Account
መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝

+ከተለያዩ ፅሁፎች የተገኙትን መንፈሳዊ ህይወትን የሚሰብኩ ፅሑፎችንና ትምህርቶችን እናካፍላችሁ፡፡ ''አንብበን እንለወጥ።'' +መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ https://t.me/menfesawe12+

Username
@menfesawe12
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers11,889
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR9.84%30-day average

Latest posts

#5765Text
Views1,1700%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#5755Text

#እውነተኛውን_ጥበብ_እንዴት_እንቀበል? ማክሲመስ መስካሪው እንዲህ ይላል፦ "አንድ ክርስቲያን አምላካዊውን ጥበብ የሚቀበለው በሦስት መንገድ ነው። በትእዛዝ፣ በትምህርትና በእምነት ነው። ትእዛዝ ሐሳብን ከክፉ ስሜት ያነጻል፤ ትምህርት ወደ ርቱዕ የተፈጥሮ ዕውቀት ይመራል፤ እምነት በተቀደሰ ሦስትነት ወደ መመሰጥ ይመራል።" St. Maximus the Confessor, Chapters on Love, 4.47)። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚያውቅና በዚያም ለመጓዝ የሚፈቅድ ሰው ሐሳቡን በርቱዕ መሠረት ላይ ያንጻል። የሐሳብ ጥራት መነሻው በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ ባለችው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና። ሐሳባችን የሚበከለው በማንኛውም መንገድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ አፈንግጠን ስንወጣ ነው። ጥበብ ማለት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ የመኖር ጉዳይ ነው። ከዚያ ውጭ ስንኾን ርቱዕ ከኾነው ጥበብ ውጭ እንኾናለን፤ ያን ጊዜ ድንቍርናው በራሱ ጥበብ መስሎ ሐሳባችንን ይረብሸዋል፡ ወደ ርኲሰትም ይመራዋል! ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ወደ እውነተኛው ዕውቀት መግቢያ በር ነው። በዓለም ከሚወረወረው የስሕተት ቀስት የምንጠበቀው በኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው። ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን መውደድ ማለት እውነተኛ ዕውቀትን መውደድ ማለት ነው። ስለ ዓለም ያለን ዕውቀት ትክክለኛ ቅርጹን የሚዪዘው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት በኩል ነው። ቤተ ክርስቲያን በዋናነት እውነትን ትገልጣለች፡ በትምህርት በኩልም በልጆቿ ልብ ውስጥ እውነትን ትዘራለች፡ በዘራችው እውነትም ወደ ርቱዕ ዕውቀት የልጆቿን ልብ ትመራለች። እንግዲህ በዚህ ደግሞ ጥበብ ራሱ ርቱዕ ዕውቀት መኾኑን ርቱዐዊነት ባለው ዕውቀት በኩል መቅመስ እንችላለን። እምነት ደግሞ የማይመረመረውን ምሥጢረ ሥላሴ በምንችለው ልክ ቀምሰን እንድንመሰጥበት ወደዚያ የሚመራ ረቂቅ መሣሪያ ነው። እምነት የምእመናንን ልብ ከምድር ወደ ሰማይ የሚያስገባ ታላቅ ኃይል ነው። የማይታየውን የሚያሳይ፣ ልቡናን በጽኑዕ መሠረት ላይ የሚያንጽ መንፈሳዊ ኃይል ነው። በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን። እርሱ ደግሞ የጥበብ ቤቷ ነው። እንግዲያውስ ከእርሱ ንጹሕ ጥበብን በእምነት ቀድተን ለዓለም እናፈሳለን። ዓለምንም ወደ ርቱዕ እምነትና ጥበብ እናስገባ ዘንድ አደራ አለብን። ምክንያቱም የጥበብ ምንጭ የኾነው ክርስቶስ አምላካችን ራስ ኾኖን ክርስቲያን ተሰኝተናልና። እርሱ ደግሞ ኹሉን ወደ እርሱ እንድንማርክ ይፈልጋል። ይህም የሚኾነው ከንግግር ባለፈ እርሱ ክርስቶስን በእውነተኛ ሕይወት ስንገልጠው ነው። የእርሱን ፈቃድ ትተን የየግላችንን አጽድቀን የምንኖር ከኾነ ክርስቲያን የሚለው ስሙ እንጅ ትክክለኛ ትርጒሙ በእኛ ገቢራዊ ሕይወት አይገለጥምና ሌሎች ከሕይወት ድንቍርና ይላቀቁ ዘንድ ቀርቶ እኛው ራሳችን በራሳችን የፈቃድ ጥመት ድንቍርና ውስጥ ተቀብረን ያለን አሳዛኞች እንኾናለን። ትእዛዛተ እግዚአብሔር ሕይወታችንን የሚያጣፍጥ ኾኖ ሳለ ከዚያ አፈንግጠን ምሬትን ገንዘብ በማድርግ ትእዛዙን ከመፈጸም ደንቍረናል። በዚህም ላይ እንደ ገና ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንንም ጠልተን ወይም ከልብ ለመማር ወይም ለመረዳት ባለመፈለጋችንም ሌላ ድንቍርናን ጨምረናል። ስለዚህ በንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ምሥጢር ከመመሰጥ እና ከመደነቅ ይልቅ የጥርጣሬን ብርድልብስ ለራሳችንን ደራርበናል። እንግዲያውስ ጥበብ ከወዴት ይደርብን? ሕይወታችንስ እንዴት አይምረር? ፍሬ ምግባርስ እንዴት አይጉደልብን? ጸጋስ እንዴት አይራቀን? ሕማመ ነፍስስ እንዴት አይጽናብን? ሌሎችስ እውነት የሌለን እንዴት አይምሰላቸው? ወዳጆች ሆይ ትእዛዘ እግዚአብሔርን በመፈጸም፤ ትምህርቱንም (እውነተኛ ዕውቀት የሚቀዳበትን መንገድ) በመጠጣት፣ በርቱዕ እምነት ሰውነታችንን አጽንተን የጠቢባንን አኗኗር አሐዱ ብለን እስኪ እንጀምረው!https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,230+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5722Text
Views1,360+16%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#5721Text

