Account
ከመጽሐፍት መንደር💠

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @Gesam12 & @zeeddr

Username
@manbabemulusewyaderegal
Category
Books
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers4,930
Avg views per post, 7d378−39.2% vs prev 7d
ERR7.67%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 14, 2026528
Nov 15, 2026578
Nov 16, 2026745
Nov 17, 2026569
Nov 19, 2026610
Nov 21, 2026495
Nov 22, 2026404
Nov 23, 2026397
Nov 25, 2026284

Most viewed this month

  1. 01

    አብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ። ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገር ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ። አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ። ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣  ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ። " ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?" "እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?" ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ  በመራቅ  ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ። አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ "ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ። "ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም። ቃልዬ ቀጠለች •••• "እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች "ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ  ሴት ጋር  ያለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት። ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ  ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት  ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር  ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ። እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ  ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር። ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር።  መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ። በቃ ታረቅን።  እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ።  ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር። አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ። " ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣  ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው  ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ። መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት።  ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ። ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም። "ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች። እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ። አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ  ታመምኩ  ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ። ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና "ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት። ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቁልቁል ወረደ። ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን  ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ••• "ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ። ፊቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች። ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር  ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት። እሷም እህቴ ነች። የምኖረው ለኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር። የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ። ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን  ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም። ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው። "ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ብትንትኑ ወጣ።ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም። ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ። ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት  በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ  እየጠበኩ ነው። መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ  ልጅ እግር  በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ።  አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና••• "እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት። ወረቀቱ ላይ የተፃፈው  •••• "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም" የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ።           ✨ተፈፀመ✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

    Text
    Views844
    Forwards—
    Reactions18
    Comments—
  2. 02
    Views785
    Forwards—
    Reactions1
    Comments—
  3. 03
    Views715
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    ማስጠንቀቂያውን አብዝተው አስተላልፈው ወደነ ሲፈን ተመለሱ:: ማነው የላከብኝ? ማን.. ማን....... ======= የጠዋት ፀሐይ ከወደ ምስራቅ ብቅ እያለች ነው ፡ሰውም የተለመደ ስራውን ለማከናወን ነቃ ነቃ እያለ ነው ፡እትዬ ፅጌም በላስቲክ ቆሻሻ ይዘው ወደገንዳው በመድፋት ወደቤታቸው  ያገኙት የጎረቤት ሰው ደና አደራቹ እያሉ ሰላምታ እየሰጡ ተመለሱ ፡ወደ ውስጥም በመግባት "ኤዶም ኤዶሜ አንተ ተነስ አስኪ ይበቃል ወንድምህንም ቀስቅሰው፡!"እያሉ ተጣሩ ከመንትያ ልጃቸው አንዱን "እእ እሺ እማ እየተነሳው ነው "አለ ኤዶም እትዬ ፅጌ እጃቸውን እየተጣጠቡ ያ እብድ ወንድምህ ምነው ዛሬ እንቅልፋም ሆነ!"አሉት ኤዶም መጥቶ ከፊታቸው ሲቆም "አይ አይ እማዬ አዳም ትላንት ወደ አምስት ሰአት አካባቢ እነ ብሩክ እየጠበቁኝ ነው ብሎ ላንቺ እንዳል ነግርሽ አስጠንቅቆኝ ነው የወጣው ስገምት ብሩክ ጋር ነው ያደረው "አለ ኤዶም  "ኧረ እንዴት በል ደውልለት ከሆነም " እሺ ብሎ ሞባይሉን አንስቶ ደወለ ፡ብሩክ አንስቶ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ "አዳም አነተጋር ነኝ ብሎነበር ?" "ኧረ በጭራሽ አላገኘውትም" "እውነት" "አዎ እኔጋር አልመጣም" "እሺ ብሩክ ደናዋል"ብሎ ዘጋው ወደናቱ ተመለከተ፡እናት ተጨነቀች "ለምንድነው በራሱ ስልክ የማትደውለው " "አይሰራም"አለ ኤዶም ፍርሃት ፍርሃት እያለው "ልጄ የፈለገ ቢያመሽ አድሮ አያውቅም አባትህ ጋር ደውል!" "አባባ ወጥቷል እንዴ?ግን እማዬ ይቅር ይደነግጣል ትንሽ እንጠብቅ !"አለ ኤዶም፡ እትዬ ፅጌ ተረበሹ መንትያው የት ነው አዳም የት ነው ያደረው እንዴት በለሊት ወጣ.. የት ነው መንትያው?...እትዬ ፅጌ ግራ ግብት ብሏቸዋል ፡አንዴ ይቆማሉ አንዴ ይቀመጣሉ፡ይወጣሉ ይገባሉ፡መላ አተዋል ፡'የት ገባ ይባላል !በጨለማ ሲጓዝ አንዱ ደፍቶብኝ ይሆን !እንደው ምን አድርገውት ይሆን፡እንዴት በጤናው አድሮም ቀኑን ሙሉ ሳይመጣ ይቀራል፡አንዳች ነገርማ አለ!'እያሉ በጭንቀት ያምሰለስላሉ ፡ኤዶም ቆይቷል ከቤት ከወጣ ወንድሙን ፍለጋ ፡የአዳም ጓደኞችን ሁሉ ካሉበት ድረስ እየሄደ ፡ጠይቋል ግን አንዳቸውም አየነው አላሉትም፡ ኤዶም ገራገር ቢጤ ነው፡ በዛላይ ብዙም ከሰው ጋር አይቀርብም፡ ትንሽ ትንሽም አይናፋርነት አለችበት፡ ከወንድሙ አዳም አንፃር፡ተቃራኒ ነው፡ አዳም ሁሌም ሊያበሳጨው ሲፈልግ፡ 'አንተ ጅል፡እኔና አንተ አንድ ቦታ መሰራታችንን እጠራጠራለው፡መልክህ እኔን ከመምሰሉ ውጪ በጭራሽ ውስጣዊ አሰራራችን ይለያያል!'ይለዋል ፡ኤዶም ለሱ መልስ ሳይሰጥ 'እማዬ አየሺው እንዴት እንደሚናገረኝ ይሄ ስረሃት አልባ ልጅሽ፡አንቺ ነሽ እያቀበጥሽ ፡እንደፈለገ እንዲሆን የምታደርጊው፡ አፉን አዘጊልኝ አለበለዚያ ...!'ይላል ወደ እናቱ እያየ አዳም በማልመጥ እያሽካካ'ኧረ ሼባው አልቀረቦትም ልታስፈራራኝም ያምርሃል !' ይለዋል ፡ኤዶም እንዲም ሆኖ ግን፡መንትያውን ከልቡ ነው የሚወደው፡ ለዛም ነው፡ብዙ ችግሮቹን የሚሸፍንለት ፡ሲመሻሽ ተነስቶ መውጣቱን ከቅርብጊዜ ወዲ የተለመደ ቢያደርገውም፡ ኤዶም ጨርሶ ለወላጆቹ ነግሮ አያውቅም፡ሊነጋጋ ሲል ሲመጣ፡ቀስብሎ በር ከፍቶ ያስገባዋል፡ ዛሬግን አዳም አልመጣም፡ ስልኩ እንኳ ዝግ ነው፡ኤዶም የት ብሎ እንደሚፈልገው ግራ ገባው እሱ የሚውልበት አይውል፡ እንዲው ቢጨንቀው መንገድ ለመንገድ ሲዞር ውሎ ወደቤቱ ተመለሰ ፡እትዬ ፅጌ ኤዶም ሲገባ ብድግ ብለው ቆሙ "ኤዶሜ ምንም አላገኘህም!አየው የሚል ጠፋ ልጄን? ነው የደበከኝ ነገር አለ እባክህ !" ብለው አስጨነቁት "እባክሽ ፅግዬ፡ልጄን አታስጨንቂው፡ኤዶም አዳም ከሚውልበት አይውል፡ደሞስ አንድ ቀን ቀረ ብለሽ፡ምን እንዳይሆን ነው ወንድ ልጅ አደል እንዴ፡እስኪ ተረጋግተን እንጠብቅ!" አሉ የመንትዮቹ አባት አቶ አይሉ "አንተ ዝም በለኝ መጥተህ አንድ መፍትሔ ታመጣለህ እላለው እዚ ተጎልተህ ምን እንዳይሆን ነው ትላለህ እሬሳውን እስኪሰጡኝ ነው የምጠብቀው !" "እባክሽ ፅጌ ተይ ካልሆነ ካልሆነ ነገ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ አመለክታለው!"አሉ አቶ አይሉ ለሚስታቸው እየተጠነቀቁ፡ "ኧረ እንዴት ልሁነው ልቤ አንዳች ነገር እንዳለ ነው የሚነግረኝ"አሉ እናት ሆዳቸውን ጭምቅ እያደረጉ፡ኤዶም በናቱ ሁኔታ አዘነ ሄዶ አቀፋቸው"እማ ይመጣል አይዞሽ ፈጣሪ ያውቃል !"አለ ፡ግን ይህን ይበል እንጂ ውስጡ ፈርቷል፡ይሄ በድብቅ በለሊት የመውጣቱ አባዜ፡አንድ ቀን ችግር እንደሚያመጣ ጠርጥሮ ነበር፡ በራሱ አዘነ ይህን ሁኔታ ለወላጆቹ ነገሮ ማስቆም ነበረበት፡የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው፡እራሱንወቀሰ የኔ ስህተት ነው፡አለ፡ኤዶም "እንደው አይልዬ ለምን አሁኑኑ ከኤዶሜ ጋር ፖሊስ ጣቢያ ሄዳቹ አታመለክቱም?!" አሉ እናት "አይ ፅግዬ እነሱም እኮ አካሄድ ይኖራቸዋል ዛሬን አድረን ነገ ሁኔታውን አይተን ይሻላል እሺ በይኝ ፅግዬ እናቴ!"አሉ አቶ አይሉ ሚስታቸውን በፍቅርና በጨንቀት እያባበሉ ሚስት ባይዋጥላቸውም እሺ አሉ ፡እናም እጥፍጥፍ ብለው ዱካ ወንበር ላይ ተቀመጡ ፡ልጄ እምን ውስጥ ገብተህ ይሆን ...ልጄ.....አዬ ጉዴ ....ብቻ ክፉ ነገር አታሰማኝ... ፈጣሪዬ ....ፈጣሪዬ.......እህህህ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

