Account
የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads

የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

Username
@janyared_2
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers45,707
Avg views per post, 7d3,970last 7 days
ERR8.69%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 4, 202613,100
Nov 10, 202610,400
Nov 25, 20264,865
Nov 28, 20262,180

Most viewed this month

  1. 01
    Views13.1K
    Forwards—
    Reactions101
    Comments—
  2. 02

    No text

    Video
    Views10.4K
    Forwards—
    Reactions182
    Comments—
  3. 03
    Views4.94K
    Forwards—
    Reactions123
    Comments—
  4. 04
    Views4.79K
    Forwards—
    Reactions86
    Comments—

Latest posts

#2539Photo

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና 14 ቀን 2019 ዓ/ም በመርቲ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎራ ሲሊንጎ 14 ምእመናን፣ በሸርካ ወረዳ ጠሬታ ጮሌ ቢርቦ 46 ምእመናን ግፍን በተሞላ ጭካኔ ተገድለው ሕይወታቸው ማለፉን፣ የ20 ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውን፣ ከ20 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል እንደሚገኙ ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የቀረበውን ሪፖርት የሰማነው በከፍተኛ ኀዘን ነው፡፡ በአርሲ ሀገረ ስብከትና በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ንፁሐን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ተከታታይነት ባለው ሁኔታ፣ ያለማቋረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱና ከአሁን በፊትም በዞኑ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ምእመናን መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ አሳዛኝ ግፍና መከራ ጥልቅ በሆነ የኃዘን ስሜት ተመልክቶ እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በየትኛውም እምነት አስተምህሮም ሆነ በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ የሃይማኖት ነፃነትና በሕይወት የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብትን የጣሰ፣ ከሃይማኖትም ሆነ ከተፈጥሮ ሕገ ሰብእና የወጣ፣ ተከባብሮ የመኖር ሀገራዊ ዕሴቶቻችንን የሚያጠፋ፣ ሊወገዝ የሚገባው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጽኑ አውግዞታል፡፡ የንፁሐኑ ግድያ እንዲቆም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላትም ይህን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር በይፋ በማውገዝና በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና በነጻነት የማምለክ መብትን እንዲያስከብሩልን፣ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን ወንጀለኞችም ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ተግባር ከእንግዲህ በኋላ እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በደረሰው የልጆቻችን ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ከፍተኛ ኃዘን በድጋሚ እየገለጽን፣ ምእመናን ልጆቻችን በያሉበት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይደርስባቸው መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ፣ የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ እንደመንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉና አደጋዎችን ማስቀረት የሚያስችል ሥራ እንዲሠሩ እያሳሰብን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን በመመኘት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላክ ዕረፍተ ነፍስንና ክብረ ሰማዕታትን እንዲያድልልን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጸልያለች፡፡ በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባላት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ፍትሐት እንዲፈጸም፣ ነገ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማትና አድባራት በሙሉ ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከሚመለከተው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር ቀጠሮ ተይዞለት ውይይት እንዲያደርግና በቀጣይም ችግሩን በዛላቂነት ለመፍታት ተገቢው ጥረት እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ወስኗል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ምንጭ :- EOTC TV

Open in Telegram
Views13,900+96%vs avg
Forwards—
Reactions106
Comments—
#2538Photo

​​ብፁዕ አቡነ ገሪማ የዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ጥሪ አቀረቡ:: ጃንደረባው ሚድያ | ጥቅምት 15 2015 ዓመተ ምሕረት የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በአርሲ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ የሐዘን መግለጫ መሥጠታቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ዘገበ:: “ለእመ አሐዱ አባል ሐመ የሐምም ምስሌሁ ኩሉ ነፍስትነ ወእመኒ ተፈሥሐ አሐዱ አባል ይትፌሣሕ ምስሌሁ ኩሉ ነፍስትነ - አንድ ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ አንድ ብልትም ቢከብር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል” ፩ኛ ቆሮ ፲፪፥፳፮ በሚለው ቃለ ሐዋርያ የተነሡት ብፁዕነታቸው “በአርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳ በንጹሐን ክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና ማፈናቀል ሀገረ ስብከቱ ከሰጠው መግለጫ ስንሰማ እጅግ አሳዝኖናል። ሀገረ ስብከቱ ከመንግሥት አካላት ጋር በመወያየት መፍትሔ ለማግኘት ያደረጉትን ጥረት መልካም ሆኖ ሳለ እስካሁን ዘላቂ መፍትሔ አለመገኘቱ ደግሞ እጅግ አሳሳቢ ነው። የሚመለከተው አካል በሙሉ የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት” ብለዋል:: ብፁዕ አቡነ ገሪማ አያይዘው “ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለተጎዱት መጽናናትን እንመኛለን። የሚመለከተው አካል በሙሉ ለዚህ የከፋ የጸጥታ ችግር በአስቸኳይ ዘላቂ እልባት እንዲሰጡ እያሳሰብን ሁሉም ማኅበረሰብ የተጎዱትን እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::