በዘመነ መጸው ውስጥ ፭ ንዑሳን ክፍሎች አሉ።  እነሱም፡-   ፩.ዘመነ ጽጌ            ፬. ብርሃን እና                 ፪. አስተምህሮ       ፭. ኖላዊ ናቸው ።                 ፫.  ስብከት                                                              ከእነዚህም መካከል ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ለ፵ቀናት ያህል የሚቆየው በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ የእመቤታችን ስደት የሚታወስበትና እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘ ክፍል ዘመነ ጽጌ(ወርኀ ጽጌ) ይባላል። ጽጌ ማለት ‹ጸገየ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ‹አበበ፤ አፈራ፤ በውበት ተንቆጠቆጠ፤ በደም ግባት አጌጠ፤ የፍሬ ምልክት አሣየ› ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በአበባ የተመሰለች እመቤታችንንና በፍሬ የተመሰለ ልጇን ከወቅቱ ጋር በማዛመድ የምናመሰግንበት ጊዜ ነው። በወርኃ ጽጌ በዋናነት እመቤታችን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋር በሄሮድስ ምክንያት ወደ ምድረ ግብጽ መሰደዳቸውን በማስታወስና  በቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በደረሱት ድርሰት (ማኅሌተ ጽጌና ሰቆቃወ ድንግል) በማኅሌት ይከበራል። የስደትን  ነገር ስናነሳ እንዲሁ እንደውሃ ፈሳሽ እንደ ወንዝ ደራሽ ሳይሆን አስቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ  እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተጭኖ ወደ ግብጽ ይመጣል ኢሳ ፲፱፡፩ በማለት የተነገረ ነው። የስደት ወቅት በምንመለከትበት ጊዜ ወደ ምድረ ግብጽ የተሰደዱት ግንቦት ፳፬ ነው። ታዲያ ስለምን ቤተክርስቲያናችን ወደ መስከረም ቀይራ ታከብራለች ? ቢሉ ስለ ፪ ምክንያት ነው።                                    ፩. የስደት መነሻቸው ግንቦት 24 የሚውለው በበዓለ ኀምሳ በመሆኑ  በደስታ ወቅት የስደትን ነገር ማዘከር ስለማይገባ ነው።  ፪. ዘመነ ጽጌን ፍለጋ ነው።ምክንያቱም አበባዎች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምና ለልጇ ምሳሌዎች ናቸውና ።ይህንን ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል። ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም አበባ ይገኛል።ኢሳ ፲፩፡፩በማለት እንደነገረን ምሳሌን ከምሥጢር ጋር አዋሕዶ ለማክበር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርተዋል። ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን በዘመነ ጽጌ  በሄሮድስ የተመሰሉ ከልባችን የክርስቶስን ፍቅር የሚያሳድዱ ቅናትንና ትዕቢት አስወግደን ዘወትር ሕፃኑንና እናቱን በልባችን ጽላት አንግሠን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን። የልባችን ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰደድ አብራ ትሰደዳለችና። ድንግል ሆይ "እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ በምድረ ነኪር ሀገረኪ ገሊላ እትዊ፤  እስከ መቼ ድረስ በባዕድ ሀገር ትኖሪአለሽ? ወደ ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ።” የሰላም መገኛ ሰላማዊት ርግብ ሱላማጢስ ሆይ፥ ሰላምን ትሰጭን ዘንድ ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ኢትዮጵያና ወደ ልቡናችን ጓዳ ተመለሽ በማለት መለመን ይገባል።         የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን!                      ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,230+5%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#5720Photo

