"ኧረ እውነቴን ነው በጓሮ አንድ ሰው ልክ እንደሰረቀሰው እየተጣደፈ ሲወጣ አይቼ ነው !"አለ መንገደኛው "ምምን አይነት ሰው ?!"ሲፈን ሰውዬውን በድንጋጤ በጥያቄ አፋጠጠችው "ኧረ ጎልማሳቢጤ ነው ሰውነቱ ደልደል ያለነው ጥቁር ፀጉሩ መለጥ ያለ!"አለ መንገደኛው ሰውዬውን ለመግለፅ እየሞከረ ፡ "በበየት በበኩል ነው ያያልከው?ወዴት ሄሄደ ?"ሲፈን ክንዴ ነው አለች በውስጧ ፡ወዲያው እነሱን ትታ እየከነፈች ወደጓሮው በር እሮጠች፡ ስትደርስ በጥድ የተሸፋፈነው በር እንደነበር ነው ወደዚ ከመጣች በጣም ብዙ ጊዜ ሆኗታል ምንስ ፍለጋ ትመጣለች ፡ሲፈን በሩን ገፋ ገፋ አደረገችው ብዙ አላስቸገራትም ወደውስጥ እየፈራች ገባች ሰውነቷ ሽብር ብሎባታል፡የመጋዘኑን ዙሪያ ቃኘች፡ አንዳች ነገር ተዘርሮ ያየች መሰላት፡ጨነቃት አፏ ደረቀ ለማረጋገጥ እየቀረበች እየቀረበች ሄደች ፡ሰው ነው በድንጋጤ አፋን ከፍታ ቀረች፡ባለጭንብሉ በፀጥታ ተዘርሯል፡ ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ ቀዝቃዛ ላብ ከወደጀርባዋ ሲወርድ ተሰማት፡ ወደዋላዋ አፈገፈገች ሲሳይ ደርሶ ያዛት ፡ከዛም እሱም የወደቀውን ሰው አይቶ በድንጋጤ ክው ብሎ ወደሷ መልሶ በጥያቄ አስተዋላት ሲፈን ከሩቅ የሚመጣ ድምፅ በሚመስል "ሞቶሃል "አለች ሲሳይ ለቋት እየተንቀጠቀጠ ወደ ወጣቱ በመጠጋት ፊቱላይ ያለውን የሹራብ ጭንብል በማንሳት ትንፋሹን ለማዳመጥ ሞከረ ግራ ገባው መልሶ ወደአንገቱ አካባቢ እጁን ሰደደ "ሕይወቱ አላለፈም አአለ ግግን መመፍጠን አአለብን ሐኪም ቤት መመሄድ አለበት!"አለ ሲሳይ ዘበኛው ሲፈን እንደባነነ ሰው ሆነች "እእውነት በበምን አወክ ?!" "ትንሽ ጊዜ ወወታደር ቤት የቀሰምኳት ትምርት አለችኝ አሁን እሱ አደለም ዋናው ነገር መኪናሽን ይዘሻት ነይና ሐኪም ቤት እንውሰደው!"ሲፈን ደመነፍሷን እሮጠች መንገደኛው አካባቢው ሄዷል ጭር ብሏል መኪናዋን በፍጥነት ማንም ሳያያት አስነስታ መጣች እቤትም ገና አልተሰበሰቡም ጥሩ አጋጣሚ ሆነላት፡ ሲሳይ የተሰባበረውንና በደም የተጨማለቀውን የወጣቱን የከሳ ሰውነት ተሸክሞ መኪናውስጥ ማንም ሳያየው በጥንቃቄ አስገብቶ አስቀመጠው እናም ተከትሎ ሊገባ ሲል "ቆይ ሲሳይ ይህን ጉዳይ በኔና አንተ ብቻ መሃል እንድንይዘው እፈልጋለው ማንም መስማት የለበትም አስታውስ የቤተሰቡ አካልም ሆነ ሌላ ማንም አደራ ይሄን የማደርገው ልጁን ለማዳን ነው፡ባለውለታዬ ነህ አደራ ስለዚህ አንተ ከግቢው መራቅ የለብህም ምንም እንዳልተፈጠረ ሁን አደራ እሱን ለኔ ተውልኝ ስለሁኔታው በሚስጥር አሳውቅሃለው !"ብላ ሲፈን ማረጋገጫ ሳጠብቅ የሰው ሕይወት ለማዳን መኪናዋን ይዛ ተፈተለከች ፡ብርርርርርርር ቢቢቢቢቢቢቢ ፍጥነት ሲፈን የባለ ጭንብሉ ሕይወት አደጋ ላይ ነው አባባ ....አባባ...ምንድነው ያደረከው.....ክንዴዴዴዴ...አባባባ======== ቤቱ በጠያቂ ተሞልቷል ሰው ሁሉ የየራሱን ግምት ይሰጣል አንዱ የአንዱን አሳብ ያፈርሳል አንዱ በአንዱ አሳብ ይስማማል በዛውም የራሱንም ግምት ይሰጣል አንዳንዱ ለማውራት ብቻ ብሎ እንደው እንደነገሩም አሳቡን የሚሰነዝርም አለ ብቻ የነ ኤዶም ቤት ሰሞኑን በትዬ ፅጌ ለቅሶ በመደናገጥ የሚሰበሰብ ሰው አላጣውም በቀን በማታ ልክ እንደ ሐዘን ቤት እንዴት ሆነ መልካም ዜና አለ አሁንም አልተገኘም ፖሊሶቹ ምን አሉ ምን ይሻላል አንዱ ጋር ገለው ጥለውት ይሆን ?የሴጣን ጆሮ ይደፈን ከአገር ወጥቶ ይሆን እንዴት አንድ መልእክት ሳይተው? አዬ እንደ እናት ጡት ሁለት ብቻ ሆነው ተፈጥረው አሄሄሄሄ በመሃል እትዬ ፅጌ ለቅሶ ይጀምራሉ ልጄ ልጄ እንደወጣህ ቅርት አልከው ኧረ ምን አየብኝ !ኧረ ወዴት ልፈልገው! ኧረ ምን ውስጥ አሰመጡህ ልጄ ልጄን አስራምስት ቀን ሙሉ ምንዋጠው ይባላል በሉ የበላው ጅብ አልጮህ አለ ኧረ እናንተው ምን ይሻለኛል እያሉ ያነቡታል ኤዶም የናቱን ድምፅ በሰማ ቁጥር እንባውን መቆጣጠር ያቅተዋል ወይኔ ወንድሜ ወይኔ የት ይሆን ያለኽው ከየት ላምጣህ ይላል በጭንቀት አባት ይሄ ነገር እንደቀልድ እውን ሆነ እንዴ ኧረ ዋ አዳም ምን አገኘብኝ እያሉ ያምሰለስላሉ በአዳም መጥፋት ቤተሰብ ሰፈር ጎረቤቱ ሁሉ ተጨንቆ ነው የሰነበተው.... ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in TelegramPosts of ከመጽሐፍት መንደር💠
#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ ክንዴ ብረቱን መሬት ላይ በመጣል ቁና ቁና እየተነፈሰ ቁልቁል ወጣቱን እየተመለከተ እንቅስቃሴውን መጠባበቅ ጀመረ ድንገት የተፈጠረ የንዴት ስሜቱ እስኪበርድለት ትንሽ ጊዜ ወሰደበት እንዴት በልኩ በጄ ብቻ ጎሸም ባደረኩ ባዋራውት ሌባ መሆኑን እረስቶ ጭራሽ ከውሻ ይደምረኝ፡ይሄ ወፍ ዘራሽ እንዲህ ነውና ክንዴ ይሄ መደዴ አመዳም የማን አባቱ ወናፍ ነው በሉ የታባቱ ገና ልክህን ነው ማሳይህ ዱላ ቁርስ ምሳ እራትህ ያላደረኩልህ እንደው፡እኔ ክንዴ አይደለውም እያለ ዛተ ከዛም ብረቱን መልሶ አነሳው ወደ ባለጭንብሉ እግር በመክተት ቆስ ቆስ አደረገው እንቅስቃሴ የለም ወደ ሆዱ አካባቢ ነካካው የለም ክንዴ ደነገጠ ብረቱን ጣለው በርከክ ብሎ የባለጭንብሉን ፊት ከቀኝ ወደ ግራ ወዘወዘው ፀጥ እረጭ ብሏል ክንዴ ልቡ ክፉኛ በድንጋጤ መምታት ጀመረ "አንተ ጭንብሌ አንተ !ንቃ ጭንብሌ !ኧረ ወይኔ ክንዴ !ኧረ ዋይ ጉድ ሆንኩ እንዴ !ስማማ ውሃ ውውሃ ተትፈልጋለህ! ጭንብሌ !ጭንብሌ!ጭንብሌ!ወይኔ ክንዴ ጉድ ፈላብህ ኧረ ኧረ ......." ክንዴ ሳያስበው መጮህ ጀመረ ፡ድንገት የሚመጣውን ችግር አስቦ አፉን ዘጋ ተርበተበተ ፡ቀጥ ብሎ ቆመ ግራ ተጋባ ወዴት ልሂድ ወዴት፡ለማን ልንገር፡ለአቶ ይፍሩ ልደውል፡ኧረ በጭራሽ ጠብቅ እንጂ ግደል አላሉኝ ኧረ እኔንም ያጠፉኛል ምላድርግ የሰውሰው በጄ ጠፍቷል የሰማዩም ይቅር አይለኝ እጄን ልስጥ እንዴ ክንዴ መጋዘን ውስጥ ተሽከረከረ እንዴት ብሎ ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት እንዳለበት ግራ ገባው በመጨረሻ ፡ማምለጥ እንዳለበት ወሰነ ፡እናም በጎኑ የተኛውን ወጣት ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው፡ የሹራብ ጭንብሉን ከወደቀበት በማንሳት ወደወጣቱ ቀረብ ብሎ ፊቱን ሸፈነለትና "ይቅር በለኝ !"ብሎ ዕንባ ዕንባ እያለው በጓሮ በር በኩል፡ ወጥቶ ሄደ ....ክንዴ ሄደ....ከራሱ ጋር እያወራ ሄደ ሄደ..... ======= አቶ የሱፍ ከልጃቸው ጋር ፡በሱቃቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ ወሬ አቸው ሁሉ ምክር አዘል ነው ያቶ የሱፍ፡ መግባራቸው ጥሩ ካልሆኑ ልጆች ጋር አትዋል ሁሌ ልጅነት የለም አንተነህ የኔ ንብረት ወራሽ ሌላ ማን አለኝ የመጀመሪያ ልጄ ነህ እኔ አንድ ነገር ቢገጥመኝ እናትህን እህቶችህን ጭምር አንተነህ የምትመራው፡ እኔ የምትቀርባቸው ልጆች ብዙም ደስ አይሉኝ ፡በተለይ ጀማል ከጥሩ ልጆች ጋር አላየውም እንደው አባቱ የተከበረ ሰው ነው ልጁን ግን ቀልቤ አይወደውም ፡ ምናምን ምናምን ፡አብዲ በሆዱ ይህ ምክር ግልባጭ ላንተ ቢደርስልኝ የተከበርከው አባቴ ከኔ ይልቅ ለራስህ ስነ መግባር በተጠነቀቅክ ብቻ አንተ በምትሰራው እገወጥ ስራ ወደፊት ምን እንደሚደርሰን ሳስበው፡ ይጨንቀኛል እንደው አባባ ምን ስትል ነው እነዛን እገወጦች ጓደኛ ያደረከው አንተ እራስህ አላህ እማይወደውን ስራ እየሰራህ እኔን መምከርህ ከነ ጓደኞችህ ወንጀለኛ ነህ አባባ ይላል አብዲ "አብዱ እንደው ባለፈው መጋዘን ስለገቡት እቃዎች ከሰዎች ጋር አውርተህ ነበር ?"አሉ አቶ የሱፍ በመጠራጠር "አላወራውም፡እኔ አባባ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ ስለምትሰሩት የተለያየ እገወጥ ስራ አይመለከተኝም አላህን ካልፈራቹ ቀጥሉበት እሱ ይከፍላችሃል!"አለ አብዲ የአባቱ አይን ያወጣ ንግግር እያናደደው "ምን አልክ አንተ የምን እገወጥ ነው የምትለው ፡አንተ የማትረባ ፡አቶ ይፍሩ የተከበረ ሰው ነው እድሜ ለሱ ይህን ሁሉ አብት ያፈራውት ከሱ በመሻረኬ ነው ፡ይርጋም ቢሆን!እንዴት አባክ ነው ምትናገረኝ አባትህ እኮነኝ፡ተንደላቀህ በመኖርህ ጥጋብ ፈላብህ!"አሉ አቶየሱፍ እንደመነሳት ብለው "አሁን እየጠየኩህ ያለውት መጋዘን ሄደህ አስተካክል ያልኩህ ጊዜ ከማን አባክ ጋር ነው የሄድከው ዘበኛው ጓደኛው አብሮት ነበር ብሎኛል ይዘህው ከሄድከው ልጅ ጋር በእቃው ጉዳይ ላይ አውርተሃል?!"አሉ እጃቸውን ለዱላ እንደማዘጋጀት እያሉ "ምንድነው ዛሬ ስላለፈ የመጋዘን እቃ ዛሬ የምጠየቀው አልገባኝም ችግር አለ ፡እገወጥ እና ጊዜው ያለፈበት መሆኑ ታወቀ ፡ምንድነው፡ስለሱ ይህን ያህል፡ ሌላ ብዙ ስራ ነበራቹ ለምን ስለሱ ብቻ!?"ቱግ አለ አብዲ "አፈር ብላ ማንን ነው ይዘህ የሄድከው የዛኔ!"በጥፊ አላሱት "ከ አዳም ጋር ነው የሄድኩት !" አለ አብዲ በንዴት "ማን አባክ ነው አዳም!" "እታች ሰፈር ያለው !" "ማነው እሱ እታች ሰፈር ስንት ሰው አለ የማን ልጅ ነው!?" "ምንድነው ከመጋዘን የጠፋ እቃ አለ እንዴ እንዳለ አደል እንዴ ወዲያው የተሸጠው ፡ድርሻችሁን ተካፍላችዋል ምንድነው ፡የምትለኝ ፡እሱ አብሮኝ ሄደ እንጂ ምንም የሚያውቀው ጉዳይ የለም፡ ችግር ስላለባቹ ያገኛችሁትን ከመጠርጠር ወደዋላ አትሉም!"አለ አብዲ በቁጭት "አንተ አህያ የጠየኩህን መልስ!ማነው አዳም?!" "የአቶ ሀይሉ ልጅ !" "ሀይሉ ሀይሉ"አሉ አቶ የሱፍ ለማስታወስ እየሞከሩ "ሀይሉ የወይዘሮ ፅጌ ባለቤት!በቃ የትዬ ፅጌልጅ ከመንታዎቹ አንዱ ነው በጣም ጥሩ ስነ መግባር አላቸው ስትለኝ ነበር እንግዲ ባንተ አሳብ መሰረት ከነጀማል ጋር ትቼ ከመንትዮቹ ጋር ጓደኛ ሆኛለው አሁን ደስ አለህ!?"በትህቢት እና በንቀት አባቱን እያየ ተነፈሰ አብዲ "በአላህ አንተ ምን እያልክ ነው ?! "አሉ አቶ የሱፍ "በቃ እንደዛ ነው እንደውም ሰሞኑን አዳም ጠፍቶ እየፈለግነው ነው የሰነበት ነው፡ እንኳን ስለናንተ መጋዘን ቁብ ሊኖረው ቀርቶ!"አለ አብዲ የአባቱ ባልሆነ ነገር እራሳቸውን ችግር ውስጥ ማስገባታቸው እያሳመመው 'እባክህ አባቴን ከገባበት ችግር አውጣው ፈጣሪዬ አቶ የሱፍ በሰሙት ነገር ክፉኛ ደነገጡ ያ አላህ ይፍሩ አሰርኩ የሚለው ልጅ አዳም እንዳይሆን ብቻ ኧረ ጉድ ሆኛለው አብዲ አብዲ ምን አይነት የልጅ ክፉ ሰጠኽኝ በቃ ስለኛ ጓደኛ አገኘው ብሎ ልጄ ያለውን ነገር እንዳለ ዘርግፎለታል ማለት ነው ወይ ጉዴ ባለ ጭንብሉ አዳም ከሆነ ይፍሩ ለኔም አይተኛልኝ ሆነ ብዬ እንዳደረኩት ነው የሚሰማው ጉድ ፈላብኝ ፡ግን ጥርጣሬ እንጂ ላይሆንም ይችላል"ምነው አባ የፈራህ ትመስላለህ አዳም እኮ ዱርዬ አይደለም እንዴ ምንድነው ይሄን ያህል!" አለ አብዲ ቢናደድባቸውም ትካዜአቸው አሳስቦት ፡፡አቶ የሱፍ ጥሩ ስሜት አልተሰማቸውም ወደወንበራቸው ተመልሰው ሽብሽብ እንደማለት ብለው ተቀመጡ ስቅቅ ጭንቅ ጭንቅንቅ አሉ አቶ የሱፍ ፍርሃት ...ፍርሃት.....ፍርሃት...... ========= አዲሱ ዘበኛ መንገደኛው ሰው የነገረውን ወሬ ተከትሎ የግቢውን አጥር ዞረው ምንም አይነት ፍንጭ ማግኘት አልቻለም ፡ምኑ ሰካራም ነው እያለ ወደቦታው ተመለሰ ሲመለስ ሰውዬውን የጊቢው በር አካባቢ እንደቆመ አየው ኧረረረ ምን አባቱ ነው እኔን አዘናግቶ ወደውስጥ ለመግባት ይሆን እንዴ አላማው !አለመጠርጠሬ ብሎ ዱላውን እያስተካከለ ተጠጋው "አሃ ምን አስበህ ነው በል ዱላህን ሰብሰብ አድርገው እኔ የረዳውህ መስሎኝ እንጂ !"አለው መንገደኛው እንደመሽሽ እያለ "ምን ትረዳኛለህ ዘዴ መፍጠርህ ነው ባንተቤት ዞርበል ከዚ እወርድብሃለው !"አለ ዘበኛው እየጮኽበት በዚ መሃል ሲፈን መጣች በጣም ተደናገጠች የሰሞኑ ሁኔታ እያስፈራራት ነው ያለው ይሄ ሲጨመር ቀጥታ አያያዘችው፡ እናም ወደዘበኛው እጇን እያወናጨፈች እንዳያደርገው አስጠነቀቀች "ምንድነው ሲሳይ ምነካህ ችግር አለ?!"ጠየቀች ሲፈን ሰውዬውን እየተከላከለችለት "ኧረ በጓሮ ሰው ሲወጣ አየው ብሎ ሊያዘናጋኝ ሞከረ ምን እንደፈለገ አልገባኝም!"ቆጣ አለ ዘበኛው
