#ኮሬ "ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም ብቻ 11 ንጹሐን ሲገደሉ፣ 23 ተጎድተዋል፤ ከ200 በላይ እንስሳት ተዘርፈዋል" - ወረዳው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሶሮ ባርጉዳና ገላና ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የ "ሸኔ" ታጣቂዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ፣ ጎርካ ወረዳ በመግባት ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም ብቻ 11 ንጹሐን ሲገደሉ፣ 23 ተጎድተዋል ሲል ጎርካ ወረዳ ነግሮናል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አቶ መልካሙ አስፋው እንዳሉን፤ 12 ሺሕ 182 ሰዎች ከወረዳው ጀሎና ዶርባዴ ቀበሌዎች ተፈናቅለዋል፤ 215 እንስሳት ተዘርፈዋል፤ ለምርት የደረሰ በቆሎ፣ አደንጓሬ፣ የሙዝ እና የቡና ተክሎች ወድመዋል። ህዝቡ ለንግድ የሚንቀሳቀስበት ከኮሬ ዞን በምዕራብ ጉጂ አድርጎ ወደ ዲላ የሚወስደው የፌዴራል መንገድ በጸጥታ ችግር ለ11 ዓመት በመዘጋቱ ነጋዴዎች ዲላ የሚጓዙት፣ ቡርጂን፣ ኮንሶን፣ ጋርዱላን፣ ጋሞን፣ ወላይታን ዞረው ስለሚዞሩ ትራንስፖርቱ በሺሕ ብር የሚቆጠር ጭማሪ እንዳለው አስረድተዋል። የምርት ዋጋ ንሯል፤ ለአብነትም ሌላ ቦታ 40 ብር የሚሸጠው ሳሙና እነርሱ ጋር በሦስት እጥፍ መጨመሩን፣ የጸጥታው ችግር ኑሮው እንዲቃወስ ማድረጉን ተናግረዋል። "ችግሩ በሰላም አማራጭ እንዲፈታ ነው የምፈልገው፤ ግን የሰላም አማራጩ በኔ ፍላጎት ብቻ አይሆንም። ለሰላም አማራጭ ምቹ ሁኔታ የለም" ብለዋል። በሁለቱ የጉጂ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች "የፈለገውን እያደረገ ያለው ሸኔ" በመሆኑ፣ ከስፍራው መንግስት ጋር ተወያይቶ ችግሩን መፍታት እንዳልተቻለ ገልጸዋል። "በኦሮሚያ ክልል በኩል በህዝቡ ውስጥ እየኖረ ያለው ታጣቂ ቀጠናውን እንዲለቅ ከማድረግ አንጻር አይቶ መተው በተጨባጭ ይተስተዋላል" ብለዋል። ዋናው መንግስት ጣልቃ ይግባ ተብሏል። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in TelegramPosts of THIQAH
የአውሮፓ መሪዎች በዩክሬን ጉዳ በብራሰልስ በነበራቸው ስብሰባ ለዩክሬን በቀረበው የረጅም ጊዜ ብድር ላይ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት በ2027 45 ቢሊየን ዩሮ ለማበደር የያዘውን እቅድ የደገፉት ሶስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ፤ ህብረቱ ከ2025 ጀምሮ 1.58 ትሪሊየን ዩሮ በብድር እና ድጋፍ መልክ ስጠቱ ተገልጿል። #polskieradio @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramበአፍጋኒስታኗ ኩናር ግዛት ዋና ከተማ አሳዳባድ ዳርቻ በ"ሻጋይ" ትምህርት ቤት አቅራቢያ በሚገኝ የማዕድን ቁፋሮ ኩባንያዎች ፈንጂ ማከማቻ መጋዘን ዛሬ በተከሰተ ፍንዳታ 10 ተማሪዎች ሲሞቱ፣ ከ90 እስከ 110 የሚደርሱ መቁሰላቸውን ባለልጣናት ተናግረዋል። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegram"ፋኖ" ለቢቢሲ ምን አለ? የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) "ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እና ልምድ ባላቸው ተቋማት" የሚመራ፤ "አፈጻጸሙንም የሚከታተሉት" ድርድር ከመንግሥት ጋር እንዲደረግ ጥያቄ የሚቀርብ ከሆነ "ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ" መሆኑን ቃል አቀባይ አስረስ ማረ ነገሩኝ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። "መንግስት የድርድር ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ" ከሆነ፣ የሚያቀርቧቸውን "ስልቶች በሰነድ" ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በሰሞኑ የፓርላማ ገለጻ፣ ታጣቂ ኃይሎች "ልክ ወንድሞቻችሁ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከትግራይ ገብተው ተነጋግረው አቋማቸውን ቀይረው እየሰሩ እንዳሉት በሠላም