እዚሁ አካባቢ በነጋ ቁጥር ዉስጤ ሰላም በላቸው እያለ የሚገፋፋኝ፣ እንዲሁ ብቻ ሁኔታቸው ሁሉ የሚጠራኝ ሷሒቦች አሉ። ስለለሰው ማሰብና መጨነቅ፣ በሙእሚን ልብ ዉስጥ ደስታን ማስረጽ፣ መልካም ጓደኝነት እና አብሮ የመዝለቅ ታማኝነት ... ለሌሎች የምትሰጣቸው ነገሮች ናቸው። ትሰጣለህ ምላሹን አትጠብቅም። እነኚህን ባህርያት ህሊናህ ዕረፍት ያገኝባቸዋል፣ አላህም ይወዳቸዋል። ዉዴታ እስከጀነት እንዲሉ። እናመልከው እና እንዋደድበት ዘንድ አዲስ ቀን ለሠጠን አላህ ምስጋና ይሁን። ሰባሐል ኸይር አሕባብ ❤️። https://t.me/MuhammedSeidAbx
Open in Telegram
ABX
ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 16, 2026 | 2,920 |
| Nov 17, 2026 | 2,860 |
| Nov 18, 2026 | 3,093 |
| Nov 19, 2026 | 2,970 |
| Nov 20, 2026 | 3,057 |
| Nov 23, 2026 | 1,845 |
| Nov 25, 2026 | 1,480 |
| Nov 26, 2026 | 970 |
Most viewed this month
- 01Views3.39KForwards—Reactions98Comments—
- 02Views3.12KForwards—Reactions101Comments—
- 03Views3.07KForwards—Reactions106Comments—
- 04Views3.05KForwards—Reactions142Comments—
Latest posts
ሶብር ... **** የዱንያ ሐያታችን እርከኖቿ ሁሉ በፈተና የተሞላ ነው። ከአንዱ ሲወጡ ሌላው ይከተላል፣ አንዱን ሲያልፉ ሌላኛው ይደቀናል ፣ እነኚህን ፈተናዎች ለማለፍ ሶብር ግድ ይላል። ወዳጆች ሆይ .. በየፈተናው ላይ ሁሉ ለማለፍ ታገሉ እንጂ እህህ ... እያላችሁ ህመማችሁን አታባብሱ። ትዕግስት ትልቅ ዒባዳ ነው። ምንዳዉም የትየሌሌ ነው። ዱንያ ላይ እስካለን ድረስ ... * ምክንያቱንም ሆነ መፍትሄዉን በማናውቀው መከራ ላይ እንታገሳለን፣ * ዱዓችን ተሰሚነት የሚያገኘው መቼ እንደሆነ ሳናውቅ እንታገሳለን፣ * በበሽታ፣ በኪሳራ፣ በወዳጅ ሞት ...እንታገሳለን፣ * አብሮት መኖሩ አስቸጋሪ በሆነ ሰው ላይ እንታገሳለን፣ * በየእለት የኑሮ ፈተና ላይ እንታገሳለን። አውቃለሁ ... መታገስ ቃሉ ራሱ ከባድ ነው፣ ምርጫዉም አስቸጋሪ ነው። ከባድ በመሆኑም ነው አላህ "وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ / ታጋሾችን አብስር" የሚለው። አላህ ሆይ በትዕግስታችን ልክ ደስታችንንም አብዛው። https://t.me/MuhammedSeidAbx
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 22 h | 1,290 |
| 26 h | 1,400 |
- After 24 hours1,290
- Total to date1,400
Forwarded from Nejashi Printing Press
ሰው በሰላም ከዋለ ሰላም ማደርን ይመኛል። በሰላም ካደረም ለጌታው ምስጋና አድርሶ ለዕለት ጉርሱ ሥራ ያስባል፣ ሪዝቅ ፍለጋ ያማትራል። ኢስላም የሥራ ሃይማኖት ነውና ሠራተኛን ያበረታታል፣ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) በጠዋት ማለደው ለሚንቀሳቀሱ የሥራ ሰዎች “አላህ ሆይ ለህዝቦቼ ማለዳቸውን ባርክላቸው፡፡” ብለው ዱዓ አድርገዋል፡፡ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆነና ሐላፊነት ያለበት ሰው የመሥራትና ሲሳይን ሸሪዓዊ ግዴታ አለበት፡፡ ይህን ግዴታ አለመወጣት ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሰው አይተው ሁኔታው ደስ ካላቸው ‹‹ሥራ አለው?