✨ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ክብር ✨ ✍️በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ✦ ፩. ቅዱስ ሚካኤልና የመሐላው ስም 💥 በመጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 20 ላይ እንደምናነበው ከመላእክት በተለየ መልኩ "አካዕ" የሚለው ስመ አምላክ በእጁ ላይ ቀርጾለታል። ደራሲውም፦ ╬ “ሰላም ለእራኅከ ስመ መሐላ ዘጸበጠ” (የመሐላ ስምን ለጨበጠ መዳፍኽ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያወድሰዋል። ✦ ፪. የቅዱስ ሚካኤል ክብርና ትሕትና 💥❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡- 👉 ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡- ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ” ትርጉም፦ (የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡- ✦ ፫. ቅዱስ ሚካኤልና ሰባቱ ሊቃነ መላእክት 💥❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ፦ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየኹ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፡- ╬ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ” ትርጉም፦ (የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት ለሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘይስእል በእንተ ምሕረት መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት” ትርጉም፦ (የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡ ✦ ፬. የ«ሚካኤል» ስም ትርጓሜ 💥❖የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡ 👉 የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ፦ ╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” ትርጉም፦ (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ✦ ፭. ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ፍሥሐ 💥❖ቅዱስ ያሬድም፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ መልአኮሙ ሥዩሞሙ የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ” ትርጉም፦ (ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል። ✦ ፮. የቅዱስ ሚካኤል ብርሃናዊ ውበት 💥❖በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር፤ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ” ትርጉም፦ (መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው) 💥❖የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡- ╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ” ትርጉም፦ (የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ 💥❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡- ╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ” ትርጉም፦ (ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡ ✦ ፯. የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት 💥❖የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ "በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ በመንክር ትሕትናከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ” ትርጉም፦ (በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ) ╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ” ትርጉም፦ (ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡ ✦ ፰. በቀንና በሌሊት የሚጠብቀው ቅዱስ ሚካኤል ╬ የቅዱስ ያሬድ ውዳሴ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” ትርጉም፦ (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል። ✍️ ኹሌም በተራዳኢነቱ ያልተለየን የማይለየን የቅዱስ ሚካኤል ጠባቂነት ከኹላችን ጋር ይኹን።
Open in Telegram
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 19, 2026 | 6,790 |
| Nov 20, 2026 | 6,060 |
Most viewed this month
- 01Views6.98KForwards—Reactions45Comments—
- 02Views6.6KForwards—Reactions89Comments—
- 03Views6.06KForwards—Reactions163Comments—
Latest posts
📣📖👑 መልካም ዜና ለ«አክሊለ ድንግል» አንባብያን! 🔥 በአንባቢብያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘው «አክሊለ ድንግል» መጽሐፍ ቢያልቅም፣ አሁን በድጋሚ የተወሰኑ ቅጂዎች በሰርድዮን መጻሕፍት መደብር ይገኛሉ። በአማዞንም (Amazon) ላይ ማግኘት ይቻላል! 📚 የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 31ኛ መጽሐፍ፤ በቅዱስ ደቅስዮስ የተደረሰው «አክሊለ ድንግል»! 📘 28 ምዕራፎች! 📄 250 ገጾች! 🖋️ 370 የግርጌ ማስታወሻዎች! 👑 24 የምስጋና ምሥጢራት! 💎 12 የከበሩ ድንጋዮች! 🌟 6 የሰማይ አካላት! 🌹 6 ውብ አበቦች! 👑 24 የፍጥረት ምሳሌዎች፤ 24 መንፈሳዊ ምሥጢራት፤ አንድ የምስጋና አክሊል! ✨ ቅዱስ ደቅስዮስ ለድንግል ማርያም የምስጋና አክሊል ጎነጎነላት፤ እመቤታችንም በክብር ልብስና መንበር አከበረችው! 💎 መረግድ፣ ሰንፔርና ቶጳዝዮን ስለ ድንግል ማርያም ምን ይመሰክራሉ? 🌌 ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ኦሪዮንና አርክቱረስ በእመቤታችን ምስጋና ውስጥ ምን ያመለክታሉ? 🌹 ጽጌረዳ፣ የሱፍ አበባና የበረሓ አበባ የእመቤታችንን ንጽሕና፣ ትሕትናና ቅድስና እንዴት ይገልጻሉ? 📖 እነዚህን ሁሉ ምሥጢራት የሚያብራራውን ልዩ መጽሐፍ ዛሬውኑ ያግኙ! ⏳📣 ውድ አንባብያን! በድጋሚ የቀረቡት ቅጂዎች የተወሰኑ በመሆናቸው፣ መጽሐፉ እንደገና ከማለቁ በፊት የራስዎን ቅጂ ያግኙ! 📍 በኢትዮጵያ፦ 📚 ሰርድዮን የመጽሐፍ ማከፋፈያ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ 📞 0910934578 🌍 በውጭ ሀገራት ለምትገኙ አንባቢያን፦ 🛒📦 በAmazon አሁኑኑ ለመግዛት፦ https://a.co/d/0dzFVCCu 🎁 አንድ ቅጂ ለራስዎ፣ ሌላ ቅጂ ለሚወዱት ሰው ! 👑💎🌹 «አክሊለ ድንግል» — የምድር ዕንቁዎች፣ የሰማይ ከዋክብትና የአበቦች ውበት በአንድ የምስጋና አክሊል የሚገናኙበት ድንቅ መጽሐፍ! 📣 መጽሐፉን ሳያገኙ ለቀሩ ወዳጆችዎ ይህን መልእክት ያጋሩ! 🔥 አይዘግዩ! በዚህ የዕውቀት ዘመን ጊዜዎን ይጠቀሙበት። ያንብቡ፣ ምሥጢራቱን ይመርምሩ!
Open in Telegram🚨📖👑 ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ የበቃው «አክሊለ ድንግል» አሁን በAmazon ላይ ይገኛል! 🌹💎 12 የከበሩ ድንጋዮች፣ 6 የሰማይ አካላትና 6 ውብ አበቦች ለድንግል ማርያም የምስጋና አክሊል እንዴት ሆኑ? ✨ 24 አስደናቂ ምሥጢራትን የያዘውን ይህን ልዩ መንፈሳዊ መጽሐፍ አሁኑኑ ያግኙ! 🛒📦 በAmazon ለመግዛት ይጫኑ፦ https://a.co/d/0dzFVCCu 📖 «አክሊለ ድንግል» ✍️ በቅዱስ ደቅስዮስ 📚 በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተዘጋጀው 31ኛ መጽሐፍ! 📘 28 ምዕራፎች! 📄 250 ገጾች! 🖋️ 370 የግርጌ ማስታወሻዎች! 👑 24 የምስጋና ምሥጢራት! ✨ በትውፊቱ እንደሚነገረው፣ ቅዱስ ደቅስዮስ ለድንግል ማርያም የምስጋና አክሊል ጎነጎነላት፤ እመቤታችንም በክብር ልብስና መንበር አከበረችው! 💎 መረግድ፣ ሰንፔርና ቶጳዝዮን ስለ ድንግል ማርያም ምን ይመሰክራሉ? 🌌 ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ኦሪዮንና አርክቱረስ በእመቤታችን ምስጋና ውስጥ ምን ያመለክታሉ? 🌹 ጽጌረዳ፣ የሱፍ አበባና የበረሓ አበባ የእመቤታችንን ንጽሕና፣ ትሕትናና ቅድስና እንዴት ይገልጻሉ? 👑 24 የፍጥረት ምሳሌዎች፤ 24 መንፈሳዊ ምሥጢራት፤ አንድ የምስጋና አክሊል! 🌟 የአበቦችን ውበት፣ የዕንቁዎችን ድምቀትና የከዋክብትን ብርሃን ከነገረ ማርያም ረቂቅ ምሥጢራት ጋር የሚያስተሳስር ልዩ መጽሐፍ! 🔥📣 ውድ አንባቢያን፣ የ24ቱን ምሥጢራት ለማወቅ በመጓጓት ብቻ አይቅሩ! 📖 መጽሐፉን ዛሬውኑ ይግዙ፤ ያንብቡት፤ የእመቤታችንን ምስጋና ጥልቀት በራስዎ ንባብ ያስተውሉ! 🌍 በዓለም ዙሪያ ያላችሁ አንባቢያን፣ የራሳችሁን ቅጂ ለማግኘት የAmazon ሊንኩን አሁኑኑ ይጫኑ! 🛒👇 አሁኑኑ ለመግዛት፦ https://a.co/d/0dzFVCCu 📍 በኢትዮጵያ የመጽሐፉ መገኛ፦ 📚 ሰርድዮን የመጽሐፍ ማከፋፈያ 5 ኪሎ፣ ቅድስት ማርያም ሕንፃ 📞 0910934578 🎁 አንድ ቅጂ ለራስዎ፣ ሌላ ቅጂ ለሚወዱት ሰው ይግዙ! 📣 መጽሐፉን ለሚጠባበቁ ወዳጆችዎ ይህን መልእክትና የAmazon ሊንክ ያጋሩ! 👑💎🌹 «አክሊለ ድንግል» — 24 ምሥጢራት፣ 28 ምዕራፎች፣ 250 ገጾች፤ አንድ አስደናቂ የመንፈሳዊ ንባብ ጉዞ! 🔥📖 በስሙ ብቻ አይደነቁ፤ መጽሐፉን ይግዙ፣ ያንብቡ፣ ምሥጢራቱን ይመርምሩ! #አክሊለ_ድንግል #ቅዱስ_ደቅስዮስ #ድንግል_ማርያም #ዶክተር_ሮዳስ_ታደሰ #AmazonBooks #AkilileDingil #EthiopianOrthodox
Open in Telegram📖👑 አክሊለ ድንግል 🌹 በቅዱስ ደቅስዮስ 📚✍️ የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 31ኛ መጽሐፍ ታተመ። 👑🌹 «አክሊለ ድንግል» እመቤታችን መንበርና ልብስ በሰጠችው በቅዱስ ደቅስዮስ የተደረሰ፣ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን ቅድስና፣ ንጽሕና፣ ትሕትና፣ ፍቅርና መንፈሳዊ ክብር በረቂቅ ምሳሌዎች የሚያወድስ መንፈሳዊ ድርሰት ነው። 📖🕊️ ይኽ መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተዘጋጅቶ ለአማርኛ አንባቢያን የቀረበ ሲሆን፣ የእመቤታችንን ምስጋና ከሥነ መለኮት፣ ከምሳሌያዊ ትርጓሜና ከመንፈሳዊ ማስተዋል ጋር ያስተሳስራል። ✨👑 በመጽሐፉ ውስጥ በቅዱስ ደቅስዮስ የተገለጹት 24 የምስጋና ምሥጢራት በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይቀርባሉ፦ 💎 12 የከበሩ ዕንቁዎች፦ የእመቤታችንን ቅድስና፣ ንጽሕና፣ ጥበብና በጎ ምግባራት በዕንቁዎች ውበትና ክቡርነት የሚገልጹ ምሳሌዎች። 🌟 6 የሰማይ አካላት፦ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የድንግል ማርያምን መንፈሳዊ ክብርና የጸጋ ብርሃን እንዴት እንደሚያመለክቱ የሚያብራሩ ትርጓሜዎች። 🌹 6 ውብ አበቦች፦ የአበቦችን መዐዛ፣ ውበትና ለምለምነት ከእመቤታችን ፍቅር፣ ትሕትናና ንጽሕና ጋር የሚያስተሳስሩ መንፈሳዊ ምሳሌዎች። 📚 የመጽሐፉ ይዘት፦ 📘 28 ምዕራፎች 📄 250 ገጾች 🖋️ 370 የግርጌ ማስታወሻዎች (Footnotes) 👑 24 ምሳሌያዊ የምስጋና ምስጢራት ⛪📖 ይኽ መጽሐፍ ለነገረ ማርያም ተመራማሪዎች፣ ለሥነ መለኮት ተማሪዎች፣ ለመንፈሳዊ ሥነ ጽሑፍ አፍቃሪዎችና የጥንታዊ ክርስቲያናዊ ምሳሌያዊ ትርጓሜዎችን ማጥናት ለሚፈልጉ አንባብያን የተዘጋጀ ነው። 