Open in Telegramተዋነይ ዘጎንጅ ተዋነይ ሀገሩ ጎጃም ይልማና ወረዳ ቆለላ ምክትል ሲሆን የተወለደበት ደብርም ወልደን ተክለሀይማኖት እንደሚባል ተገልጿል ። እግዚአብሔር ሲፈጥረው ጥበብን ሀሉ ገልፆለታል ተዋነይ ብዙ አስደናቂ እና አስደማሚ እውነት የማይመስሉ ነገሮችን ፈፅሟል ሊቃውንቱ እንደሚናገሩትና ታሪኩ እንደሚመሰክረው በደመና ተጭኖ አለምን እስከመዞር ደርሶ ነበር ሀገሩ ጎጃም ጎንጂ ሲሆን ጎንደር በአፄ በካፋ ጊዜ ንጉሱ ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ ተዋናይ እፀ መሰውር በመጠቀም መጦ እሳቸውም ሆነ ማንም ሳያየው ከንጉሡ ማዕድ ቀርቦ ይመገብ ነበር ታድያ ለንጉሡ የሚሰጠው ምግብ የተወሰነ ምግብ ሲሆን ተዋነይ አብሮ በሚበላበት ጊዜ ንጉሡ ሳይጠግቡ እየቀሩ ስጡኝ እንዳይሉም እየፈሩ በረሀብ ሊሞቱ ሆነ በጣም ከሱ ሰውነታቸው በጣም መነመነ ይሄን ያዩት ሊቃውንቶች እና መኳንንቶች ቀርበው በምን ምክንያት ነው ሰውነትዎ እያለቀ የሄደው አይበሉም እንዳንል ይበላሉ ታመዋል እንዳንል አልታመሙም ምንድን ነው ምክንያቱ በማለት ንጉሡን አፄ በካፋን ጠየቋቸው አፄ በካፋም ነገሩ እየገረማቸው ከጠየቋቸው ዘንድ እኔ ምግብ የምትሰጡኝ የተወሰነልኝ አላናሰኝም ነበር ነገር የሚወስደውን አላውቅም ያልቃል እኔም አልጠግብም አሉዋቸው ከዚ ብኋላ ሊቃውንትና ብዙ ጠቢባን ስለነበሯቸው ነገሩን መከታተል ጀመሩ ከሊቃውንቶች አንዱ በረቂቅ ፍልስፍና የታወቀ ሰው ስለነበረ እፀ መክስት ይዞ በማዕዱ ገዜ ሲጠባበቀው ተዋናይን ያየዋል ከንጉሡ ጋርም አብሮ ሲበላ ያዘው ከዛም ብኋላ ከንጉሡ ከሊቃውንቶች ጋርም ይነጋገር ጀመረ ። በአንድ በሌላ ወቅትም ደግሞ ተዋነይ የደብረ ጥበብ ሊቃውንትን መጋበዝ ፈልጎ ጥበቡን አስቀድሞ ለፍየሏ አስበልቶ ፍየሏን ያሳርዳታል ታናሽ እህቱ አደይ ወጥ ሰራች ወጡን ስትሰራም ተዋናይ እንዳትቀምሰው አስጠነቀቃት ይሁን እንጂ አላስችል ብሏት ቀመሰች ወድያውኑም ሚስጥረ ጥበብ ሚስጥረ ቅኔ ተገለጠላት ተዋነይ ወደ እሷ ሲመጣ እህቱ በጥበብ ቅኔ ተሞልታ አገኛት በዚህ ጊዜ በቅኔ ክፉ ደግ ተነጋግረዋልም ተዋናይ ቅኔን ያመነጨው እሱ ነው ይባልለታል ጎጃም ሀገር ያሉት ባለቅኔዎች እጅግ ሚስጥራዊ ስለሆነ ማንም ሰው ሚስጥሩን ሊደርስበት አይችልም ተዋነይ ቅኔ የተማረው ከሰው ሳይሆን በመንፈስ ደርሶት ነው ብለው አባቶች ያምናሉ እዚ ቦታ ሂዶ እገሌ በተባለ መምህር ቅኔውን ተማረ የሚል ታሪክ እንዳልተገኘም ይናገራሉ ተዋናይ በደመና ተጭኖ ከጎጃም ወደ ጎንደር ይመጣ ነበር እግዚአብሔር በገለጠለት ጥበብ በጣና ሀይቅ ላይ በእግሩ ይመላለስም ነበር ለዚህም ነው ተዋነይ በጣና ይመስላል ደመና ተብሎለታል ። በነገራችን ላይ ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው በሚሰኘው አልበሙ ላይ የተዋነይ ስምን ጠርቷል ። ተዋነይ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየቀኑ ሙሉ ቤት ቅኔ ያደርስላት ነበረ ተዋነይ ከጥበቡ ብዛት የተነሳ እፀ ሂወት የተባለውን እፀ አግኝቶ ከቤቱ ደጀፍ እፁን ቀብሮት ነበረ መላእከ ሞት ሊወስደው ወደሱ ሲመጣ ወደ ቤቱ መግባት አቅቶት ለ7 ዓመታት በር ላይ ቁሞ ቀርቷል ከሰባት አመት ብኋላ እመቤታችን ተገልጣለት << ልጄ እግዚአብሔር የሞተለትን ሞት አልሞትም ብለህ እስከ መቼ መላከ ሞትን አስረኸው ትኖራለህ ብላ ጠየቀችው ? >> ተዋናይም እመቤቴ ሆይ እኔ ጌታየን በድየዋለሁ የት እገባ ይሆን ሲላት አይዞህ እኔ አማልድሀለው አለችው ይሄን ግዜ ተዋናይ ቅኔ ተቀኘ ይህ የተቀኘው ቅኔ እንደንስሀ ተቆጥሮለታል ፦ << ከኔ ጋር ስላሉ 5 ነገሮች እፈራለሁ እንቀጠቀጣለሁ 1ኛ ነፍሴ ከስጋየ ስትለይ 2ኛ በስጋየ ባህሪ ስጋየ ወደ መቃብር ስትወርድ 3ኛ አካላቶቼ እየንተንቀጠቀጡ አምላክ ፊት ስቆም 4ኛ የኩነኔ ፍርድ ጆረየ ስትሰማ 5ኛ ወደ ስቃይ ቦታ አጋንንት ሲወስዱኝ ይሄ ሁሉ በእኔ ላይ ከሚፈፀም በተባረከችው በእናቴ ማህፀን ውስጥ ደም ወይም ውሃ በቀረሁ ነበረ >> በማለት ተዋነይ ቅኔ ተቀኘ ይህ ቅኔው ነው እንደ ንስሐ የተቆጠረለት ይህን ቅኔ ከተቀኘ በኋላ በደጃፉ ላይ የቀበረውን እፀ ሂወት እንዲያወጡት ዘመዶቹን አዘዛቸው ከዛ ለ7 ዓመት የተኛበት አልጋ ላይ አፈር ሁኖ ተገኘ ።
Open in Telegram"ማለቴ የዘንድሮ ልጆች ደረቆች ናቸው ለምን ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው እንኳ ጠንቅቀው አያውቁትም ዋላ ሰበብ እንዳይሆንብህ "አሉ ይርጋ የጓደኛቸውን አይበገሬነት ቢያውቁትም እንደው ለማለት ያህል የሁለቱንም ንግግር ሲሰሙ ቆይተው አቶ የሱፍ የሃይላንድ ውሃቸውን ጥጥት አደረጉና "እንደኔ እንደኔ ይህ ልጅ ኩርኩም ብቻ ነበር የሚያስፈልገው እንደው ልምድም ያለው ሌባ አይመስለኝም እንደው ስራ አልሆን ሲለው አሳቡን ቀይሮ በዚ ካለፈልኝ ብሎ ይመስለኛል፡" አሉ "እሱ ግን አሁን እናንተ እንደምትሉት አይደለም ሁኔታው፡!"አሉ አቶ ይፍሩ አሳስቧቸዋል እንዴት አድርገው ነው የሚያውጣጡት በምን መልኩ ይህን ልጅ አንድ ነገር ቢያረጉት የላከው ሰው ኖሮ የበለጠ ጉዳዩ ቢከርስ ከየት ነው የመጣብኝ ?... === ሲፈን ቤት ውስጥ ከናቷ ጋር ተቀምጣ ታወራለች፡ሰሞኑን ሁሉ ባለጭንብሉን ካየችበት ቀን ጀምሮ ተረብሻለች፡ ያ ሊደፍራት የታገላትን ሁኔታ ሁሉ ላለማስታወስ ጥራለች ፡ከዛ የበለጠ ግን እያሳሰባት ያለው፡ አባቷ ልጁን በትክክል እንዳሉት ለቀውት ይሆን ወይ የሚለው ነው፡አባባ የዛን ያክል ተናዶ እንዴት ነው እንደተራ ነገር በቃ አንተ ባለጌ ወደቤትህ ሂድ እንደማለት አይነት የሚሸኙት ምንም አልተዋጠላትም እናትም በዚ ጉዳይ እርግጠኛ አደሉም ግን ክፉ ነገር እሰከሚያደርሱበት ሳይሆን የሚገባውን ቅጣት ሰጥተው እንደሚለቁት ነው የተሰማቸው "እማ ይመስልሻል፡አባባ እንዲ በቀላሉ የሚተወው ? "የኔ ቆንጆ አባትሽን ክፉኛ መጠርጠርሽ ተገቢ አይደለም !ምን ያደርገዋል ብለሽ ነው፡እኔ አባትሽ ሲገባ አይቼዋለው ከመናደዱ በስተቀር የተለየ ነገር እንዳረገ ሰው አልነበረም፡ሲፈኔ ተይ፡በቃ እርሺ ስለዚ ነገር!" "እማ አዎ ልጁ ችኩል ቢጤ ነበር እሱ አይካድም ፡ግን እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ይገባዋል፡ብሎ ውስጤ በፍፁም ሊነግረኝ አልቻለም፡እማዬ እኔ ጭንብሉን ሳወልቅበት ያየውት ፊት እንደው በድፍረት ተነሳስቶ እንጂ ልምድም ያለው አይመስለኝም!" አለች ሲፈን "እንዴ አባትሽ ነብሰ ገዳይ መስሎ ታየሽ እንዴ!?ደሞ ሊደፍርሽ ለነበረ አንድ ዱርዬ የምን መራራት ነው ፡ምንድነው ነገርሽ ከዚ በፊት እንደሚያውቀው ሁሉ የምትሆኚው ምን አገባሽ!"የሮዛ እናት ቱግ አሉ "እማዬ እኔ ስለማውቀው ስለማላውቀው አደለም፡ እሱ እንደ ደፋሪም አይደለም እኔነኝ በመታገሌ ለፀብ ያነሳሳውት !"አለች ሲፈን ግራ በገባው እኔታ "እሰይ አሁን ገና ጉድ መጣ!አጥር ዘሎ ውሾች ገሎ ቤትሽ ድረስ ገብቶ በላይሽ ሊሰፍር የነበረው ለፍቅር ነበር እንዴ ሆሆሆ ምን እያልሽ ነው?" "እማዬ እኔ በርግጥ ጥፋተኛ አይደለም እያልኩሽ አይደለም፡ልጁ ግን አጋጣሚ ሆኖ እነጂ ለኔ ብሎ አይደለም የመጣው ፡ለዘረፋ ነው በቃ!" "እንግዲ ዘረፋው አንቺንም ያካተተ ነበር አፍኖ በርሽን ዘግቶት ነበር!" "አዎ እማዬ አሁን ስለተፈጠረው ነገር አይደለም ፡ስለ ባለጭንብሉ ልጅ ነው በሕይወት ነው ወይ የተለቀቀው እሱን ማወቅ እፈልጋለው!"አለች ሲፈን ቁርጥ ባለ ቃል "እሺ ይፍሩ ገድሎታል ነው አሳብሽ፡ምንድነው አንቺ ልጅ?!"ቆጣ ብለው "እሱን አላልኩሽም፡ግን ትክክል የሆነ ነገር እየሸተተኝ አይደለም !"አለች ሲፈን ፊቷን ቅጭም አድርጋ "እንግዲያው ይሄን ሽታ የፈጠረብሽ ያ በሽተኛ ልጅ ነውና እንፍ ብለሽ አስወግጂው፡አባትሽንም ያለ አግባብ መጠርጠርሽንም አቁሚ !" "ምክንያት አለኝ !" "ደሞ ምንድነው ምክንያትሽ ?"ተናደዱም ደነገጡም "ክንዴ ከዛን ለት ጀምሮ በጭራሽ አላየውትም ፡ድንገት ስራውን ለቀቀ ተባለ ፡መቶ እንኳ አልተሰናበተንም ሲሄድም አላየነው ፡ወዲያው ወደማታ ሌላ ዘበኛ ተቀጠረ !እንደገና የዛን ለት ማታ ልብ አላልሽ እንደው እንጂ አባባ ልብሱ ደም ነበረበት እጁ እስካሁን ቆስሏል በመጠኑም ቢሆን እኔ ስገምት ልጁ አንዳች ነገር ሆኗል ክንዴ ደሞ ያውቃል ስለዚ የሱ እዚ መኖር አስፈላጊ አይደለም ለምን አይታይሽም እማ፡አባባ ልክ አይደለም ችግር ውስጥ ነው!!"አለች ሲፈን ውስጧ ያለውን እየተነፈሰች "አንቺ ልጅ እንግዲያው ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም፡ ማንም ሰው የሰው ቤት በውድቅት ሊት ሰብሮ ሲገባ የማባበል ግዴታም የለብንም ፡ይሄ ድፍረት ነው፡የተከበረ ቤት ነው መሪ ያለው ፡ይፍሩን የመሰለ አባወራ ያለው ምነካት ልጅቷ አጉል ሚዛናዊነትሽ አልተዋጠልኝም !" "ኧረ እማዬ፡ይህ ልጅ እንደኛ ወላጅ ይኖረዋል "ምን ዋጋ አለው ወላጅ ሁሉ ወላጅ ነው እንዴ ? "እማ ከመቼ ጀምሮ ነው ጨካኝ የሆንሺው?" ሮዛ፡ወደውስጥ ድንገት ገባች"እእ ማሚን ጨካኝ ሲፍ ማሚን?