Account

Posts of መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝

newest first

#5765Text
Views1,1700%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#5755Text

#እውነተኛውን_ጥበብ_እንዴት_እንቀበል? ማክሲመስ መስካሪው እንዲህ ይላል፦ "አንድ ክርስቲያን አምላካዊውን ጥበብ የሚቀበለው በሦስት መንገድ ነው። በትእዛዝ፣ በትምህርትና በእምነት ነው። ትእዛዝ ሐሳብን ከክፉ ስሜት ያነጻል፤ ትምህርት ወደ ርቱዕ የተፈጥሮ ዕውቀት ይመራል፤ እምነት በተቀደሰ ሦስትነት ወደ መመሰጥ ይመራል።" St. Maximus the Confessor, Chapters on Love, 4.47)። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚያውቅና በዚያም ለመጓዝ የሚፈቅድ ሰው ሐሳቡን በርቱዕ መሠረት ላይ ያንጻል። የሐሳብ ጥራት መነሻው በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ ባለችው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና። ሐሳባችን የሚበከለው በማንኛውም መንገድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ አፈንግጠን ስንወጣ ነው። ጥበብ ማለት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ የመኖር ጉዳይ ነው። ከዚያ ውጭ ስንኾን ርቱዕ ከኾነው ጥበብ ውጭ እንኾናለን፤ ያን ጊዜ ድንቍርናው በራሱ ጥበብ መስሎ ሐሳባችንን ይረብሸዋል፡ ወደ ርኲሰትም ይመራዋል! ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ወደ እውነተኛው ዕውቀት መግቢያ በር ነው። በዓለም ከሚወረወረው የስሕተት ቀስት የምንጠበቀው በኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው። ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን መውደድ ማለት እውነተኛ ዕውቀትን መውደድ ማለት ነው። ስለ ዓለም ያለን ዕውቀት ትክክለኛ ቅርጹን የሚዪዘው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት በኩል ነው። ቤተ ክርስቲያን በዋናነት እውነትን ትገልጣለች፡ በትምህርት በኩልም በልጆቿ ልብ ውስጥ እውነትን ትዘራለች፡ በዘራችው እውነትም ወደ ርቱዕ ዕውቀት የልጆቿን ልብ ትመራለች። እንግዲህ በዚህ ደግሞ ጥበብ ራሱ ርቱዕ ዕውቀት መኾኑን ርቱዐዊነት ባለው ዕውቀት በኩል መቅመስ እንችላለን። እምነት ደግሞ የማይመረመረውን ምሥጢረ ሥላሴ በምንችለው ልክ ቀምሰን እንድንመሰጥበት ወደዚያ የሚመራ ረቂቅ መሣሪያ ነው። እምነት የምእመናንን ልብ ከምድር ወደ ሰማይ የሚያስገባ ታላቅ ኃይል ነው። የማይታየውን የሚያሳይ፣ ልቡናን በጽኑዕ መሠረት ላይ የሚያንጽ መንፈሳዊ ኃይል ነው። በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን። እርሱ ደግሞ የጥበብ ቤቷ ነው። እንግዲያውስ ከእርሱ ንጹሕ ጥበብን በእምነት ቀድተን ለዓለም እናፈሳለን። ዓለምንም ወደ ርቱዕ እምነትና ጥበብ እናስገባ ዘንድ አደራ አለብን። ምክንያቱም የጥበብ ምንጭ የኾነው ክርስቶስ አምላካችን ራስ ኾኖን ክርስቲያን ተሰኝተናልና። እርሱ ደግሞ ኹሉን ወደ እርሱ እንድንማርክ ይፈልጋል። ይህም የሚኾነው ከንግግር ባለፈ እርሱ ክርስቶስን በእውነተኛ ሕይወት ስንገልጠው ነው። የእርሱን ፈቃድ ትተን የየግላችንን አጽድቀን የምንኖር ከኾነ ክርስቲያን የሚለው ስሙ እንጅ ትክክለኛ ትርጒሙ በእኛ ገቢራዊ ሕይወት አይገለጥምና ሌሎች ከሕይወት ድንቍርና ይላቀቁ ዘንድ ቀርቶ እኛው ራሳችን በራሳችን የፈቃድ ጥመት ድንቍርና ውስጥ ተቀብረን ያለን አሳዛኞች እንኾናለን። ትእዛዛተ እግዚአብሔር ሕይወታችንን የሚያጣፍጥ ኾኖ ሳለ ከዚያ አፈንግጠን ምሬትን ገንዘብ በማድርግ ትእዛዙን ከመፈጸም ደንቍረናል። በዚህም ላይ እንደ ገና ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንንም ጠልተን ወይም ከልብ ለመማር ወይም ለመረዳት ባለመፈለጋችንም ሌላ ድንቍርናን ጨምረናል። ስለዚህ በንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ምሥጢር ከመመሰጥ እና ከመደነቅ ይልቅ የጥርጣሬን ብርድልብስ ለራሳችንን ደራርበናል። እንግዲያውስ ጥበብ ከወዴት ይደርብን? ሕይወታችንስ እንዴት አይምረር? ፍሬ ምግባርስ እንዴት አይጉደልብን? ጸጋስ እንዴት አይራቀን? ሕማመ ነፍስስ እንዴት አይጽናብን? ሌሎችስ እውነት የሌለን እንዴት አይምሰላቸው? ወዳጆች ሆይ ትእዛዘ እግዚአብሔርን በመፈጸም፤ ትምህርቱንም (እውነተኛ ዕውቀት የሚቀዳበትን መንገድ) በመጠጣት፣ በርቱዕ እምነት ሰውነታችንን አጽንተን የጠቢባንን አኗኗር አሐዱ ብለን እስኪ እንጀምረው!https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,230+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5722Text
Views1,360+16%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#5721Text