    Text
    Views655
    Forwards—
    Reactions6
    Comments—

Latest posts

#12100Text

​​"ኧረ እውነቴን ነው በጓሮ አንድ ሰው ልክ እንደሰረቀሰው እየተጣደፈ ሲወጣ አይቼ ነው !"አለ መንገደኛው "ምምን አይነት ሰው ?!"ሲፈን ሰውዬውን በድንጋጤ በጥያቄ አፋጠጠችው "ኧረ ጎልማሳቢጤ ነው ሰውነቱ ደልደል ያለነው ጥቁር ፀጉሩ መለጥ ያለ!"አለ መንገደኛው ሰውዬውን ለመግለፅ እየሞከረ ፡ "በበየት በበኩል ነው ያያልከው?ወዴት ሄሄደ ?"ሲፈን ክንዴ ነው አለች በውስጧ ፡ወዲያው እነሱን ትታ እየከነፈች ወደጓሮው በር እሮጠች፡ ስትደርስ በጥድ የተሸፋፈነው በር እንደነበር ነው ወደዚ ከመጣች በጣም ብዙ ጊዜ ሆኗታል ምንስ ፍለጋ ትመጣለች ፡ሲፈን በሩን ገፋ ገፋ አደረገችው ብዙ አላስቸገራትም ወደውስጥ እየፈራች ገባች ሰውነቷ ሽብር ብሎባታል፡የመጋዘኑን ዙሪያ ቃኘች፡ አንዳች ነገር ተዘርሮ ያየች መሰላት፡ጨነቃት አፏ ደረቀ ለማረጋገጥ እየቀረበች እየቀረበች ሄደች ፡ሰው ነው በድንጋጤ አፋን ከፍታ ቀረች፡ባለጭንብሉ በፀጥታ ተዘርሯል፡ ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ ቀዝቃዛ ላብ ከወደጀርባዋ ሲወርድ ተሰማት፡ ወደዋላዋ አፈገፈገች ሲሳይ ደርሶ ያዛት ፡ከዛም እሱም የወደቀውን ሰው አይቶ በድንጋጤ ክው ብሎ ወደሷ መልሶ በጥያቄ አስተዋላት ሲፈን ከሩቅ የሚመጣ ድምፅ በሚመስል "ሞቶሃል "አለች ሲሳይ ለቋት እየተንቀጠቀጠ ወደ ወጣቱ በመጠጋት ፊቱላይ ያለውን የሹራብ ጭንብል በማንሳት ትንፋሹን ለማዳመጥ ሞከረ ግራ ገባው መልሶ ወደአንገቱ አካባቢ እጁን ሰደደ "ሕይወቱ አላለፈም አአለ ግግን መመፍጠን አአለብን ሐኪም ቤት መመሄድ አለበት!"አለ ሲሳይ ዘበኛው ሲፈን እንደባነነ ሰው ሆነች "እእውነት በበምን አወክ ?!" "ትንሽ ጊዜ ወወታደር ቤት የቀሰምኳት ትምርት አለችኝ አሁን እሱ አደለም ዋናው ነገር መኪናሽን ይዘሻት ነይና ሐኪም ቤት እንውሰደው!"ሲፈን ደመነፍሷን እሮጠች መንገደኛው አካባቢው ሄዷል ጭር ብሏል መኪናዋን በፍጥነት ማንም ሳያያት አስነስታ መጣች እቤትም ገና አልተሰበሰቡም ጥሩ አጋጣሚ ሆነላት፡ ሲሳይ የተሰባበረውንና በደም የተጨማለቀውን የወጣቱን የከሳ ሰውነት ተሸክሞ መኪናውስጥ ማንም ሳያየው በጥንቃቄ አስገብቶ አስቀመጠው እናም ተከትሎ ሊገባ ሲል "ቆይ ሲሳይ ይህን ጉዳይ በኔና አንተ ብቻ መሃል እንድንይዘው እፈልጋለው ማንም መስማት የለበትም አስታውስ የቤተሰቡ አካልም ሆነ ሌላ ማንም አደራ ይሄን የማደርገው ልጁን ለማዳን ነው፡ባለውለታዬ ነህ አደራ ስለዚህ አንተ ከግቢው መራቅ የለብህም ምንም እንዳልተፈጠረ ሁን አደራ እሱን ለኔ ተውልኝ ስለሁኔታው በሚስጥር አሳውቅሃለው !"ብላ ሲፈን ማረጋገጫ ሳጠብቅ የሰው ሕይወት ለማዳን መኪናዋን ይዛ ተፈተለከች ፡ብርርርርርርር ቢቢቢቢቢቢቢ ፍጥነት ሲፈን የባለ ጭንብሉ ሕይወት አደጋ ላይ ነው አባባ ....አባባ...ምንድነው ያደረከው.....ክንዴዴዴዴ...አባባባ======== ቤቱ በጠያቂ ተሞልቷል ሰው ሁሉ የየራሱን ግምት ይሰጣል አንዱ የአንዱን አሳብ ያፈርሳል አንዱ በአንዱ አሳብ ይስማማል በዛውም የራሱንም ግምት ይሰጣል አንዳንዱ ለማውራት ብቻ ብሎ እንደው እንደነገሩም አሳቡን የሚሰነዝርም አለ ብቻ የነ ኤዶም ቤት  ሰሞኑን  በትዬ ፅጌ ለቅሶ በመደናገጥ የሚሰበሰብ ሰው አላጣውም በቀን በማታ ልክ እንደ ሐዘን ቤት እንዴት ሆነ መልካም ዜና አለ አሁንም አልተገኘም ፖሊሶቹ ምን አሉ  ምን ይሻላል አንዱ ጋር ገለው ጥለውት ይሆን ?የሴጣን ጆሮ ይደፈን ከአገር ወጥቶ ይሆን እንዴት አንድ መልእክት ሳይተው? አዬ እንደ እናት ጡት ሁለት ብቻ ሆነው ተፈጥረው አሄሄሄሄ በመሃል እትዬ ፅጌ ለቅሶ ይጀምራሉ ልጄ ልጄ እንደወጣህ ቅርት አልከው ኧረ ምን አየብኝ !ኧረ ወዴት ልፈልገው! ኧረ ምን ውስጥ አሰመጡህ ልጄ ልጄን አስራምስት ቀን ሙሉ ምንዋጠው ይባላል በሉ የበላው ጅብ አልጮህ አለ ኧረ እናንተው ምን ይሻለኛል እያሉ ያነቡታል ኤዶም የናቱን ድምፅ በሰማ ቁጥር እንባውን መቆጣጠር ያቅተዋል ወይኔ ወንድሜ ወይኔ የት ይሆን ያለኽው ከየት ላምጣህ ይላል በጭንቀት አባት ይሄ ነገር እንደቀልድ እውን ሆነ እንዴ ኧረ ዋ አዳም ምን አገኘብኝ እያሉ ያምሰለስላሉ በአዳም መጥፋት ቤተሰብ ሰፈር ጎረቤቱ ሁሉ ተጨንቆ ነው የሰነበተው....   ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

Open in Telegram
Views309−44%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#12099Text

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ ክንዴ ብረቱን መሬት ላይ በመጣል ቁና ቁና እየተነፈሰ ቁልቁል ወጣቱን እየተመለከተ  እንቅስቃሴውን መጠባበቅ ጀመረ ድንገት የተፈጠረ የንዴት ስሜቱ እስኪበርድለት ትንሽ ጊዜ ወሰደበት እንዴት  በልኩ በጄ ብቻ ጎሸም ባደረኩ ባዋራውት ሌባ መሆኑን እረስቶ ጭራሽ ከውሻ ይደምረኝ፡ይሄ ወፍ ዘራሽ እንዲህ ነውና ክንዴ ይሄ መደዴ አመዳም የማን አባቱ ወናፍ ነው በሉ የታባቱ ገና ልክህን ነው ማሳይህ ዱላ ቁርስ ምሳ እራትህ ያላደረኩልህ እንደው፡እኔ ክንዴ አይደለውም እያለ ዛተ ከዛም ብረቱን መልሶ አነሳው  ወደ ባለጭንብሉ እግር በመክተት ቆስ ቆስ አደረገው  እንቅስቃሴ የለም ወደ ሆዱ አካባቢ ነካካው የለም ክንዴ ደነገጠ ብረቱን ጣለው በርከክ ብሎ የባለጭንብሉን ፊት ከቀኝ ወደ ግራ ወዘወዘው ፀጥ እረጭ ብሏል ክንዴ ልቡ ክፉኛ በድንጋጤ መምታት ጀመረ "አንተ ጭንብሌ አንተ !ንቃ ጭንብሌ !ኧረ ወይኔ ክንዴ !ኧረ ዋይ ጉድ ሆንኩ እንዴ !ስማማ ውሃ ውውሃ ተትፈልጋለህ! ጭንብሌ !ጭንብሌ!ጭንብሌ!ወይኔ ክንዴ ጉድ ፈላብህ ኧረ ኧረ ......." ክንዴ ሳያስበው መጮህ ጀመረ ፡ድንገት የሚመጣውን ችግር አስቦ አፉን ዘጋ ተርበተበተ ፡ቀጥ ብሎ ቆመ ግራ ተጋባ ወዴት ልሂድ ወዴት፡ለማን ልንገር፡ለአቶ ይፍሩ ልደውል፡ኧረ በጭራሽ ጠብቅ እንጂ ግደል አላሉኝ ኧረ እኔንም ያጠፉኛል ምላድርግ የሰውሰው በጄ ጠፍቷል የሰማዩም ይቅር አይለኝ እጄን ልስጥ እንዴ ክንዴ መጋዘን ውስጥ ተሽከረከረ እንዴት ብሎ ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት እንዳለበት ግራ ገባው በመጨረሻ ፡ማምለጥ እንዳለበት ወሰነ ፡እናም በጎኑ የተኛውን  ወጣት ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው፡ የሹራብ ጭንብሉን ከወደቀበት በማንሳት ወደወጣቱ ቀረብ ብሎ ፊቱን ሸፈነለትና "ይቅር በለኝ !"ብሎ ዕንባ ዕንባ እያለው በጓሮ በር በኩል፡ ወጥቶ ሄደ ....ክንዴ ሄደ....ከራሱ ጋር እያወራ ሄደ ሄደ..... ======= አቶ የሱፍ ከልጃቸው ጋር ፡በሱቃቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ ወሬ አቸው ሁሉ ምክር አዘል ነው ያቶ የሱፍ፡ መግባራቸው ጥሩ ካልሆኑ ልጆች ጋር አትዋል ሁሌ ልጅነት የለም አንተነህ የኔ ንብረት ወራሽ ሌላ ማን አለኝ የመጀመሪያ ልጄ ነህ እኔ አንድ ነገር ቢገጥመኝ እናትህን እህቶችህን ጭምር አንተነህ የምትመራው፡ እኔ የምትቀርባቸው ልጆች ብዙም ደስ አይሉኝ ፡በተለይ ጀማል ከጥሩ ልጆች ጋር አላየውም እንደው አባቱ የተከበረ ሰው ነው ልጁን ግን ቀልቤ አይወደውም ፡ ምናምን ምናምን ፡አብዲ በሆዱ ይህ ምክር ግልባጭ ላንተ ቢደርስልኝ የተከበርከው አባቴ ከኔ ይልቅ ለራስህ ስነ መግባር በተጠነቀቅክ ብቻ አንተ በምትሰራው እገወጥ ስራ ወደፊት ምን እንደሚደርሰን ሳስበው፡ ይጨንቀኛል እንደው አባባ ምን ስትል ነው እነዛን እገወጦች ጓደኛ ያደረከው አንተ እራስህ አላህ እማይወደውን ስራ እየሰራህ እኔን መምከርህ ከነ ጓደኞችህ ወንጀለኛ ነህ አባባ  ይላል አብዲ "አብዱ እንደው ባለፈው መጋዘን ስለገቡት እቃዎች ከሰዎች ጋር አውርተህ ነበር ?"አሉ አቶ የሱፍ በመጠራጠር "አላወራውም፡እኔ አባባ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ ስለምትሰሩት የተለያየ እገወጥ ስራ አይመለከተኝም አላህን ካልፈራቹ ቀጥሉበት እሱ ይከፍላችሃል!"አለ አብዲ የአባቱ አይን ያወጣ ንግግር እያናደደው "ምን አልክ አንተ የምን እገወጥ ነው የምትለው ፡አንተ የማትረባ ፡አቶ ይፍሩ የተከበረ ሰው ነው እድሜ ለሱ ይህን ሁሉ አብት ያፈራውት ከሱ በመሻረኬ ነው ፡ይርጋም ቢሆን!እንዴት አባክ ነው ምትናገረኝ አባትህ እኮነኝ፡ተንደላቀህ በመኖርህ ጥጋብ ፈላብህ!"አሉ አቶየሱፍ እንደመነሳት ብለው "አሁን እየጠየኩህ ያለውት መጋዘን ሄደህ አስተካክል ያልኩህ ጊዜ ከማን አባክ ጋር ነው የሄድከው ዘበኛው ጓደኛው አብሮት ነበር ብሎኛል ይዘህው ከሄድከው ልጅ ጋር በእቃው ጉዳይ ላይ አውርተሃል?!"አሉ እጃቸውን ለዱላ እንደማዘጋጀት እያሉ "ምንድነው ዛሬ ስላለፈ የመጋዘን እቃ ዛሬ የምጠየቀው አልገባኝም ችግር አለ ፡እገወጥ እና ጊዜው ያለፈበት መሆኑ ታወቀ ፡ምንድነው፡ስለሱ ይህን ያህል፡ ሌላ ብዙ ስራ ነበራቹ ለምን ስለሱ ብቻ!?"ቱግ አለ አብዲ "አፈር ብላ ማንን ነው ይዘህ የሄድከው የዛኔ!"በጥፊ አላሱት "ከ አዳም ጋር ነው የሄድኩት !" አለ አብዲ በንዴት "ማን አባክ ነው አዳም!" "እታች ሰፈር ያለው !" "ማነው እሱ እታች ሰፈር ስንት ሰው አለ የማን ልጅ ነው!?" "ምንድነው ከመጋዘን የጠፋ እቃ አለ እንዴ እንዳለ አደል እንዴ ወዲያው የተሸጠው ፡ድርሻችሁን ተካፍላችዋል ምንድነው ፡የምትለኝ ፡እሱ አብሮኝ ሄደ እንጂ ምንም የሚያውቀው ጉዳይ የለም፡ ችግር ስላለባቹ ያገኛችሁትን ከመጠርጠር ወደዋላ አትሉም!"አለ አብዲ በቁጭት "አንተ አህያ የጠየኩህን መልስ!ማነው አዳም?!" "የአቶ ሀይሉ ልጅ !" "ሀይሉ ሀይሉ"አሉ አቶ የሱፍ ለማስታወስ እየሞከሩ "ሀይሉ የወይዘሮ ፅጌ ባለቤት!በቃ የትዬ ፅጌልጅ ከመንታዎቹ አንዱ ነው በጣም ጥሩ ስነ መግባር አላቸው ስትለኝ ነበር እንግዲ ባንተ አሳብ መሰረት ከነጀማል ጋር ትቼ ከመንትዮቹ ጋር ጓደኛ ሆኛለው አሁን ደስ አለህ!?"በትህቢት እና በንቀት አባቱን እያየ ተነፈሰ አብዲ "በአላህ አንተ ምን እያልክ ነው ?! "አሉ አቶ የሱፍ "በቃ እንደዛ ነው እንደውም ሰሞኑን አዳም ጠፍቶ እየፈለግነው ነው የሰነበት ነው፡ እንኳን ስለናንተ መጋዘን ቁብ ሊኖረው ቀርቶ!"አለ አብዲ የአባቱ ባልሆነ ነገር እራሳቸውን ችግር ውስጥ ማስገባታቸው እያሳመመው 'እባክህ አባቴን ከገባበት ችግር አውጣው ፈጣሪዬ አቶ የሱፍ በሰሙት ነገር ክፉኛ ደነገጡ ያ አላህ ይፍሩ አሰርኩ የሚለው ልጅ አዳም እንዳይሆን ብቻ ኧረ ጉድ ሆኛለው አብዲ አብዲ ምን አይነት የልጅ ክፉ ሰጠኽኝ በቃ ስለኛ ጓደኛ አገኘው ብሎ ልጄ ያለውን ነገር እንዳለ ዘርግፎለታል ማለት ነው ወይ ጉዴ ባለ ጭንብሉ አዳም ከሆነ ይፍሩ ለኔም አይተኛልኝ ሆነ ብዬ እንዳደረኩት ነው የሚሰማው ጉድ ፈላብኝ ፡ግን ጥርጣሬ እንጂ ላይሆንም ይችላል"ምነው አባ የፈራህ ትመስላለህ አዳም እኮ ዱርዬ አይደለም እንዴ ምንድነው ይሄን ያህል!" አለ አብዲ ቢናደድባቸውም ትካዜአቸው አሳስቦት ፡፡አቶ የሱፍ ጥሩ ስሜት አልተሰማቸውም ወደወንበራቸው ተመልሰው ሽብሽብ እንደማለት ብለው ተቀመጡ ስቅቅ ጭንቅ ጭንቅንቅ አሉ አቶ የሱፍ ፍርሃት ...ፍርሃት.....ፍርሃት...... =========                            አዲሱ ዘበኛ መንገደኛው ሰው የነገረውን ወሬ ተከትሎ የግቢውን አጥር ዞረው ምንም አይነት ፍንጭ ማግኘት አልቻለም ፡ምኑ ሰካራም ነው እያለ ወደቦታው ተመለሰ ሲመለስ ሰውዬውን የጊቢው በር አካባቢ እንደቆመ አየው ኧረረረ ምን አባቱ ነው እኔን አዘናግቶ ወደውስጥ ለመግባት ይሆን እንዴ አላማው !አለመጠርጠሬ  ብሎ ዱላውን እያስተካከለ ተጠጋው "አሃ ምን አስበህ ነው በል ዱላህን ሰብሰብ አድርገው እኔ የረዳውህ መስሎኝ እንጂ !"አለው መንገደኛው እንደመሽሽ እያለ "ምን ትረዳኛለህ ዘዴ መፍጠርህ ነው ባንተቤት ዞርበል ከዚ እወርድብሃለው !"አለ ዘበኛው እየጮኽበት በዚ መሃል ሲፈን መጣች በጣም ተደናገጠች የሰሞኑ ሁኔታ እያስፈራራት ነው ያለው ይሄ ሲጨመር ቀጥታ አያያዘችው፡ እናም ወደዘበኛው እጇን እያወናጨፈች እንዳያደርገው አስጠነቀቀች "ምንድነው ሲሳይ ምነካህ ችግር አለ?!"ጠየቀች ሲፈን ሰውዬውን እየተከላከለችለት "ኧረ በጓሮ ሰው ሲወጣ አየው ብሎ ሊያዘናጋኝ ሞከረ ምን እንደፈለገ አልገባኝም!"ቆጣ አለ ዘበኛው