ይሄኔ ለፍራንክ ብለሽ እኮ ነው!?"አለቻት ሲፈን ደንገጥ ብላ ወሬዋን አቋረጠች ቀስ እያለም ቤቱ በቆነጃጂቶች ደመቀ አራቱም እህታማቾች እየተቀላለዱ ማሽካካት ጀመሩ ካካካካካ".... ===== ክንዴ የመረረው ይመስላል ይህን ልጅ ሲጠብቅ ሳምንት አለፈው አቶ ይፍሩ ለማየት የቀፈፋቸው ይመስል፡ወደዚም ድርሽ አይሉ ብቻ አሳባቸውን በስልክ ማስተላለፍ ብቻ ትንሽ ምግብ ስጠው ውሃ ስጠው ጎሸም እያደረክ ማን እንደላከው አውጣጣው ፡እምቢ ካለ እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገህ ግረፈው 'እንዴ እኔ ደከመኝ አሁንስ እኔ እራሱ እየተደበደብኩ መሰለኝ ኧረ ክንዴ እሱ በዱላ ያደገ ይመስል አይሰማው ደነዝ ኧረ ሰለቸኝ !ይላል ክንዴ እጁን እያሻሸ "ስማ ጭንብሌ እኔ የምለው ሰው ነህ እንዴ? እንደው ምን አለበት ማን እንደላከህ ተናግረህ፡አቶ ይፍሩም ሌላ ተደብዳቢ ቢያመጡ፡አንተም ከዚ በዋላ በዱላ ብዛት መልክህ ከሚጠፋ ባይጠፋ!እኔም ሌላ ተደብዳቢ እስኪመጣ እረፍት እንድወስድ ብትረዳኝ፡ኧረ ባክህ ባክህ!!" አለ ክንዴ እንደማሾፍ እንደመናደድም ብሎ ወጣቱ ያባበጠ ፊቱ የሸፈነበትን አይኑን በስቃይ እያቁለጨለጨ "ማንም አላከኝም አልኩ እኮ እእ ግግን አአንተ ከጌታህ የየበለጠ መጥፎ ሰው ነህ የማይገባህ እራሴ ነኘ የየራሴ አዛዥ አልኩ እኮ አንተ ባባሪያ ለለፍርፋሪ ብብለህ ነነብሴን ልልታወጣኝ ነው ከከውሾቹ ጋጋር በበገደልኩህ ሰሰው መስለኽ......"ባለጭንብሉ ተናግሮ ሳይጨርስ ክንዴ ተነስቶ በፍጥነት አቶ ይፍሩ በመቱት ብረት አናቱ ላይ ሰነዘረበት !ባለጭንብሉ ከዱላው አይለኝነት የተነሳ ከመሬቱጋር ተጋጨ ፡አይኖቹ ብዥዥዥ .....ጭልምልም መሞቴ ነው እንዴ አለ በሰመመን ውስጥ እናቱ ወይዘሮ ፅጌ ታዩት ወፍራም ቀይ ፊታቸው ሲፀይም እማማ እማማ ይቅርታ እእእአባዬ አባዬ ዳመና የጋረደው መሰለው ፀጥጥጥ ጥቁርቁር ........ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ....ዘበኛው ባለ ጭንብሉን ደጋግሞ አጠገቡ እየመጣ መንቃት አለመንቃቱን ያረጋግጣል፡በእግሩም ነካ ነካ ያደርገዋል፡ወጣቱ ያለምንም ድምፅ ፀጥ እንዳለ ነው፡ዘበኛው፡ሆሆሆ እሬሳ ስጠብቅ እያመሸው ላንጋ እንዴ፡አቶ ይፍሩ ግን ግፋቸው፡ከልክ ያልፋል፡አሁን ይሄን እሬሳ ከምጠብቅ ፡እነዛን ቆነጃጂቶች፡ በሄዱበት፡እየሄድኩ ብጠብቅ፡ብሎ ለራሱ ፈገግ አለ ፡ መልሶ ወደ ወጣቱ ጠጋ ብሎ ትንፋሹን አዳመጠ አለ በሕይወት አለ ግን ባይኖር ይሻላል በድመት የተያዘች አይጥ ነው ነገሩ 'አቶ ይፍሩ እንደው መቼም ከዚ ጊቢ በሕይወት አያስወጡትም እኔም ፈርዶብኝ ቅበር መባሌ አይቀር አሄሄ እኔ ለራሴ! እያለ ዘበኛው ብቻውን ይለፈልፋል ሰአቱ ይነጉዳል ባለ ጭንብሉ እንደ ተጋደመ ነው ዘበኛው ብዙ ሲጠብቅ ስለቆየ ሰለቸው እንቅልፍ እንቅልፍ ሲለው ወደ ወጣቱ ቀረብ ብሎ እጁን ያሰረበትን ገመድ ድጋሚ አጠባበቀው እናም ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ ብዙ ነገር አመላለሰ በሃሳቡ እንደው ይህ ልጅ ምን ፍለጋ ነው ከዚ የመጣ? ገንዘብ ፈልጎ ይሆን ወይስ ቆንጆዎቹን ኧረ እዲያ እቴ ደሞ አገር ምድሩን በሞላ ቆንጆ ምን ይሁነኝ ብሎ ነው እንደ መጋኛ በለሊት የሚመጣ አያደረገውም! እንደው ሌላስ አላማ ኖሮት ቢሆን አቶ ይፍሩ ማነው የላከህ ብለውትም አደለ ፡አሃ ምናልባት እሳቸውን ሊገድል ይሆን እንዴ' ኧረ ! ትልቅ ሰው ይገደላል !እንደው ምን አይነቱ ደፋር ነው፡እንደው ምናምኒይቱን አጭሶት ይሆን እንዴ እንዲ የጀገነው፡ ድንገት ከአሳቡ ተናጠበ "እእ ውሃ እባካቹ ው..ሃ"አለ ባለጭንብሉ እንደመንቃት እያለ እና ሊወድቅ የደረሰ የመሰለውን ጭንቅላቱን በታሰረው እጁ ለመንካት እየጣረ "አሃ አንተ ሞት እምቢ ነቃህ፡!"ብሎ ዘበኛው ውሃ ይዞ ተጠጋው ፡"እሺ እኔው ላጠጣህ መሰል አንተማ አቅሙን ከየት አምጥተኽው ጎበዝ ምን ልበልህ ቸገረኝ!"ብሎ እያለመጠ ውሃውን አጠጣው፡እናም እየጠጣ አቋረጠበት "አሃ ፍጆታ የሚባል ነገር አለ ወንድሜ! አለው፡ባለጭንብሉ ቅጣቱ ከሚገባው በላይ የተጋነነ መሰለው "አንተ የማትረባ እንቅልፍህ አልመጣም!"አለው ባለ ጭምብሉ እልህኛ ነው "ዋላስ ከዚም በቀላሉ ለታመልጪኝ ነው አንቺ ትንኝ አታደርጊውም ግን እንደው ይሄን የለሊት ጉዞ ከየት ተማርሺው በይ!?" አለ ዘበኛው እያለመጠበት ፡ወጣቱ ይበልጥ ተበሳጨ "አንተ የማትረባ ፡ይሄን ገመድ ከላዬላይ ፍታ ልቀቀኝ"አለ በእልህ እየተወራጨ "ይህ የአባወራው ትህዛዝ ነው፡እናም እኔ ከሳቸው ብቻ ነው ትእዛዝ የምቀበለው አባብለህ አስተኛው ካሉኝ አስተኛሃለው ዝፈንለት ካሉ እዘፍንልሃለው ዘምርለት ቢሉም፡እዘምርልሃለው ቅበረውም ካሉ እንደዛው መቼስ ስራ አይደል!"አለ በማልመጥ "ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ!" አለ ባለጭንብሉ የበለጠ ሊሰድበው ቃላት እየፈላለገ "አይጥ ድመትን ለጫወታ ትጋብዛለች ደሞ ካንተ ጋር የሚሄድ ተረት ነው፡ሀሀሀሀ እኔ የምለው፡ቀን ላይ የሆነ የጀግና ፊልም አይተህ ነበር እንዴ በለሊት ካልሲህን ቀደህ አናትህ ላይ አጥልቀህ የመጣኽው ሀሀሀሀ ሲያረጉ አይተሻል እንደው እመጣለው እንኳ አይባልም ሀ.ሀ.ሀ..ሀ የማትረባ ዱርዬ !" ብሎ ዘበኛው በርግጫ ከቆሰለው ፊቱ ላይ መታው፡ ባለ ጭንብሉ ወደኋላው ፍንግል አለ ዘበኛው መምታቱ ያስደሰተው ይመስል ፡ደጋግሞ እረገጠው ወጣቱ ስቃዩ በረታበት በቁስሉ ላይ የሚሰነዘረው ዱላ በጣም አሳመመው ሞቱን እስኪመኝ አሳለው አቃሰተ ተሰቃየ ዱላው ቀጠለ...... ==== አቶ ይፍሩ እራት ላይ አብረዋቸው የቀረቡትን አራቱንም ልጆቻቸውን በስስት እየተመለከቱ ፡ሁኔታቸውን ይከታተላሉ ፡ሮዛ 26 አመቷን ይዛለች ራሄል 23 ሲፈን 21 ሊያ 16 ይገረማል ልጆቼ አሁን ሁሉም እኩያ እስኪመስሉ ተቀራርበዋል፡አንድ ወቅት ሁሉም የሚ ያስቸግሩ እፃናት ነበሩ ዛሬ ላይ መኩሪያዬ ሆነዋል ተመስገን ምንም ነገር ስለናንተ ነው የማደርገው በዚች ምድር ላይ እስካላቹ ሁሌም የሚገባችሁን ማግኘት አለባቹ እሱን ለመስጠት ስለናንተ የማይታለፈውን ሁሉ አልፋለው እኔ እኔ ነኝ ይፍሩ አባታቹ አሉ በኩራት በውስጣቸው ያንን ውሻ ግን ማን እንደላከው ካላወኩ እንቅልፍ አይኖረኝም ፡በጭራሽ ሲፈኔን ነክቶብኝ ይሆን እንዴ እናትና ልጅ የደበቁኝ ነገር ይኖር እንዴ?አይደረግም እንደዛ አድርጎ ከሆነ ፡እንትኑን ቆርጬ አሰቃይቼ ነው ማጠፋው አይማረኝ ከማርኩት፡ሌሎቹ ልጆቼ ሰለተፈጠረው ነገር አለመስማታቸው ጥሩ ነው እንዲያ ባይሆን ኖሮ ከፊታቸው ደስታ በራቀ ነበር ስለ ጉዳዩ መስማት የለባቸውም እያሉ እያምሰለሰሉ ፡ወደሲፈን በትኩረት አዩ ዝምታ በዝቶባታል እናትየውም እንደዛው የናቲቱ እንኳ ችግር የለውም፡ልጄ እኔ ልሸማቀቅ ብለው ተቆጩ በጣም "ሲፈኔ አንዴ ትመጪ ላናግርሽ "ብለው ተነስተው ከሳሎን ወጥተው በረንዳ ላይ ከተቀመጠው ወንበር ቁጭ አሉ ፡ሲፈን እየተጎተተች ሄዳ አጠገባቸው ተቀመጠች "ሲፈኔ ዝምታሽ በረታብኝ እኮ ፡ምነው የደበቅሺኝ ነገር አለ ከዛን ለቱ ሁኔታ ንገሪኝ ሳደብቂ አባትሽ ነኝ!?" "አይ አባዬ ምንም አልደበኩህም ከማስፈራራት ሌላ ነገር አላረገኝም እንደዛ ቢሆን አውጥተህ ስትለቀው ዝም የምል ይመስልሃል!ሲፈን እኮ ነኝ !"አለች በማረጋገጥ "ሀሀሀሀ ያባቷልጅ የኔ ልዩ አንቺን ምናለ ፈጣሪ ወንድ ባደረገልኝ!"አሉ አቶ ይፍሩ "አይ እንግዲ አባባ !አንቺን ሰው ያርግልኝ ነው የሚባለው ሰው መሆን በቂ ነው! ፆታ አያመፃድቅምም፡ አያሳፍርምም ፡የሁሉ ሰሪ እሱ ብቻ ነው፡!"አለች ሲፈን ኮስተር እንደማለት ብላ "እሰይ የኔ አዋቂ የኔ ጀግና ልክ ነሽ !" "አባባ የዛን ለት እውነት ባለ ጭንብሉን አውጥተህ ነው የለቀቅከው ምንም አይነት ቅጣት አላደረስክበትም ?" "አዎ የኔልጅ ከሱ ጋር ምን አላፋኝ የፈለገው ተራ የስርቆት ጉዳይ ለመከወን ነበር ስለዚህ ጥቂት ጎሸም አደረኩትና ለቀቅኩት፡" "ከሆነ ጥሩ ነው፡ግን ደሞ ስህተትም አለብህ የግድ ቤትህን ሰብሮ የገባን ሌባ ጎሻሽሞ መልቀቁ አልታየኝም፡ለፖሊስ ማስያዝ ነበረብህ!"አለች ሲፈን በቁጭት የአባቷ ድርጊት አልዋጥ እያላት "እኔ በወቅቱ እሱ አልታየኝም ፡ሲፈኔ አሁን እሱን ተይውና ይልቅ እንደፊቱ ተጫዋችነትሽን አምጪው እህቶችሽ ግራ እንዳይጋቡ ደሞም መቼም እንዳይሰሙ!" "ኧረ አባባ እነሱ መቼም አይሰሙም እንኳን ይህን አውቀው እንዲሁም ፈሪ ናቸው !"አለች ሲፈን ፈገግ ለማለት እየሞከረች፡አቶ ይፍሩ በልጃቸው፡ ሁሌም እንደተደመሙ ነው ትለያለች ሲፈን ይላሉ አስተዋይ ናት ቆንጆ ናት ፡ተወዳጅ ናት... ======== አቶ ይፍሩ ኮራ ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር እየተገባበዙ ከአንድ ግሮሰሪ ተቀምጠዋል ወሬያቸው ሁሉ ስለ ባለ ጭንብሉ ወጣት ነበር ሁለቱም ጓደኞቻቸው ከሳቸው ጋር በሚስጥር የተሳሰሩ ናቸው ነገርግን ለመጀመሪያ ጊዜ በባለጭንብሉ ምክንያት አቶይፍሩ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል ማነው ከሁለት አንዱ የከዳኝ ወይስ ያልጅ ተራ ሌባ ነው! ግን እንዴት ሙሰኛ አጭበርባሪ፡ሊለኝ ቻለ እያሉ በጨዋታቸው መሃል ግራ በመጋባት ያይዋቸዋል ከግንባራቸው ይነበብ ይመስል አቶ ይርጋ ሜታ ቢራቸውን ጎንጨት ብለው "አና ይፍሩ ልጁን ከቤትህ አስረህ ማቆየትህ ተገቢ ነው!"አሉ "አሃ ማንነቱን ሳታውቅ ልቀቀው ነው የምትለኝ?"አሉ ቆጣ ብለው አቶ ይፍሩ።
Open in Telegramአንድ ቪዲዮ እያየሁኝ ነበር 👇🏾 አሜሪካ የሚኖር ጋናዊ ሹፌር ነው: እድሜው ገፍቷል "ለወጣቶች ምን ምክር ትሰጣለህ?" ተብሎ ሲጠየቅ 👇🏾 አንዳንዶች በጠዋቱ ስኬታማ ይሆናሉ . አንዳንዶች ደግሞ ስኬታማ የሚሆኑት ከሰአት በኃላ ሊሆን ይችላል . ለአንዳንዶች ስኬት ምሽት ላይ ትመጣለች Everyone has his/her own time Wait for your time 👇🏾 የአንተ ጊዜ ይመጣል!! ❤️🙌🏼