በዘመነ መጸው ውስጥ ፭ ንዑሳን ክፍሎች አሉ።  እነሱም፡-   ፩.ዘመነ ጽጌ            ፬. ብርሃን እና                 ፪. አስተምህሮ       ፭. ኖላዊ ናቸው ።                 ፫.  ስብከት                                                              ከእነዚህም መካከል ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ለ፵ቀናት ያህል የሚቆየው በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ የእመቤታችን ስደት የሚታወስበትና እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘ ክፍል ዘመነ ጽጌ(ወርኀ ጽጌ) ይባላል። ጽጌ ማለት ‹ጸገየ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ‹አበበ፤ አፈራ፤ በውበት ተንቆጠቆጠ፤ በደም ግባት አጌጠ፤ የፍሬ ምልክት አሣየ› ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በአበባ የተመሰለች እመቤታችንንና በፍሬ የተመሰለ ልጇን ከወቅቱ ጋር በማዛመድ የምናመሰግንበት ጊዜ ነው። በወርኃ ጽጌ በዋናነት እመቤታችን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋር በሄሮድስ ምክንያት ወደ ምድረ ግብጽ መሰደዳቸውን በማስታወስና  በቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በደረሱት ድርሰት (ማኅሌተ ጽጌና ሰቆቃወ ድንግል) በማኅሌት ይከበራል። የስደትን  ነገር ስናነሳ እንዲሁ እንደውሃ ፈሳሽ እንደ ወንዝ ደራሽ ሳይሆን አስቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ  እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተጭኖ ወደ ግብጽ ይመጣል ኢሳ ፲፱፡፩ በማለት የተነገረ ነው። የስደት ወቅት በምንመለከትበት ጊዜ ወደ ምድረ ግብጽ የተሰደዱት ግንቦት ፳፬ ነው። ታዲያ ስለምን ቤተክርስቲያናችን ወደ መስከረም ቀይራ ታከብራለች ? ቢሉ ስለ ፪ ምክንያት ነው።                                    ፩. የስደት መነሻቸው ግንቦት 24 የሚውለው በበዓለ ኀምሳ በመሆኑ  በደስታ ወቅት የስደትን ነገር ማዘከር ስለማይገባ ነው።  ፪. ዘመነ ጽጌን ፍለጋ ነው።ምክንያቱም አበባዎች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምና ለልጇ ምሳሌዎች ናቸውና ።ይህንን ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል። ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም አበባ ይገኛል።ኢሳ ፲፩፡፩በማለት እንደነገረን ምሳሌን ከምሥጢር ጋር አዋሕዶ ለማክበር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርተዋል። ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን በዘመነ ጽጌ  በሄሮድስ የተመሰሉ ከልባችን የክርስቶስን ፍቅር የሚያሳድዱ ቅናትንና ትዕቢት አስወግደን ዘወትር ሕፃኑንና እናቱን በልባችን ጽላት አንግሠን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን። የልባችን ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰደድ አብራ ትሰደዳለችና። ድንግል ሆይ "እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ በምድረ ነኪር ሀገረኪ ገሊላ እትዊ፤  እስከ መቼ ድረስ በባዕድ ሀገር ትኖሪአለሽ? ወደ ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ።” የሰላም መገኛ ሰላማዊት ርግብ ሱላማጢስ ሆይ፥ ሰላምን ትሰጭን ዘንድ ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ኢትዮጵያና ወደ ልቡናችን ጓዳ ተመለሽ በማለት መለመን ይገባል።         የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን!                      ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,230+5%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#5720Photo

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!                    ወርኀ ጽጌ ክፍል ፩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት በአንድ ዓመት ውስጥ ያሉት ፫፻፷፭/፮ ቀናት በ ፬ ወቅቶች  ይከፈላሉ፡፡እነሱም፦                              ፩. ዘመነ መጸው (መከር)መስከረም ፳፮-ታኅሣሥ ፳፭ ፪. ዘመነ ሐጋይ (በጋ) ከታኅሣሥ ፳፮-መጋቢት ፳፭ ፫. ዘመነ ጸደይ (በልግ) ከመጋቢት ፳፮-ሰኔ ፳፭ ፬. ዘመነ ክረምት ከሰኔ ፳፮-መስከረም ፳፭ ናቸው። እነዚህ ወቅቶች እያንዳንዳቸው ፺ ቀናት ሲኖራቸው ዘመነ ክረምት ብቻ ፺፭/፺፮ ቀናት አሉት። በዚህም መሠረት  ከመስከረም ፳፮ ቀን  እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ወቅት  ‹‹ዘመነ መጸው››(መኸር) ይባላል፡፡ መጸው ማለት ‹‹መጸወ ፤ መጽለወ ጠወለገ›› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ወርኀ ነፋስ (የነፋስ ወቅት)ማለት ነው። ወቅቱም ከዘመነ ክረምት ቀጥሎ የሚገባና  በክረምት ዝናብ የበቀሉ ዕፀዋት አዝርት የሚያብቡበትና ፍሬ የሚያፈሩበት እንዲሁም ወንዞችና ምንጮች የሚጠሩበት  የአበባ፣የነፋስ፣ የፍሬ ወቅት ነው፡ ጠቢቡ ሰሎሞን  ይህን ሲገልጽ ‹‹እስመ ናሁ ክረምት ኀለፈ ወዝናም ገብአ ድኅሬሁ  ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ  ቃለ ማዕነቅ ተሰምዐ በምድርነ  በለስ አውፅአ ሠርጸ  አውያን ጸገዩ ወወሀቡ መዓዛ፡  እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም ዐልፎ ሔደ፡፡ አበባ በምድር ላይ ታየ፤ የመከርም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዓዛቸውንም ሰጡ፤›› (መኃ. ፪፥፲፩-፲፫) በማለት ያስረዳል፡፡