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!                    ወርኀ ጽጌ ክፍል ፩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት በአንድ ዓመት ውስጥ ያሉት ፫፻፷፭/፮ ቀናት በ ፬ ወቅቶች  ይከፈላሉ፡፡እነሱም፦                              ፩. ዘመነ መጸው (መከር)መስከረም ፳፮-ታኅሣሥ ፳፭ ፪. ዘመነ ሐጋይ (በጋ) ከታኅሣሥ ፳፮-መጋቢት ፳፭ ፫. ዘመነ ጸደይ (በልግ) ከመጋቢት ፳፮-ሰኔ ፳፭ ፬. ዘመነ ክረምት ከሰኔ ፳፮-መስከረም ፳፭ ናቸው። እነዚህ ወቅቶች እያንዳንዳቸው ፺ ቀናት ሲኖራቸው ዘመነ ክረምት ብቻ ፺፭/፺፮ ቀናት አሉት። በዚህም መሠረት  ከመስከረም ፳፮ ቀን  እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ወቅት  ‹‹ዘመነ መጸው››(መኸር) ይባላል፡፡ መጸው ማለት ‹‹መጸወ ፤ መጽለወ ጠወለገ›› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ወርኀ ነፋስ (የነፋስ ወቅት)ማለት ነው። ወቅቱም ከዘመነ ክረምት ቀጥሎ የሚገባና  በክረምት ዝናብ የበቀሉ ዕፀዋት አዝርት የሚያብቡበትና ፍሬ የሚያፈሩበት እንዲሁም ወንዞችና ምንጮች የሚጠሩበት  የአበባ፣የነፋስ፣ የፍሬ ወቅት ነው፡ ጠቢቡ ሰሎሞን  ይህን ሲገልጽ ‹‹እስመ ናሁ ክረምት ኀለፈ ወዝናም ገብአ ድኅሬሁ  ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ  ቃለ ማዕነቅ ተሰምዐ በምድርነ  በለስ አውፅአ ሠርጸ  አውያን ጸገዩ ወወሀቡ መዓዛ፡  እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም ዐልፎ ሔደ፡፡ አበባ በምድር ላይ ታየ፤ የመከርም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዓዛቸውንም ሰጡ፤›› (መኃ. ፪፥፲፩-፲፫) በማለት ያስረዳል፡፡

Open in Telegram
Views929−21%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5717Text
Views868−26%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5716Text