Open in Telegramማስጠንቀቂያውን አብዝተው አስተላልፈው ወደነ ሲፈን ተመለሱ:: ማነው የላከብኝ? ማን.. ማን....... ======= የጠዋት ፀሐይ ከወደ ምስራቅ ብቅ እያለች ነው ፡ሰውም የተለመደ ስራውን ለማከናወን ነቃ ነቃ እያለ ነው ፡እትዬ ፅጌም በላስቲክ ቆሻሻ ይዘው ወደገንዳው በመድፋት ወደቤታቸው ያገኙት የጎረቤት ሰው ደና አደራቹ እያሉ ሰላምታ እየሰጡ ተመለሱ ፡ወደ ውስጥም በመግባት "ኤዶም ኤዶሜ አንተ ተነስ አስኪ ይበቃል ወንድምህንም ቀስቅሰው፡!"እያሉ ተጣሩ ከመንትያ ልጃቸው አንዱን "እእ እሺ እማ እየተነሳው ነው "አለ ኤዶም እትዬ ፅጌ እጃቸውን እየተጣጠቡ ያ እብድ ወንድምህ ምነው ዛሬ እንቅልፋም ሆነ!"አሉት ኤዶም መጥቶ ከፊታቸው ሲቆም "አይ አይ እማዬ አዳም ትላንት ወደ አምስት ሰአት አካባቢ እነ ብሩክ እየጠበቁኝ ነው ብሎ ላንቺ እንዳል ነግርሽ አስጠንቅቆኝ ነው የወጣው ስገምት ብሩክ ጋር ነው ያደረው "አለ ኤዶም "ኧረ እንዴት በል ደውልለት ከሆነም " እሺ ብሎ ሞባይሉን አንስቶ ደወለ ፡ብሩክ አንስቶ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ "አዳም አነተጋር ነኝ ብሎነበር ?" "ኧረ በጭራሽ አላገኘውትም" "እውነት" "አዎ እኔጋር አልመጣም" "እሺ ብሩክ ደናዋል"ብሎ ዘጋው ወደናቱ ተመለከተ፡እናት ተጨነቀች "ለምንድነው በራሱ ስልክ የማትደውለው " "አይሰራም"አለ ኤዶም ፍርሃት ፍርሃት እያለው "ልጄ የፈለገ ቢያመሽ አድሮ አያውቅም አባትህ ጋር ደውል!" "አባባ ወጥቷል እንዴ?ግን እማዬ ይቅር ይደነግጣል ትንሽ እንጠብቅ !"አለ ኤዶም፡ እትዬ ፅጌ ተረበሹ መንትያው የት ነው አዳም የት ነው ያደረው እንዴት በለሊት ወጣ.. የት ነው መንትያው?...እትዬ ፅጌ ግራ ግብት ብሏቸዋል ፡አንዴ ይቆማሉ አንዴ ይቀመጣሉ፡ይወጣሉ ይገባሉ፡መላ አተዋል ፡'የት ገባ ይባላል !በጨለማ ሲጓዝ አንዱ ደፍቶብኝ ይሆን !እንደው ምን አድርገውት ይሆን፡እንዴት በጤናው አድሮም ቀኑን ሙሉ ሳይመጣ ይቀራል፡አንዳች ነገርማ አለ!'እያሉ በጭንቀት ያምሰለስላሉ ፡ኤዶም ቆይቷል ከቤት ከወጣ ወንድሙን ፍለጋ ፡የአዳም ጓደኞችን ሁሉ ካሉበት ድረስ እየሄደ ፡ጠይቋል ግን አንዳቸውም አየነው አላሉትም፡ ኤዶም ገራገር ቢጤ ነው፡ በዛላይ ብዙም ከሰው ጋር አይቀርብም፡ ትንሽ ትንሽም አይናፋርነት አለችበት፡ ከወንድሙ አዳም አንፃር፡ተቃራኒ ነው፡ አዳም ሁሌም ሊያበሳጨው ሲፈልግ፡ 'አንተ ጅል፡እኔና አንተ አንድ ቦታ መሰራታችንን እጠራጠራለው፡መልክህ እኔን ከመምሰሉ ውጪ በጭራሽ ውስጣዊ አሰራራችን ይለያያል!'ይለዋል ፡ኤዶም ለሱ መልስ ሳይሰጥ 'እማዬ አየሺው እንዴት እንደሚናገረኝ ይሄ ስረሃት አልባ ልጅሽ፡አንቺ ነሽ እያቀበጥሽ ፡እንደፈለገ እንዲሆን የምታደርጊው፡ አፉን አዘጊልኝ አለበለዚያ ...!'ይላል ወደ እናቱ እያየ አዳም በማልመጥ እያሽካካ'ኧረ ሼባው አልቀረቦትም ልታስፈራራኝም ያምርሃል !' ይለዋል ፡ኤዶም እንዲም ሆኖ ግን፡መንትያውን ከልቡ ነው የሚወደው፡ ለዛም ነው፡ብዙ ችግሮቹን የሚሸፍንለት ፡ሲመሻሽ ተነስቶ መውጣቱን ከቅርብጊዜ ወዲ የተለመደ ቢያደርገውም፡ ኤዶም ጨርሶ ለወላጆቹ ነግሮ አያውቅም፡ሊነጋጋ ሲል ሲመጣ፡ቀስብሎ በር ከፍቶ ያስገባዋል፡ ዛሬግን አዳም አልመጣም፡ ስልኩ እንኳ ዝግ ነው፡ኤዶም የት ብሎ እንደሚፈልገው ግራ ገባው እሱ የሚውልበት አይውል፡ እንዲው ቢጨንቀው መንገድ ለመንገድ ሲዞር ውሎ ወደቤቱ ተመለሰ ፡እትዬ ፅጌ ኤዶም ሲገባ ብድግ ብለው ቆሙ "ኤዶሜ ምንም አላገኘህም!አየው የሚል ጠፋ ልጄን? ነው የደበከኝ ነገር አለ እባክህ !" ብለው አስጨነቁት "እባክሽ ፅግዬ፡ልጄን አታስጨንቂው፡ኤዶም አዳም ከሚውልበት አይውል፡ደሞስ አንድ ቀን ቀረ ብለሽ፡ምን እንዳይሆን ነው ወንድ ልጅ አደል እንዴ፡እስኪ ተረጋግተን እንጠብቅ!" አሉ የመንትዮቹ አባት አቶ አይሉ "አንተ ዝም በለኝ መጥተህ አንድ መፍትሔ ታመጣለህ እላለው እዚ ተጎልተህ ምን እንዳይሆን ነው ትላለህ እሬሳውን እስኪሰጡኝ ነው የምጠብቀው !" "እባክሽ ፅጌ ተይ ካልሆነ ካልሆነ ነገ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ አመለክታለው!"አሉ አቶ አይሉ ለሚስታቸው እየተጠነቀቁ፡ "ኧረ እንዴት ልሁነው ልቤ አንዳች ነገር እንዳለ ነው የሚነግረኝ"አሉ እናት ሆዳቸውን ጭምቅ እያደረጉ፡ኤዶም በናቱ ሁኔታ አዘነ ሄዶ አቀፋቸው"እማ ይመጣል አይዞሽ ፈጣሪ ያውቃል !"አለ ፡ግን ይህን ይበል እንጂ ውስጡ ፈርቷል፡ይሄ በድብቅ በለሊት የመውጣቱ አባዜ፡አንድ ቀን ችግር እንደሚያመጣ ጠርጥሮ ነበር፡ በራሱ አዘነ ይህን ሁኔታ ለወላጆቹ ነገሮ ማስቆም ነበረበት፡የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው፡እራሱንወቀሰ የኔ ስህተት ነው፡አለ፡ኤዶም "እንደው አይልዬ ለምን አሁኑኑ ከኤዶሜ ጋር ፖሊስ ጣቢያ ሄዳቹ አታመለክቱም?!" አሉ እናት "አይ ፅግዬ እነሱም እኮ አካሄድ ይኖራቸዋል ዛሬን አድረን ነገ ሁኔታውን አይተን ይሻላል እሺ በይኝ ፅግዬ እናቴ!"አሉ አቶ አይሉ ሚስታቸውን በፍቅርና በጨንቀት እያባበሉ ሚስት ባይዋጥላቸውም እሺ አሉ ፡እናም እጥፍጥፍ ብለው ዱካ ወንበር ላይ ተቀመጡ ፡ልጄ እምን ውስጥ ገብተህ ይሆን ...ልጄ.....አዬ ጉዴ ....ብቻ ክፉ ነገር አታሰማኝ... ፈጣሪዬ ....ፈጣሪዬ.......እህህህ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ ...የበሩ መንኳኳት ከሚገባው በላይ አሰለቸው ፡ተቅበዘበዘ ፡እቺ ሴትዮ ምንድነው እንዲ ችክ የሚያረጋት ፡በቃ ተኝታለች፡ለምን አትሄድም፡እንዴ በለሊት እየዞረች ምን ያስረብሻታል፡ፀጥ ካለች ተኝታነው ብላ አትሄድም እንዴ!! ኳኳኳኳኳኳኳ....... ፈጣሪዬ ትዕግስቴን ልታስጨርሰኝ ነው አለ በውስጡ ሽጉጡን በጎን በኩል ከራስ ፀጉሩ ላይ እያሻሸ ፡አልፎ አልፎ ሁሌም ጭንቅ ሲለው እንደሚያደርገው በግራ እጁ ጀሮውን ሳብ ሳብ ያደርጋል፡ የሮዛ እናት ወይ ፍንክች ፡ልጃቸው ሲፈን በሩን የዘጋችበትን ምክንያት ሳያውቁ እንዴት ይተኛል ያሉ ይመስላል ፡አዲስ ነገር ነዋ ፡ኳኳኳኳኳኳ .. ባለጭንብሉ ቱግ አለ ፡ሽጉጡን በበሩ ትክክል ደቀነው፡ሲበሳጭ፡እንዲ ነው፡ለውሳኔ ይቸኩላል፡ ሲፈን በድንጋጤ ቃላት አመለጣት "በፈጠረህ!"ብላ ለእናቷ ለመከላከል ጮኸች ፡ባለጭንብሉ ክው አለ ወይኔ ይች የማትረባ ፡ብሎ ሽጉጡን አልጋው ላይ በፍጥነት አስቀምጦ ፡ፕላስተር በመፍታት አፏን ደፈነው፡እንደገናም እጅና እግሯላይ በችኮላ በፕላስተሩ አቆላልፎ ጠመጠመባት፡ሲፈን ድምፅ ለማውጣት ሞከረች፡ከደጅ የሮዛ እናት ማንኳኳታቸውን አቁመው ፀጥ ብለዋል ወዴት ገቡ፡ባለጭንብሉ ተጠራጠረ ፡ለምን ዝም አሉ፡የሲፈንን ድምፅ አልሰሙ ሆነው ነው፡ ወይስ ?.... ትንሽ በዚ ሁኔታ ከቆዩ በዋላ "ሲፈን ሲ ፈን"ብለው በሹክሹክታ ተጣሩ፡ባለጭንብሉ እሰካሁን የት ሄደው ነው፡በድንጋጤ ይሆን ዝም ያሉት፡ምናልባት በህልሟ የተናገረች መስሏቸው ይሆን ለማጣራት ብለው....እንደዛ አስበው መሆን አለበት ብሎ ተመኘ ፡ቀስብሎ ጭንብሉን በማንሳት አጠለቀው ሽጉጡን ያዘ እናም በሩን ከፈት አደረገው የሮዛ እናት በተከፈተው በር ዘው ሲሉ ባለጭንብሉ በፍጥነት አናታቸውን በሽጉጡ ጫፍ መቶ ጣላቸው ፡ሴትዮዋ ከአልጋው ጋር ተገጫጭተው መሬት አረፉ ሲፈን የታፈነ የስቃይ ጩኽት አሰማች፡ባለጭንብሉ ወደሴትዮዋ አጎነበሰ፡በዛው ፍጥነት ፡ከደጅ የሚያርበደብድ ወፍራም አስፈሪ ድምፅ ተሰማ "እንዳትነቀሳቀስ ባለህበት ሆነህ ሽጉጥህን ጣል፡!!"አቶ ይፍሩ ነበሩ የሲፈን አባት የቤቱ አባወራ፡በደንብ የተዘጋጁበት ይመስላል ፡የሮዛ እናት በትክክል የልጃቸው ሲፈንን ድምፅ በትክክል መስማታቸውን፡እና ባለቤታቸውን እንደቀሰቀሱና እንዳዘጋጁአቸው፡ባለጭንብሉ ተረዳ፡በራሱ በሸቀ፡ሽጉጡን ወደጎን ወረወረው ፡አቶ ይፍሩ ግዙፍ እና ደንደን ያሉ የ55አመት ጠንካራ ሰው ናቸው ፡ሽጉጡን ጠጋብለው፡ በእግራቸው በመምታት ወደ አልጋው ስር አስገቡት ባለጭንብሉ ተሰፋ ቆረጠ "ተነስ አንተውሻ እንዴት አባክ አድርገ እዚ እንደገባህ ትናገራለህ፡እገልሃለው!፡ ውጣ !"አሉ በጣም ተናደዋል እንዴት ተደፈርኩ በሚል ስሜት ጨሰዋል፡ባለ ጭንብሉ በተሸናፊነት ስሜት፡አንገቱን አቀርቅሮ፡ወጣ አቶ ይፍሩ ባለቤታቸውን፡ተመለከቱ ለክፉ አይሰጡም፡ወደልጃቸው፡አዩ፡ግን ለጊዜው፡የሚቀድመው፡ የባለጭንብሉ ጉዳይ ነው፡ማነው የላከብኝ፡በቅርቡ በህገወጥ መልኩ አንድ ቢዝነስ ፡ሰርተዋል ከጓደኞቻቸው ጋር፡ግን ለምን ሶስታችንም፡በድርሻችን ፡አልተከፋንም፡አቶ የሱፍ ይሆን፡በጭራሽ፡ጠዋት አግኝቼው ነበር ፡ምንም አይነት ቅሬታም አላየውበት ደሞስ ለምን ቅር ይለዋል አይ አይ እሱ ሊሆን አይችልም ይርጋ ይሆን፡እሱም በድርሻው ተስማምቷል!! አይ ሊሆን አይችልም ይህ የዘረፋ ጉዳይ አይደለም ፡ይሄ ሴቶችን በመድፈር የሚረካ አንድ አለሌ ብቻ ነው፡የገንዘብ ጉዳይ ቢሆን፡የሲፈን ክፍል ምን ይሰራል ፡አዎ ይሄ ሴሰኛ በልጄ ላይ ነው የመጣው እንዴት ቢደፍረኝ ነው አያውቀኝማ!አሉ "አንተ ውሻ ይሄ የፊት ጌጥህን አንሳና በዚ በኩል ሂድ!"አሉት ግቢውስጥ ሲደርሱ ወደ ቀኝ በኩል ካለው በጊቢ ውስጥ እራቅ ብሎ ከሚገኘው መጋዘን እያሳዩት ፡ግቢው እንደዚ ሰፊ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየ መሰለው፡ በራሱ ከሚገባው በላይ አፍሯል የመጣበትን አላማ በመተው፡የተልከሰከሰበትን ሁኔታ ሲያስተውሰው እራሱን ጠላ'፡ምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባውት ፡እኚ ሰውዬ ከገመትኩት በላይ ክፉ ሳይሆኑ አይቀሩም ፡መጋዘን ውስጥ ሊቆልፉብኝ ነው ማለት ነው፡በቃ ጉድ ሆኛለው ፡የልጃቸው ሁኔታ እንኳ አልገረማቸው የናትየው እራሳቸውን ስቶ መውደቅም ቁብ የሰጣቸው አይመስልም የነሱን ደህንነት ሳያረጋግጡ እኔን አንዳች ነገር ለማድረግ ብቻ መቸኮላቸው ፡ጭካኔ ያቸውን ያሳብቃል፡'እያለ በውስጡ እያወራ ፊትፊት ሄዶ መጋዘን መሰሉ ቤት ጋር ደረሰ አቶይፍሩ በጥንቃቄ በሩን ከፍተው ወደውስጥ እንዲገባ አስገደዱት፡ወደውስጥ ሲገባ አይለኛ ቦክስ ሰነዘሩበት ወጣቱ ባለጭንብል ያላሰበው ስለነበር መቋቋም አልቻለም ወደቀ በወደቀበት ደጋግመው ፊት ለፊታቸው ባገኙት ብረት ሰባበሩት ፡ባለጭንብሉ በህመሙ መጠንከር የተነሳ ጮኽ ሁሁታውን አቀለጠው አፉን በቦክስ መቱት ጥርሱ የተነቃነቀ መሰለው፡ "አንተ ሌባ አንተ ሙሰኛ አንተ አጭበርባሪ ሽማግሌ!!"ባለጭንብሉ እልህ ያዘው ለመነሳት ሞከረ እዛው እረግጠው ያዙት"አጭበርባሪ ነው ያልከው ማነው የላከህ ፡ተናገር!!"አሉት አሃ ለልጄ ሳይሆን ለኔነዋ የመጣው ዱላውን አባሱት ፡ባለጭንብሉ በዱላብዛት በደም ተጨማልቆ እራሱን ሊስት ሆነ ያጠለቀውን ጭንብል ከፊቱ ላይ በማውለቅ አዩት ፊቱ ደም በደም ስለሆነ ማንነቱን መለየት አቃታቸው ወደጥግ በመሄድ በሀይላንድ የነበረ ውሃ አምጥተው ፡ፊቱላይ አፈሰሱት፡ውሃው ደሙን እያጠበው ወረደ ፡አሁን ፊቱን በግልፅ ማየት ጀመሩ ፡ይህንልጅ ሰሞኑን አይተውታል የመብራት ቆጣሪያችሁን ለማየት በሚል ሰበብ መጥቶ አዎ በትክክል አይተውታል፡እንደውም፡ እንደቤቱ ትልቅነት አይደለም ፍጆታቹ ብሎም አሰቋቸው ነበር፡አሃ አሉ አሃ ጥናት ላይ ነበርክ፡ልጆቼ ላይ ነው እኔ ላይ አንላቀቃትም፡አሉ አቶይፍሩ ፡ከደጅ "ማነው ማነው እዚ የገባ ሰው አለ !!"እያለ... ዘበኛው ወደመጋዘኑ ገባ "አፈር ጉድጓድ ግባ ቤቴ በሌባ ሲደፈር አንተ ተኝተሃል አንተም ውሾቹም አንድ ናቹ ቀለብ ብቻ!!"አሉ አቶ ይፍሩ "ኧረ ለወትሮ ውሾቹ ኮሽታ ሲሰሙ ይቀሰቅሱኝ ነበር !እእኔ በውነት በዬት አድርጎ እንደ ገገባ እእ ሁለቱም ውሾሾች ሞተዋልእእ !!"አለ እርብትብት እያለ "እነሱ ፍንችር ማለታቸውን ባይ ጊዜ እኮ ነው አንዳች ነገር እንደተፈጠረ በመጠርጠር ግቢውን ስዞር እርሶ ከዚ ነዎት!"አለ እንደጨነቀው አንዴ የወደቀውን ወጣት የት ነበር የማውቀው በሚል ለማስታወስ እየጣረ በሌላበኩል አቶ ይፍሩ የያዙትን በደም የራሰ ብረት እየተመለከተ ገለውታል በቃ አይተርፍም በሚል፡ጨካኔያቸውን እያደነቀ፡"አንት ውሻ ውሾቼን ገድለሃቸዋል ለዚ ጥፋትህ አሰከፍልሃለው!"ብለው ፊቱን ደግመው እረገጡት፡እናም "አንተ የማትረባ ይሄ ነገር ከኔና አንተ ውጪ እንዳይወጣ በጭራሽ ፡ነግሬሃለው ፡ገና ማን እነደላከው ሳይናገር በሕይወት ከዚ መጋዘን አይወጣም ፡በሩን በደንብ መዝጋትህን አረጋግጥ ፡አንተ ጠብደል ከዛሬ ጀምሮ የሱና የሱ ጠባቂ ነህ ፡ለጊቢው ሌላ ዘበኛ እቀጥራለው አንድም ሰው ወደዚ መጋዘን ድርሽ እንዲል እነዳታደርግ ፡አንተ እራስህ በፊለፊት ሳይሆን በዋላበር ነው መውጣት ያለብህ አስታውስ ፡አንዲት ስህተት ባይ ወዳንተ ነው የምዞረው ታውቀኛለህ!!"አሉ አቶ ይፍሩ በጭካኔ ፡ዘበኛው ክንዴ ደጋግሞ እሺ እሺ አለ አቶ ይፍሩን በፍርሃት እያየ እናም እሳቸውን ለማስደሰት ይመስል፡ባለጭንብሉን ሆድ ሆዱን እረገጠው ወጣቱ አጥወለወለው ማስመለስ ጀመረ ፡እንደማሳል አለ ፡ አቶ ይፍሩ "ይበቃል ትፋቱን ሲጨረስ ወደጥግ ወስደ አስረ አሰቀምጠው "ብለው
Open in Telegramተንቀሳቀሰች ፡ባለጭንብሉ "ቁሚ የማትረቢ ጨዋታውን አበላሸሺው እንቀሳቀሳለው ብትዪ እተኩሳለው !ተመለሽ አፍሽን ዝጊና ከነበርሽበት ተመለሽ!!"አለ ሽጉጡን ደቅኖ ሲፈን ወደነበረችበት ተመለሰች፡ይበልጥ እየተንቀጠቀጠች፡ለመነች ፡ባለጭንብሉ ፡የለበሰውን ካፖርት አወለቀው ካወለቀው በዋላ ኪሱ ውስጥ በመግባት ብላስተር አወጣ ብላስተሩን በመፍታት ባጭሩ ቆረጠው፡ "እባክህን ምንድነው የምትፈልገው ፡አንተማነህ ተው እኔ ምንም አልጮህም ተወው ፕላስተሩን.."አለች ሲፈን በልመና "አሃ ካንቺ ጋር የምስማማበት ምንም ምክንያት የለም ፡የምፈልገውን ላንቺ መንገርም አይጠበቅብኝም !!"አለ በቁጣ እናም የሱሪውን ዚፕ ፈታው ሱሪውን ወደታች ዝቅ በማድረግ ወደሲፈን በመጠጋት"ማንን እንዳስቆጣሽ አየሽ! ተመልከች !ተመልከች! ይህ እራስሽ የፈጠርሺው ግርግር ነው እና ስለዚ እራስሽ ታስተካክይዋለሽ!እይው እይው!"አለ ባለ ጭንብሉ በማስገደድ ፡ሲፈን ፡አለቀሰች ፡እንደመሸሽ እየለች ከአልጋው ኮርነር ተጣበቀች ፡ባለጭንብሉ እይ ምን እነደሰራሽ እያለ ተከተላት ፡አናም እግሯቿን ጎትቶ በመክፈት ወደራሱ አስጠጋት፡ፊቷን በተሸፋፈነው ፊቱ መተሻሸት ጀመረ ለማን ለምን ነካሽብኝ እንደዛ ማድረግ አነበረብሽም አለደጋግሞ ቁረጥ ቁርጥ በማል ድምፅ ፡ሲፈን ከእግሮቿ መሃል የገባውን ሰውነቱን ለመሸሽ ተንፈራፈረች እጆቿን ለመከላከል ወደፊቷ የቀረበውን ጨንቅላቱን ለማራቅ ስትጠቀምባቸው ድንገት ጨንብሉን ከፊቱ ላይ አወለቀችው፡ባለጭንብሉ ካሰበው ቅጣት ሳይደርስ በድንጋጤ ፡ተስፈንጥሮ ተነሳ ፡ሲፈን እግሮቿን በፍጥነት ሰብስባ ፡የባለ ጭንብሉን የተጋለፀ ፊት ላይ አፈጠጠች፡እሱም እንደዛው፡ በጣም ተናደደ ፡ፊቱን ስላየችው፡ እንደሚገድላት ዛተ በቃ፡በዝች የማትረባ ከምጋለፀ ፀጥ አድር ጌያት፡ ወደዋናው አላማይ መጓዝ አለብኝ ፡ብሎ ሽጉጡን በማንሳት፡ፊት ለፊቷ አቀባበለባት፡ሲፈን አለቀሰች መጮህ አማራት፡መልሳ እህቶቿን እንደምታጣ እንዲሁም ወላጆቿን የነገራትን አስታውሳ ድምፀጿን ቀንሳ እያለቀሰች ተማፀነችው፡ "እባክህ አትግደለኝ እባክህ የምትፈልገውን ሁሉ ውሰድ እኔ እረዳሃለው እባክህ!!" "አይ ፊቴን ማየት አልነበረብሽም ፡ብተውሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም፡አንቺ በሕይወት እድትኖሪ መፍቀድ በራሴላይ ታናዳፊ እባብ የመጠምጠም ያህል አደጋ አለው !ይቅርታ አድርጊልኝ! "አለና ትራስ ይዞ ተጠጋት የመሳሪያውን ድምፅ ለማፈን እንዲ ጠቅመው ሲፈን እንደ እፃን ልጅ እጇን ዘረጋች "በናትህ እኔ መሞት አልፈልግም እህት የለህም ..በበናት ትህ እእእእ መሞት አአአልፈ ፈልግምም እእእእ እፈራለው መሞ ት እእእእ በፈጣሪ ይ"ቁጭ ብድግ እያለች ለመነች ፡የባለጭንብሉን ቆንጆ እና ጠይም ምንም ወንጀለኛ የማይመስል ፊት፡ እያየች፡ "አይ ነገረኩሽ ባታይኝ ጥሩ ነበር "ብሎ በመጠጋት ትራሱን ወደፊቷ አቅጣጫ አደረገው፡ ምትለው ግራ ገባት በሕይወት ለመትረፍ ምን አይነት የመለመኛ ቃላት እንደምትጠቀም ጠፋት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጣ ተንዘፈዘፈች፡ በዛ በለሊት፡ ምን አይነት ሴጣን ነው፡ እሷን ብቻ መርጦ ሕይወቷን ሊነጥቃት የመጣው፡ ካሁኑ ቤተሰቦቿ ናፈቋት የእንስፍስፍ እናቷ ፍቅር የአባቷ ኮራ ያለ ትእዛዝ የእህቶቿ ውበት ከነሳቃቸው ከነጨዋታቸው እንባዋ የባስ ዱብ ዱብ አለ "ወንድሜ እባክህ እኔ እኔ.......እእእእ ከደጅ የእግር ኮቴ ተሰማ ባለጭንብሉ ትራሱን አልጋው ላይ ወርውሮ ወደበሩ በመሄድ በሩን ከውስጥ ቀስብሎ ዘጋው ፡እናም ኮቴው እየቀረበ መጣ " እናም ከሲፈን አጠገብ ያለው በር ሲጢጢ ብሎ ተከፈተ ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ የመዘጋት ድምፅ አሰማ ቀጥሎ ሌላኛው ክፍል ተከፈተ መልሶም ተዘጋ ፡ቀጥሎ የሲፈን ክፍል ተገፋ ባለጭንብሉ መውጫ ቀዳዳ አማተረ ምንም መደበቂያ አጣ ፡ኮስተር ብሎ ወደሲፈን በማየት አስጠነቀቃት ጠጋብሎም "አፍሽን ብትከፍቺ እንጨራረሳለን !"አላተ ቀስ ብሎ "እማዬ ናት ሁሌም ለሊት ላይ ለሽንት ስትነሳ ታየናለች ለዛ ነው በር የማንዘጋው፡የኔበር ሲዘጋ አዲስ ስለሚሆንባት መረበሿ አይቀርም" "እና ምን ይሁን ነው የምትይው?!" "ቀስ ብለህ ክፍት አድርገውና ጥግ ላይ ተደበቅ!" እሺ ብሎ ሊከፍት ሲጠጋ በሩ መንኳኳት ጀመረ ለስለስብሎ ኳኳኳኳኳ ቀጠለ የሮዛ እናት ፡የሲፈን በልተለመደ ሁኔታ በር መዝጋት ደስ አላሰኛቸውሙ ከሮዛ ጀምረው ሁሌም እንደሚያደርጉት ልጆቻቸውን በተራ ተራ አይተው ብርድልብሱን ለበስ አድርገው ነው ወደቀረቻቸው ሲፈን የመጡት በሯ ተዘግቷል እንዴት............ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ጨመረ ማንኳኳቱ ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ... ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ ፀጥታ በወረሰው በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ፡አንድ ሰው የሆነ ቦታ ለመድረስ ይጣደፋል ፡የሆነ አላማ ያለው ይመስላል አንዳንዴ እንደ መደናቀፍ ይላል ኮሮኮንቻማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በጣም አስቸግሮታል ፡ትዕግስት የለሽ ቢጤ ነው ቶሎ ቶሎ ይናደዳል አጠገቡ ማንም ባይኖርም አልፎ አልፎ ይራገማል ፡ይሳደባል ፡እንዲ እንዲ እየተቻኮለ ተጉዞ ያን አስቀያሚ ጨለማ ሰፈር ጨርሶ ሲወጣ ድምፅ አውጥቶ "የማይረባ አገር ሁሉን ነገር ማጨለም ቲ!"አለ እናም ቀኝ እግሩን ከመሬቱጋር አጋጨው መብራት የለም፡ ውሃ የለም፡.....ችግር ቲ ፡አሁን እኛ ጠግበን ሳንበላ ጤፍ ጤፍ እንኳ በአቅሙ ለውጭ ይሸጣል ፡መብራት መብራት በስርሃት ሳናበራ ፡ለውጭ ይሸጣል ቲ! ኧረ ስንቱን ስንቱን ትሸጣለች..... !ነጋዴ አገር! ግን ያላተረፈች ! ቲሽ፡ ባዶ ባዶ ፡ሰርተህ ባዶ ፡ነግደህ ባዶ ፡ሰርቀህ ባዶ .... ኪኪኪኪኪ ...ነገሩ የሚሰረቀውን ሰው ጠንቅቆ ያለማወቅ እራሱ ባዶነት ነው ኪኪኪኪኪ.... ስንት ሙሰኛ በተንጣለለ ጊቢ ውሻና ዘበኛ ሰብስቦ የሚኖረውን ትቶ እነማዘር በመከራ ያገኟትን ሳንቲም ከነቦርሳው መንትፎ መሮጥ መስረቅ ነው እንዴ ኪኪኪኪኪ ..... ኧረረረ ከሰረቁ አይቀር እንደኛ የጀግና ተልእኮ ማካሄድ ነው ኪኪኪኪኪ!!" እያለ ለብቻው እየለፈለፈ እየሳቀ በብርሃን ወደ ተሞላው ግን ፀጥ እረጭ ካለው ፕሮግራሙ ውስጥ ከከተተው ሰፈር ደረሰ ፡ ቆም ብሎም አካባቢውን በጥሞና ማስተዋል ጀመረ ፡እናም ሰሞኑን ጊዜ ወስዶ ሲያጠናው ወደሰነበተው ፡አንድ ትልቅ ነጭ በጥቁር የተቀባ ብረት በር ላይ አተኮረ "፡አንድ ዘበኛ፡ ሁለት ውሻ አንድ እማወራ ፡አንድ አባወራ ፡አራት ሴት ልጆች ኪኪኪኪኪኪ.. ይሄ ሌባ አባወራ ቲ አራት በሙሉ ሴት ይወልዳል የማይረባ በደንብ አይሰራም ነበር ኪኪኪኪ ይሄኔ ሙስናውን ቢሆን በደንብ ይሰራው ነበር ፡ልክ የአንዱን ንብረት ለአንዱ እየሰጠ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ ፡ሁለቱን ሴቶች ፡ከኛቤት አባወሮች ጋር ፡እኔን በመሰለ ጀግናና በዛ ጅል መንትያ ወንድሜ በቀየረ ነበር ኪኪኪኪኪ ..."እያለ ብቻውን ገለፈጠ ፡መልሶ አፉን እንደመያዝ አድርጎ እራሱ በራሱ ላይ አለመጠ ፡ለሱ ይሄ ጉዳይ ምንም አይነት መረበሽን ባያስከትልበትም ፡ፀጥታው ግን የሞት ያህል ያስፈራል ፡ቀስ እያለ የግቢውን ዙሪያ ዞር ዞር ካለው በዋላ ከለበሰው ጥቁር እረዥም ካፖርቱ ውስጥ የፊት መሸፈኛ የሹራብ ጭንብል አውጥቶ አጠለቀ ለአይኖቹ ብቻ የሚታዩትን ቀዳዳዎች በትክክል ካደረጋቸው በዋላ፡ አንዲት አነስተኛ ሽጉጥ በማውጣት በሁለት እጁ እያቀያየረ አሻሻት እናም ፈገግ አለ ፡እናም ከሌላኛው ኪሱ ውስጥ በላስቲክ የተጠቀለለውን በመርዝ ያበደ ስጋ አወጣ ፡በጊቢ ውስጥ ዘበኛው ልክ ከለሊቱ 6:00ሰሃት ላይ የሚፈታቸው ውሾች እንደሚንቀሳቀሱ ያውቃል ፡ዘበኛውም በዚ ሰሃት አሳቡን ለውሾቹ ጥሎ ለሽ እንደሚልም ያውቃል ፡ስለዚ የስጋዎቹን ቁርጥራጮች ይወረውረው ጀመር ወደጊቢው ፡ድምፆች ተሰሙት፡ባሰበውልክ ሁኔታዎች እየሄዱ መሆኑንም ተገነዘበ ለራሱ 'አዎ እንደሱ!'አለ እናም ለጥቂት ጊዜ ወደዛ ወደዚ እያለ ጠበቀ ፡ አዎ በዚያ አስፈሪ ለሊት ከጨረቃና ጭል ጭል ከሚሉት ክዋከብት በስተቀር አንዳች ታዛቢ በሌለበት ብቻውን ፡በድፍረት ከዛቤት ለመግባት ቆርጧል ፡ እናም ውሾቹ ዝም ማለታቸውን ሲያረጋግጥ እንደጦጣ እየተንጠላጠለ ቀልጠፍ ብሎ ወደ ጊቢው ገባ ዘበኛው እንደተኛ ነው ውሾቹ ተራርቀው በድካም ተንጋለዋል መርዙ ስራውን እንደሰራ አወቀ ፡ 'እንግዲ መሆን ስላለበት እንጂ ፀቤ ከናንተ አይደለም ብሎ ውሾቹን አልፎ ወደ ሚያምረው ቪላ ተጠጋ እናም ብዙም በማትከብደዋ አነስተኛ መስኮት እጁን ሰደድ በማድረግ ፈተሻት እንደገመተው ነበርና ያለችግር ከፈታት ፡እናም በቀስታ ወደውስጥ ዘለቀ ፡እናም በመጀመሪያ እነዛ ልዕልት ወደመሰሉት እህትማማቾች ክፍል ነው መሄድ ኪኪኪኪ እያንዳንዳቸውን ነው መጎብኘት ኪኪኪኪ መቼም እንግዳ አቀባበሉ አይጠፋቸውም እንዴ ሳኩ እንዴ ምን አባቴ ነው የምሰራው ፡ አለ ለራሱ እናም እንዳለው በመጀመሪያ የቤቱ ታላቅ ወደሆነችው ሮዛ መኝታ ክፍል ዘው አለ በፀጥታ እግሮቿን አጣጥፋ ተኝታለች ፡'ስታምር ' አለ እናም ትቷት ወጣ ቀጥሎ ከሮዛ ጎን ወዳለው ክፍል ቀስ ብሎ ገባ ፡በአልጋው ላይ ሊያና ራሔል ጎን ለጎን ተኝተዋል ብዙጊዜ ራሔል የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንም ብቻዋን መተኛት ከመፍራቷ የተነሳ የቤቱ መጨረሻ ከሆነችው ሊያ ጋር ነው የምታድረው ፡ባለጭንብሉ ፡ለብቻ ለብቻ ነበር መተኛት የነበረባቹ ቲ 'ግን ይህ የማይረባ እንዴት ነው ዘሩ እንዲ የሚያምረው 'አለ እናም ዞር ዞር እያለ ውበታቸውን አደነቀ ፡በመጨረሻም፡ የሊያ ታላቅ የቤቱ ሦስተኛ ልጅ ወደሆነችው ሲፈን ክፍል ገባ ፡እንደገባ ለራሱም ያስገረመው ድንጋጤ ተሰማው፡ሲፈን በጀርባዋ ተንጋላ ነው የተኛችው የለበሰችው ሰፊ ቢጃማ በከፊል ተገልፆ እርቃኗ ይታያል እረዥም ፀጉሯ ወዲያና ወዲ ተበታትኖ በሚያምረው ፊቷ ላይ ሳይቀር ነስነስ ብሏል ፡ባለጭንብሉ ፡ትንፋሹ ፀጥ አለ ለረዥም ደቂቃ በመገረም አያት እናም ቀስእያለ ደመነፍሱን ተጠጋት ....ቀስስ እያለ እያለ. እየቀረባት ሲመጣ የልብ ምቱም አብሮ ጨመረ ፡እጆቹን በቀስታ ወደ ተራቆተው ጡቷ ሰደድ አደረገው መልሶ በፍጥነት እሳት እንደነካ አይነት ሰበሰበው እንደገና በፊቷ ላይ የተነሰነሰውን ፀጉር ወደጎን ወደጎን እያደረገ አስተካከለው ፡ይህን ሲያደርግ ውበቷ የበለጠ ቁልጭ ብሎ ታየው ከንፈሮቿን መሳም ፈለገ እናም ቀረብ አላት ፡ሲፈን በሆነ ታምር ያወቀች ይመስል ተገላበጠች ባለጭንብሉ በድንጋጤ ወደዋላው አፈገፈገ እንቅስቃሴው ፡የረበሻት ይመስል ፡ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች ፡አይኖቿ ተከፈቱ ፡ፊትለፊት ባለ ጭንብሉን ከለላ ሲፈልግ አየችው፡ሲፈን ከመቅፅበት አልጋው ላይ ያለውን አንሶላ ወደራሷ በመሰብሰብ ቁጭ አለች ፡ሰውነቷ በድንጋጤ ደረቀ፡ባለጭንብሉ ፡ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለገባው ፡እራሱን አረጋጋ ፡ቀረብ አላትና ፡ልትጮህ ያሰናዳችውን አፋን በሰፊ መዳፉ በማፈን ፀጥ አደረጋት "ስሚ አንዳች እረብሻ አስነሳለው ብትዪ ሁሉንም ቤተሰብ ችግር ውስጥ ነው የምትከቺው !ገባሽ! ተመልከች እዚች ሽጉጥ ውስጥ አምስት ቀልሃ አለ ለአምስቱ ቤተሰቦችሽ በቂ ነው፡ ዝም ብትዪ ላንቺ ነው የሚጠቅመው!!!"አላት በጭንብሉ ቀዳዳ የፈጠጡ አይኖቿ ውስጥ እየተመለከታት፡ሰውነቷን ብርድ ብርድ አላት መንቀጥቀጥ ጀመረች፡'ማነው !ይህ ሰው ምን ፈልጎነው?እህቶቼ ደና ይሆኑ ?እማሚ እና አባቢስ ውሾቹ እንዴት አስገቡት ?ዘበኛውስ ? በሩስ እንዴት ተከፈተለት?በምን በየት በኩል...?!!'የጭንቀት ጥያቄዎች በተራበተራ አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ፡ፍርሃቷ ወደር አጣ፡ባለጭንብሉን አፋን እንዳፈናት አልጋዋላይ ፈርከክ ብሎ ዝም እንድትል ሲያስጠነቅቃት እያየችው ነው ጥቁሩ የሹራብ ጭንብል ይበልጥ አስፈራራት ትዝ አላት ፊልም ላይ ያየቻቸው የመደፈር አደጋዎች በርቀት ትሰማቸው የነበረ የሴቶች ጥቃት ፡እያንዳንዱ ፡ሲታወሷት፡ዛሬ በሷ ላይ ለዛውም በገዛ አልጋዋ ላይ ፡ምን አይነት የቀን ጎዶሎ ነው እዚ ሴጣን ላይ የጣለኝ አለች ስቅቅ ብላ፡፡ባለጭንብሉ ዝም እንዳለች ለመፈተሽ ይመስል ቀስ ብሎ ለቀቅ ፡ሲያደርጋት ፡በተከፈቱት እግሮቹ መሃል ጉልበቷን በማስገባት፡እንትኑን ክፉኛ አገኘችው፡እንደማቃሰት ብሎ ለቋት ወደዋላው በመሸሽ ፡አጉተመተመ ፡ለጥቂት ሰከንድ፡ አፉን ከፍቶ ተሰቃየ ፡ሲፈን እንደምንም እራሷን አበርትታ ከክፍሏ ለመውጣተሸ ወደበሩ
Open in Telegramሰላም የመጽሐፍት መንደር ቤተሰብ እንዴት ናችሁ👐 ዛሬ በአንድ በጥያቄ መጥቻለሁ🤗 እስቲ 👇👇👇 👉 በህይወታችሁ ዉስጥ ሌሎች ሰዎች ይማሩበታል የምትሉት የሰራችሁት ስህተት ምንድነው ❓
Open in Telegramአብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ። ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገር ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ። አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ። ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣ ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ። " ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?" "እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?" ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ በመራቅ ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ። አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ "ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ። "ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም። ቃልዬ ቀጠለች •••• "እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች "ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ ሴት ጋር ያለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት። ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ። እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር። ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር። መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ። በቃ ታረቅን። እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ። ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር። አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ። " ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣ ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ። መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት። ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ። ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም። "ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች። እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ። አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ ታመምኩ ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ። ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና "ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት። ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቁልቁል ወረደ። ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ••• "ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ። ፊቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች። ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት። እሷም እህቴ ነች። የምኖረው ለኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር። የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ። ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም። ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው። "ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ብትንትኑ ወጣ።ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም። ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ። ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ እየጠበኩ ነው። መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ ልጅ እግር በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ። አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና••• "እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት። ወረቀቱ ላይ የተፃፈው •••• "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም" የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ። ✨ተፈፀመ✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ተማሪዋ! ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን ፡ ፡ ራመድ ራመድ እያልኩ ወደሆቴሉ ዘው ብዬ እንደገባሁ ፊት ለፊት ባየሁት ነገር ልቤ ስንጥቅ አለች። ወይኔ አምላኬ ምንድን ነው የማየው ? ጭራሽ እኔ የገዛሁላትን አዲሷን ልብስ••• እያልኩ በሁለቱም እጆቼ ሁለት ሁለት ባዶ የቢራ ጠርሙዝ እንዳንጠለጠልኩ ድንጋጤዬ አብረክርኮት አልራመድ ያለኝን እግሬን በግድ እየጎተትኩ በቀስታ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ተጠጋሁ•• •••• በሆቴሉ ውስጥ ጭልም ደሞ ብርት የሚሉ ሲበሩም ደብዛዛ ብርሀን የሚፈነጥቁ ጌጣማ አንፖሎች እዛም እዛም ተሰቅለዋል ፣ ቀረብ ስል ግራ ገባኽ አብሯት ያለው ወንድ ፊቱ በደንብ ታየኝ። ዛኪ አይደለም።ገዘፍ ያለ ነው። አስተያየቱ ደሞ ያስፈራል። ገልመጥመጥ ሲያደርገኝ እነሱን እያየሁ በቀጥታ ወደነሱ መሄዴን ቀየር አደረኩና እንደማለፍ ብዬ አየት ሳደርግ ልጅቷም ቃልዬ አይደለችም። ቀሚሱዋም ዲዛይኗ የቃልዬ አይነት ቢሆንም ' ከለሯ 'በተወሰነ መልኩ ይለያል። የስራሽን ይስጥሽ ቃልዬ፣ ግራ የገባኝ ደግሞ ተከትያት ሀረር ከመጣሁ በሁዋላ የተጠናወተኝ በቅርብ ርቀት ያየኋት ሴት ሁሉ ቃልዬን የምትመስለኝ በሽታ ነው ፣ ይሄ መታመም ካልሆነ ምን ይሆናል ? እያልኩ ቢራውን ገዝቼ ተመለስኩ። የግቢው ጥበቃ የቀራቸውን ምርቃት ሁሉ አሟጠው መረቁኝ። "የእኔን እድሜ ያድለህ ፣ ጧሪ አያሰጣህ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ የልጅ ልጅ ያሳይህ•••••" ሌላም ሌላም ብዙ ምርቃቶች። "አባባ " አልኳቸው እንደጨረሱ። "ወዬ የኔ ልጅ" "ፍቅር ይዝለቅልህ!" ብለው ይመርቁኝ አልኳቸው እንባ እየተናነቀኝ። "ፍቅር ይዝለቅልህ ፣ የወድድካትን ያፈቀርከትን ክፉ አይይብህ ፣ ትዳርህን ይባርክልህ ! " አሜን አሜን አሜን አባቴ" አልኳቸው ዋናው እሱ ነው ። እኔ የልጅ ልጅ ማየት የምፈልገው ከቃልዬ ነው። ከቃልዬ ከነጠለኝ በሁዋላ ረጅም እድሜ ምን ሊጠቅመኝ። እያልኩ ቢራውን ሰጥቻቸው ወደ ክፍሌ ገባሁ። ቃልዬ ከዛኪ ጋር ማደሯን ማሰብ አስፈሪ እንደሆነብኝ ድካምና ረሀቡ ነው መሰለኝ የወደቅኩበትን ሳላውቅ ነጋ። ጥዋት ወደ ድሬ ዳዋ ስመለስ ቃልዬ እራሷ እስክትደውል ላልደውልላት በናቴ ማልኩ። ሳትደዉል መሸ፣ ሳትደውል ነጋ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀንም እንደዛው ልደውል ስልኬን ካወጣሁ በሁዋላ በናቴ መማሌ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ወደ ኪሴ እመልሰዋለሁ። በአራተኛው ቀን ደወለች ። "ይቅርታ ኤፍዬ በዚህ ምርቃት ሰበብ ተዋክቤ፣ ቻርጀሬ ጠፍቶ ፣ ባትሪ ዘግቶ••••" ብዙ ብዙ አለች ፣ ለመጥፋቷ ብዙ ምክንያት ብዙ ሰበብ ተናገረች ቃል። ዝም ብዬ ሰማኋት። ስትጨርስ አንድ ነገር ብቻ ተናገርኩ አንድና አንድ ነገር ብቻ አልኳት። "ችግር የለውም ቃልዬ በጣም ላገኝሽ እፈልጋለሁ መች ይመችሻል?" የሚል ጥያቄ ብቻ ሰነዘርኩላት። ድምፄ መሰባበሩ ለኔ ቢታወቀኝም ለሷ አላታወቃትም አልያም አላስተዋለችውም። "ኤፍዬ አብረን ለመዋል ከሆነ ነገ ፣ ለማደር ከሆነ ግን ከነገ ወድያ" "አይ ችግር የለውም አብረን ውለን ትሄጃለሽ" "በቃ ነገ ከሰአት ደውልልኝ " የቃልን ስልክ እንደዘጋሁ ጌትነት ስልክ ላይ ደወልኩ። እቤቱን ለአንድ ቀን እንደምፈልገው ነገርኩት። "ችግር የለውም ኤፍዬ ማደርም ትችላለህ እኔ ጀለሶቼ ጋር እሄዳለሁ" አለኝ። ቃልዬን ላመጣት ስሄድ ለጌትነት ደውዬ ልመጣ ነውና ቁልፉን አስቀምጠህልኝ ሂድ አልኩት። ደረስኩ ተገናኘን ። ስማኝ ከጀርባ ገባች። ደንዝዣለሁ። ምንም አላወራም ቃልዬ ግን ምን ያህል እንደናፈቅኳት ፣ ስለሰሞኑ የምርቃታቸው ወከባ ምን ያህል ግዜ እንዳሳጣት እያወራችልኝ የማውራት እድል ሳትሰጠኝ እነ ጌትነት ቤት ደረስን። የማውራት እድል ብትሰጠኝ ምን እንደማውራ አላውቅም። ገብተን ትንሽ እንደቆየን ከምን እንደምጀምር ምን እንደምላት ጨነቀኝ። ካንድም ሁለት ሶስቴ ልጀምር እልና የሆነ የሚረብሽ ስሜት እየተናነቀኝ አቋርጠዋለሁ። ተነስቼ ወደ መታጠቢያ ቤት እሄድና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጥቤ እመለሳለሁ። ቃልዬ ቡና ለማፍላት እየተንጎዳጎደች ሁኔታዬን ማስተዋል አልቻለችም። አቦሉን እንደጠጣን ••• "በቃ ሁለተኛውን አታፍይ ይቅር " አልኳት። "ለምን ኤፍዬ?" አለችኝ ፊት ፊቴን እያየች።ፊቴ ልክ እንዳልሆነ ያስተዋለችው ያኔ ነበር። መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች። "ምን ሆነሃል ኤፍዬ ችግር አለ?" አለችኝ አገጬን ይዛ ወደግራም ወደቀኝም ገልበጥ ገልበጥ እያደረችኝ። "አዎ ችግር አለ ቃል"አልኳት አገጬ ላይ ያለውን እጇን ይዤ ከአገጬ ላይ እያወረድኩት። "ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ልቧን በግራ እጇ ደገፍ አድርጋ እየተመለከተችኝ። ልቧ ነገራት ብዬ በውስጤ እያሰብኩ ዝም አልኩ። "ኤፊዬ!" ብላ ተጣራች። "ወዬ ቃል" "ምን ሆነሀል ?" ምን ሆንኩ እንደምላት ቸገረኝ። "ቃልዬ" አልኳት። "ውዬ" "ታፈቅሪኛለሽ?" "ምን እሚሉት ጥያቄ ነው እስከዛሬ ምን ያህል እንደማፈቅርህ አታውቅም እና ነው ቆይ ምንድን ነው የሆንከው ፊትህ እኮ ልክ አይደለም?" "ፊቴ ብቻ አይደለም ሁሉ ነገሬ ልክ አይደለም ቃል እባክሽ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ብቻ መልስ ስጪኝ አንቺ ምንም ነገር አትጠይቂኝ" "እሺ" "ታፈቅሪኛለሽ ቃል" "አዎ ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ" "ዛኪንስ ታፈቅሪዋለሽ ቃል?" ስላት ፊቷ ላይ ያየሁት ድንጋጤ እኔኑ አስደነገጠኝ። ያ ድንጋጤዋ ነበር የመጨረሻውን መርዶ ያረዳኝ። በቃ የቃልዬን መልስ ድንጋጤዋ ውስጥ አየሁት። ቃልዬ ብዬ ጠራሁዋት አይን አኗን እየተመለከትኩ። ወዬ ማለት አልቻለችም። በቃ አቃታት። የኔም የሷም አይኖች እኩል እንባ አቀረሩ። " ቃልዬ!" ብዬ ደግሜ ጠራኋት። አይን አይኔን ከማየት ውጪ አቤትም ወዬም ማለት ተሳናት ቃል አፏ ተለጎመ። የስረኛው ከንፈሯ ይንቀጠቀጥ ጀመር። ጣቶቼን በጣቶቿ እያፍተለተለች ተለጎመች የኔ ቃል። ሁሉን ነገር እንደደረስኩበት ውስጧ ነግሯታል። ይህን ሳስብ አመመኝ ። ቃልዬ ሁኔታዋ አንጀት ይበላል። የሚታዘንልኝ እኔ ሆኜ ሳለሁ ቃልዬ በዛ ልክ ጭንቅ ጥብብ ሲላት ሳይ አሳዘነችኝ። ያን ሲተናነቀኝ የነበረውን እውነት መናገር ጀመርኩ••• ቃልዬ አውቃለሁ ሁሉን አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሀረር እስከሄዳችሁባት አስቀያሚ ቀን ድረስ ይቺ ቅፅበት በኔና ባንቺ መሀል እንዳትፈጠር ስሸሻት ኖሪያለሁ። ነገር ግን እውነትን መሸሽ ከሞት እንደማያድነኝ ተረዳሁ። አዎ ቃልዬ አንቺን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ፣ መሞት አልፈልግምና አንቺን ማጣት እፈራለሁ። እኔ ስለፈራሁት እኔ ስለሸሸሁት የሚቀር ነገር የለም። ሁሌም አፈቅርሻለሁ። ምንም ብትበድይኝ ምንም ብትጎጂኝ አንቺን አለማፍቀር እስክችል ድረስ አፈቅርሻለሁና ዛሬም ቢሆን አንቺን ክፉ የምናገርበት አንደበት የለኝም። ክፉ ይናገረኛል አልያም ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ እሺ? ፣ እኔ አንቺን የማፈቅርሽ የእውነት ነው ፣ የማፈቅርሽ ግን የኔ ስለሆንሽ ብቻ አይደለም። ዛሬም የማልፈልገው አንቺን አለማፍቀር ሳይሆን እየታመምኩ፣ እየተረበሽኩ፣ እንቅልፍ እያጣሁ፣ የተበዳይነት፣ የተገፊነት ስሜት እያንገላታኝ ማፍቀርን ነው። ነገ ከነገ ወድያ ላጣሽ ልትለይኝ እንደምትችይ እያሰብኩ ማፍቀር ደከመኝ ቃልዬ።
Open in Telegram❣ የደወልኩላት ስለናፈቀችኝ ነበር።ለብዙ ጊዜያት ሞክሬው ከራስ ጋር እየተጣሉ መኖር እየደከመኝ፣ማረፍያዬ ከሷ ውጭ አልታይህ እያለኝ ስረበሽ፣ይቅርታ ልላት ነበር ስልኬን ያነሳውት ....ያኔ ለመጨረሻ ጊዜ ላያት በሰልስቱ ስንገናኝ ''ላንተነትህ ነፍሴን ባልሰስት ለእኔነቴ ግን ህመምን ሰጠኸኝ።'አለች ባለ ማጥፋቴ ስለቀጣኸኝ አዝኛለው።" አትሂድ አልልህም መንገድ ምንኛ ሸክም እንደሆነ እነዚህ ስብርባሪ ቀናቶች በቂ ናቸው። ሀሳብህ ምንድነው ? አለች ከመሄድ በማያስቀሩኝ ተስፋዎቿ ውስጥ በስስት ምናልባት እያየችኝ...... 'አላውቅም አላውቅም እየሆነ ላለው ነገር ግን አዝናለው' 'የመጨረሻ ቃልህ ኢሄ ነው...? እንድታስብ ጊዜ የሰጠውህ መልስ አለቀ..? አለች በትኩረት እያየችኝ 'አ...አዎ' በቃ አትጨነቅ የኮበለለን ልብ እግር አያስቆመውም አይደል ዝም ብዬ ነዋ የለፋውት(የማጣት ፈገግታ)።በነፍስ ካልተጣመሩ ስጋኮ ፈራሽ ነው፤ይቀየራል።እንደማልጨክንብህና ላንተ ልከፍል የነበረውን የህይወቴን ዋጋ ታውቃለህ፣ ብዙ ባወራ ደስታዬ ነበር ግን ምን ሊጠቅም ብለህ.... በቃ ቻው አልያዝህ አለች ድካምና ስብራት ባዘለው ፊቷ ልታቅፈኝ እየቀረበች። ያኔ እውነት የመሰለኝ አለም እንደ ጉም ተኖ ከእጄ ወጣ። የሄድኩባቸው መንገዶች በሙሉ ወደ እርሷ እየመለሱኝ፣የመለሱኝ መንገዶች ደግሞ ከእርሷ አላደርስህ አሉኝ።የተለየ የመሰለኝ ነገር የተለየውበት ወንፊት ሆነ እንደ ብናኝ እፍታ ገለባዬ ብቻ ቀረ ማምሻዬ ላይ የትዝታና የናፍቆቷ ንፋስ እየወሰዱኝ ክቡር ፍቅሯን፤ ክቡር ክብሯን አጉልተው አሳዩኝ...ዋጋ የለሽ፣ራስ ወዳድ፣አሁንን ብቻና ለብልጭልጭ የተሸነፍኩኝ ብኩን መሆኔን የስብእናዋ ምስል አሳየኝ።ከሷ ውጪ መኖር ህልም ሆነብኝ።የእውነት ናፈቀችኝ፣የእውነት ላያት ጓጓው......ስልኬን አንስቼ ደወልኩላት ዝምምምም.......'የደወሉላቸው ደንበኛ ቁጥር አገልግሎት ላይ አልዋለም' ደጋግሜ ሞከርኩኝ ግን ተመሳሳይ መልስ አዲስ ነገር የለውም። ከወራት በኋላ ግን.........በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ በፈገግታ ታቅፋ አየኋት....ሌላ ህይወት... . . . #ሻሎም ትዝታዬ..... #ሻሎም የኔ ናፍቆት......Shalom.....😔 የሁላችንም ልክ በሀቃችን የተመዘነ ነው:: ''ሌላ ለመሙላት አጉድለን ስንሄድ ነው የቀነስነው የሚወሰድብን።'' ✍....... #ካነበብኩት
Open in Telegram"አትሳቂ ቃልዬ ኮተታ ኮተቱን ሁሉ እንድታወሪልኝ ሳይሆን በጥቅሉ ያለውን ነገር እና ወጣ ያለ ፕሮግራም ምናምን ሲኖርሽ መናገሩ ጥሩ ነው ፣ ደስ ይላል እኮ፣ ደስ ስለሚል ብቻ ሳይሆን አብረን ባልሆንበትም ሰአት አብረን እንዳለን ያህል እንዲሰማን ያደርጋል፣ ግልፅነትን እና መተማመንን ያጠነክራል፣ •••ብዙ ጥቅም አለው ቃሌ" "ኦ. ማይ. ጋድ. ግን በጣም አሰልቺ አይሆንም ኤፍዬ እሺ ሌላስ?" "ሌላውም ያው የዚሁ ግልባጭ ነው ። ስለነገ ማውራትም አትወድን ቃልዬ። ይሄም ግን አስፈላጊ ነው። ስለነገ ስልሽ ሰለነገ ሳይሆን ስለወደፊት እንዲሆን እምትፈልጊውን እንዲሁም ለማድረግ ያሰብሽውን ነገር ማውራት ደስ ይላል ለምሳሌ እኔ ሁሌም ሀሳብ የሚሆንብኝ ቃልዬ ከተመረቀች በሁዋላ የት ነው ተቀጥራ ስራ መስራት የምትፈልገው ድሬ ነው ወይስ አዲስ አበባ የሚለው ነገር በጣም ያሳስበኛል። እንኳን ስለወደፊቱ ስለዛሬም ስጠይቅሽ ጭቅጭቅ ስለሚመስልሽና ቶሎ ስለሚሰለችሽ ግን ጠይቄሽ አላውቅም ።" ስላት በስስት እያየችኝ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደኔ መጣችና አቀፈችኝ። ኤፍዬ ሙት አንጀቴን አላወስከው። እንደተመረቅኩ ያው ቤተሰቦቼ ለምርቃቴ መምጣታቸው ስለማይቀር አብሪያቸው ሄዳለሁ ትንሽ ቆይቼ ወደዚህ ተመልሼ ነው ስራ መፈለግ የምጀምው ከፈለክ አንተ ወደ አዲስ አበባ ትመጣና ወደዚህ አብረን እንመለሳለን ፣ይሄንን ቀደም ብዬ ሳስብት ነበር ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ እሺ" ስትለኝ ያለንበት ቤት ብቻ አይደለም ምድር የጠበበችኝ እስኪመስለኝ በደስታ ተጥለቀለቅኩ። እንቅፋት የገጠመው የመሰለኝ ፍቅራችን በዚች በቃልዬ ንግግር እንቅልፋቱ ሁሉ ሲጠራረግ ታየኝ። ተስፋዬን አለመለመችው። በዚች ምሽት ቃልዬ ልትመረቅ ሁለት ወር ነበር የቀራት። መድረሱ ያስፈራኝ የቃልዬ ምርቃት ቀን ናፈቀኝ። እህቴ እገዛልሀለሁ ያለችኝ ሚኒባስ ደግሞ ሶስት ወር ነው የቀረው። እያንዳንዷ ቀን መሽታ በነጋች ቁጥር የምመኘውን ሂወት ወደምጀምርበት ቀን የምታወጣኝን መሰላል እየወጣሁ ያጋመስኩ ያገባደድኳት መስሎ ይሰማኝ ነበር። •••• ቃክዬ መመረቂያ ግዜዋ እየደረሰ ነው አንድ ወር አከባቢ ሲቀረው የመመረቂያ ፅሁፍ ገለመሌ እያለች በጣም ትዋከብ ነበር። ልክ ቃልዬ ልትመረቅ ሁለት ሳምንት ሲቀራት ስራ ላይ እያለሁ፣ በአንድ ቀን አመሻሹ ላይ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከበቢ ባጃጄ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሞባይሌን እየነካካሁ ቴሌግራም አካውንቴ ላይ መልዕክት ገባ። ቴሌግራሜን ከፍቼ ስመለከተው መልዕክቱ የተላከው ደግሞ ከዛ ከማላውቀው ቁጥር ነው። ቃልዬ ጭፈራ ቤት ከዛኪ ጋር ያመሸች ቀን የጭፈራ ቤቱ ስም ተፅፎ የተላከበትን ቁጥር የማይታወቅ ብዬ ይዤው ነበር። ቴሌግራም ላይ የተላከው መልክት በዛ ቁጥር ነው፣ የተላከው መልክት ፎቶ ነው። ጫን ብዬ ካልከፈትኩት ምንነቱ የማይታወቅ ፎቶ መልክቱን ከፍቼ ማየት ፈራሁ። ሳመነታ ቆየሁ፣ በመጨረሻም ከፈትኩት ። ፎቶው የሰው ፎቶ አይደለም፣ ሁለት ሰዎች የተላላኩትን መልክት 'እስክሪን ሹት' አድርገው ነው የላኩልኝ። የመልክት ልውውጡ እንዲህ ይላል••• "ዛኪ ነገ የት ነህ አንገናኝም?" "ነገ ግቢ የለሁም ባክህ?" "የት ልትሄድ ነው?" " ከችኳ ጋር ሀረር ልንሄድ ነው" "ኧረ ባክህ ደስ ይላል ፈታ ልትሉ ነዋ ፣ ስንት ሰአት ነው የምትሄዱት በጥዋት ነው ያቺን መፃፍ ፈልጌ ነበር?" "አይ በጥዋት አይደለም ከምሳ ሰአት በኋላ የምንሄድ ይመስለኛል እስከስድስት ሰአት አለሁ ናና ውሰድ ወይ እኔ እራሴ አቀብልሀለሁ" "በቃ ለማንኛውም ጥዋት እንደዋወል" የሚል ነበር ። ዛኪ ከአንድ ግቢ ካለ ወንድ ጋደኛው ጋር የተለዋወጠው መልክት መሆኑ ግልፅ ነው። ያንን ፎቶ አንስተው የላኩልኝ ዛኪ ሀረር የሚሄደው ከቃል ኪዳን ጋር እንደሆነ ሊነግሩኝ መሆኑን ሳስበው በተቀመጥኩበት ቢዥዥዥ አለብኝ። አዞረኝ። ባጃጄ ውስጥ የነበረውን ኮዳ አነሳሁና ውስጡ ያለውን ውሃ አናቴ ላይ አፈሰስኩት። በውሃ የሚቀዘቅዝ መች ሆነና። ምን እንደማስብ ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ። ከባጃጄ ላይ ወርጄ ጭለማ ቦታ መርጬ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ። ለብዙ ደቂቃዎች ምናልባትም ለአንድ ሰአት ያህል ቁጭ አልኩ። ትንሽ ስረጋጋ ወደ ቃልዬ ስልክ ደወልኩ። በቃ ነገ እፈልግሻለሁ እላታለሁ፣ አይመቸኝም ካለች የማይመቻት ከዛኪ ጋር ሀረር ለመሄድ እንደሆነ በግልፅ እነግራታለሁ። እኔ ብሸሸውም እየተከተለ ስቃዬን ያበላኝን እውነት አፍርጬው የምትለውን እሰማታለሁ ። ብዬ ከወሰንኩ በኋላ ነበር ወደ ቃልዬ ስልክ የደወልኩት። ስልኩን አንስታ •••"እንዴት ነህ ኤፍዬ?" ስትለኝ ደፍሬ ያንን ልበላት አልበላት ግን እርግጠኛ ልነበርኩም ። ብቻ ደውልኩ ። የቃልዬ ስልክ ጥሪ አይቀበልም።ከደረሰኝ መልክት በላይ የቃልዬ ስልክ ዝግ መሆኑ ቅስሜን ሰበረው። በሩጫ ግቢያቸው ድረስ ሂድና ስሟን እየጠራህ ጩህ ጨህ አለኝ ። ነገርግን ከተቀመጥኩባት ድንጋይ ላይ አልተነሳሁም። ሶስት ግዜ እየቆየሁ እየቆየሁ ብሞክርላትም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም። ሀሳቤን ቀየርኩ ቃልዬ ስልክ ላይ መደወሌን ትቼ ፍፁም ወደሚባል እንደኔው ባጃጅ ያለው ጋደኛዬ ጋር ደወልኩ። ለነገ ባጃጁን እንዲያውሰኝ እና ከፈለገ የኔን ባጃጅ መጠቀም እንደሚችል ስነግረው ። እኔ ነገ ስራ አልወጣም ናና ውሰድ አለኝ። ምንም ሳልተኛ አደርኩ። ጥዋት ሶስት ሰአት ላይ የሱን ባጃጅ ይዤ እነቃልዬ ዩንቨርስቲ መግቢያ አከባቢ አደፈጥኩ። ልክ እሩብ ጉዳይ ለሰባት ላይ ዛኪ በርሳ ጀርባው ላይ ጣል አድርጎ ከግቢ ብቅ ሲል አየሁት።ቃልዬ ተከተለችው ፣ ዘንጣለች። ቀድመው ደወለው ነው መሰል ባጃጅ በር ላይ ነበር የጠበቃቸው። ተከታትለው ገቡ፣ ከሀለቱ ውጪ ሌላ ሰው ወደባጃጇ አልገባም። ባጃጇ ተነስታ መሄድ እንደጀመረች ብዙም ሳትርቅ ተከተልኳት። ቀጥታ ወደ መነሀሪያ ነው እየሄዱ ያሉት። የምይዝ የምጨብጠው ግራ ገባኝ። ልክ ሼል ደርሰው ወደ መናሀሪያ ከመዞራቸው በፉት አንዲት ሚኒባስ ስትክለፈለፍ መጣች። ሀረር ሁለት ሰው አለ ረዳቱ አንገቱን ብቅ አድርጎ። እነቃልዬን የጫነው ባለባጃጅ ለሚኑባስ ረዳት በእጁ ምልክት አሳየው ሚኒባሷ ቆመች ። እነቃልዬ ከባጃጇ ላይ ወርደው ሚኒባሷ ውስጥ ገቡ። ወደ ሀረር ነጎዱ። የሰው ባጃጅ መሪ በቡጢ እየመታሁ እዛው በቅርቤ ወዳለው ማደያ አስጠጋሁና አቆምኳት፣ ቀልፉን እኔም ጋደኛዬም ለምናውቀው ነዳጅ ቀጂ ሰጥቼው ለጋደኛዬ ደውዬ ነገርኩትና ወደ ሀረር ለመሳፈር ወደመናሀሪያ ሮጥኩ።የገባሁበት ሚኒባስ አልሞላም። ተቁነጠነጥኩ። እንደምንም ሞላ እነቃልዬ ወደሀረር ጉዞ ከጀመሩ ከሀያ አምስት ደቂቃ በኃላ የተሳፈርኩባት ሚኒባስ ወደ ሀረር ጉዞ ጀመረች ከፊት ለፊት ሚኒባስ ባየሁ ቁጥር ይሄ እነቃልዬ ያሉበት ይሆን? እያልኩ። እነሱን ተከትዬ ወደሀረር እየተጓዝኩ ነው ። ከቃልዬ ጋር ስንሄድ አምስት ደቂቃ የተጓዝኩት ያልመሰለኝ መንገድ አምስት ቀን የተጓዝኩ ያህል ቢረዝምብኝም ሀረር ደረስኩ•••• ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ተማሪዋ! ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን ፡ ፡ ሄሎ አልኩ ደግሜ ካሁን አሁን ዛኪ ነው መቸስ ስልኳን ያነሳሁ ማነህ አንተ ቢለኝ ማነኝ እንደምለው እያሰብኩ ሄሎ አልኩ። ቃልዬ "ኤርሚያስ ምነካህ የሰው ስልክ አይነሳም እሺ ብልግና ነው " እያለች ስልኩን ስትቀበለው ተሰማኝ። "ሄሎ ቃልዬ!" አልኩ በልቤ አወይ ጣጣዬ ኤርሚያስ ደሞ ማን ይሆን እያልኩ። "ሄሎ ኤፍዬ ይቅርታ እሺ አንዱ የክላስ ልጅ ነው መመረቂያ ፅሁፉን በግሩፕ ስለምናዘጋጅ አንድ ግሩፕ ነን እና ዶክመንት ልላክ ብሎ ተቀብሎኝ ስልኬ እሱ ጋር ነበር ይቅርታ እሺ?" አለችኝ። "ችግር የለውም ቃልዬ ናፍቀሽኛል ቃሌ ነገ ላገኝሽ እፈልጋለሁ" አልኳት። "እኔም ንፍፍፍቅ ነው ያልከኝ" አለችኝ። በቃ ምንም እንዳልተፈጠረ በንጋታው ምሳ ሰአት ላይ ቃልዬን እስካገኛት ጓጓሁ። በንጋታው ምሳ ሰአት ደረሰ አልደረሰ እያልኩ አራት ሰአት ላይ ጌትነት ስልኬ ላይ ደወለ። የደወለው ማን እንደሆነ እንዳየሁ ነበር ገና ስልኩን አንስቼ ሳላናግረው የኔና የቃልዬ የምሳ ቀጠሮ ወደ አዳር እንደሚቀየር እርግጠኛ የሆንኩት። "ሄሎ ጌትሽ አማን ነው ?" "ወዬ ኤፍዬ እንዴት ነህ ? አቦ ድንገት ለሆነ ጉዳይ ተደወለልኝ እና ከድሬ ልወጣ ነው ፣ እቤት እንድታድርልኝ ላስቸግርህ ነው ጋደኛዬ" "ኧረ ጣጣ የለውም አባቴ ገና ስትደውል ነው ባየር ላይ የምሳ ቀጠሮዬን ወደ እራት የቀየርኩት" "ካካካ ያው እራት ማለት ደሞ አዳር ነው በለኛ" "እሱ ግልፅ ነው መጠየቁስ" "ሀዬ ኤፍዬ በቃ ቁልፉን የተለመደው ቦታ ሱቋ ውስጥ አስቀምጬ ሄዳለሁ" "እሺ ጌት ሰላም ግባ" ወድያው ለቃልዬ ደውዬ የምሳ ቀጦሮኣችን ወደ አዳር መቀየሩን ከነ ምክንያቱ ስነግራት "እሺ ኤፍዬ ልትወስደኝ ስትመጣ ደውልልኝ" አለችኝ። እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት ስሰራ አመሸሁና ቃልዬን ይዣት ወደዛው አመራን። "ዛሬ እራት ምርጥ ጥብስ ነው የምሰራልህ ስጋ ገዝተን እንግባ ኤፍዬ" "ጥሬ አይሻልም ቃል?" "ጥሬማ ምን ስራ ያስፈልገዋል? እኔ ግን ጥብስ ሰርቼ ባብላህ ነው ደስ የሚለኝ ቡናም እናፈላለን " አለችኝ። አልገባትም ቃልዬ። ጥሬ አይሻልም ስላት የሀረሩ ትዝ ብሏት ትስቃለች ብዬ ጠብቄ ነበር። ገብተን እየተጋገዝን እራት ሰርተን እየተጎራረስን በልተን እንዳበቃን ቡና እየጠጣን "ቃልዬ ቅድም ጥሬ ምናምን ስልሽ ምንም ትዝ አላለሽም እኔ ታስታውሽዋለሽ ብዬ ጠብቄ ንበር" "ምኑን ኤፍዬ?" "ትገርሚያለሽ የሀረሩን ቆይታችንን ረስተሽዋል ማለት ነው" "ኦኬ. ካካካካ የእውነት ግን ጥሬ ስትለኝ አልመጣልኝም እንጂ የሀረሩን ቆይታችንን አንድም ቀን ሳላስታውሰው አድሬ አላውቅም ሁሌ ነው ስተኛ ስተኛ ትዝ የሚለኝ" "እህ ለምንድን ነው ስተኚ ስተኚ ትዝ የሚልሽ ቀንስ?" "ያው ቀን በተለያየ ነገር ማለት በትምህርት፣ በጥናት፣ ባንተ ሀሳብ፣ በቃ በብዙ ነገር ቢዚ ሆኜ ስለምውል ነዋ ። ጋደም እንዳልኩም ስላንተ አስባለሁ ያኔ ለመጀመሪያ ግዜ አብረን ያደርንበት ሀረር ትዝ ትለኛለች ። ከዛ ያንተ ወሬ ፣ ጥሬ ስጋው ዳንሱን ሁሉ በየተራ አስታውሰዋለሁ" "ለመጀመሪያ ግዜ አብረን ያደርነው ሀረር ነው እንዴ ቃል" "ሂድ ወደዛ እና በተገናