኑ የፓርላማ ገለጻ፣ ታጣቂ ኃይሎች "ልክ ወንድሞቻችሁ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከትግራይ ገብተው ተነጋግረው አቋማቸውን ቀይረው እየሰሩ እንዳሉት በሠላም መንገድ ብትሰሩ ይሻላል" ብለዋል። "መቼም ቢሆን አይሳካላችሁም" ሲሉ ደግሞ መንግስታቸውን መጣል እንደማይችሉ ገልጸው፣ "ይሄ መንግሥት በጣም ይቆያል። ብዙ ባትቸገሩ ጥሩ ነው" ብለዋል፣ "እናንተ አንድ እርምጃ ስታስቡ 20 እጥፍ የሚያስብ መንግሥት ነው ያለው" ሲሉም ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ አስረስ ለቢቢሲ ምን አሉ? "ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሌሎችም የሚናገሯቸው የሰላም ጥሪዎች የእጅ ስጡ ጥሪዎች እንጂ የድርድር ጥሪዎች አይደሉም። ይፋዊ በሆነ መንገድ አጠቃላይ የአገሪቱ ቀውስ የሚፈታ፤ በሦስተኛ ወገን ቁጥጥር የሚደረግበት የሰላም ንግግር ለማድረግ ከመንግሥት በኩል ፈቃደኝነት የለም። የታጣቂ አመራሮችን እና አባላትን በስልት በማባበል ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ የማድረግ ሙከራ ነው የሚካሄደው። የአማራ ሕዝብ የህልውና ጥያቄ የተሸከመው ኃይል ተጨባጭ የፖለቲካ ጥያቄ ያለው መሆኑን አምኖ፣ ጥያቄውን በድርድር ለመፍታት የተደረገ ተጨባጭ እንቅስቃሴ የለም። ያ ፍላጎት ቢኖር ኖሮ በብዙ ርቀት የኢትዮጵያን ሰላም መመለስ ይቻላል" ብለዋል። @EyobTikuye  @ThiqahEth

Open in Telegram
Views1,820−11%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—
#7610Photo
Views1,800−12%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#7608Photo
Views1,960−4%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7605Photo
Views2,200+8%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#7603Photo
Views2,090+3%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#7602Photo
Views2,0400%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#7601Photo

#Ethiopia በቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ 8 እስረኞች በተለምዶ "ታንከር" በሚባለው "የቅጣት ቦታ" እንዲገቡ መገደዳቸውን ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃ ገለጹ። እስረኞቹ፥ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ አቶ እስክንድር ሽፈራው፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ አቶ መለሰ ቸሩ እና መንበረ አለሙ ናቸው። አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የታሳሪ ቤተሰብ በሰጡን ቃል፤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የማረሚያ ቤቱ አካል አቶ ዮሐንስ ከክፍላቸው እንዲወጡ የጠየቋቸው ሲሆን፣ ለምን እንደሚወጡ ሲጠይቁ "ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው" መባላቸውን ተገልጿል። በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ መንበረ አለሙ እና እስክንድር ሽፈራው ከክፍሎቻቸው ለመውጣት ካመነቱ በኋላ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሰግተው መውጣታቸውን ተመልክቷል። እስረኞቹ የተወሰዱበት ክፍል ጠባብ እንደሆነ፣ ከስምንት በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ተጣበው እንዳሉ፣ በቂ ብርሃን እንደሌለው፣ ይህም በእስረኞቹ ጤና ላይ ስጋት እንደፈጠረ የታሳሪ ቤተሰብ ገልጸዋል። ይህ ትዕዛዝ ሰጠ የተባለው "የበላይ" የተባለው አካል ማንነው? መንግስትስ ያውቀዋል? የሚል ጥያቄ ያነሱት የታሳሪ ቤተሰብ መፍትሄ እንዲጥ ጠይቀዋል። የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ሰባቱ እስረኞች ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም፣ አቶ ዮሐንስ ደግሞ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ወደ "ታንከር" ተወስደዋል ብለዋል። አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት ዳኛ ባለመሟላቱ "ሲሟላ" ምላሽ እሰጣለሁ ማለቱን ጠበቃው ነግረውናል። አቶ ዮሐንስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከዚሁ የቅጣት ቦታ እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ በፍ/ቤት ትዕዛዝ ከወር በፊት እንዲወጡ ተደርገው ነበር። @EyobTikuye @ThiqahEth

Open in Telegram
Views2,150+6%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—

All posts