Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 55 |
| 6 h | 222 |
- After 1 hour55
- After 6 hours222
- Total to date222

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW
By publication day
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 22, 2026 | 804 |
| Nov 23, 2026 | 765 |
| Nov 24, 2026 | 819 |
| Nov 25, 2026 | 593 |
| Nov 26, 2026 | 528 |
| Nov 27, 2026 | 380 |
| Nov 28, 2026 | 222 |
Hours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 55 |
| 6 h | 222 |
"ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት 2 በመቶ የሚሆኑት እንኳን ሚዲያን በአግባቡ አይጠቀሙም" የሚዲያ ባለሞያ ዘሪሁን ግርማ ዛሬ ላይ ምናልባት አብዛኛው አገልጋዮች እራሳቸውን ከፕልፒት ይልቅ ሚዲያ ላይ እያስተዋወቁ እንደሆነ የሚታዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። ይህንን እኔም በግሌ አምናለሁ። ነገር ግን የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሞያዎች ማሕበር ፕሬዝደንት እና የሚዲያ ባለሞያ የሆኑት ወንድም ዘሪሁን ግርማ ግን ይህንን ሃሳብ በተቃራኒው ይሞግታል። ከሰሞኑ "ሚዲያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን" የሚል 2ኛ መጽሀፉን ለንባብ ለማቅረብ እየተዘጋጀ የሚገኘው ወንድም ዘሪሁን ግርማ ከኢቫንጀሊካል ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን (የወንጌላውያን) ሚዲያን 2 በመቶ እንኳን እየተጠቀመችበት አይደለም ይላል። መሪዎች ሊነቁ እና ሚዲያን በትክክለኛው መንገድ ሊጠቀሙ ይገባል የሚለው ወንድም ዘሪሁን አሁን ላይ ምን ያክል ቤተክርስቲያን እና አጥቢያዎች እንዳሉ በማንሳት ከእነዚህ መካከል ምን ያክሉ ውጤታማ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሚዲያን ይጠቀማሉ የሚለውን ሃሳብ አንስቶ በመሞገት ቤተክርስቲያን ሚዲያን ዋነኛው የወንጌል ማዳረሻ መንገድ አድርጋ ልትጠቀም ይገባል ይላል። እንደ ወንድም ዘሪሁን ገለጻ ይህ ዋናኛ መንገድ መሆን አለብት እንጂ ብቻኛ መንገድ እንዳልሆነም ይጠቅሳል። በዮሐንስ ግርማ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=1QXLIbaoR5c
Open in Telegram#ሰበር #ዜና መካነ ኢየሱስ አዲስ ፕሬዝደንት መረጠች። 22ኛው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዓብይ ጉባኤ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩ መሪዎችን መርጧል። «በፍቅር የጸና መሠረት» (ኤፌሶን 3፥17) በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው ዓብይ ጉባኤ፣ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን በታማኝነትና በትሕትና የሚያገለግሉ መሪዎችን በፀሎት መርጧል። በዚሁ መሠረት፦ 1. ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል — የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት፤ 2. ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ — የቤተ ክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት፤ 3. አቶ መላኩ አመኑ — የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓቃቤ ንዋይ በመሆን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን በመሪነት የሚያገለግሉ ይሆናል። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለተመረጡት አዳዲስ መሪዎች መልካም ምኞቷን እየገለጸች ለአገልግሎታቸው ስኬት ትጸልያለች! The Christian News - የክርስቲያን ዜና የክርስቲያን ዜና ለተመረጡ አዳዲስ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆን ይመኛል።