መንገድ ብትሰሩ ይሻላል" ብለዋል። "መቼም ቢሆን አይሳካላችሁም" ሲሉ ደግሞ መንግስታቸውን መጣል እንደማይችሉ ገልጸው፣ "ይሄ መንግሥት በጣም ይቆያል። ብዙ ባትቸገሩ ጥሩ ነው" ብለዋል፣ "እናንተ አንድ እርምጃ ስታስቡ 20 እጥፍ የሚያስብ መንግሥት ነው ያለው" ሲሉም ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ አስረስ ለቢቢሲ ምን አሉ? "ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሌሎችም የሚናገሯቸው የሰላም ጥሪዎች የእጅ ስጡ ጥሪዎች እንጂ የድርድር ጥሪዎች አይደሉም። ይፋዊ በሆነ መንገድ አጠቃላይ የአገሪቱ ቀውስ የሚፈታ፤ በሦስተኛ ወገን ቁጥጥር የሚደረግበት የሰላም ንግግር ለማድረግ ከመንግሥት በኩል ፈቃደኝነት የለም። የታጣቂ አመራሮችን እና አባላትን በስልት በማባበል ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ የማድረግ ሙከራ ነው የሚካሄደው። የአማራ ሕዝብ የህልውና ጥያቄ የተሸከመው ኃይል ተጨባጭ የፖለቲካ ጥያቄ ያለው መሆኑን አምኖ፣ ጥያቄውን በድርድር ለመፍታት የተደረገ ተጨባጭ እንቅስቃሴ የለም። ያ ፍላጎት ቢኖር ኖሮ በብዙ ርቀት የኢትዮጵያን ሰላም መመለስ ይቻላል" ብለዋል። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegram"ኢራን ከእኛ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ሁሉም እድል አላት" - ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተከበረ በሚገኘው "የምስጋና ቀን (Thanks giving day)" የሀገሪቱን ጦር አባላት አድንቀዋል። አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት የምታቆመው ኢራን ቅድመ ሁኔታዎችን ስታሟላ ብቻ መሆኑን ገልጸው፣ "ኢራን ከእኛ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ሁሉም እድል አላት" ብለዋል። "ድሉ በእጃችን ነው" በማለት ሀገራቸው በጦርነቱ የበላይነት መውሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል። በተያያዘ፥ የአሜሪካ ጦር ሁለት የኢራን መርከቦችን አውድሚያለሁ ብሏል። መርከቦቹ የአሜሪካን የወደብ እገዳ ህግ ተላልፈው ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸው ነው ጥቃት ያደረስኩት ብሏል። አሜሪካ በኢራን ላይ የወደብ እገዳ ከጣለች በኋላ ስድስት መርከቦች መምታቷ እና 158 አቅጣጫ ቀይረው እንዲጓዙ ማድረጉን ፔንታጐን አስታውቋል። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከትግራይ "ባለአደራ አስተዳደር" ጋር የክትትል ግምገማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፤ በውይይቱ የታዩ "እርምጃዎችን"፣ ተግዳሮቶችን እና "የጋራ የቅድሚያ" ጉዳዮችን መገምገማቸውን አስታውቀዋል። ስለተወያዩባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ያሉት ነገር የለም። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramየሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ባለፉት አራት ወራት በትንሹ 90 ጊዜ ድንበር መጣሳቸው ተገለጸ፡፡ በደቡብ ኮሪያ የሕግ አውጪ ቢሮ በወጣው መረጃ መሰረት በመስከረም እና ጥቅምት በእያንዳንዱ ወር 30 ወረራዎች ተፈጽመውብኛል ብሏል፡፡ ተደጋጋሚ የድንበር ጥሰቶቹ የተከሰቱት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በግንባሩ አካባቢ ፈንጂዎችን በመቅበርና የእሾህ ሽቦ አጥሮችን በመዘርጋት ድንበሩን የማጠናከር ሥራ በሚያከናውኑበት ወቅት ነው፡፡ ከጦር መሣሪያ ነፃ በሆኑ ቀጠናዎች በደረሰ የፈንጂ ፍንዳታ የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ ሴዑል ፈንጂዎቹን የቀበረችው ፒዮንግያንግ ናት ስትል የከሰሰች ቢሆንም ሰሜን ኮሪያ ግን እስካሁን ኃላፊነቱን አልወሰደችም ነው የተባለው፡፡ #anadoluagency @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramየተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም እ.ኤ.