“ኢየሱስ” - ለሰዎች የተሰጠ ስም “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና /ሐዋ 4፥12/። ይህ ጥቅስ የትምህርታችን እና የተልእኮአችን ብቻ ሳይሆን የቅዳሴያችን እና በአጠቃላይ የሥርዐተ አምልኮታችን ሁሉ መሠረት ነው። የምንሰበሰበው በእርሱ ስም ነው። የምናመልከውም እርሱን ብቻ ነው። የአብንም ስም የምንጠራው እርሱ በትምህርቱ ‘እኔ በር ነኝ’ እንዳለው እርሱን ወልድ በማለት አባቱን አብ ለማለት በር አድረገነው ስለገባን ነው። በዚህ በር ካልገቡ እና አንድ አምላክ እና አንድ ኃይል አለ ከሚሉት የምንለየውም በዚህ ነው። መሥዋዕተ ቁርባን የምንሠራው በእርሱ ስም በመከራ መስቀሉም አትመን ነው። ማኅሌት ሰዓታት የምንቆመው በእርሱ ስም ነው። ቅዱሳንን ሳይቀር የምናከብረው እርሱ አድሮባቸው ስለኖረ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ‘ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል’ /ገላ 2 ፤ 20/ ሲል እንደገለጸው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስ በውስጡ የሚኖርበትን ማክበር ክርስቶስን ማክበር ነውና። ሌላው ቀርቶ ጌታም በመስቀል ላይ ሆኖ ለእናቱ ለድንግል ማርያም “እነሆ ልጅሽ” ሲል ዮሐንስን የሰጣት በዮሐንስ አድሮ ስለሚኖር ነው። እናስተውል ክርስቲያኖች ‘ልጅ ይሁን’፣ ሳይሆን ያላት “ልጅሽ” ነው ያላት። ይህም የሆነው በዮሐንስ አድሮ የሚኖረው እርሱ ስለሆነ ነው። እርሱን ባናምነውና ባናመልከው ኖሮ ቅዱሳንን ምን ብለን ልናከብራቸው እንችል ነበር? እናቱንስ ማንን ብለን እናከብራት ነበር? ለዚህ ነው ጌታ እውነተኛው በር እኔ ነኝ ያለን። በሥላሴ ለማመን በራችን እርሱ ነው። እርሱን ወልድ ያላለ አባቱን አብ ሊል መንፈስቅዱስንም ሕይወት ብሎ ሊቀበል አይችልምና። እናቱን እና ቅዱሳንን ለማክበርም በራችን እርሱ ነው። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አንድነትን ገንዘብ አድርገን ለማምለክም በራችን እርሱ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ የሚደረገውም በእርሱ መድኃኒትነት በማመናችን እና መድኃኒቱንም እየበላነው እየጠጣነው በመኖራችን ነው። ስለዚህ ያለዚህ ስም ምንም ምን ልናደርግ አንችለም። ሌላው ቀርቶ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማለት የቻልነው ኢየሱስን ወልድ ነው በማለታችን ነው። ይህን የማያምን ሰው ቅዱስ ዮሐንስ “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” /1ኛ ዮሐ 5፤12/ ሲል እንደተናገረው የሕይወት ተስፋ የለውም። ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ለዚህ ስም ለብቻው በዓል የምታከብረው። በአይሁድ ሥርዓት መሠረት ወንዶች በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ተገዝረው ስም ይሰጣቸዋል። ቅዱስ ሉቃስ “ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ” /ሉቃ 2 ፤ 21/ ሲል እንደመዘገበልንም በስምንተኛው ቀን በይፋ ኢየሱስ ተብሏል። በተወለደ በስምንተኛው ቀን ጥር ስድስት የስሙ በዓል የሚከበረውም ለዚህ ነው። የጌታችንን ኢየሱስ የሚለውን ስሙን ቀደም ብሎ መልአኩ ለእመቤታችንም የተናገረውም ስሙ ቀድሞ በራሱ ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ነው። ታዲያ ጥር ስድስት በየዐመቱ የስሙን በዓል ስናከብር በቅዳሴው ጊዜ ከዳዊት መዝሙር ምስባኩን ስትዘምር “ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል” /መዝ 71(72) ፤ 16/ የሚለውን መርጣ ትዘምራለች። እውነት ነው ስሙ ብርሃናት ሳይፈጠሩ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው። ይህ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ንዑሳት በዐላት አንዱ ነው። ዋና ዋና (ዐበይት በዐላት የሚባሉ የጌታችን ጽንሰቱ (ሰው ሆኖ የተጸነሰበት)፣ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት ወይም ደብረታቦር የምንለው፣ ሆሣዕና (በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያልን ጌትነቱን የምናውጅበት)፣ ስቅለቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱ እና ጰራቅሊጦስን ለቤተ ክርስቲያን የላከበት ናቸው። ከእነዚህ ቀጥለው የሚከበሩት ደግሞ ስብከት (ነቢያት አስቀድመው የሰበኩለት መሆኑ)፣ ብርሃን (ጨለማውን ሊያርቅልን የመጣ ብርሃን መሆኑ) እና ኖላዊ (የነፍሳችን እረኛ እርሱ መሆኑ) እነዚህ ከታኅሣሥ 7 ቀን ጀምሮ አንድ አንደ ሳምንት እየተሰጣቸው ከልደቱ በፊት ባሉት ሦስት ሰንበቶች የሚከበሩ እና የክርስቶስን የመጀመሪያ ምጽአቱን (ልደቱን) በናፍቆት በመጠባበቅ የምናከብራቸው ናቸው። ከዚያም ጌና በታኅሣሥ 28 ቀን የምናከብረው ነው። በዐሉም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን የምናውጅበት እና በየወሩ አማኑኤል እያልን የምናስቀጥለው ማለት ነው። ግዝረት (ለስሙ የምናከብረው) ፣ ቃና ዘገሊላ ( በሠርግ ቤት ባደረገው ተአምር አምላክነቱ የገለጠበት)፣ ልደተ ስምዖን (በ40 ቀኑ ቤተ መቅደስ ገብቶ ስምዖን እርሱን በመታቀፍ የሚጠበቀው እርሱ መሆኑን የመሰከረበት)፣ ደብረ ዘይት (ይህም ዳግመኛ የሚመጣበት መታሰቢያ ወይም ዳግም ምጽአቱን የምናምንና የምንጠብቀው መሆኑ የምናውጅበት) በመጨረሻም ዐለሙን ያዳነበትን መስቀሉን መገኘት በተመለከተ የምናክብረው የመስቀል በዓላችን ነው። ይህ ማለት ግን ከእነዚህ የበዐላት ቀናት ውስጥ እነዚህ ድርጊቶች አይታሰቡም ማለይ አይደለም። የክርስቶስ ከጽንሰቱ እስከ ምጽአቱ ድረስ ፣ ባጠቃላይ ድኅነታችንን መፈጸሙን ሁልጊዜ የምናስበው መሆኑ የታወቀ ነው። በእነዚህ ቀናት ደግሞ በተለየ ሁኔታ እናከብረዋለን ለማለት ነው። ስሙ የተባረከ ብቻ ሳይሆን የሚባርክ ፣ የሚያነጻ፣ የሚፈውስ፣ የሚሾም፣ የሚያክብር፣ አጋንንተን የሚያባርር፣ ሁሉንም ቅዱስ ነገር የሚፈጽም ነው። ለዚህ ነው ሁልጊዜ በቅዳሴያችን “ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር፣ ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፣ ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ፤ ለይኩን፣ ለይኩን ቡሩከ ለይኩን ” – ‘የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው፤ የጌትነት ስሙ ይመስገን፣ ይሁን ፣ ይሁን፣ የተመሰገነ ይሁን” እያልን ለስሙ ሳንታክት ሁልጊዜም ምስጋና የምናቀርበው። ይህ ብቻም አይደለም። ገና ቅዳሴ ሲጀመር በዐቢይ ዜማ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ከሚለው ልዩ ምስጋናዋ ጀምሮ ቅዳሴያችን ተጀምሮ እስከሚፈጸም ድረስ በዚህ ስም ሥርየተ ኃጢአት እና ዕርቅ የሚለመንበት መሠረታዊ ሥርዓተ አምልኮታችን ነው። ስለዚህ ከዚህ ስም ውጭ የመዳናችን ምሥጢር የሚፈጸምበት ሌላ ስም የለም። በእውነት ለዚህ ስም ተገቢውን ክብር እና ምስጋና እንሠጣለን። በስሙም እውነተኛ አምልኮ መልሰን ለእርሱ እናቀርባለን። ይህን ስም እጅግ ከማክበራችን የተነሣም በማንኛውም ሁነት ያለ አግባብ አንጠራውም። ሲጀመር የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የሚለው ትእዛዝ የተሰጠውም ለስሙ የሚገባውን ክብር መስጠት ከአማኞች ሁሉ የሚጠበቅ መሠረታዊ ሥርዓተ አምልኮት ስለሆነ ነው። በብሉይ ኪዳን ያህዌህ የሚለውን ስሙን የሚጠራው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ሲሆን እርሱም ቢሆን በዓመት አንድ ጊዜ የዕለተ አሥተሥርዮ ዕለት ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የደኅንነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ሰዓት ብቻ ነበረ። አሁንም እኛ ይህን ስም በመቅደስ ውስጥ ካህኑ የራሱን የጌታን ሥጋ እና ደም በሚያክብርብት ጊዜ በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ በልዩ ክብር ይጠራዋል። እኛም አማኞቹ እርሱን ተከትለን በታላቅ አክብሮት በመቅደሱ ውስጥ እንጠራዋለን። በትምህርት እና በመዝሙርም ራስን በመግዛት እና ለስሙ ተገቢውን ክብር በመስጠት እንጠራዋለን። ይህ ስም

Open in Telegram
Views1,120−4%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#5710Text
Views984−16%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—

All posts

Connections