Open in Telegram
Views258−53%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#12097Text

ተዋነይ ዘጎንጅ ተዋነይ ሀገሩ ጎጃም ይልማና ወረዳ ቆለላ ምክትል ሲሆን የተወለደበት ደብርም ወልደን ተክለሀይማኖት እንደሚባል ተገልጿል ። እግዚአብሔር ሲፈጥረው ጥበብን ሀሉ ገልፆለታል ተዋነይ ብዙ አስደናቂ እና አስደማሚ እውነት የማይመስሉ ነገሮችን ፈፅሟል ሊቃውንቱ እንደሚናገሩትና ታሪኩ እንደሚመሰክረው በደመና ተጭኖ አለምን እስከመዞር ደርሶ ነበር ሀገሩ ጎጃም ጎንጂ ሲሆን ጎንደር በአፄ በካፋ  ጊዜ ንጉሱ ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ ተዋናይ እፀ መሰውር በመጠቀም መጦ እሳቸውም ሆነ ማንም ሳያየው ከንጉሡ ማዕድ ቀርቦ ይመገብ ነበር ታድያ ለንጉሡ የሚሰጠው ምግብ የተወሰነ ምግብ ሲሆን ተዋነይ አብሮ በሚበላበት ጊዜ ንጉሡ ሳይጠግቡ እየቀሩ ስጡኝ እንዳይሉም እየፈሩ በረሀብ ሊሞቱ ሆነ በጣም ከሱ ሰውነታቸው በጣም መነመነ ይሄን ያዩት ሊቃውንቶች እና መኳንንቶች ቀርበው በምን ምክንያት ነው ሰውነትዎ እያለቀ የሄደው አይበሉም እንዳንል ይበላሉ ታመዋል እንዳንል አልታመሙም ምንድን ነው ምክንያቱ በማለት ንጉሡን አፄ በካፋን ጠየቋቸው አፄ በካፋም ነገሩ እየገረማቸው ከጠየቋቸው ዘንድ እኔ ምግብ የምትሰጡኝ የተወሰነልኝ አላናሰኝም ነበር ነገር የሚወስደውን አላውቅም ያልቃል እኔም አልጠግብም አሉዋቸው ከዚ ብኋላ ሊቃውንትና ብዙ ጠቢባን ስለነበሯቸው ነገሩን መከታተል ጀመሩ ከሊቃውንቶች አንዱ በረቂቅ ፍልስፍና የታወቀ ሰው ስለነበረ እፀ መክስት ይዞ በማዕዱ ገዜ ሲጠባበቀው ተዋናይን ያየዋል ከንጉሡ ጋርም አብሮ ሲበላ ያዘው ከዛም ብኋላ ከንጉሡ ከሊቃውንቶች ጋርም ይነጋገር ጀመረ ። በአንድ በሌላ ወቅትም ደግሞ ተዋነይ የደብረ ጥበብ ሊቃውንትን መጋበዝ ፈልጎ ጥበቡን አስቀድሞ ለፍየሏ አስበልቶ ፍየሏን ያሳርዳታል ታናሽ እህቱ አደይ ወጥ ሰራች ወጡን ስትሰራም ተዋናይ እንዳትቀምሰው አስጠነቀቃት ይሁን እንጂ አላስችል ብሏት ቀመሰች ወድያውኑም ሚስጥረ ጥበብ ሚስጥረ ቅኔ ተገለጠላት ተዋነይ ወደ እሷ ሲመጣ እህቱ በጥበብ ቅኔ ተሞልታ አገኛት በዚህ ጊዜ በቅኔ ክፉ ደግ ተነጋግረዋልም ተዋናይ ቅኔን ያመነጨው እሱ ነው ይባልለታል ጎጃም ሀገር ያሉት ባለቅኔዎች እጅግ ሚስጥራዊ ስለሆነ ማንም ሰው ሚስጥሩን ሊደርስበት አይችልም ተዋነይ ቅኔ የተማረው ከሰው ሳይሆን በመንፈስ ደርሶት ነው ብለው አባቶች ያምናሉ እዚ ቦታ ሂዶ እገሌ በተባለ መምህር ቅኔውን ተማረ የሚል ታሪክ እንዳልተገኘም ይናገራሉ ተዋናይ በደመና ተጭኖ ከጎጃም ወደ ጎንደር ይመጣ ነበር እግዚአብሔር በገለጠለት ጥበብ በጣና ሀይቅ ላይ በእግሩ ይመላለስም ነበር ለዚህም ነው ተዋነይ በጣና ይመስላል ደመና ተብሎለታል ።  በነገራችን ላይ ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው በሚሰኘው አልበሙ ላይ የተዋነይ ስምን ጠርቷል ። ተዋነይ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየቀኑ ሙሉ ቤት ቅኔ ያደርስላት ነበረ ተዋነይ ከጥበቡ ብዛት የተነሳ እፀ ሂወት የተባለውን  እፀ አግኝቶ ከቤቱ ደጀፍ እፁን ቀብሮት ነበረ መላእከ ሞት ሊወስደው ወደሱ ሲመጣ ወደ ቤቱ መግባት አቅቶት ለ7 ዓመታት በር ላይ ቁሞ ቀርቷል ከሰባት አመት ብኋላ እመቤታችን ተገልጣለት << ልጄ እግዚአብሔር የሞተለትን ሞት አልሞትም ብለህ እስከ መቼ መላከ ሞትን አስረኸው ትኖራለህ ብላ ጠየቀችው ? >> ተዋናይም እመቤቴ ሆይ እኔ ጌታየን በድየዋለሁ የት እገባ ይሆን ሲላት አይዞህ እኔ አማልድሀለው አለችው ይሄን ግዜ ተዋናይ ቅኔ ተቀኘ ይህ የተቀኘው ቅኔ እንደንስሀ ተቆጥሮለታል ፦ << ከኔ ጋር ስላሉ 5 ነገሮች እፈራለሁ እንቀጠቀጣለሁ 1ኛ ነፍሴ ከስጋየ ስትለይ 2ኛ በስጋየ ባህሪ ስጋየ ወደ መቃብር ስትወርድ 3ኛ አካላቶቼ እየንተንቀጠቀጡ አምላክ ፊት ስቆም 4ኛ የኩነኔ ፍርድ ጆረየ ስትሰማ 5ኛ ወደ ስቃይ ቦታ አጋንንት ሲወስዱኝ ይሄ ሁሉ በእኔ ላይ ከሚፈፀም በተባረከችው በእናቴ ማህፀን ውስጥ ደም ወይም ውሃ በቀረሁ ነበረ >> በማለት ተዋነይ ቅኔ ተቀኘ ይህ ቅኔው ነው እንደ ንስሐ የተቆጠረለት ይህን ቅኔ ከተቀኘ በኋላ በደጃፉ ላይ የቀበረውን እፀ ሂወት እንዲያወጡት ዘመዶቹን አዘዛቸው  ከዛ ለ7 ዓመት የተኛበት አልጋ ላይ አፈር ሁኖ ተገኘ ።

Open in Telegram
Views397−28%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#12096Text