💎🌟🌹 «አክሊለ ድንግል» የእመቤታችን በረከት የበዛለት ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችንን ምስጋና በዕንቁዎች ድምቀት፣ በከዋክብት ብርሃንና በአበቦች ውበት የመሰለበት፣ የልባዊ ፍቅርና የመንፈሳዊ ማስተዋል የምስጋና አክሊል ነው። 📖 የ24ቱን የምስጋና ምሥጢራት በጥልቀት ለማወቅ መጽሐፉን ያንብቡ! 📚 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ሕንጻ ሰርድዮን መጻሕፍት መደብር 📞 0910934578 ያገኙታል። 💥 አማዞን ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ይወጣል። 🎁 ለራስዎ ያንብቡት፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ ያበርክቱት! 👑💎🌹 «ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ" ((ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ) (ማሕሌተ ጽጌ)
Open in Telegram📖👑 "አክሊል ድንግል በቅዱስ ደቅስዮስ" ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተዘጋጀ ገጽ 166 🌹 አንቺ በእምነትና በትዕግሥት ከአባቶች ይልቅ የከበርሽ ነሽ፤ በዕውቀትና በማስተዋል (በትንቢት እይታ) ከነቢያት ይልቅ የላቅሽ ነሽ፤ በቅድስና ፍጹምነትም ከሐዋርያት ኹሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልሽ ነሽ። 🕊️ ስለ ክርስቶስ መከራን በመቀበልና በመታገስ ከሰማዕታት ኹሉ በላይ የላቅሽ ነሽ፤ በበጎ ምግባርም ሥራ ቅዱሳንን ኹሉ ቀድመሻል። 🌸 በንጽሕናሽ ከደናግል ኹሉ በላይ ነሽ፤ በጸጋሽም መብዛት (ሙላት) መላእክትንና ሊቃነ መላእክትን ኹሉ ትበልጫለሽ። ✨ በጥበብሽ ግርማ ከኪሩቤል ይልቅ እጅግ የምታበሪ ነሽ፤ በፍቅርሽም ኃይልና ሙቀት (ትኩሳት) ከሱራፌል ይልቅ እጅግ የገዘፍሽ (የበራሽ) ነሽ! 👑 በእውነት አንቺ በጥበብ፥ በቅድስናና በጸጋ ከተፈጠሩት ፍጥረታት ኹሉ በላይ እጅግ የላቅሽ ነሽ፤ በአጽናፈ ዓለምም የሚወዳደርሽ (የሚስተካከልሽ) ማንም የለም። 💎 ስለዚኽም ለአንቺ የሚገባሽን ክብርና ምስጋና ለማቅረብ የምናፍቅ ምስኪን ኃጢአተኛ የኾንኊ እኔ በዚያ በከበረው አክሊልሽ በዐሥራ አንደኛው ስፍራ ላይ የከበረውን የኢያሰጲድ ዕንቁ አኖራለኊ። 💠 ኢያሰጲድ በሚያስደንቅ የሕብረ ቀለማት ውበት የተሞላና ድብቅ (ረቂቅ) የፈውስ በረከቶች ያሉት ድንቅ ዕንቁ ነው። እርሱ ከቁስል የሚፈሰውን ደም የመግታትና የማቆም ተፈጥሯዊ የፈውስ ኃይል አለው። 🌹 እመቤቴ ሆይ! ይኽ ዕንቁ ለተቀደሰው አክሊልሽ ፍጹም የሚስማማ ጌጥ ነው፤ ምክንያቱም አንቺ በተለያዩ የበጎ ምግባራት ውበቶች የተሸለምሽ፥ የድንግልናና የቅድስናም ጥምር ኃይላት የተዋሐዱብሽ ነሽና። 📚 የቅዱስ ደቅስዮስ መጽሐፉን ሰርድዮን መጻሕፍት መደብር ያገኙታል 0910934578 ይገኛል
Open in TelegramConnections
Similar channels
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka@bahrutekaReligion41.8K
ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር@ortodokstewahidoReligion43.6K
Minber TV@minbertvReligion43.7K
ikhlas Tube@ikhlas_post1Religion44.6K
የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ@buharimuslimamharicReligion44.9K
የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads@janyared_2Religion45.7K
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ@kinexebebeReligion45.9K
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች@ethiopian_orthodoxReligion33.6K