Open in Telegram
Views8,910+26%vs avg
Forwards—
Reactions82
Comments—
#2537Photo

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይጠናቀቅ በአርሲ የምእመናን ግድያና መፈናቀል መቀጠሉ ተገለጸ:: ጃንደረባው ሚድያ | ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በርካታ ክርስቲያኖች እየተገደሉና እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ሲል ሀገረ ስብከቱ አስታወቀ። ሀገረ ስብከቱ “በአርሲ ሺርካ ክርስቲያኖች ላይ በታጠቁ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጥቷል። ይህም ትልቅ ኀዘን ፈጥሮብናል። ይህንን ችግር ለመፍታት ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ እና የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ውይይቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል” ብሏል ። የሚደረገው ጥረት  ግን ችግሩን እንዳልቀረፈና ተባብሶ መቀጠሉን ሀገረ ስብከቱ ገልጾ “ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለዚህ ችግር ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቷቸዋል፤ ለዚህም ሲሉ ከታች ካሉት የመንግሥት አካላት እስከ ሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጉዳዩን በተደጋጋሚ እያሳወቁ ይገኛሉ፤  እስካሁን ድረስ ግን የተሰጠ መፍትሔ የለም” ብሏል። አያይዞም  የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ  ለዚህ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ከባድ ሀዘን ውስጥ በመግባት ማነጋገር የሚገባቸውን አካላት ሁሉ በማነጋገር እና ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል:: የአርሲ ሀገረ ስብከት  ፣  ቅዱስ ሲኖዶስ ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው  የመንግስት አካላትም ይህንን የከፋ የጸጥታ ችግር በመቆጣጠር ለችግሩ እልባት እንዲሰጡት ሀገረ ስብከቱ መጠየቁን የአርሲ ሀገረ ስብከት መግለጫው አስታውቆአል ። ይህ በእንዲህ አንዳለ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሔደ ባለው ምልዓተ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ላይ በመላው ሀገሪቱ የካህናትና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰላም ችግር  አስመልክቶ በቀዳሚ አጀንዳነት መወያየቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ጥቅምት 12 ቀን በሠጡት መግለጫ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል ::  ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ሀገረ ስብከትን የሚደርሰውን የምእመናን ግድያና መፈናቀል ያወገዘ ሲሆን ችግሩ እንዲቀረፍ ከመንግሥት ጋር ውይይት እንዲደረግ መመሪያና አቅጣጫ መሥጠቱ ተገልጾአል:: ይሁንና በመጀመርያ አጀንዳ ላይ የቀረበው ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይጠናቀቅ ተባብሶ መቀጠሉና ምእመናን በግፍ እየተገደሉና እየተፈናቀሉ መሆኑ ተገልጾአል:: ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት በደረሰበት ወቅት ሀገረ ስብከቱ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ፣ ደጆችሽ አይዘጉን ጨምሮ ጥቂት ማኅበራትን በመጥራት ችግሩን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የልጅነታቸውን ግዴታ እንዲወጡ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል:: ሆኖም ችግሩ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ውስብስብ መሆኑን በመግለጽ በዘላቂነት ካልተፈታ ምንም ዓይነት የተራድኦ ሥራዎች ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም በመባሉ የተገታ ሲሆን ማኅበራቱ ግን ችግሩን ለመቅረፍ ቤተ ክርስቲያን በምታዝዘው ማንኛውም ሥራ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ሆነው የሀገረ ስብከቱን መመሪያ እየተጠባበቁ ይገኛሉ::  ምልዓተ ጉባኤው ሲጠናቀቅ በሚያወጣው ዝርዝር ውሳኔ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ የሚጠበቅ ሲሆን የምእመናን ሞት እስከ አሁንም ባለመቆሙ ጉዳዩን ጊዜ የማይሠጥ ያደርገዋል :: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህን አጀንዳ ዘንድሮ በቀዳሚነት ማስቀመጡ እጅግ ተስፋ ሰጪ ሲሆን ቀዳሚነቱ በስብሰባ አጀንዳ ላይ እንደሆነው ሥራውም ቅድሚያ እንዲሠጠው እንዲያደርግ ይጠበቃል:: “የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን” መዝ. 79:11

Open in Telegram
Views8,570+21%vs avg
Forwards—
Reactions90
Comments—
#2536Photo

በጃን ቂርቆስ ፕሮጀክት ሥር ታቅፈው ለሦስት ዓመታት እገዛ የሚደረግላቸው ሕፃናት/ታዳጊዎች እና እናቶች ከሚደረግላቸው ድጋፎች መካከል አንዱ በስድስት ወር አንድ ጊዜ የሚሰጣቸው ኹለንተናዊ እድገት ላይ ያተኮረ ሥልጠናነው። በመኾኑም ከሐምሌ 11 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል፣ በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን፣ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን፣ በገነተ አየሱስ ገነተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እና በሐመረ ወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያዎች ሲሰጥ የነበረው የኹለት ቀናት የልጆች እና የወላጆች ሥልጠና ጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም. ተጠናቋል። በሥልጠናው ላይ ከ400 (አራት መቶ) በላይ ዕድሜያቸው ከ7-18 ዓመት የኾኑ ሕፃናት እና ታዳጊዎች እንዲኹም ከ250 (ኹለት መቶ ሀምሳ) በላይ የሚኾኑ እናቶች ተሳትፈዋል። የታዳጊዎቹ ሥልጠና የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት፣ የተግባቦት ክህሎት፣ የአቻ ግፊት ተጽእኖን መቋቋም፣ የጥናት ዘዴ፣ ሕይወትን በእቅድ መምራት፣ ግጭት አፈታት እና የመሳሰሉትን ያካተተ ሲኾን ወላጆቹ ደግሞ የኦርቶዶክሳዊ የልጆች አስተዳደግ እና የንስሐ ሕይወት ላይ ያተኮረ ሥልጠናን ወስደዋል።

Open in Telegram
Views12,800+81%vs avg
Forwards—
Reactions87
Comments—

All posts

Connections