እናማ... አንቺም ሂጂ ቀን ይውጣልሽ የገፋሽው ገላ አደናቅፎ ይጣልሽ የደጃችን ጉበን ያድማሽ ፍቀጅለት ጠባሳ ይሻላል ከመርዛም አንደበት ዘረሠናይ @Prince_zeresenay
Open in Telegram
ጥበበ ሠናይ 🥀
ጸጥታ የሰፈነበት የትህትና እና የጸጋ ግዛት ወደ ሆነው የዘረ ሠናይ መቅደስ እንኳን በደህና መጡ። የትህትና ቃላት ውበትን እና እውነትን ወደሚያንሸኳሽኩበት፣ጸጥ ወዳለው የዘረ ሠናይ መቅደስ ይግቡ። በዘረ ሠናይ ቃላት ውስጥ፣ መፅናናትን እና ነጸብራቅን ያግኙ፣ የህይወት ትንንሽ ተአምራትን ረጋ ብለው ያስቡ። እያንዳንዱ ስንኝ ለአለም ተወዳጅ ስጦታ የሚያቀርብበትን @Prince_Zeresenay ስራ ያጣጥሙ።
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 23, 2026 | 287 |
| Nov 27, 2026 | 113 |
Latest posts
"በመንፈቀ ሌሊት ሲያላዝን ዉሻው እሞት ይሆን እኔ ማለት ያቃተው ማን ሊሞት ነው ይላል... አይ ሰው... አይ ሰው... አይ ሰው... አይ ሰው " እሱቤ
Open in Telegramቁስሌን ነካሁት. . . የነካሁበትን - እጄን ተጠየፍኩት እንዴት ህሊናዬ ገላዬን ይጠላል !? የነካሁት ቁስሌ - አንቺን አንቺን ይላል ሰይፍ
Open in Telegramሲዖል ስትገባ ከረፋት እግዜሩን ለመነች ሰማት ዘለቀች ወደ ገነቱ ግን እዚያም... ብሶ ቢቆያት ክርፋቱ አንድ ነው ብላ ሁለቱ ለአምላኳ ሰደደች ክሷን ምስኪን... ያሸተተችው ራሷን Red-8
Open in Telegramእስኪ ምን ላርግልሽ ካንቺ የተፀናወተኝ ማፍቀሬ እንዲገባሽ ከአይኖችሽ የያዘኝ መውደዴ እንዲታይሽ ንገሪኝ የኔ ዓለም እስኪ ምን ላርግልሽ ከሰማይ እስከ ምድር ወጥቼ ወርጄ ስልጣን ተበድሬ በዓለም ሚኖሩትን ሕዝቡን ሚገዙትን ነገስታትን ሽሬ ለዘውድሽ እንድትሆን ከሰማየ ሰማይ ፀሐይን አውርጄ ግርማሽ እንዲያስፈራ መጎናፀፍያሽን በእሳት ጋርጄ ከሰው ሁሉ እንድትልቂ ተከብረሽ ተነግሰሽ ዉበትሽ እንዲታይ እንዲጎላ መልክሽ ጨረቃን አውርጄ ልሰራት ካንገትሽ ? ኮከብ አዋቅሬ ልብስሽን ልስራልሽ ? ከእሳት እና ከዉሃ ዙፋን ልገንባልሽ ? ስምሽ እንዳይረሳ ዓለም እንዲያስታውስ ትውልድ ሁሉ እንዲያውቀው ቃላት እየመረጥኩ ግጥም እየፃፍኩኝ መልክሽን ልሳለው ማፍቀሬ እንዲገባሽ መውደዴ እንዲታይሽ ንገሪኝ ፍቅሬ ሆይ እስኪ ምን ላርግልሽ ? ንገሪኝ ዓለሜ የሚሆን ባይመስልም እኔ አደርገዋለው
Open in Telegram[ እንዴት አመሻችሁ ፥ ግጥም እንገርብ እስኪ] የስለት ልጅ የሆንኩ ይመስል በጠዋት ማታ ስቆስል ሥጋዬ የልመት ፥ ነፍሴ የድባቴ ከናቴ ነው ወይስ ካባቴ ከማን ቢጠጋ እጣዬ እንዲህ የበዛው ጣጣዬ? ኩሬ እንኳን ሲሆን አስጣሚ ዕድል ነው ወይ አጋጣሚ? ድር እንኳን ሲጥለኝ ጥልፎ ሁልጊዜም ባይሆን አልፎ አልፎ አልፎ አልፎ [ስስቅ] አልፎ አልፎ አልፎ አልፎ [ሳለቅስ] አልፎ አልፎ ድብታ እምባዬን ልፎ ሲሸቀሽቀኝ እንደ ጦር ባልጋ ላይ ተኝቼ ስጦር እንቁዬን ለማንም ስጥል እንደ ባላባት ቅምጥል ልክ እንደ አመለ-ቅንጡ ኧረ ምኑ ቅጡ! ኧረ ምኑ ቅጡ! ጌታዬ አንተ ጌታዬዋ አትሞላልኝም ወይ የተስፋዬን ፅዋ? ባላድርም እንኳን ለማምሻ ተስፋ ስጠኝ እንጂ ለቅምሻ ምን አልኩኝ የነፍሴ ልምሻ አብሮኝ ሲያድግ እንደ መንታዬ? ተስፋ እኮ ነው የሚርበኝ ጌታዬ! ተስፋ እኮ ነው የሚጠማኝ ጌታዬ! መቅደስ እንደገባ ውሻ እንድ ሰካራም ቅርሻ "ክፍ" አልባል "እንትፍ" አትስጠኝ የዕድሜ ትርፍ ልክ እንደ ጨርቅ ስተረተር ልታድነኝ አትውተርተር ልትጠግነኝ ተው አትልፋ ብቻ ስጠኝ ተስፋ ትንሽ ተስፋ ብቻ አትተወኝ ለብቻ! አባብለኝ ጌታዬ ፥ አባብለኝ ደልለኝ ጌታዬ ፥ ደልለኝ ባታድነኝ እንኳን ፥ "ትድናለህ" በለኝ! 🖤 🖤 🖤 ዮናታን
Open in Telegramበቀን ወይ በሌሊት በፆም በቅበላ የበላ ይኖራል ይብላኝ ለተበላ ጋጋሪው ቢራቀቅ ቢሰወር ምጣዱ የዕለት እንጀራ ነው አንደኛው ሰው ላንዱ በዕውቀቱ
Open in Telegram"ትንሽ ቅር ብሎኛል, ግን ደስም ብሎኛል:: ትዝታሽ እየደበዘዘ ናፍቆትሽ እየፈዘዘ ነው :: ከመልክሽ በላይ የተሰሙኝ ስሜቶች ብቻ ትዝ ይሉኛል:: ተረስቶ ለማስታወስ እንደምንሞክረው የሌሊት ህልም, ልትጠፋ እንደደረሰች እንደሻማ ብርሃን:: ትንሽ ጭላንጭል ብቻ. . . ትንሽ ትውስታ ብቻ . . . እየረሳሁሽ ነው"
Open in Telegramወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ቀለም ይንጠፍ ስንት ብዕር ልጨርስ ስንት ግጥም ልፃፍ ስንት መጽሃፍ ልድረስ እስክታዪ ናፍቆቴን እስክትመጪ ድረስ ልብሽ እስኪወስን ስንት ቃላት ልድማ እስክትወጂኝ ድረስ ስንት ሀረግ ላስማማ ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ግዜ ኪሪያላይሶን ስንቴ እግዚኦ ልበል ሱባኤ ገብቼ ስንት አመት ልከልከል ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት መስክረም ይጥባ ስንት አደይ ይርገፍ ስንት ክረምት መጥቶ ስንት በጋ ይለፍ ስንት ዝናብ ይምታኝ ስንቴ ልደር ዉጪ መወደዴ አሸንፎሽ ወደ እኔ እስክትመጪ @Prince_zeresenay
Open in Telegram