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 10 h | 319 |
| 25 h | 454 |
"ሙስናን መከላከልና መታገል የመንግሥትና የተወሰኑ ተቋማት ተግባር ብቻ አይደለም" መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በይፋ መከበር በጀመረው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከሃይማኖት አባቶች ጋር በተደረገው ምክክር መድረክ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመሆን ከሃይማኖት መሪዎች ጋር የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ምክክር አድርገዋል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ሙስናን መከላከልና መታገል የመንግሥትና የተወሰኑ ተቋማት ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጎች፣ ማለትም የሃይማኖት ተቋማት የሲቪል ማኅበራትና፣ የሙያ ተቋማት በአጠቃላይ የማህበሰረሰብ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። መጋቢ ታምራት አበጋዝ አክለው የሃይማኖት ተቋማት የሥርዓተ የአምልኮ ማካሄጃ ማዕከላት ብቻ ሳይሆኑ፣ የሥነ-ምግባርና የሞራል እሴት መገንቢያ፣ ማኅበራዊ ኃላፊነትና መልካም እሴቶች የሚጎለብቱባቸው ተቋማት መሆናቸውን ጠቅሰው ሙስናን ለመከላከል ጠንካራ መንፈሳዊና ሞራላዊ መሠረት የሆኑትን ሃይማኖቶች ሐቀኝነትን፣ ታማኝነትን፣ ፍትሕን፣ ትሕትናን፣ ለሌሎች የመጠንቀቅ ኃላፊነትን አበክረው ሊያስተምሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ሙስና የሀገርን ሀብት ከማባከኑም በላይ የሕግ የበላይነትን፣ የፍትሕ ሥርዓትንና የሕዝብን እምነት የሚሸረሽር አደገኛ ወንጀል በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች በቁርጠኝነት ሊታገሉት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 16 h | 410 |
| 26 h | 460 |
GTA 6 የዲጂታል መዝናኛ ወይስ የሥነ ምግባር ፈተና? አንድ ጨዋታ በሰዓታት ውስጥ በቢሊዮን ዶላር ገቢ ሊያስገኝ ይችላል። በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችንም ትኩረት ሊስብ ይችላል። ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ እነዚህ ጨዋታዎች በወጣቶች አስተሳሰብ፣ ባህሪና የሥነ ምግባር እሴት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ? ይህ ጥያቄ በአሁኑ ወቅት ከዓለም አቀፉ የቪዲዮ ጌም ኢንዱስትሪ ትልቁ የውይይት ርዕስ ከሆነው Grand Theft Auto 6 ጋር ተያይዞ ተነስቷል። የብሪታኒያዊው ጋዜጠኛና ተንታኝ Peter Hitchens በኖቬምበር 20 በDaily Mail ላይ ባሳተመው የአስተያየት ጽሑፍ GTA 6ን ከባድ ትችት አቅርቦበታል። Hitchens ጨዋታውን ከሥነ ምግባርና ከክርስቲያናዊ ሥልጣኔ አንጻር በመመልከት፣ በጨዋታው ውስጥ የሚታዩ የወንጀል፣ የጥቃትና የሌሎች አጥፊ ድርጊቶች ይዘቶችን ተችቷል። በዚህም ተነስቶ ጨዋታውን "Electronic Poison" ሲል ገልጾታል፤ የ2,000 ዓመታት የክርስቲያናዊ ሥልጣኔን ያዳክማል የሚል ከባድ ትችትም አቅርቧል። የአሜሪካው ESRB የጨዋታዎች የዕድሜ ምደባ ተቋም GTA 6ን ለ17 ዓመት እና ከዚያ በላይ ብሎ መድቦታል። የምደባው ምክንያቶችም ከባድ ጥቃት፣ ደምና ግፍ፣ ወሲባዊ ይዘት፣ እርቃን፣ ጸያፍ ቋንቋ፣ አደንዛዥ ዕፅና አልኮልን ያካትታሉ። ይህም ወላጆች የልጆቻቸውን የዲጂታል መዝናኛ ምርጫ በጥንቃቄ እንዲከታተሉ የሚያሳስብ ነው። ወጣቶች ሆይ፤ ዛሬ በስልካችንና በኮምፒውተራችን ላይ የምናየውና የምንጫወተው ነገር የመዝናኛ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ለማሰብ፣ ለመማርና ለመዝናናት የምናሳልፈው ጊዜ የሕይወታችን አካል ነው። ስለዚህ ራሳችሁን ጠይቁ፤ የምመለከተው ይዘት ምን እያስተማረኝ ነው?
Open in Telegramበኬንያ የቤተክርስቲያናት የአምልኮ አገልግሎትን በቀጥታ ማሰራጨት እንዲገደብ የተደረገው ጥረት በሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ። የቤተክርስቲያን መሪዎች እርምጃውን አድሎአዊና በአምልኮ ነፃነት ላይ ጫና የሚፈጥር በማለት ተቃውመዋል። በኬንያ የመረጃ ጥበቃ ኮሚሽነር የነበሩት ኢማኩሌት ካሳይት፣ ቤተክርስቲያናት የምእመናንን ምስልና ድምፅ በቀጥታ ከማሰራጨታቸው ወይም ቪዲዮና ፎቶዎችን በኢንተርኔት ከመልቀቃቸው በፊት ግልጽ ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ማሳሰባቸው ውዝግቡን አስነስቷል። የኬንያ የቤተክርስቲያንና ቀሳውስት ማኅበር ሊቀመንበር ኤጲስ ቆጶስ ሁድሰን ንዴዳ፣ ኮሚሽኑ ቤተክርስቲያናትን ብቻ ለምን እንደለየ ጠይቀዋል። ፖለቲከኞችም ሰልፎቻቸውን በቀጥታ እያሰራጩ ሳለ የሃይማኖት ተቋማት ብቻ ላይ ገደብ መጣሉ አድሎአዊ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ቤተክርስቲያናት ይህንን መመሪያ ካልተከተሉ እስከ 5 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል ተገልጿል። የሃይማኖት ባለሙያዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤዝቅኤል ሙኤንዶ በበኩላቸው፣ መመሪያው በተለይ ትናንሽ የሃይማኖት ተቋማትን ሊጎዳ እንደሚችል ገልጸዋል። ማኅበሩም በመንግሥት አካልና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ ጠይቋል። መፍትሔ ካልተገኘም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለማቅረብ እንደሚያስቡ አስታውቋል። ይህ ጉዳይ በዘመናዊው ዓለም የወንጌል ስርጭትን ማስፋፋትና የምእመናንን የግል መብት መጠበቅ እንዴት ሊጣጣሙ ይችላሉ? የሚለውን ትልቅ ጥያቄ አስነስቷል። ለማንኛውም ይህ ነገር መቼም በኢትዮጵያ እንዴት እንደተስፋፋ ግልፅ ነዉ ? ሕጉን እንዴት አያችሁት ኢትዮጵያ ቢመጣ አዋጭ ይመስላችኋል ? ሃሳባችሁን አጋሩን 🙏 በዮሐንስ ግርማ
Open in Telegramበኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል ክርስቲያን አገልጋዮች የጤና ባለሙያዎችን እየደገፉ ነው። በዲሞክራቲክ ኮንጎ እየተስፋፋ ያለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ክርስቲያን አገልጋዮችና የሃይማኖት መሪዎች በቤት ለቤት የግንዛቤ ሥራ ከጤና ባለሙያዎች ጋር እየተባበሩ እንደሚገኙ ተዘገበ። የReligion News Service እንደዘገበው፣ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በተለይም በሰሜን ኪቩ ግዛት በቤኒ ከተማ የሚገኙ ክርስቲያን አገልጋዮች ስለ በሽታው ትክክለኛ መረጃ ለማኅበረሰቡ በማድረስ ላይ ናቸው። በአካባቢው የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አገልጋይ ፓትሪክ ሎኮምቤ እንደገለጹት፣ አንዳንድ ማኅበረሰቦች በጤና ባለሙያዎች ላይ እምነት በማጣታቸው ወደ ሕክምና ተቋማት ለመሄድ ፈቃደኛ አልነበሩም። በዚህም ምክንያት የእምነት መሪዎች ወደ ማኅበረሰቡ በመግባት ስለ በሽታው ስርጭት፣ መከላከያ ዘዴዎችና የሕክምና አስፈላጊነት ማብራሪያ እየሰጡ ነው። የአንግሊካን የጎማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማርቲን ጎርደን በበኩላቸው፣ ማኅበረሰቡ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ስለሚያምን ትክክለኛ መረጃን በእነርሱ በኩል ማድረስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 20 ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ ኖቬምበር 17 ድረስ በኮንጎ 11,613 የተረጋገጡ የኢቦላ ተጠቂዎችና 5,678 ሞት ተመዝግቧል። ወረርሽኙም በስምንት ክልሎች ወደሚገኙ 68 የጤና ዞኖች መዳረሱን ድርጅቱ ገልጿል። የግጭት ሁኔታዎች፣ የሕዝብ መፈናቀልና የጤና ተቋማት እጥረት የወረርሽኙን ቁጥጥር እያወሳሰቡት መሆኑም ተጠቁሟል። ምንጭ፦ Religion News Service፣ World Health Organization በዮሐንስ ግርማ
Open in Telegram"ሚድያ እና የኢትዮጵያ ቤተክስርቲያን" የሚል ርዕስ ያለው አዲሱን መጽሐፉን አስመልክቶ ዛሬ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል። በፍሬንድሽፕ ሆቴል በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲሱን የመጽሐፉ ይዘትና ዓላማ፣ የምረቃው ቀንና ቦታ እንዲሁም አንባቢዎች መጽሐፉን የሚያገኙበት መንገድ በዝርዝር የተገለጸ ሲሆን በምርቃት መረሃ ግብሩ ቀን ሚዲያን በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ስናውል ለቤተክርስቲያንና ለማኅበረሰብ ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽኦ፣ እንዲሁም ያለ ኃላፊነት ሲጠቀሙበት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለውይይት እንደሚያቀርብ ተገልጿል። "ሚዲያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን" የተሰኘው ይህ አዲስ መጽሀፍ ታሪካዊ ሂደትን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እንዲሁም ተያያዥ የሕግ ማዕቀፎችን የያዘ እንደሆነ የመጽሀፉ አዘጋጅ ወንድም ዘሪሁን ግርማ በመግለጫው ላይ ተናግሯል። የመጽሀፉን አሁናዊ ጠቀሜታ በተመለክተ ንግግር ያደረገችው የሚዲያ ባለሞያ እና አገልጋይ እህት ትዕግስት እጅጉ በበኩሏ የመጽሀፉ ዋና ዓላማ "የዘርፉን ተሞክሮ ለትውልድ በጽሁፍ ማስተላለፍ" ነው ብላለች። እንደ እህት ትዕግስት ገለጻ ከሆነ በሚዲያ ስራ ላይ የሚገጥሙን ውሳኔዎችን በቡድን ለመመርመር መጽሀፉ ጉልህ ጠቀሜታ ያለው ነው ስትል ገልጻዋለች። የአባቶቻችሁን ታሪክ እንድታውቁ እድል የሚሰጥ መጽሐፍ ነው ያሉት ደግሞ አርቲስት እና አገልጋይ የሆኑት እንዲሁም በሚዲያ ረዥም ዓመት ልምድ ያላቸው አርቲስት ሽዋፈራው ደሳለኝ ናቸው። አንጋፋዎች የሰሩትን እና ያዩትን እንዲያካፍሉ ወጣቶችም ዛሬ ያላቸውን ቴክኖሎጂ እና እውቀት ከቀደመው ተሞክሮ ጋር እንዲያገናኙ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ያለችው ደግሞ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ነች። ተጨማሪ ዝርዝር ከፌስቡክ ገጻችን ያንብቡ ! https://web.facebook.com/share/p/1TqY
Open in Telegramተነሳና ብላ 📖📖📖 ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ላለማወቅ ቆርጫለሁ! በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት Zadok Perth የዩቱብ ቻናል subscribe ያድርጉ።
Open in Telegram
The Urban Center ( Kebet Eske Ketema)@theurbancenterNews and media5.66K
Warka Times@warkatimesofficialNews and media4.65K
Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе@rcscethiopiaNews and media4.57K
Finfinnee Post@waaqoofNews and media3.74K
C R R S A - የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ@addisvaitalpressNews and media7.33K
LinkUp Premium@linkuppremiumNews and media7.51K
Borkena@borkenaNews and media7.53K
EthioTube@ethiotubeNews and media7.87K