​​"ማለቴ የዘንድሮ ልጆች ደረቆች ናቸው ለምን ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው እንኳ ጠንቅቀው አያውቁትም  ዋላ ሰበብ እንዳይሆንብህ "አሉ ይርጋ የጓደኛቸውን አይበገሬነት ቢያውቁትም እንደው ለማለት ያህል የሁለቱንም ንግግር ሲሰሙ ቆይተው አቶ የሱፍ የሃይላንድ ውሃቸውን ጥጥት አደረጉና "እንደኔ እንደኔ ይህ ልጅ ኩርኩም ብቻ ነበር የሚያስፈልገው እንደው ልምድም ያለው ሌባ አይመስለኝም እንደው ስራ አልሆን ሲለው አሳቡን ቀይሮ በዚ ካለፈልኝ ብሎ ይመስለኛል፡" አሉ "እሱ ግን አሁን እናንተ እንደምትሉት አይደለም ሁኔታው፡!"አሉ አቶ ይፍሩ አሳስቧቸዋል እንዴት አድርገው ነው የሚያውጣጡት በምን መልኩ ይህን ልጅ አንድ ነገር ቢያረጉት የላከው ሰው ኖሮ የበለጠ ጉዳዩ ቢከርስ ከየት ነው የመጣብኝ ?... === ሲፈን ቤት ውስጥ ከናቷ ጋር ተቀምጣ ታወራለች፡ሰሞኑን ሁሉ ባለጭንብሉን ካየችበት ቀን ጀምሮ ተረብሻለች፡ ያ ሊደፍራት የታገላትን ሁኔታ ሁሉ ላለማስታወስ ጥራለች ፡ከዛ የበለጠ ግን እያሳሰባት ያለው፡ አባቷ ልጁን በትክክል እንዳሉት ለቀውት ይሆን ወይ የሚለው ነው፡አባባ የዛን ያክል ተናዶ እንዴት ነው እንደተራ ነገር በቃ አንተ ባለጌ ወደቤትህ ሂድ እንደማለት አይነት የሚሸኙት ምንም አልተዋጠላትም እናትም በዚ ጉዳይ እርግጠኛ አደሉም ግን ክፉ ነገር እሰከሚያደርሱበት ሳይሆን የሚገባውን ቅጣት ሰጥተው እንደሚለቁት ነው የተሰማቸው "እማ ይመስልሻል፡አባባ እንዲ በቀላሉ የሚተወው ? "የኔ ቆንጆ አባትሽን ክፉኛ መጠርጠርሽ ተገቢ አይደለም !ምን ያደርገዋል ብለሽ ነው፡እኔ አባትሽ ሲገባ አይቼዋለው ከመናደዱ በስተቀር የተለየ ነገር እንዳረገ ሰው አልነበረም፡ሲፈኔ ተይ፡በቃ እርሺ ስለዚ ነገር!" "እማ አዎ ልጁ ችኩል ቢጤ ነበር እሱ አይካድም ፡ግን እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ይገባዋል፡ብሎ ውስጤ በፍፁም ሊነግረኝ አልቻለም፡እማዬ እኔ ጭንብሉን ሳወልቅበት ያየውት ፊት እንደው በድፍረት ተነሳስቶ እንጂ ልምድም ያለው አይመስለኝም!" አለች ሲፈን "እንዴ አባትሽ ነብሰ ገዳይ መስሎ ታየሽ እንዴ!?ደሞ ሊደፍርሽ ለነበረ አንድ ዱርዬ የምን መራራት ነው ፡ምንድነው ነገርሽ ከዚ በፊት እንደሚያውቀው ሁሉ የምትሆኚው ምን አገባሽ!"የሮዛ እናት ቱግ አሉ "እማዬ እኔ ስለማውቀው ስለማላውቀው አደለም፡ እሱ እንደ ደፋሪም አይደለም እኔነኝ በመታገሌ ለፀብ ያነሳሳውት !"አለች ሲፈን ግራ በገባው እኔታ "እሰይ አሁን ገና ጉድ መጣ!አጥር ዘሎ ውሾች ገሎ ቤትሽ ድረስ ገብቶ በላይሽ ሊሰፍር የነበረው ለፍቅር ነበር እንዴ ሆሆሆ ምን እያልሽ ነው?" "እማዬ እኔ በርግጥ ጥፋተኛ አይደለም እያልኩሽ አይደለም፡ልጁ ግን አጋጣሚ ሆኖ እነጂ ለኔ ብሎ አይደለም የመጣው ፡ለዘረፋ ነው በቃ!" "እንግዲ ዘረፋው አንቺንም ያካተተ ነበር አፍኖ በርሽን ዘግቶት ነበር!" "አዎ እማዬ አሁን ስለተፈጠረው ነገር አይደለም ፡ስለ ባለጭንብሉ ልጅ ነው በሕይወት ነው ወይ የተለቀቀው እሱን ማወቅ እፈልጋለው!"አለች ሲፈን ቁርጥ ባለ ቃል "እሺ ይፍሩ ገድሎታል ነው አሳብሽ፡ምንድነው አንቺ ልጅ?!"ቆጣ ብለው "እሱን አላልኩሽም፡ግን ትክክል የሆነ ነገር እየሸተተኝ አይደለም !"አለች ሲፈን ፊቷን ቅጭም አድርጋ "እንግዲያው ይሄን ሽታ የፈጠረብሽ ያ በሽተኛ ልጅ ነውና እንፍ ብለሽ አስወግጂው፡አባትሽንም ያለ አግባብ መጠርጠርሽንም አቁሚ !" "ምክንያት አለኝ !" "ደሞ ምንድነው ምክንያትሽ ?"ተናደዱም ደነገጡም "ክንዴ ከዛን ለት ጀምሮ በጭራሽ አላየውትም ፡ድንገት ስራውን ለቀቀ ተባለ ፡መቶ እንኳ አልተሰናበተንም ሲሄድም አላየነው ፡ወዲያው ወደማታ ሌላ ዘበኛ ተቀጠረ !እንደገና የዛን ለት ማታ ልብ አላልሽ እንደው እንጂ አባባ ልብሱ ደም ነበረበት እጁ እስካሁን ቆስሏል በመጠኑም ቢሆን  እኔ ስገምት ልጁ አንዳች ነገር ሆኗል ክንዴ ደሞ ያውቃል ስለዚ የሱ እዚ መኖር አስፈላጊ አይደለም ለምን አይታይሽም እማ፡አባባ ልክ አይደለም ችግር ውስጥ ነው!!"አለች ሲፈን ውስጧ ያለውን እየተነፈሰች "አንቺ ልጅ እንግዲያው ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም፡ ማንም ሰው የሰው ቤት በውድቅት ሊት ሰብሮ ሲገባ የማባበል ግዴታም የለብንም ፡ይሄ ድፍረት ነው፡የተከበረ ቤት ነው መሪ ያለው ፡ይፍሩን የመሰለ አባወራ ያለው ምነካት ልጅቷ አጉል ሚዛናዊነትሽ አልተዋጠልኝም !" "ኧረ እማዬ፡ይህ ልጅ እንደኛ ወላጅ ይኖረዋል "ምን ዋጋ አለው ወላጅ ሁሉ ወላጅ ነው እንዴ ? "እማ ከመቼ ጀምሮ ነው ጨካኝ የሆንሺው?" ሮዛ፡ወደውስጥ ድንገት ገባች"እእ ማሚን ጨካኝ ሲፍ ማሚን?ይሄኔ ለፍራንክ ብለሽ እኮ ነው!?"አለቻት ሲፈን ደንገጥ ብላ ወሬዋን አቋረጠች ቀስ እያለም ቤቱ በቆነጃጂቶች ደመቀ አራቱም እህታማቾች እየተቀላለዱ ማሽካካት ጀመሩ ካካካካካ".... ===== ክንዴ የመረረው ይመስላል ይህን ልጅ ሲጠብቅ ሳምንት አለፈው አቶ ይፍሩ ለማየት የቀፈፋቸው ይመስል፡ወደዚም ድርሽ አይሉ ብቻ አሳባቸውን በስልክ ማስተላለፍ ብቻ ትንሽ ምግብ ስጠው ውሃ ስጠው ጎሸም እያደረክ ማን እንደላከው አውጣጣው ፡እምቢ ካለ እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገህ ግረፈው 'እንዴ እኔ ደከመኝ አሁንስ እኔ እራሱ እየተደበደብኩ መሰለኝ ኧረ ክንዴ እሱ በዱላ ያደገ ይመስል አይሰማው ደነዝ ኧረ ሰለቸኝ !ይላል ክንዴ እጁን እያሻሸ "ስማ ጭንብሌ እኔ የምለው ሰው ነህ እንዴ? እንደው ምን አለበት ማን እንደላከህ ተናግረህ፡አቶ ይፍሩም ሌላ ተደብዳቢ ቢያመጡ፡አንተም ከዚ በዋላ በዱላ ብዛት መልክህ ከሚጠፋ ባይጠፋ!እኔም ሌላ ተደብዳቢ እስኪመጣ እረፍት እንድወስድ ብትረዳኝ፡ኧረ ባክህ ባክህ!!" አለ ክንዴ እንደማሾፍ እንደመናደድም ብሎ ወጣቱ ያባበጠ ፊቱ የሸፈነበትን አይኑን በስቃይ እያቁለጨለጨ "ማንም አላከኝም አልኩ እኮ እእ ግግን አአንተ ከጌታህ የየበለጠ መጥፎ ሰው ነህ የማይገባህ እራሴ ነኘ የየራሴ አዛዥ አልኩ እኮ አንተ ባባሪያ ለለፍርፋሪ ብብለህ ነነብሴን ልልታወጣኝ ነው ከከውሾቹ ጋጋር በበገደልኩህ ሰሰው መስለኽ......"ባለጭንብሉ ተናግሮ ሳይጨርስ ክንዴ ተነስቶ በፍጥነት አቶ ይፍሩ በመቱት ብረት አናቱ ላይ ሰነዘረበት !ባለጭንብሉ ከዱላው አይለኝነት የተነሳ ከመሬቱጋር ተጋጨ ፡አይኖቹ ብዥዥዥ .....ጭልምልም መሞቴ ነው እንዴ አለ በሰመመን ውስጥ እናቱ ወይዘሮ ፅጌ ታዩት ወፍራም ቀይ ፊታቸው ሲፀይም እማማ እማማ ይቅርታ እእእአባዬ አባዬ  ዳመና የጋረደው መሰለው ፀጥጥጥ ጥቁርቁር ........ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

Open in Telegram
Views428−22%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#12095Text

#ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ....ዘበኛው ባለ ጭንብሉን ደጋግሞ አጠገቡ እየመጣ መንቃት አለመንቃቱን ያረጋግጣል፡በእግሩም ነካ ነካ ያደርገዋል፡ወጣቱ ያለምንም ድምፅ ፀጥ እንዳለ ነው፡ዘበኛው፡ሆሆሆ እሬሳ ስጠብቅ እያመሸው ላንጋ እንዴ፡አቶ ይፍሩ ግን ግፋቸው፡ከልክ ያልፋል፡አሁን ይሄን እሬሳ ከምጠብቅ ፡እነዛን ቆነጃጂቶች፡ በሄዱበት፡እየሄድኩ ብጠብቅ፡ብሎ ለራሱ ፈገግ አለ ፡ መልሶ ወደ ወጣቱ ጠጋ ብሎ ትንፋሹን አዳመጠ  አለ በሕይወት አለ ግን ባይኖር ይሻላል በድመት የተያዘች አይጥ ነው ነገሩ 'አቶ ይፍሩ እንደው መቼም ከዚ ጊቢ በሕይወት አያስወጡትም እኔም ፈርዶብኝ ቅበር መባሌ አይቀር አሄሄ እኔ ለራሴ! እያለ ዘበኛው ብቻውን ይለፈልፋል ሰአቱ ይነጉዳል ባለ ጭንብሉ እንደ ተጋደመ ነው ዘበኛው ብዙ ሲጠብቅ ስለቆየ ሰለቸው እንቅልፍ እንቅልፍ ሲለው ወደ ወጣቱ ቀረብ ብሎ እጁን ያሰረበትን ገመድ ድጋሚ አጠባበቀው እናም ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ  ብዙ ነገር አመላለሰ በሃሳቡ  እንደው ይህ ልጅ ምን ፍለጋ ነው ከዚ የመጣ? ገንዘብ ፈልጎ ይሆን ወይስ ቆንጆዎቹን ኧረ እዲያ እቴ  ደሞ አገር ምድሩን በሞላ ቆንጆ ምን ይሁነኝ ብሎ ነው እንደ መጋኛ በለሊት የሚመጣ አያደረገውም! እንደው ሌላስ አላማ ኖሮት ቢሆን አቶ ይፍሩ ማነው የላከህ ብለውትም አደለ ፡አሃ ምናልባት እሳቸውን ሊገድል ይሆን እንዴ' ኧረ ! ትልቅ ሰው ይገደላል !እንደው ምን አይነቱ ደፋር ነው፡እንደው ምናምኒይቱን አጭሶት ይሆን እንዴ እንዲ የጀገነው፡ ድንገት ከአሳቡ ተናጠበ "እእ ውሃ እባካቹ ው..ሃ"አለ ባለጭንብሉ እንደመንቃት እያለ እና ሊወድቅ የደረሰ የመሰለውን ጭንቅላቱን በታሰረው እጁ ለመንካት እየጣረ "አሃ አንተ ሞት እምቢ ነቃህ፡!"ብሎ ዘበኛው ውሃ ይዞ ተጠጋው ፡"እሺ እኔው ላጠጣህ መሰል አንተማ አቅሙን ከየት አምጥተኽው  ጎበዝ ምን ልበልህ ቸገረኝ!"ብሎ እያለመጠ ውሃውን አጠጣው፡እናም እየጠጣ አቋረጠበት "አሃ ፍጆታ የሚባል ነገር አለ ወንድሜ! አለው፡ባለጭንብሉ ቅጣቱ ከሚገባው በላይ የተጋነነ መሰለው "አንተ የማትረባ እንቅልፍህ አልመጣም!"አለው ባለ ጭምብሉ እልህኛ ነው "ዋላስ ከዚም በቀላሉ ለታመልጪኝ ነው አንቺ ትንኝ አታደርጊውም ግን እንደው ይሄን የለሊት ጉዞ ከየት ተማርሺው በይ!?" አለ ዘበኛው እያለመጠበት ፡ወጣቱ ይበልጥ ተበሳጨ "አንተ የማትረባ ፡ይሄን ገመድ ከላዬላይ ፍታ ልቀቀኝ"አለ በእልህ እየተወራጨ "ይህ የአባወራው ትህዛዝ ነው፡እናም እኔ ከሳቸው ብቻ ነው ትእዛዝ የምቀበለው አባብለህ አስተኛው ካሉኝ አስተኛሃለው ዝፈንለት ካሉ እዘፍንልሃለው ዘምርለት ቢሉም፡እዘምርልሃለው ቅበረውም ካሉ እንደዛው መቼስ ስራ አይደል!"አለ በማልመጥ "ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ!" አለ ባለጭንብሉ የበለጠ ሊሰድበው ቃላት እየፈላለገ "አይጥ ድመትን ለጫወታ ትጋብዛለች ደሞ ካንተ ጋር የሚሄድ ተረት ነው፡ሀሀሀሀ እኔ የምለው፡ቀን ላይ የሆነ የጀግና ፊልም አይተህ ነበር እንዴ በለሊት ካልሲህን ቀደህ አናትህ ላይ አጥልቀህ የመጣኽው ሀሀሀሀ ሲያረጉ አይተሻል እንደው እመጣለው እንኳ አይባልም ሀ.ሀ.ሀ..ሀ የማትረባ ዱርዬ !" ብሎ ዘበኛው በርግጫ ከቆሰለው ፊቱ ላይ መታው፡ ባለ ጭንብሉ ወደኋላው ፍንግል አለ ዘበኛው መምታቱ ያስደሰተው ይመስል ፡ደጋግሞ እረገጠው ወጣቱ ስቃዩ በረታበት በቁስሉ ላይ የሚሰነዘረው ዱላ በጣም አሳመመው ሞቱን እስኪመኝ አሳለው አቃሰተ ተሰቃየ ዱላው ቀጠለ...... ==== አቶ ይፍሩ እራት ላይ አብረዋቸው የቀረቡትን አራቱንም ልጆቻቸውን በስስት እየተመለከቱ ፡ሁኔታቸውን ይከታተላሉ ፡ሮዛ 26 አመቷን ይዛለች ራሄል 23 ሲፈን 21  ሊያ 16 ይገረማል ልጆቼ አሁን ሁሉም እኩያ እስኪመስሉ ተቀራርበዋል፡አንድ ወቅት ሁሉም የሚ ያስቸግሩ እፃናት ነበሩ ዛሬ ላይ መኩሪያዬ ሆነዋል ተመስገን ምንም ነገር ስለናንተ ነው የማደርገው በዚች ምድር ላይ እስካላቹ ሁሌም የሚገባችሁን ማግኘት አለባቹ እሱን ለመስጠት ስለናንተ የማይታለፈውን ሁሉ አልፋለው እኔ እኔ ነኝ ይፍሩ አባታቹ አሉ በኩራት በውስጣቸው ያንን ውሻ ግን ማን እንደላከው ካላወኩ እንቅልፍ አይኖረኝም ፡በጭራሽ ሲፈኔን ነክቶብኝ ይሆን እንዴ እናትና ልጅ የደበቁኝ ነገር ይኖር እንዴ?አይደረግም እንደዛ አድርጎ ከሆነ ፡እንትኑን ቆርጬ አሰቃይቼ ነው ማጠፋው አይማረኝ ከማርኩት፡ሌሎቹ ልጆቼ ሰለተፈጠረው ነገር አለመስማታቸው ጥሩ ነው እንዲያ ባይሆን ኖሮ ከፊታቸው ደስታ በራቀ ነበር ስለ ጉዳዩ መስማት የለባቸውም እያሉ እያምሰለሰሉ ፡ወደሲፈን በትኩረት አዩ ዝምታ በዝቶባታል እናትየውም እንደዛው የናቲቱ እንኳ ችግር የለውም፡ልጄ እኔ ልሸማቀቅ ብለው ተቆጩ በጣም "ሲፈኔ አንዴ ትመጪ ላናግርሽ "ብለው ተነስተው ከሳሎን ወጥተው በረንዳ ላይ ከተቀመጠው ወንበር ቁጭ አሉ ፡ሲፈን እየተጎተተች ሄዳ አጠገባቸው ተቀመጠች "ሲፈኔ ዝምታሽ በረታብኝ እኮ ፡ምነው የደበቅሺኝ ነገር አለ ከዛን ለቱ ሁኔታ ንገሪኝ ሳደብቂ አባትሽ ነኝ!?" "አይ አባዬ ምንም አልደበኩህም ከማስፈራራት ሌላ ነገር አላረገኝም እንደዛ ቢሆን አውጥተህ ስትለቀው ዝም የምል ይመስልሃል!ሲፈን እኮ ነኝ !"አለች በማረጋገጥ "ሀሀሀሀ ያባቷልጅ የኔ ልዩ አንቺን ምናለ ፈጣሪ ወንድ ባደረገልኝ!"አሉ አቶ ይፍሩ "አይ እንግዲ አባባ !አንቺን ሰው ያርግልኝ ነው የሚባለው ሰው መሆን በቂ ነው! ፆታ አያመፃድቅምም፡ አያሳፍርምም ፡የሁሉ ሰሪ እሱ ብቻ ነው፡!"አለች ሲፈን ኮስተር እንደማለት ብላ "እሰይ የኔ አዋቂ የኔ ጀግና ልክ ነሽ !" "አባባ የዛን ለት እውነት ባለ ጭንብሉን አውጥተህ ነው የለቀቅከው ምንም አይነት ቅጣት አላደረስክበትም ?" "አዎ የኔልጅ ከሱ ጋር ምን አላፋኝ የፈለገው ተራ የስርቆት ጉዳይ ለመከወን ነበር ስለዚህ ጥቂት ጎሸም አደረኩትና ለቀቅኩት፡" "ከሆነ ጥሩ ነው፡ግን ደሞ ስህተትም አለብህ የግድ ቤትህን ሰብሮ የገባን ሌባ ጎሻሽሞ መልቀቁ አልታየኝም፡ለፖሊስ ማስያዝ ነበረብህ!"አለች ሲፈን በቁጭት የአባቷ ድርጊት አልዋጥ እያላት "እኔ በወቅቱ እሱ አልታየኝም ፡ሲፈኔ አሁን እሱን ተይውና ይልቅ እንደፊቱ ተጫዋችነትሽን አምጪው እህቶችሽ ግራ እንዳይጋቡ ደሞም መቼም እንዳይሰሙ!" "ኧረ አባባ እነሱ መቼም አይሰሙም እንኳን ይህን አውቀው እንዲሁም ፈሪ ናቸው !"አለች ሲፈን ፈገግ ለማለት እየሞከረች፡አቶ ይፍሩ በልጃቸው፡ ሁሌም እንደተደመሙ ነው ትለያለች ሲፈን ይላሉ አስተዋይ ናት ቆንጆ ናት ፡ተወዳጅ ናት... ======== አቶ ይፍሩ ኮራ ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር እየተገባበዙ ከአንድ ግሮሰሪ ተቀምጠዋል ወሬያቸው ሁሉ ስለ ባለ ጭንብሉ ወጣት ነበር ሁለቱም ጓደኞቻቸው ከሳቸው ጋር በሚስጥር የተሳሰሩ ናቸው ነገርግን ለመጀመሪያ ጊዜ  በባለጭንብሉ ምክንያት አቶይፍሩ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል ማነው ከሁለት አንዱ የከዳኝ ወይስ ያልጅ ተራ ሌባ ነው! ግን እንዴት ሙሰኛ አጭበርባሪ፡ሊለኝ ቻለ እያሉ በጨዋታቸው መሃል  ግራ በመጋባት ያይዋቸዋል ከግንባራቸው ይነበብ ይመስል አቶ ይርጋ ሜታ ቢራቸውን ጎንጨት ብለው "አና ይፍሩ ልጁን ከቤትህ አስረህ ማቆየትህ ተገቢ ነው!"አሉ "አሃ ማንነቱን ሳታውቅ ልቀቀው ነው የምትለኝ?"አሉ ቆጣ ብለው አቶ ይፍሩ።

Open in Telegram
Views381−31%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#12094Text
Views495−10%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#12093Text