›› ብለው ይጠይቃሉ፤ ‹‹የለውም›› ከተባሉ በሰውየው ደስተኛ አይሆኑም፤ ያለ ሲሆን ይህ ለምንድን እንደሆነ ተጠይቀውም ‹‹ምክንያቱም አንድ አማኝ ሥራ ከሌለው በሐይማኖቱ ለመኖር ይገደዳል፡፡›› አሉ ብሏል፡፡ ሙስሊም ለቤተሰቦቹ በሚያወጣው ገንዘብ ከአላህ ዘንድ ምንዳ ያገኝበታል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በአላህ መንገድ ላይ ወጭ ካደረግከው ዲናር፣ አለያም ባሪያን ነጻ ለማውጣት ካወጣኸው ዲናር፣ ወይም ለሚስኪን ከመፀወትከው ዲናር ሁሉ ለቤተሰብህ ወጭ ያደረግከው ዲናር ምንዳው የላቀ ነው፡፡›› ታላቁ ታቢዒና ዓሊም ሱፍያን አሥ-ሠውርይ (አላህ ይዘንላቸው) ፡ ‹‹የጀግኖች ተግባር የሆነውን ሐላል መሥራትና ቤተሰብን ማስተዳደር ጠንክረህ ያዝ፡፡›› ብለዋል፡፡ አንድ ሰው እርሳቸው ዘንድ ዕውቀት ለመማር ሲመጣ መተዳደሪያ እንዳለውና እንደሌለው ይጠይቁትና አለኝ ካላቸው እንዲማር ያዙታል፤ የለኝም ካለቸው ደግሞ ሥራ እንዲፈልግና እንዲሠራ ያዙት ነበር፡፡ አቡ አሲኽቲያኒይ አቡ ቂላባ ‹‹ሱቅህን አጥብቀህ ያዝ፤ እርሷ የሰውን እጅ ከማየት ታድንሃለች፤ ለዲንም ትረዳሃላች፡፡›› በማለት መከረኝ ብሏል፡፡ መልካም የሥራና የሲሳይ ቀን ይሁንልን። ከሪዝቅ መጽሐፍ የተወሰደ ትርጉም ፡ ጁነይድ ዐብዱልመናን መጽሐፏ ልዩ ልዩ የሪዝቅ ማግኛ መንገዶችንም ትጠቁማለች። ነጀሺ የዕውቀት ማዕድ https://nejashibooks.com/ https://t.me/Nejashipp
Open in Telegramበራቅን ቁጥር ወደርሱ ለመመለስ እንጂ በወደቅን ቁጥር ከርሱ ተስፋ ለመቁረጥ አይደለም የተፈጠርነው። አዲስ ቀን በተሠጠን ቁጥር የትናንቱን ስህተታችንን ዛሬ ለማረም ዕድሉ አለን። ሰባሐል ኸይር ወዳጆች ሰላም አደራችሁ ወይ https://t.me/MuhammedSeidAbx
Open in Telegramብቻዬን ፈገግ ከሚያሠኙኝ ንግግሮች ውስጥ ... አንድ ቀን ከባለቤቴ ጋር ፍሪጅ ልንገዛ ፒያሳ ሄደን አንዱን ከመረጥን በኋላ "ቁልፍ የለውም እንዴ!" አልኩት እኔ ለሻጩ። ሻጩም ቀና ብሎ አየኝና "ምግብ ላይ እንዴት ይዘጋል? " አለኝ። ሀሳብ ስጡበት እስቲ። አሁን ፍሪጅ ሳይ ትዝ ብሎኝ ነው። መሳአል ኸይር https://t.me/MuhammedSeidAbx
Open in Telegramሰላም ለነዚያ በአላህ ዲን ላይ ለዓመታት በፅናታቸው ለዘለቁ፣ ሰላም ለነዚያ ትልቅ ትንሽ፣ አዋቂ ጃሂል ሳይባል ሰዎች ሁሉ ሐራምን እየተላመዱ መጥተው ሐራም ውስጥ ሲዘፈቁ፣ ዛሬም በተለያዩ ፈተናዎች ላልተፈቱና ላልተበገሩ፡፡ አላህ አብዝቶ ይካሳቸው!! እንዴት እንደምቀናባቸው እኮ!! አላህ ሆይ አጽናን!! https://t.me/MuhammedSeidAbx
Open in TelegramConnections
Similar channels
Nejashi Printing Press@nejashippReligion4.58K
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ@abizeeotcReligion11.5K
#KALTUBE@kaltubeReligion11.8K
አስ-ሱናህ ቴቪ | As-Sunnah TV@assunnahtvofficialReligion10.7K
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC@egbccReligion12.2K
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸@hamdquanteReligion12.2K
ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል@dania_islamicReligion10.3K
እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net@ewnetlehuluReligion10.2K
Mentions
Nejashi Printing Press@nejashipp1 mention