Open in Telegram
Views929−21%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5717Text
Views868−26%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5716Text

“ኢየሱስ” - ለሰዎች የተሰጠ ስም “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና /ሐዋ 4፥12/። ይህ ጥቅስ የትምህርታችን እና የተልእኮአችን ብቻ ሳይሆን የቅዳሴያችን እና በአጠቃላይ የሥርዐተ አምልኮታችን ሁሉ መሠረት ነው። የምንሰበሰበው በእርሱ ስም ነው። የምናመልከውም እርሱን ብቻ ነው። የአብንም ስም የምንጠራው እርሱ በትምህርቱ ‘እኔ በር ነኝ’ እንዳለው እርሱን ወልድ በማለት አባቱን አብ ለማለት በር አድረገነው ስለገባን ነው። በዚህ በር ካልገቡ እና አንድ አምላክ እና አንድ ኃይል አለ ከሚሉት የምንለየውም በዚህ ነው። መሥዋዕተ ቁርባን የምንሠራው በእርሱ ስም በመከራ መስቀሉም አትመን ነው። ማኅሌት ሰዓታት የምንቆመው በእርሱ ስም ነው። ቅዱሳንን ሳይቀር የምናከብረው እርሱ አድሮባቸው ስለኖረ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ‘ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል’ /ገላ 2 ፤ 20/ ሲል እንደገለጸው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስ በውስጡ የሚኖርበትን ማክበር ክርስቶስን ማክበር ነውና። ሌላው ቀርቶ ጌታም በመስቀል ላይ ሆኖ ለእናቱ ለድንግል ማርያም “እነሆ ልጅሽ” ሲል ዮሐንስን የሰጣት በዮሐንስ አድሮ ስለሚኖር ነው። እናስተውል ክርስቲያኖች ‘ልጅ ይሁን’፣ ሳይሆን ያላት “ልጅሽ” ነው ያላት። ይህም የሆነው በዮሐንስ አድሮ የሚኖረው እርሱ ስለሆነ ነው። እርሱን ባናምነውና ባናመልከው ኖሮ ቅዱሳንን ምን ብለን ልናከብራቸው እንችል ነበር? እናቱንስ ማንን ብለን እናከብራት ነበር? ለዚህ ነው ጌታ እውነተኛው በር እኔ ነኝ ያለን። በሥላሴ ለማመን በራችን እርሱ ነው። እርሱን ወልድ ያላለ አባቱን አብ ሊል መንፈስቅዱስንም ሕይወት ብሎ ሊቀበል አይችልምና። እናቱን እና ቅዱሳንን ለማክበርም በራችን እርሱ ነው። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አንድነትን ገንዘብ አድርገን ለማምለክም በራችን እርሱ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ የሚደረገውም በእርሱ መድኃኒትነት በማመናችን እና መድኃኒቱንም እየበላነው እየጠጣነው በመኖራችን ነው። ስለዚህ ያለዚህ ስም ምንም ምን ልናደርግ አንችለም። ሌላው ቀርቶ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማለት የቻልነው ኢየሱስን ወልድ ነው በማለታችን ነው። ይህን የማያምን ሰው ቅዱስ ዮሐንስ “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” /1ኛ ዮሐ 5፤12/ ሲል እንደተናገረው የሕይወት ተስፋ የለውም። ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ለዚህ ስም ለብቻው በዓል የምታከብረው። በአይሁድ ሥርዓት መሠረት ወንዶች በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ተገዝረው ስም ይሰጣቸዋል። ቅዱስ ሉቃስ “ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ” /ሉቃ 2 ፤ 21/ ሲል እንደመዘገበልንም በስምንተኛው ቀን በይፋ ኢየሱስ ተብሏል። በተወለደ በስምንተኛው ቀን ጥር ስድስት የስሙ በዓል የሚከበረውም ለዚህ ነው። የጌታችንን ኢየሱስ የሚለውን ስሙን ቀደም ብሎ መልአኩ ለእመቤታችንም የተናገረውም ስሙ ቀድሞ በራሱ ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ነው። ታዲያ ጥር ስድስት በየዐመቱ የስሙን በዓል ስናከብር በቅዳሴው ጊዜ ከዳዊት መዝሙር ምስባኩን ስትዘምር “ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል” /መዝ 71(72) ፤ 16/ የሚለውን መርጣ ትዘምራለች። እውነት ነው ስሙ ብርሃናት ሳይፈጠሩ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው። ይህ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ንዑሳት በዐላት አንዱ ነው። ዋና ዋና (ዐበይት በዐላት የሚባሉ የጌታችን ጽንሰቱ (ሰው