ማስጠንቀቂያውን አብዝተው አስተላልፈው ወደነ ሲፈን ተመለሱ:: ማነው የላከብኝ? ማን.. ማን....... ======= የጠዋት ፀሐይ ከወደ ምስራቅ ብቅ እያለች ነው ፡ሰውም የተለመደ ስራውን ለማከናወን ነቃ ነቃ እያለ ነው ፡እትዬ ፅጌም በላስቲክ ቆሻሻ ይዘው ወደገንዳው በመድፋት ወደቤታቸው  ያገኙት የጎረቤት ሰው ደና አደራቹ እያሉ ሰላምታ እየሰጡ ተመለሱ ፡ወደ ውስጥም በመግባት "ኤዶም ኤዶሜ አንተ ተነስ አስኪ ይበቃል ወንድምህንም ቀስቅሰው፡!"እያሉ ተጣሩ ከመንትያ ልጃቸው አንዱን "እእ እሺ እማ እየተነሳው ነው "አለ ኤዶም እትዬ ፅጌ እጃቸውን እየተጣጠቡ ያ እብድ ወንድምህ ምነው ዛሬ እንቅልፋም ሆነ!"አሉት ኤዶም መጥቶ ከፊታቸው ሲቆም "አይ አይ እማዬ አዳም ትላንት ወደ አምስት ሰአት አካባቢ እነ ብሩክ እየጠበቁኝ ነው ብሎ ላንቺ እንዳል ነግርሽ አስጠንቅቆኝ ነው የወጣው ስገምት ብሩክ ጋር ነው ያደረው "አለ ኤዶም  "ኧረ እንዴት በል ደውልለት ከሆነም " እሺ ብሎ ሞባይሉን አንስቶ ደወለ ፡ብሩክ አንስቶ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ "አዳም አነተጋር ነኝ ብሎነበር ?" "ኧረ በጭራሽ አላገኘውትም" "እውነት" "አዎ እኔጋር አልመጣም" "እሺ ብሩክ ደናዋል"ብሎ ዘጋው ወደናቱ ተመለከተ፡እናት ተጨነቀች "ለምንድነው በራሱ ስልክ የማትደውለው " "አይሰራም"አለ ኤዶም ፍርሃት ፍርሃት እያለው "ልጄ የፈለገ ቢያመሽ አድሮ አያውቅም አባትህ ጋር ደውል!" "አባባ ወጥቷል እንዴ?ግን እማዬ ይቅር ይደነግጣል ትንሽ እንጠብቅ !"አለ ኤዶም፡ እትዬ ፅጌ ተረበሹ መንትያው የት ነው አዳም የት ነው ያደረው እንዴት በለሊት ወጣ.. የት ነው መንትያው?...እትዬ ፅጌ ግራ ግብት ብሏቸዋል ፡አንዴ ይቆማሉ አንዴ ይቀመጣሉ፡ይወጣሉ ይገባሉ፡መላ አተዋል ፡'የት ገባ ይባላል !በጨለማ ሲጓዝ አንዱ ደፍቶብኝ ይሆን !እንደው ምን አድርገውት ይሆን፡እንዴት በጤናው አድሮም ቀኑን ሙሉ ሳይመጣ ይቀራል፡አንዳች ነገርማ አለ!'እያሉ በጭንቀት ያምሰለስላሉ ፡ኤዶም ቆይቷል ከቤት ከወጣ ወንድሙን ፍለጋ ፡የአዳም ጓደኞችን ሁሉ ካሉበት ድረስ እየሄደ ፡ጠይቋል ግን አንዳቸውም አየነው አላሉትም፡ ኤዶም ገራገር ቢጤ ነው፡ በዛላይ ብዙም ከሰው ጋር አይቀርብም፡ ትንሽ ትንሽም አይናፋርነት አለችበት፡ ከወንድሙ አዳም አንፃር፡ተቃራኒ ነው፡ አዳም ሁሌም ሊያበሳጨው ሲፈልግ፡ 'አንተ ጅል፡እኔና አንተ አንድ ቦታ መሰራታችንን እጠራጠራለው፡መልክህ እኔን ከመምሰሉ ውጪ በጭራሽ ውስጣዊ አሰራራችን ይለያያል!'ይለዋል ፡ኤዶም ለሱ መልስ ሳይሰጥ 'እማዬ አየሺው እንዴት እንደሚናገረኝ ይሄ ስረሃት አልባ ልጅሽ፡አንቺ ነሽ እያቀበጥሽ ፡እንደፈለገ እንዲሆን የምታደርጊው፡ አፉን አዘጊልኝ አለበለዚያ ...!'ይላል ወደ እናቱ እያየ አዳም በማልመጥ እያሽካካ'ኧረ ሼባው አልቀረቦትም ልታስፈራራኝም ያምርሃል !' ይለዋል ፡ኤዶም እንዲም ሆኖ ግን፡መንትያውን ከልቡ ነው የሚወደው፡ ለዛም ነው፡ብዙ ችግሮቹን የሚሸፍንለት ፡ሲመሻሽ ተነስቶ መውጣቱን ከቅርብጊዜ ወዲ የተለመደ ቢያደርገውም፡ ኤዶም ጨርሶ ለወላጆቹ ነግሮ አያውቅም፡ሊነጋጋ ሲል ሲመጣ፡ቀስብሎ በር ከፍቶ ያስገባዋል፡ ዛሬግን አዳም አልመጣም፡ ስልኩ እንኳ ዝግ ነው፡ኤዶም የት ብሎ እንደሚፈልገው ግራ ገባው እሱ የሚውልበት አይውል፡ እንዲው ቢጨንቀው መንገድ ለመንገድ ሲዞር ውሎ ወደቤቱ ተመለሰ ፡እትዬ ፅጌ ኤዶም ሲገባ ብድግ ብለው ቆሙ "ኤዶሜ ምንም አላገኘህም!አየው የሚል ጠፋ ልጄን? ነው የደበከኝ ነገር አለ እባክህ !" ብለው አስጨነቁት "እባክሽ ፅግዬ፡ልጄን አታስጨንቂው፡ኤዶም አዳም ከሚውልበት አይውል፡ደሞስ አንድ ቀን ቀረ ብለሽ፡ምን እንዳይሆን ነው ወንድ ልጅ አደል እንዴ፡እስኪ ተረጋግተን እንጠብቅ!" አሉ የመንትዮቹ አባት አቶ አይሉ "አንተ ዝም በለኝ መጥተህ አንድ መፍትሔ ታመጣለህ እላለው እዚ ተጎልተህ ምን እንዳይሆን ነው ትላለህ እሬሳውን እስኪሰጡኝ ነው የምጠብቀው !" "እባክሽ ፅጌ ተይ ካልሆነ ካልሆነ ነገ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ አመለክታለው!"አሉ አቶ አይሉ ለሚስታቸው እየተጠነቀቁ፡ "ኧረ እንዴት ልሁነው ልቤ አንዳች ነገር እንዳለ ነው የሚነግረኝ"አሉ እናት ሆዳቸውን ጭምቅ እያደረጉ፡ኤዶም በናቱ ሁኔታ አዘነ ሄዶ አቀፋቸው"እማ ይመጣል አይዞሽ ፈጣሪ ያውቃል !"አለ ፡ግን ይህን ይበል እንጂ ውስጡ ፈርቷል፡ይሄ በድብቅ በለሊት የመውጣቱ አባዜ፡አንድ ቀን ችግር እንደሚያመጣ ጠርጥሮ ነበር፡ በራሱ አዘነ ይህን ሁኔታ ለወላጆቹ ነገሮ ማስቆም ነበረበት፡የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው፡እራሱንወቀሰ የኔ ስህተት ነው፡አለ፡ኤዶም "እንደው አይልዬ ለምን አሁኑኑ ከኤዶሜ ጋር ፖሊስ ጣቢያ ሄዳቹ አታመለክቱም?!" አሉ እናት "አይ ፅግዬ እነሱም እኮ አካሄድ ይኖራቸዋል ዛሬን አድረን ነገ ሁኔታውን አይተን ይሻላል እሺ በይኝ ፅግዬ እናቴ!"አሉ አቶ አይሉ ሚስታቸውን በፍቅርና በጨንቀት እያባበሉ ሚስት ባይዋጥላቸውም እሺ አሉ ፡እናም እጥፍጥፍ ብለው ዱካ ወንበር ላይ ተቀመጡ ፡ልጄ እምን ውስጥ ገብተህ ይሆን ...ልጄ.....አዬ ጉዴ ....ብቻ ክፉ ነገር አታሰማኝ... ፈጣሪዬ ....ፈጣሪዬ.......እህህህ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

Open in Telegram
Views655+19%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#12092Text

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡                               ...የበሩ መንኳኳት ከሚገባው በላይ አሰለቸው ፡ተቅበዘበዘ ፡እቺ ሴትዮ ምንድነው እንዲ ችክ የሚያረጋት ፡በቃ ተኝታለች፡ለምን አትሄድም፡እንዴ በለሊት እየዞረች ምን ያስረብሻታል፡ፀጥ ካለች ተኝታነው ብላ አትሄድም እንዴ!! ኳኳኳኳኳኳኳ....... ፈጣሪዬ ትዕግስቴን ልታስጨርሰኝ ነው አለ በውስጡ ሽጉጡን በጎን በኩል ከራስ ፀጉሩ ላይ እያሻሸ ፡አልፎ አልፎ ሁሌም ጭንቅ ሲለው እንደሚያደርገው በግራ እጁ ጀሮውን ሳብ ሳብ ያደርጋል፡ የሮዛ እናት ወይ ፍንክች ፡ልጃቸው ሲፈን በሩን የዘጋችበትን ምክንያት ሳያውቁ እንዴት ይተኛል ያሉ ይመስላል ፡አዲስ ነገር ነዋ ፡ኳኳኳኳኳኳ .. ባለጭንብሉ ቱግ አለ ፡ሽጉጡን በበሩ ትክክል ደቀነው፡ሲበሳጭ፡እንዲ ነው፡ለውሳኔ ይቸኩላል፡ ሲፈን በድንጋጤ ቃላት አመለጣት "በፈጠረህ!"ብላ ለእናቷ ለመከላከል ጮኸች ፡ባለጭንብሉ ክው አለ ወይኔ ይች የማትረባ ፡ብሎ ሽጉጡን አልጋው ላይ በፍጥነት አስቀምጦ ፡ፕላስተር በመፍታት አፏን ደፈነው፡እንደገናም እጅና እግሯላይ በችኮላ በፕላስተሩ አቆላልፎ ጠመጠመባት፡ሲፈን ድምፅ ለማውጣት ሞከረች፡ከደጅ የሮዛ እናት ማንኳኳታቸውን አቁመው ፀጥ ብለዋል ወዴት ገቡ፡ባለጭንብሉ ተጠራጠረ ፡ለምን ዝም አሉ፡የሲፈንን ድምፅ አልሰሙ ሆነው ነው፡ ወይስ ?....     ትንሽ በዚ ሁኔታ ከቆዩ በዋላ "ሲፈን ሲ ፈን"ብለው በሹክሹክታ ተጣሩ፡ባለጭንብሉ እሰካሁን የት ሄደው ነው፡በድንጋጤ ይሆን ዝም ያሉት፡ምናልባት በህልሟ የተናገረች መስሏቸው ይሆን ለማጣራት ብለው....እንደዛ አስበው መሆን አለበት ብሎ ተመኘ ፡ቀስብሎ ጭንብሉን በማንሳት አጠለቀው ሽጉጡን ያዘ እናም በሩን ከፈት አደረገው የሮዛ እናት በተከፈተው በር ዘው ሲሉ ባለጭንብሉ በፍጥነት አናታቸውን በሽጉጡ ጫፍ መቶ ጣላቸው ፡ሴትዮዋ ከአልጋው ጋር ተገጫጭተው መሬት አረፉ ሲፈን የታፈነ የስቃይ ጩኽት አሰማች፡ባለጭንብሉ ወደሴትዮዋ አጎነበሰ፡በዛው ፍጥነት ፡ከደጅ የሚያርበደብድ ወፍራም አስፈሪ ድምፅ ተሰማ "እንዳትነቀሳቀስ ባለህበት ሆነህ ሽጉጥህን ጣል፡!!"አቶ ይፍሩ ነበሩ የሲፈን አባት የቤቱ አባወራ፡በደንብ የተዘጋጁበት ይመስላል ፡የሮዛ እናት በትክክል የልጃቸው ሲፈንን ድምፅ በትክክል መስማታቸውን፡እና ባለቤታቸውን እንደቀሰቀሱና እንዳዘጋጁአቸው፡ባለጭንብሉ ተረዳ፡በራሱ በሸቀ፡ሽጉጡን ወደጎን ወረወረው ፡አቶ ይፍሩ ግዙፍ እና ደንደን ያሉ የ55አመት ጠንካራ ሰው ናቸው ፡ሽጉጡን ጠጋብለው፡ በእግራቸው በመምታት ወደ አልጋው ስር አስገቡት  ባለጭንብሉ ተሰፋ ቆረጠ "ተነስ አንተውሻ እንዴት አባክ አድርገ እዚ እንደገባህ ትናገራለህ፡እገልሃለው!፡ ውጣ !"አሉ በጣም ተናደዋል እንዴት ተደፈርኩ በሚል ስሜት ጨሰዋል፡ባለ ጭንብሉ በተሸናፊነት ስሜት፡አንገቱን አቀርቅሮ፡ወጣ አቶ ይፍሩ ባለቤታቸውን፡ተመለከቱ ለክፉ አይሰጡም፡ወደልጃቸው፡አዩ፡ግን ለጊዜው፡የሚቀድመው፡ የባለጭንብሉ ጉዳይ ነው፡ማነው የላከብኝ፡በቅርቡ በህገወጥ መልኩ አንድ ቢዝነስ ፡ሰርተዋል ከጓደኞቻቸው ጋር፡ግን ለምን ሶስታችንም፡በድርሻችን ፡አልተከፋንም፡አቶ የሱፍ ይሆን፡በጭራሽ፡ጠዋት አግኝቼው ነበር ፡ምንም አይነት ቅሬታም አላየውበት ደሞስ ለምን ቅር ይለዋል አይ አይ እሱ ሊሆን አይችልም ይርጋ ይሆን፡እሱም በድርሻው ተስማምቷል!! አይ ሊሆን አይችልም ይህ የዘረፋ ጉዳይ አይደለም ፡ይሄ ሴቶችን በመድፈር የሚረካ አንድ አለሌ ብቻ ነው፡የገንዘብ ጉዳይ ቢሆን፡የሲፈን ክፍል ምን ይሰራል ፡አዎ ይሄ ሴሰኛ በልጄ ላይ ነው የመጣው እንዴት ቢደፍረኝ ነው አያውቀኝማ!አሉ "አንተ ውሻ ይሄ የፊት ጌጥህን አንሳና በዚ በኩል ሂድ!"አሉት ግቢውስጥ ሲደርሱ ወደ ቀኝ በኩል ካለው በጊቢ ውስጥ እራቅ ብሎ ከሚገኘው መጋዘን እያሳዩት ፡ግቢው እንደዚ ሰፊ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየ መሰለው፡ በራሱ ከሚገባው በላይ አፍሯል የመጣበትን አላማ በመተው፡የተልከሰከሰበትን ሁኔታ ሲያስተውሰው እራሱን ጠላ'፡ምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባውት ፡እኚ ሰውዬ ከገመትኩት በላይ ክፉ ሳይሆኑ አይቀሩም ፡መጋዘን ውስጥ ሊቆልፉብኝ ነው ማለት ነው፡በቃ ጉድ ሆኛለው ፡የልጃቸው ሁኔታ እንኳ አልገረማቸው የናትየው እራሳቸውን ስቶ መውደቅም ቁብ የሰጣቸው አይመስልም የነሱን ደህንነት ሳያረጋግጡ እኔን አንዳች ነገር ለማድረግ ብቻ መቸኮላቸው ፡ጭካኔ ያቸውን ያሳብቃል፡'እያለ በውስጡ እያወራ ፊትፊት ሄዶ መጋዘን መሰሉ ቤት ጋር ደረሰ አቶይፍሩ በጥንቃቄ በሩን ከፍተው ወደውስጥ እንዲገባ አስገደዱት፡ወደውስጥ ሲገባ አይለኛ ቦክስ ሰነዘሩበት ወጣቱ ባለጭንብል ያላሰበው ስለነበር መቋቋም አልቻለም ወደቀ በወደቀበት ደጋግመው ፊት ለፊታቸው ባገኙት ብረት ሰባበሩት ፡ባለጭንብሉ በህመሙ መጠንከር የተነሳ ጮኽ ሁሁታውን አቀለጠው አፉን በቦክስ መቱት ጥርሱ የተነቃነቀ መሰለው፡ "አንተ ሌባ አንተ ሙሰኛ አንተ አጭበርባሪ ሽማግሌ!!"ባለጭንብሉ እልህ ያዘው ለመነሳት ሞከረ እዛው እረግጠው ያዙት"አጭበርባሪ ነው ያልከው ማነው የላከህ ፡ተናገር!!"አሉት አሃ ለልጄ ሳይሆን ለኔነዋ የመጣው ዱላውን አባሱት ፡ባለጭንብሉ በዱላብዛት በደም ተጨማልቆ እራሱን ሊስት ሆነ ያጠለቀውን ጭንብል ከፊቱ ላይ በማውለቅ አዩት ፊቱ ደም በደም ስለሆነ ማንነቱን መለየት አቃታቸው ወደጥግ በመሄድ በሀይላንድ የነበረ ውሃ አምጥተው ፡ፊቱላይ አፈሰሱት፡ውሃው ደሙን እያጠበው ወረደ ፡አሁን ፊቱን በግልፅ ማየት ጀመሩ ፡ይህንልጅ ሰሞኑን አይተውታል የመብራት ቆጣሪያችሁን ለማየት በሚል ሰበብ መጥቶ አዎ በትክክል አይተውታል፡እንደውም፡ እንደቤቱ ትልቅነት አይደለም ፍጆታቹ ብሎም አሰቋቸው ነበር፡አሃ አሉ አሃ ጥናት ላይ ነበርክ፡ልጆቼ ላይ ነው እኔ ላይ አንላቀቃትም፡አሉ አቶይፍሩ ፡ከደጅ "ማነው ማነው እዚ የገባ ሰው አለ !!"እያለ... ዘበኛው ወደመጋዘኑ ገባ "አፈር ጉድጓድ ግባ ቤቴ በሌባ ሲደፈር አንተ ተኝተሃል አንተም ውሾቹም አንድ ናቹ ቀለብ ብቻ!!"አሉ አቶ ይፍሩ "ኧረ ለወትሮ ውሾቹ ኮሽታ ሲሰሙ ይቀሰቅሱኝ ነበር !እእኔ በውነት በዬት አድርጎ እንደ ገገባ እእ ሁለቱም ውሾሾች ሞተዋልእእ !!"አለ እርብትብት እያለ "እነሱ ፍንችር ማለታቸውን ባይ ጊዜ እኮ ነው አንዳች ነገር እንደተፈጠረ በመጠርጠር ግቢውን ስዞር እርሶ ከዚ ነዎት!"አለ እንደጨነቀው አንዴ የወደቀውን ወጣት የት ነበር የማውቀው በሚል ለማስታወስ እየጣረ በሌላበኩል አቶ ይፍሩ የያዙትን በደም የራሰ ብረት እየተመለከተ ገለውታል በቃ አይተርፍም በሚል፡ጨካኔያቸውን እያደነቀ፡"አንት ውሻ ውሾቼን ገድለሃቸዋል ለዚ ጥፋትህ አሰከፍልሃለው!"ብለው ፊቱን ደግመው እረገጡት፡እናም "አንተ የማትረባ ይሄ ነገር ከኔና አንተ ውጪ እንዳይወጣ በጭራሽ ፡ነግሬሃለው ፡ገና ማን እነደላከው ሳይናገር በሕይወት ከዚ መጋዘን አይወጣም ፡በሩን በደንብ መዝጋትህን አረጋግጥ ፡አንተ ጠብደል ከዛሬ ጀምሮ የሱና የሱ ጠባቂ ነህ ፡ለጊቢው ሌላ ዘበኛ እቀጥራለው አንድም ሰው ወደዚ መጋዘን ድርሽ እንዲል እነዳታደርግ ፡አንተ እራስህ በፊለፊት ሳይሆን በዋላበር ነው መውጣት ያለብህ አስታውስ ፡አንዲት ስህተት ባይ ወዳንተ ነው የምዞረው ታውቀኛለህ!!"አሉ አቶ ይፍሩ በጭካኔ ፡ዘበኛው ክንዴ ደጋግሞ እሺ እሺ አለ አቶ ይፍሩን በፍርሃት እያየ እናም እሳቸውን ለማስደሰት ይመስል፡ባለጭንብሉን ሆድ ሆዱን እረገጠው ወጣቱ አጥወለወለው ማስመለስ ጀመረ ፡እንደማሳል አለ ፡ አቶ ይፍሩ "ይበቃል ትፋቱን ሲጨረስ ወደጥግ ወስደ አስረ አሰቀምጠው "ብለው