አ ከታኅሣሥ 2026 እስከ ግንቦት 2027 ባለው ጊዜ በ16 ሀገሮች ከባድ የምግብ እጥረት እንደሚባባስ አስጠነቀቀ። ለክስተቱ በአየር ንብረት ለውጥና ግጭቶች በምክንያት ተጠቅሷል። ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ በናይጄሪያ የሚገኙ አከባቢዎች እና የመን ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው ሀገራት መካከል ተቀምጠዋል፡፡ በኤል ኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት እና ግጭቶች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የረሃብ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል ብሏል፡፡ አደጋው በ2026 ከነበሩት 13 ቀጠናዎች ወደ 16 ከፍ ማለቱም ተገልጿል፡ በሚቀጥሉት ወራት በዚምባብዌ እስከ 3 ሚሊዮን፣ በማላዊ 2.6 ሚሊየን እና በሞዛምቢክ 1.8 ሚሊየን ሰዎች ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramእንግሊዝ 100,000 ተጠባባቂ ጦር ዝግጁ እንዲሆን ጥሪ አቀረበች። ተጠባባቂ ኃይሉ በሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (NATO) የ2027 የጦር ልምምድም እንዲሳተፍ ይደረጋል ተብሏል። የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር ብዛት ላለው ሀይል የወታደራዊ ዝግጅት ጥሪ ሲያቀርብ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ጦርነት አድማሱ ከሰፋ የአውሮፓ ሀገራትን ኢላማ ልታደርግ እንደምትችል በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል። የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስትር ወስ ስትሪቲንግ ወታደራዊ ጥሪው የቀረበው ለወሳኝ ቅድመ ጥንቃቄ መሆኑን ገልፀዋል። #kyivpost @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegram#Ethiopia በቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ 8 እስረኞች በተለምዶ "ታንከር" በሚባለው "የቅጣት ቦታ" እንዲገቡ መገደዳቸውን ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃ ገለጹ። እስረኞቹ፥ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ አቶ እስክንድር ሽፈራው፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ አቶ መለሰ ቸሩ እና መንበረ አለሙ ናቸው። አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የታሳሪ ቤተሰብ በሰጡን ቃል፤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የማረሚያ ቤቱ አካል አቶ ዮሐንስ ከክፍላቸው እንዲወጡ የጠየቋቸው ሲሆን፣ ለምን እንደሚወጡ ሲጠይቁ "ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው" መባላቸውን ተገልጿል። በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ መንበረ አለሙ እና እስክንድር ሽፈራው ከክፍሎቻቸው ለመውጣት ካመነቱ በኋላ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሰግተው መውጣታቸውን ተመልክቷል። እስረኞቹ የተወሰዱበት ክፍል ጠባብ እንደሆነ፣ ከስምንት በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ተጣበው እንዳሉ፣ በቂ ብርሃን እንደሌለው፣ ይህም በእስረኞቹ ጤና ላይ ስጋት እንደፈጠረ የታሳሪ ቤተሰብ ገልጸዋል። ይህ ትዕዛዝ ሰጠ የተባለው "የበላይ" የተባለው አካል ማንነው? መንግስትስ ያውቀዋል? የሚል ጥያቄ ያነሱት የታሳሪ ቤተሰብ መፍትሄ እንዲጥ ጠይቀዋል። የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ሰባቱ እስረኞች ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም፣ አቶ ዮሐንስ ደግሞ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ወደ "ታንከር" ተወስደዋል ብለዋል። አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት ዳኛ ባለመሟላቱ "ሲሟላ" ምላሽ እሰጣለሁ ማለቱን ጠበቃው ነግረውናል። አቶ ዮሐንስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከዚሁ የቅጣት ቦታ እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ በፍ/ቤት ትዕዛዝ ከወር በፊት እንዲወጡ ተደርገው ነበር። @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramየሶማሊያ አየርመንገድ ከ35 አመት በኋላ በረራ ሊጀምር ነው። አየርመንገዱ በመጪው ወር ታህሳስ 10/2026 በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል። የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር ሞሐመድ ፋራህ ኑህ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በረራው እንደሚጀምር አረጋግጠዋል። ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ አየርመንገዱ እንደ አዲስ በረራ መጀመሩን በማስመልከት ሰፊ መርሃግብር መዘጋጀቱን አብራርተዋል። የሶማሊያ አየር መንገድ በረራ ያቆመው በ1991 ማዕከላዊ መንግስት መፍረሱን ተከትሎ ነበር። ሶማሊያ ይህን የአቪየሺን አገልግሎት ለማስጀመር በ2025 ሁለት የኤርባስ ኤ-320 አዛ ነበር። የሶማሊያ ሲቪል አቪየሺን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄነራል አህመድ ሞአሊን ሀሰን ቀደም ሲል በሰጡት አስተያየት በረራው ይጀምራል ተብሎ የታሰበው በባለፈው መስከረም ወር ነበር። አየር መንገዱ አገልግሎት በድጋሚ ይጀምራል ቢባልም የመጀመሪያው በረራ ወዴት እንደሚደረግ እና የትኬት ዋጋን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ የለም። በ1964 ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተው የሶማሊያ አየር መንገድ (Somali Air) በ1991 በይፋ ስራ እስካቆመቀት ጊዜ ድረስ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ በረራዎችን ሲያከናውን ነበር። #hiiraanonline @EyobTikuye @ThiqahEth
Open in Telegramእስራኤል ለሁለት ወር አግዳው የነበረው የዱባይ አየርመንገድ በረራ እንደሚጀምር የእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴር ፍላይዱባይ (Fly Dubai) ወደ ቴል አቪቭ በረራዎችን እንዳያደርግ የከለከለው በረራ ላይ ረዳት አብራሪው ካፕቴኑ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነበር። አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ተጓዦች እስራኤላውያን መሆናቸው አይዘነጋም። በዩኤኢ እና በእስራኤል ባለሰሰልጣናት መካከል ቀናትን ምክክሮች መደረጋቸውን ተከትሎ ነው ውሳኔው የተላለፈው። ውይይቱ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የደኅንነት ጥንቃቄዎች ትኩረት አድርጎ ነበር ተብሏል። #telegraph @EyobTikuye @ThiqahaEth
Open in Telegramበኢራን በተከታታይ ተኩሶች እና በአየር ላይ ጥቃቶች 623 ሕፃናትና ታዳጊዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 7 ሺሕ 200 ሰዎች መገደላቸውን በየኢራን የሴቶችና የቤተሰብ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ዛህራ ቤህሩዝአዛር ተናግረዋል። ከ100 በላይ የተገደሉት ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የሚሳኤል ጥቃት መሆኑ ተመልክቷል። በርካታ ህፃናትም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። በተያያዘ፥ "መርከቦቹ የተከለከለ ቦታ ተላልፈዋል" - IRGC ኢራን ሁለት የነዳጅ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ገልጻለች። መርከቦቹ በሆርሙዝ ሰርጥ የተጣለውን እገዳ ተላልፈው በመገኘታቸው ነው ጥቃት የተፈፀመባቸው ብላለች። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC)፣ መርከቦቹ "የተከለከለ ቦታ ተላልፈዋል" ብሏል። መርከቦቹ በእሳት እየጋዩ ታይተዋል። #anadoluageny #IRNA @EyobTikuye @ThiqahaEth
Open in Telegram