ሆኖ የተጸነሰበት)፣ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት ወይም ደብረታቦር የምንለው፣ ሆሣዕና (በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያልን ጌትነቱን የምናውጅበት)፣ ስቅለቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱ እና ጰራቅሊጦስን ለቤተ ክርስቲያን የላከበት ናቸው። ከእነዚህ ቀጥለው የሚከበሩት ደግሞ ስብከት (ነቢያት አስቀድመው የሰበኩለት መሆኑ)፣ ብርሃን (ጨለማውን ሊያርቅልን የመጣ ብርሃን መሆኑ) እና ኖላዊ (የነፍሳችን እረኛ እርሱ መሆኑ) እነዚህ ከታኅሣሥ 7 ቀን ጀምሮ አንድ አንደ ሳምንት እየተሰጣቸው ከልደቱ በፊት ባሉት ሦስት ሰንበቶች የሚከበሩ እና የክርስቶስን የመጀመሪያ ምጽአቱን (ልደቱን) በናፍቆት በመጠባበቅ የምናከብራቸው ናቸው። ከዚያም ጌና በታኅሣሥ 28 ቀን የምናከብረው ነው። በዐሉም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን የምናውጅበት እና በየወሩ አማኑኤል እያልን የምናስቀጥለው ማለት ነው። ግዝረት (ለስሙ የምናከብረው) ፣ ቃና ዘገሊላ ( በሠርግ ቤት ባደረገው ተአምር አምላክነቱ የገለጠበት)፣ ልደተ ስምዖን (በ40 ቀኑ ቤተ መቅደስ ገብቶ ስምዖን እርሱን በመታቀፍ የሚጠበቀው እርሱ መሆኑን የመሰከረበት)፣ ደብረ ዘይት (ይህም ዳግመኛ የሚመጣበት መታሰቢያ ወይም ዳግም ምጽአቱን የምናምንና የምንጠብቀው መሆኑ የምናውጅበት) በመጨረሻም ዐለሙን ያዳነበትን መስቀሉን መገኘት በተመለከተ የምናክብረው የመስቀል በዓላችን ነው። ይህ ማለት ግን ከእነዚህ የበዐላት ቀናት ውስጥ እነዚህ ድርጊቶች አይታሰቡም ማለይ አይደለም። የክርስቶስ ከጽንሰቱ እስከ ምጽአቱ ድረስ ፣ ባጠቃላይ ድኅነታችንን መፈጸሙን ሁልጊዜ የምናስበው መሆኑ የታወቀ ነው። በእነዚህ ቀናት ደግሞ በተለየ ሁኔታ እናከብረዋለን ለማለት ነው። ስሙ የተባረከ ብቻ ሳይሆን የሚባርክ ፣ የሚያነጻ፣ የሚፈውስ፣ የሚሾም፣ የሚያክብር፣ አጋንንተን የሚያባርር፣ ሁሉንም ቅዱስ ነገር የሚፈጽም ነው። ለዚህ ነው ሁልጊዜ በቅዳሴያችን “ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር፣ ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፣ ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ፤ ለይኩን፣ ለይኩን ቡሩከ ለይኩን ” – ‘የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው፤ የጌትነት ስሙ ይመስገን፣ ይሁን ፣ ይሁን፣ የተመሰገነ ይሁን” እያልን ለስሙ ሳንታክት ሁልጊዜም ምስጋና የምናቀርበው። ይህ ብቻም አይደለም። ገና ቅዳሴ ሲጀመር በዐቢይ ዜማ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ከሚለው ልዩ ምስጋናዋ ጀምሮ ቅዳሴያችን ተጀምሮ እስከሚፈጸም ድረስ በዚህ ስም ሥርየተ ኃጢአት እና ዕርቅ የሚለመንበት መሠረታዊ ሥርዓተ አምልኮታችን ነው። ስለዚህ ከዚህ ስም ውጭ የመዳናችን ምሥጢር የሚፈጸምበት ሌላ ስም የለም። በእውነት ለዚህ ስም ተገቢውን ክብር እና ምስጋና እንሠጣለን። በስሙም እውነተኛ አምልኮ መልሰን ለእርሱ እናቀርባለን። ይህን ስም እጅግ ከማክበራችን የተነሣም በማንኛውም ሁነት ያለ አግባብ አንጠራውም። ሲጀመር የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የሚለው ትእዛዝ የተሰጠውም ለስሙ የሚገባውን ክብር መስጠት ከአማኞች ሁሉ የሚጠበቅ መሠረታዊ ሥርዓተ አምልኮት ስለሆነ ነው። በብሉይ ኪዳን ያህዌህ የሚለውን ስሙን የሚጠራው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ሲሆን እርሱም ቢሆን በዓመት አንድ ጊዜ የዕለተ አሥተሥርዮ ዕለት ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የደኅንነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ሰዓት ብቻ ነበረ። አሁንም እኛ ይህን ስም በመቅደስ ውስጥ ካህኑ የራሱን የጌታን ሥጋ እና ደም በሚያክብርብት ጊዜ በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ በልዩ ክብር ይጠራዋል። እኛም አማኞቹ እርሱን ተከትለን በታላቅ አክብሮት በመቅደሱ ውስጥ እንጠራዋለን። በትምህርት እና በመዝሙርም ራስን በመግዛት እና ለስሙ ተገቢውን ክብር በመስጠት እንጠራዋለን። ይህ ስም

Open in Telegram
Views1,120−4%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#5710Text
Views984−16%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#5693Link preview
Views1,190+2%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5672Text

+++ የአዲስ ዓመት ስለት +++ በኖኅ ዘመን የነበሩት ሰዎች አመጸኞች ሆኑ። የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ እምቢ ብለው መንገዳቸውን በፊታቸው አበላሹ። ምድሪቱንም በግፋቸው ሞሏት። ስለዚህም እግዚአብሔር ከትውልዱ ጻድቅ የነበረው ኖኅና ቤተሰቡን አስቀርቶ ሌሎቹን ከምድር ጋር ያጠፋቸው ዘንድ የጥፋት ውኃን አዘነመ። የታላላቅ ቀላያት ምንጮች ሁሉ ተነደሉ። የሰማይ መስኮቶችም ከፈቱ። ምድር በአምላክ የቁጣ ውኃ ተጥለቀለቀች። በመርከቢቱ ከነበሩት በቀር ምድር አንዲት  ነፍስ አልቀረላትም። እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ቁጣ በኋላ በመርከቡ የነበሩትን ኖኅንና እንስሳት አራዊቱን አሰበ። በምድርም ላይ ነፋስን አሳለፈ። የቀላያቱን ምንጮች የሰማዩንም መስኮቶች ደፈነ። ዝናሙንም ከሰማይ ከለከለ። ሞልቶ የነበረውም ውኃ ቀስ በቀስ እየጎደለ መጣ። በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደ ተቀመጠው በውኃ ተጥለቅልቃ የነበረችው ምድር ግልጥ ሆና የታየችው በመጀመሪያው ወር መባቻ ላይ ነበር።(ኩፋ 7፥1) ባለ ዘመኖቹ እኛ ልክ በኖኅ ጊዜ እንደ ነበሩት የቀድሞ ሰዎች ክፋታችን ተካክሏል። መንገዳችንን በእግዚአብሔር ፊት አበላሽተናል። ምድርን በግፋችን ሞልተናታል። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ያወረደው የጥፋት ውኃ ለእኛም ይገባን ነበር። እኛ ግን እርሱ እስኪቀጣንም አልጠበቅንም። እርስ በእርሳችን እየተጋደልን ምድራችንን በጥፋት ደም አጥለቀለቅናት። ወንድም ወንድሙን በጥይት ነደለ፣ በስለትም ሰውነቱን ከፈተ። የቁጣው ደም ከሰው እየመነጨ ምድርን ሸፈነ። ታዲያ በዚህች ጎስቋላ ምድራችን ላይ የፈሰሰውን ደም የሚያደርቅ የይቅርታ ነፋስ መቼ ይነፍሳል? እንደ ውኃ ያጥለቀለቀንስ ደም መቼ ይጎድላል? የምንሰማው መጨካከንስ እያደር እያደር የሚቀለው መቼ ነው? አሁን እኮ የመጀመሪያው ወር (መስከረም) መባቻ ነው። ምድራችንን የሸፈናት ጥላቻ እና መገዳደል ተገፍፎላት ዳግመኛ ግልጥ ሆና አናያትም? የእኔ የአዲሱ ዓመት ስለቴ ይህ ነው። የእናንተስ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,280+9%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5661Text

ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡ በዚኽች ዕለት ታስበው የሚውሉት ቅዱሳን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል፣ የካህኑ መልከጼዴቅ፣ የአቡነ ሰራጵዮን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን! https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views1,090−7%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#5660Text

ጳጉሜ ፫      ቅዱስ ሩፋኤል ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡ ይኽም ጻድቅ ጦቢት በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡ ከወገኖቹ ጋራ ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር፣ ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉም ዓሥራት በኩራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር፡፡ ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች ይሰጣል፡፡ በዚያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉም ክደው በዓልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሰው ነበር፡፡ የቅዱስ ጦቢት ወገኖቹ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር፡፡ የአሕዛብንም መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና፡፡ በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት፡፡ እርሱም እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ፡፡ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረውና ፀሐይ ሲገባ ቆፍሮ ቀበረው፡፡ በዚያችም ሌሊት እንደኃጢአተኛ ሆኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ፡፡ በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስላላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ወፎች እርኩሳቸውን ዐይኖቹ ላይ ጣሉበትና ዐይኖቹ ተቃጠሉ፡፡ ከዐይኖቹም ጢስ ወጣ፡፡ ታወሩም፡፡ ባለ መድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም፡፡ መልአኩን ልኮ ነፍሱን እንዲወስዳት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ የሣራ እና የጦቢት ጸሎታቸው ተሰማላቸው፡ ይህችም ሣራ አስማንድድዮስ የሚባል የሚባል ጋኔን በጭኗ አድሮ ሰባት ባሎቿን በየተራ የገደለባት ናት፡፡  ጦቢትም በገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጠውን ገንዘብ ያስመጣለት ዘንድ ልጁን ጦቢያን አሽከር እንዲፈልግ ነገረው፡፡ ጦቢያም ለአባቱ ታዥ ሆኖ አሽከር ሲፈልግም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ስሙን አዛርያ ነኝ ብሎ በሰው አምሳል ተገለጠለትና ጦቢት አንድ ላይ ላካቸው፡፡ ጤግሮስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ ጦብያ ሊታጠብ ባለ ጊዜ ታላቅ ዓሣ ሊውጠው ሲል መልአኩ ‹‹አትራው ያዘውና ጉበቱንና ልቡን አውጣ›› አለው፡፡ እንዳዘዘውም አደረገ፡፡ ጦቢያም ‹‹አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ! ይህ የዓሣ ሐሞት፣ ጉበትና ልቡ ምን ይሠራል?›› አለው፡፡ አዛርያ ጠባለው ቅዱሱ ምአክም ‹‹ጉበቱና ልቡ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሱት ጋኔን ያደረበትን ጢሱ ያድነዋል፤ ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩበትን ሰው ቢኩሉት የታወረ ዐይኖቹ ይበራሉ›› አለው፡፡ ዳግመኛም አዛርያ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዲያገባት ነገረው፡፡ እንዳይፈራም አጽናናው፡፡ ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱም ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፡፡ ጦቢያም ሣራን ወደዳትና እርሷን ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው፡፡ አበቷም ካሁን በፊት ለሰባት ባሎች ሰጥቷት ሰባቱም እንደሞቱ ቢነግረው ጦቢያም ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› አለው፡፡ አባቷም ሣራን ሰጠውና ወደ ጫጉላ ቤት ባገቧቸው ጊዜ ጦቢያ አዛርያ የነገረውን አስታወሰ፡፡ የዓሣውን ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሰው ጋኔኑ አስማንድድዮስ ሸሸ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ይዞ ለዘለዓለም አሠረው፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሚስቱን ሣራን ወስዶ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ፡፡ የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሆኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ፡፡እርሱም ዳነና ማየት ቻለ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ራሱን ገለጠላቸውና ብዙ ምሥጢርን ከነገራቸው በኋላ ዐረገ፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢት ከወገኖቹ ጋራ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ፡፡ ስለ ጌታችንም መከራ ትንቢት ሲናገር ‹‹እርሱ በኋጢአታችን ይገርፈናል፣ ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል፣ ይፈውናልም፡፡ ሁለተኛም መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው፣ እነርሱ ክብርህን ባዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢት ብዙ ትንቢቶችን ተናገረ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌም መታነጽና የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢትን ተናገረ፡፡  ልጁን ጦቢያንም ‹‹ልጄ ሆይ! ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት›› አለው፡፡ ይህንንም ተናገሮ በአልጋው ላይ ሳለ በ158 ዘመኑ በሰላም ዐረፈ፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡ የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡

Open in Telegram
Views904−23%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5653Text

በብሕትውናው ቦታ ፈጽሞ እንዳይለቅ ከመሬት በላይ ቤት ሠርቶ እንዳይኖር፣ ፀጉሩን እንዳይላጭ፣ ጥፍሩንም እንዳይቆረጥ ሚስትም እንዳያገባ ሥርዓት ሠርቶለታል፡፡ በመላከ እግዚአብሔር እየተረዳ ምግቡን መላእክት እየመገቡት እስከ አብርሃም ድረስ በፍጹም ብሕትውና ለማንም ሳይገልጥ ኑሮአል፡፡ አብርሃም የወንድሙ ልጅ ሎጥን ያስጨንቁና ንብረቱን የዘረፉ አምስቱን ነገሥታት ኮሎዶጎሞርን ድል ነሥቶ ሲመለስ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ በዘመኑ የሚፈጸም መሆኑንና አለመሆኑን ለማወቅ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቆ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ምሳሌውን ካህኑ መልከጼዴቅን ከተሰወረበት ቦታ ሄዶ እንዲመለከት ፈቀደለት፡፡ አብርሃምም የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ኅብስተ አኮቴት ጽዋ በረከት ይዞ ወደ ማዕከለ ምድር ቀራንዮ ሄደ፤ መልከጼዴቅም ተገልጦለት ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ፤ አየም ደስም አለው ….›› እንዳለው ጌታችን (መልከጼዴቅ የእግዚአብሔር ወልድ የመድኅን ዓለም ክርስቶስ) ምሳሌ ነበር፡፡ (ዮሐ.፰፥፶፰) ለዚህ ነው ጌታችን ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ አየም ማለቱ) አብርሃም ኅብስት አኮቴት ጽዋ በረከት ለመልከጼዴቅ የሰጠው፤ (ዘፍ.፲፬፥፲፰) ትውልድ ከእርሱ የማይቆጠር ግን አብርሃም ዐሥራትን አውጥቶ ሰጥቶታል፤ የአብርሃምንም መሥዋዕት አስታኮቶለታል፤ አብርሃምንም ባርኮታል፤ የጌታችን ምሳሌ የሆነው የኦሪቱ ሊቀ ካህን መልከጼዴቅን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ታስበዋለች፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም ሊቀ ካህን የመልከጼዴቅ ጸሎት ይጠብቀን፤ አሜን!!! ጾመ ዮዲት በወርኃ ጳጉሜን ምእመናን በፈቃዳቸው ይጾሙባታል፤ መጪው ዘመን እንዲባረክ፣ ስለ ቀደመው ኃጢአት እያዘኑ በጾም በጸሎት ፈጣሪን እየተማጸኑ ያሳልፏታል፤ ይህቺ ወቅት በመጽሐፈ ዮዲት ተመዝግቦ እንደምናነበው ሆሎፎርኒስ የተባለ የናቡከደነጾር ቢትወደድ የእስራኤልን ልጆች ምንጭ ይዞ ሕዝቡን ባስጨነቀ ጊዜ ተስፋ ቆርጠው ለጠላት ምርኮ እንግባ አሉ፤እግዚአብሔርን የምትፈራ በጾም በጸሎት ተወስና የምትኖር ዮዲት የተባለች ደገኛ ሴት ከመሪዎቿ መካከል ተገኝታ ለጠላት እጅ እንዳይሰጡ ከእነርሱ የስንፍናን ንግግር እንዲያርቁ ተማጸነች፡፡ አባቶቻቸውን ከጠላት የታደገ ድንቅ ተአምራት ማድረግ ወደሚቻለው እግዚአብሔር በጾም በጸሎት ለአምስት ቀን እንዲማጸኑ አሳሰበች፤ ከአባቶች ምርቃት ተቀብላ አገልጋይዋን አስከትላ ከጠላት መንደር ተጓዘች፡፡ እግዚአብሔር ግርማ ሞገስ ሆናት፤ ለቀናት በጾም በጸሎት ተወስና አብራ ከሆሎፎርኒስ ጋር ተቀመጠች፤ በአንድ ሌሊት አብዝቶ ጠጥቶ እንቅልፍ ጥሎት ሳለ ወደ ፈጣሪዋ እንዲህ ጸለች፤ ‹‹አቤቱ የመላእክት ፈጣሪ በዚህች ሰዓት ኢየሩሳሌም ከፍ ከፍ ትል ዘንድ መከራችንን አይተህ በእኔ እጅ ይቅርታን አደርግ፤ እስራኤልን ከኃሣር የምታነሣበት ጊዜው ደርሷልና …›› (መጽሐፈ ዮዲት ፲፫፥፬-፭) ከዚያም የራሱን ሰይፍ አንሥታ ቸብቸቦውን ቆርጣ ወደ ሕዝቦቿ ተመለሰች፤ የናቡከደነጾር ጭፍሮች የመሪያቸው የሆሎፎርኒስን መሞት ሲመለከቱ ሸሹ፤ ዮዲትና ሕዝቧ በእግዚአብሔር ኃይል አስጨናቂ ጠላቶቻቸውን ድል አደረጉ፡፡ ዮዲት በመልካም ምግባሯ፣ በጾም ጸሎቷ ሰው በጠፋበት ዕለት ለወገኖቿ ሰው ሆና ተገኘች፤ በመልካም ጊዜ የጾሙት የጸለዩት ጸሎት በችግር ወቅት የመፍትሔ አካል እንደሚሆን ዮዲት አስተማረች፤ ተስፋ የቆረጠ ሕዝቧን ተስፋ ሰጠች፡፡ የወገኖቿን አስጨናቂ አስወግዳ ለተጨነቀች ነፍሳቸው ሰላም (የዕረፍት) ማግኘት ምክንያት ሆነቻቸው፡፡ ምእመናን በዚህ ይህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ፣ የዮዲትን የእምነት ጽናት፣ የጾም ጸሎትን ጥቅም ተረድተው ስለ ግል ሕይወታቸው፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ አገር ፍቅር ሰላም ብለው በፈቃዳቸው ወርኃ ጳጉሜን በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ፤ የሕይወት ኃሣር ይወገድ፣ ጥላቻ ከሕዝብ ይራቅ መጪው አዲስ ዓመት ይባረክ፤ የተዘራው ዘር ለፍሬ እንዲሆን ጠላት ዲያብሎስ ያፍር ዘንድ ይማጸናሉ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!! https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views890−24%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#5652Text

ወርኃ ጳጉሜን ዕለተ ምርያ ወርኃ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ የምትገኝ በአገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዐሥራ ሦስተኛው ወር የምትቆጠር ናት፤ ወርኃ ጳጉሜን አምስት ቀናት ያሏት ስትሆን በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ሉቃስ መውጫ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ያለው ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላታቸው ጳጉሜን እንዲህ ይተረጉሟታል፤ ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ተውሳክ፣ አምስት ቀን፣ ከሩብ፣ ከዐውደ ወር ተርፎ በዓመቱ መጨረሻ የተጨመረ ስለሆነ ትርፍ ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፱፻፭) በወርኃ ጳጉሜን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተከብረው (ታስበው የሚውሉ በዓላት አሉ፤ በሌላ ስያሜም ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች፤ ምርያ ማለት ከቀን ወደ ቀን የሚያሻግር፣ አንድም ዕለተ ኅሪት ዕለተ መድኃኒት ማለት ነው፤ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፮፻፰) ምእመናን በዚህች ወቅት ጸበል ይጠበሉባታል (ይጠመቁበታል)፡፡ ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ጳጉሜን ሦስት ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ የሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዚህች ዕለት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ በድርሳነ ቅዱስ ሩፋኤል እና በወርኃ ጳጉሜን ሦስት ቀን የሚነበበው ስንክሳርና የተጻፉት ድርሳናት እንዲህ ያስተምሩናል፤ አንዲት ክርስቲያን ሴት በቅዱስ ሩፋኤል ሰም በባሕር መካከል ባለች ደሴት ቤተ ክርስቲያን አሳነጸች፤ ሊቀ ጳጳሱ አባ ቴዎፍሎስ በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱን አከበረ፤ ከደሴቲቱ ሥር የነበረ ግዙፍ ዓሣአንበሪም ባሕሩን ባናወጠው ጊዜ በደሴቲቱ የታነጸቸውን ቤተ ክርስቲያኗን ሊያፈርስ ደረሰ፤ በውስጧም ለበዓል ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በጸሎት ወደ ቅዱስ ሩፋኤል ተማጸኑ፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ መጣ፤ ሕዝቡን ታደገ፤ ከደሴቲቱ ሥር ያለውንም ግዙፍ ዓሣአንበሪው እንዳይንቀሳቀስ በጦር ወጋው፤ ‹‹እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም!›› አለው፤ ጸጥ ብሎም ቆመ፡፡ ሕዝቡም ከባሕሩ ከመስጠም፣ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኒቱም ከመፍረስ ተረፉ፤ ቅዱስ ሩፋኤል ይህን ድንቅ ተአምር አድርጎ፣ ከፈጣሪው አማልዶ፣ ለጠሩት ፈጥኖ የደረሰበትን ይህን በዓል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓመቱ መጨረሻ ባለችው ወርኃ ጳጉሜን በሦስተኛ ቀን በድምቀት ታከብሯለች፡፡ (ስንክሳር ዘወርኃ ጳጉሜን ሦስት ቀን) በዚህች ዕለት ከሚከበሩ በዓላት ሌላኛው በመጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፈ ጦቢት እንደተጻፈው ቅዱስ ሩፋኤል በመልካም ምግባሩ፣ በምጽዋት ሥራው ለሚታወቀው ለጦቢት በችግሩ ጊዜ በሰው አምሳል ተገልጦ፣ እንደ ሠራተኛ ተቀጥሮ በማገልገለል ልጁ ጦቢያን ከዓሣአንባሪ ፣ ሣራ የተባለችን ሴት ያሠቃያት ከነበረው ርኩስ መንፈስ፣ ጦቢትን ከዓይን ሕመሙ የፈወሰበት የቅዱስ ሩፋኤል ተራዳኢነት፣ የጦቢት መልካም ምግባር፣ የእግዚአብሔር ቸርነት የተገለጠበት መታሰቢያም በዓል ነው፡፡ (መጽሐፈ ጦቢት አንድምታው መግቢያ) ይህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የተሾመበት መታሰቢያውም ነው፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ጸሎት ይጠብቀን፤ አሜን!!! ዕለተ ምጽአት ወርኃ ጳጉሜን የዕለተ ምጽአት መታሰቢያም ናት፤ እግዚአብሔር ለፍርድ ወደዚህ ምድር የሚመጣበት ወቅት መታሰቢያ ነው፤ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ከፀሐይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት፤ ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ ዝምም አይልም ….›› በማለት እንደተናገረው ጌታችንም በደብረ ዘይት ተራራ ለደቀ መዛሙርቱ ዳግመኛ ለፍርድ እንደሚመጣ በገለጸው መሠረት ወደዚህ ምድር ለጻድቃን ሊፈርድላቸው፣ በኃጥአን ሊፈርድባቸው ይመጣል፤ (መዝ. ፵፱፥፩-፫) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቼ እንደሚመጣ ዓመቱንና ዕለቲቱን በግልጽ ባይነግረንም ዳግመኛ ግን እንደሚመጣ ነግሮናል፤ ‹‹…ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና፡፡›› (ማቴ.፳፬፥፵፬) ቅዱስት ቤተ ክርስቲያንም የዕለተ ምጽአቱን መታሰቢያ በዐቢይ ጾም እኩለ ሳምንት ላይና በወርኃ ጳጉሜን ሦስተኛው ቀን ታከብራለች፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ጸሎት ላይ ‹‹ለምጽአትከ ከዋላ እስከነ ዘመን ወዕድሜ፣ ለመለኮትከ ዘአልቦ ፍጻሜ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላከ ሱላሜ፤ አመጣጥህ በኋለኛው ዘመን የሆነ ለአገዛዝህ ፍጻሜ የሌለህ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር አምላክ ነህ›› በማለት እንደተናገረው ለዘመኑ ፍጻሜ የሌለው የፍቅር አምላክ ፈጣሪያችን ዳግመኛ ይመጣል፡፡ (ስብሐተ ፍቁር) ሐዋርው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹‹ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋው ቃል አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል›› ብሎናልና፡፡ (፪ኛ ጴጥ.፫፥፱) ጌታ ስለ ተስፋው ቃል አይዘገይምና ሕይወታችንን በንስሐ አንጽተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ተዘጋጅተን ልንጠብቀው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ‹‹…ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን…›› ከሚላቸው ወገን ይደምረን! ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን!!! ርኆተ ሰማይ ይህች ዕለት ርኆተ ሰማይ (የሰማይ መስኮቶች የሚከፈቱባት)፣ ሊቃውንቱ የሰማይ ደጆች ተከፍተው የምእመናን ጸሎት የሚያርጉበት በዓመት አራት ጊዜያት እንዳሉ ይገልጻል፤ ታዲያ የመጀመሪያው ዕለት ጳጉሜን ሦስት ቀን በመሆኑ ይህች ዕለት ርኆተ ሰማይ ትባላለች፡፡ የሰማይ መስኮቶች ተከፍተው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የምእመናንን ጸሎት ለእግዚአብሔር የሚያሳርግበት ዕለትም መታሰቢያ ነው፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ደጆች የሚከፈቱባት ዕለት መታሰቢያ ናት ርኆተ ሰማይ ! አባቶችና እናቶች በትውፊት በዚህች ዕለት ዝናም ሲዘንብ በእምነት የቤታቸውን ዕቃ (ሌማቱን፣የቡሆዕቃ…) ከሰማይ በሚወርደው ዝናመ ምሕረት እንዲባረክላቸው ከውጭ አውጥተው ያስመቱታል፤ ምእመናን በዚህች ዕለት በሚዘንብ ዝናብ ይጠመቁበታል፤ በርኆተ ሰማይም በጳጉሜን ሦስት ቀን!!! የኦሪቱ ሊቀ ካህን የመልከጼዴቅ መታሰቢያ በዚህች ዕለት የጌታችን ምሳሌ የሆነው የኦሪቱ ሊቀ ካህን የመልከጼዴቅ መታሰቢያ ነው፤ መልከ ጼዲቅ ማለት ንጉሠ ጽድቅ ንጉሠ ሰላም ማለት ነው፡፡ ከተማዋም በእርሱ ኢየሩሳሌም/የሰላም ከተማ /ተብላለች፡፡ መልከ ጼዲቅ የእስራኤል እምብርት /ዋና ከተማ/ ኢየሩሳሌምን ያቀና ከካም ወገን የሆኑት የኖኅ የልጅ ልጅ ነው፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለኖኅና ለልጁ ለሴም ከካም ወገን የተለየ የተባረከ ልጅ እንደሚወለድና አጽመ አዳምን ይጠብቅ ዘንድ የተመረጠ መሆኑን ነግሮት ስለነበር ሴም በታዘዘው መሠረት ወደ ማዕከለ ምድር ቀራንዮ ወስዶ አጽመ አዳምን እንዲጠብቅ በእግዚአብሔር የተመረጠ መሆኑን ነግሮት በክህነቱ መፈጸም ስለሚገባው/በኑሮው ስለሚገልጠው/ ሥርዐት ሠርቶለታል፡፡ በክህነቱ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ እንዲያመሰግን የእንስሳት መሥዋዕት እንዳይሠዋ መሥዋዕቱ ንጹሕ ስንዴና ወይን እንዲሆን በእጁም ደም እንዳያፈስ ነግሮታል፡፡

Open in Telegram
Views836−29%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#5646Link preview

ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል" የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?! ዲያቆን አቤል ካሣሁን https://t.me/menfesawe12

Open in Telegram
Views945−19%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5639Text
Views880−25%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—