Open in Telegram
Views565+3%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#12091Text

​​ተንቀሳቀሰች ፡ባለጭንብሉ "ቁሚ የማትረቢ ጨዋታውን አበላሸሺው እንቀሳቀሳለው ብትዪ እተኩሳለው !ተመለሽ አፍሽን ዝጊና ከነበርሽበት ተመለሽ!!"አለ ሽጉጡን ደቅኖ ሲፈን ወደነበረችበት ተመለሰች፡ይበልጥ እየተንቀጠቀጠች፡ለመነች ፡ባለጭንብሉ ፡የለበሰውን ካፖርት አወለቀው ካወለቀው በዋላ ኪሱ ውስጥ በመግባት ብላስተር አወጣ ብላስተሩን በመፍታት ባጭሩ ቆረጠው፡ "እባክህን ምንድነው የምትፈልገው ፡አንተማነህ ተው እኔ ምንም አልጮህም ተወው ፕላስተሩን.."አለች ሲፈን በልመና "አሃ ካንቺ ጋር የምስማማበት ምንም ምክንያት የለም ፡የምፈልገውን ላንቺ መንገርም አይጠበቅብኝም !!"አለ በቁጣ እናም የሱሪውን ዚፕ ፈታው ሱሪውን ወደታች ዝቅ በማድረግ ወደሲፈን በመጠጋት"ማንን እንዳስቆጣሽ አየሽ! ተመልከች !ተመልከች! ይህ እራስሽ የፈጠርሺው ግርግር ነው እና ስለዚ እራስሽ ታስተካክይዋለሽ!እይው እይው!"አለ ባለ ጭንብሉ በማስገደድ ፡ሲፈን ፡አለቀሰች ፡እንደመሸሽ እየለች ከአልጋው ኮርነር ተጣበቀች ፡ባለጭንብሉ እይ ምን እነደሰራሽ እያለ ተከተላት ፡አናም እግሯቿን ጎትቶ በመክፈት ወደራሱ አስጠጋት፡ፊቷን በተሸፋፈነው ፊቱ መተሻሸት ጀመረ ለማን ለምን ነካሽብኝ እንደዛ ማድረግ አነበረብሽም አለደጋግሞ ቁረጥ ቁርጥ በማል ድምፅ ፡ሲፈን ከእግሮቿ መሃል የገባውን ሰውነቱን ለመሸሽ ተንፈራፈረች እጆቿን ለመከላከል ወደፊቷ የቀረበውን ጨንቅላቱን ለማራቅ ስትጠቀምባቸው ድንገት ጨንብሉን ከፊቱ ላይ አወለቀችው፡ባለጭንብሉ ካሰበው ቅጣት ሳይደርስ በድንጋጤ ፡ተስፈንጥሮ ተነሳ ፡ሲፈን እግሮቿን በፍጥነት ሰብስባ ፡የባለ ጭንብሉን የተጋለፀ ፊት ላይ አፈጠጠች፡እሱም እንደዛው፡ በጣም ተናደደ ፡ፊቱን ስላየችው፡ እንደሚገድላት ዛተ በቃ፡በዝች የማትረባ ከምጋለፀ ፀጥ አድር ጌያት፡ ወደዋናው አላማይ መጓዝ አለብኝ ፡ብሎ ሽጉጡን በማንሳት፡ፊት ለፊቷ አቀባበለባት፡ሲፈን አለቀሰች መጮህ አማራት፡መልሳ እህቶቿን እንደምታጣ እንዲሁም ወላጆቿን የነገራትን አስታውሳ ድምፀጿን ቀንሳ እያለቀሰች ተማፀነችው፡ "እባክህ አትግደለኝ እባክህ የምትፈልገውን ሁሉ ውሰድ እኔ እረዳሃለው እባክህ!!" "አይ ፊቴን ማየት አልነበረብሽም ፡ብተውሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም፡አንቺ በሕይወት እድትኖሪ መፍቀድ በራሴላይ ታናዳፊ እባብ የመጠምጠም ያህል አደጋ አለው !ይቅርታ አድርጊልኝ! "አለና ትራስ ይዞ ተጠጋት የመሳሪያውን ድምፅ ለማፈን እንዲ ጠቅመው ሲፈን እንደ እፃን ልጅ እጇን ዘረጋች "በናትህ እኔ መሞት አልፈልግም እህት የለህም ..በበናት ትህ እእእእ መሞት አአአልፈ ፈልግምም እእእእ እፈራለው መሞ ት እእእእ በፈጣሪ ይ"ቁጭ ብድግ እያለች ለመነች ፡የባለጭንብሉን ቆንጆ እና ጠይም ምንም ወንጀለኛ የማይመስል ፊት፡ እያየች፡ "አይ ነገረኩሽ ባታይኝ ጥሩ ነበር "ብሎ በመጠጋት ትራሱን ወደፊቷ አቅጣጫ አደረገው፡   ምትለው ግራ ገባት በሕይወት ለመትረፍ ምን አይነት የመለመኛ ቃላት እንደምትጠቀም ጠፋት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጣ ተንዘፈዘፈች፡ በዛ በለሊት፡ ምን አይነት ሴጣን ነው፡ እሷን ብቻ መርጦ ሕይወቷን ሊነጥቃት የመጣው፡ ካሁኑ ቤተሰቦቿ ናፈቋት የእንስፍስፍ እናቷ ፍቅር የአባቷ ኮራ ያለ ትእዛዝ የእህቶቿ ውበት ከነሳቃቸው ከነጨዋታቸው እንባዋ የባስ ዱብ ዱብ አለ "ወንድሜ እባክህ እኔ እኔ.......እእእእ ከደጅ የእግር ኮቴ ተሰማ ባለጭንብሉ ትራሱን አልጋው ላይ ወርውሮ ወደበሩ በመሄድ በሩን ከውስጥ ቀስብሎ ዘጋው ፡እናም ኮቴው እየቀረበ መጣ " እናም ከሲፈን አጠገብ ያለው በር ሲጢጢ ብሎ ተከፈተ ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ የመዘጋት ድምፅ አሰማ ቀጥሎ ሌላኛው ክፍል ተከፈተ መልሶም ተዘጋ ፡ቀጥሎ የሲፈን ክፍል ተገፋ ባለጭንብሉ መውጫ ቀዳዳ አማተረ ምንም መደበቂያ አጣ ፡ኮስተር ብሎ ወደሲፈን በማየት አስጠነቀቃት ጠጋብሎም "አፍሽን ብትከፍቺ እንጨራረሳለን !"አላተ ቀስ ብሎ "እማዬ ናት ሁሌም ለሊት ላይ ለሽንት ስትነሳ ታየናለች ለዛ ነው በር የማንዘጋው፡የኔበር ሲዘጋ አዲስ ስለሚሆንባት መረበሿ አይቀርም" "እና ምን ይሁን ነው የምትይው?!" "ቀስ ብለህ ክፍት አድርገውና ጥግ ላይ ተደበቅ!" እሺ ብሎ ሊከፍት ሲጠጋ በሩ መንኳኳት ጀመረ ለስለስብሎ ኳኳኳኳኳ ቀጠለ የሮዛ እናት ፡የሲፈን በልተለመደ ሁኔታ በር መዝጋት ደስ አላሰኛቸውሙ ከሮዛ ጀምረው ሁሌም እንደሚያደርጉት ልጆቻቸውን በተራ ተራ አይተው ብርድልብሱን ለበስ አድርገው ነው ወደቀረቻቸው ሲፈን የመጡት በሯ ተዘግቷል እንዴት............ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ጨመረ ማንኳኳቱ ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ... ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

Open in Telegram
Views653+19%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#12090Text

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡      ፀጥታ በወረሰው በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ፡አንድ ሰው የሆነ ቦታ ለመድረስ ይጣደፋል ፡የሆነ አላማ ያለው ይመስላል አንዳንዴ እንደ መደናቀፍ ይላል ኮሮኮንቻማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በጣም አስቸግሮታል  ፡ትዕግስት የለሽ ቢጤ ነው ቶሎ ቶሎ ይናደዳል አጠገቡ ማንም ባይኖርም አልፎ አልፎ ይራገማል ፡ይሳደባል ፡እንዲ እንዲ እየተቻኮለ ተጉዞ ያን አስቀያሚ ጨለማ ሰፈር ጨርሶ ሲወጣ ድምፅ አውጥቶ "የማይረባ አገር ሁሉን ነገር ማጨለም ቲ!"አለ እናም ቀኝ እግሩን ከመሬቱጋር አጋጨው መብራት የለም፡ ውሃ የለም፡.....ችግር ቲ  ፡አሁን እኛ ጠግበን ሳንበላ ጤፍ ጤፍ እንኳ በአቅሙ ለውጭ ይሸጣል ፡መብራት መብራት በስርሃት ሳናበራ ፡ለውጭ ይሸጣል ቲ! ኧረ ስንቱን ስንቱን ትሸጣለች..... !ነጋዴ አገር! ግን ያላተረፈች ! ቲሽ፡ ባዶ ባዶ ፡ሰርተህ ባዶ ፡ነግደህ ባዶ ፡ሰርቀህ ባዶ .... ኪኪኪኪኪ ...ነገሩ የሚሰረቀውን ሰው ጠንቅቆ ያለማወቅ እራሱ ባዶነት ነው ኪኪኪኪኪ.... ስንት ሙሰኛ በተንጣለለ ጊቢ ውሻና ዘበኛ ሰብስቦ የሚኖረውን ትቶ እነማዘር በመከራ ያገኟትን ሳንቲም ከነቦርሳው መንትፎ መሮጥ መስረቅ ነው እንዴ ኪኪኪኪኪ ..... ኧረረረ ከሰረቁ አይቀር እንደኛ የጀግና ተልእኮ ማካሄድ ነው ኪኪኪኪኪ!!" እያለ ለብቻው እየለፈለፈ እየሳቀ በብርሃን ወደ ተሞላው ግን ፀጥ እረጭ ካለው ፕሮግራሙ ውስጥ ከከተተው ሰፈር ደረሰ ፡    ቆም ብሎም አካባቢውን በጥሞና ማስተዋል ጀመረ ፡እናም ሰሞኑን ጊዜ ወስዶ ሲያጠናው ወደሰነበተው ፡አንድ  ትልቅ ነጭ በጥቁር የተቀባ ብረት በር ላይ አተኮረ "፡አንድ ዘበኛ፡ ሁለት ውሻ አንድ እማወራ ፡አንድ አባወራ ፡አራት ሴት ልጆች  ኪኪኪኪኪኪ.. ይሄ ሌባ አባወራ ቲ አራት በሙሉ ሴት ይወልዳል የማይረባ  በደንብ አይሰራም ነበር ኪኪኪኪ ይሄኔ ሙስናውን ቢሆን በደንብ ይሰራው ነበር ፡ልክ የአንዱን ንብረት ለአንዱ እየሰጠ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ ፡ሁለቱን ሴቶች ፡ከኛቤት አባወሮች ጋር ፡እኔን በመሰለ ጀግናና በዛ ጅል መንትያ ወንድሜ በቀየረ ነበር ኪኪኪኪኪ ..."እያለ ብቻውን ገለፈጠ ፡መልሶ አፉን እንደመያዝ አድርጎ እራሱ በራሱ ላይ አለመጠ ፡ለሱ ይሄ ጉዳይ ምንም አይነት መረበሽን ባያስከትልበትም ፡ፀጥታው ግን የሞት ያህል ያስፈራል ፡ቀስ እያለ የግቢውን ዙሪያ ዞር ዞር ካለው በዋላ ከለበሰው ጥቁር እረዥም ካፖርቱ ውስጥ የፊት መሸፈኛ የሹራብ ጭንብል አውጥቶ አጠለቀ ለአይኖቹ ብቻ የሚታዩትን ቀዳዳዎች በትክክል ካደረጋቸው በዋላ፡ አንዲት አነስተኛ ሽጉጥ በማውጣት በሁለት እጁ እያቀያየረ አሻሻት  እናም ፈገግ አለ ፡እናም ከሌላኛው ኪሱ ውስጥ በላስቲክ የተጠቀለለውን በመርዝ ያበደ ስጋ አወጣ ፡በጊቢ ውስጥ ዘበኛው ልክ ከለሊቱ 6:00ሰሃት ላይ የሚፈታቸው ውሾች እንደሚንቀሳቀሱ ያውቃል ፡ዘበኛውም በዚ ሰሃት አሳቡን ለውሾቹ ጥሎ ለሽ እንደሚልም ያውቃል ፡ስለዚ የስጋዎቹን ቁርጥራጮች ይወረውረው ጀመር ወደጊቢው ፡ድምፆች ተሰሙት፡ባሰበውልክ ሁኔታዎች እየሄዱ መሆኑንም ተገነዘበ  ለራሱ 'አዎ እንደሱ!'አለ እናም ለጥቂት ጊዜ ወደዛ ወደዚ እያለ ጠበቀ ፡    አዎ በዚያ አስፈሪ ለሊት ከጨረቃና ጭል ጭል ከሚሉት ክዋከብት በስተቀር አንዳች ታዛቢ በሌለበት ብቻውን ፡በድፍረት ከዛቤት ለመግባት ቆርጧል ፡ እናም ውሾቹ ዝም ማለታቸውን ሲያረጋግጥ እንደጦጣ እየተንጠላጠለ ቀልጠፍ ብሎ ወደ ጊቢው ገባ ዘበኛው እንደተኛ ነው ውሾቹ ተራርቀው በድካም ተንጋለዋል መርዙ ስራውን እንደሰራ አወቀ ፡ 'እንግዲ መሆን ስላለበት እንጂ ፀቤ ከናንተ አይደለም ብሎ ውሾቹን አልፎ ወደ ሚያምረው ቪላ ተጠጋ እናም ብዙም በማትከብደዋ አነስተኛ መስኮት እጁን ሰደድ በማድረግ ፈተሻት እንደገመተው ነበርና ያለችግር ከፈታት ፡እናም በቀስታ ወደውስጥ ዘለቀ ፡እናም በመጀመሪያ እነዛ ልዕልት ወደመሰሉት እህትማማቾች ክፍል ነው መሄድ ኪኪኪኪ እያንዳንዳቸውን ነው መጎብኘት ኪኪኪኪ መቼም እንግዳ አቀባበሉ አይጠፋቸውም  እንዴ ሳኩ እንዴ  ምን አባቴ ነው የምሰራው ፡ አለ ለራሱ እናም እንዳለው በመጀመሪያ የቤቱ ታላቅ ወደሆነችው ሮዛ መኝታ ክፍል ዘው አለ በፀጥታ እግሮቿን አጣጥፋ ተኝታለች ፡'ስታምር ' አለ እናም ትቷት ወጣ ቀጥሎ ከሮዛ ጎን ወዳለው ክፍል ቀስ ብሎ ገባ ፡በአልጋው ላይ ሊያና ራሔል ጎን ለጎን ተኝተዋል ብዙጊዜ ራሔል የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንም ብቻዋን መተኛት ከመፍራቷ የተነሳ  የቤቱ መጨረሻ ከሆነችው ሊያ ጋር ነው የምታድረው ፡ባለጭንብሉ ፡ለብቻ ለብቻ ነበር መተኛት የነበረባቹ ቲ 'ግን ይህ የማይረባ እንዴት ነው ዘሩ እንዲ የሚያምረው 'አለ እናም ዞር ዞር እያለ ውበታቸውን አደነቀ ፡በመጨረሻም፡ የሊያ ታላቅ የቤቱ ሦስተኛ ልጅ ወደሆነችው ሲፈን ክፍል ገባ ፡እንደገባ ለራሱም ያስገረመው ድንጋጤ ተሰማው፡ሲፈን በጀርባዋ ተንጋላ ነው የተኛችው የለበሰችው ሰፊ ቢጃማ በከፊል ተገልፆ እርቃኗ ይታያል እረዥም ፀጉሯ ወዲያና ወዲ ተበታትኖ በሚያምረው ፊቷ ላይ ሳይቀር ነስነስ ብሏል ፡ባለጭንብሉ ፡ትንፋሹ ፀጥ አለ ለረዥም ደቂቃ በመገረም አያት እናም ቀስእያለ ደመነፍሱን ተጠጋት ....ቀስስ እያለ እያለ. እየቀረባት ሲመጣ የልብ ምቱም አብሮ ጨመረ ፡እጆቹን በቀስታ ወደ ተራቆተው ጡቷ ሰደድ አደረገው መልሶ በፍጥነት እሳት እንደነካ አይነት ሰበሰበው እንደገና በፊቷ ላይ የተነሰነሰውን ፀጉር ወደጎን ወደጎን እያደረገ አስተካከለው ፡ይህን ሲያደርግ ውበቷ የበለጠ ቁልጭ ብሎ ታየው ከንፈሮቿን መሳም ፈለገ እናም ቀረብ አላት ፡ሲፈን በሆነ ታምር ያወቀች ይመስል ተገላበጠች  ባለጭንብሉ በድንጋጤ ወደዋላው አፈገፈገ  እንቅስቃሴው ፡የረበሻት ይመስል ፡ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች ፡አይኖቿ ተከፈቱ ፡ፊትለፊት ባለ ጭንብሉን ከለላ ሲፈልግ አየችው፡ሲፈን ከመቅፅበት አልጋው ላይ ያለውን አንሶላ ወደራሷ በመሰብሰብ ቁጭ አለች ፡ሰውነቷ በድንጋጤ ደረቀ፡ባለጭንብሉ ፡ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለገባው ፡እራሱን አረጋጋ ፡ቀረብ አላትና ፡ልትጮህ ያሰናዳችውን አፋን በሰፊ መዳፉ በማፈን ፀጥ አደረጋት "ስሚ አንዳች እረብሻ አስነሳለው ብትዪ ሁሉንም ቤተሰብ ችግር ውስጥ ነው የምትከቺው !ገባሽ! ተመልከች እዚች ሽጉጥ ውስጥ አምስት ቀልሃ አለ ለአምስቱ ቤተሰቦችሽ በቂ ነው፡ ዝም ብትዪ ላንቺ ነው የሚጠቅመው!!!"አላት በጭንብሉ ቀዳዳ የፈጠጡ አይኖቿ ውስጥ እየተመለከታት፡ሰውነቷን ብርድ ብርድ አላት መንቀጥቀጥ ጀመረች፡'ማነው !ይህ ሰው ምን ፈልጎነው?እህቶቼ ደና ይሆኑ ?እማሚ እና አባቢስ  ውሾቹ እንዴት አስገቡት ?ዘበኛውስ ? በሩስ እንዴት ተከፈተለት?በምን በየት በኩል...?!!'የጭንቀት ጥያቄዎች በተራበተራ አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ፡ፍርሃቷ ወደር አጣ፡ባለጭንብሉን አፋን እንዳፈናት አልጋዋላይ ፈርከክ ብሎ ዝም እንድትል  ሲያስጠነቅቃት እያየችው ነው ጥቁሩ የሹራብ ጭንብል ይበልጥ አስፈራራት ትዝ አላት ፊልም ላይ ያየቻቸው የመደፈር አደጋዎች በርቀት ትሰማቸው የነበረ የሴቶች ጥቃት ፡እያንዳንዱ ፡ሲታወሷት፡ዛሬ በሷ ላይ ለዛውም በገዛ አልጋዋ ላይ ፡ምን አይነት የቀን ጎዶሎ ነው እዚ ሴጣን ላይ የጣለኝ አለች ስቅቅ ብላ፡፡ባለጭንብሉ ዝም እንዳለች ለመፈተሽ ይመስል ቀስ ብሎ ለቀቅ ፡ሲያደርጋት ፡በተከፈቱት እግሮቹ መሃል ጉልበቷን በማስገባት፡እንትኑን ክፉኛ አገኘችው፡እንደማቃሰት ብሎ ለቋት ወደዋላው በመሸሽ ፡አጉተመተመ ፡ለጥቂት ሰከንድ፡ አፉን ከፍቶ ተሰቃየ ፡ሲፈን እንደምንም እራሷን አበርትታ ከክፍሏ ለመውጣተሸ ወደበሩ

Open in Telegram
Views574+5%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—

All posts

Connections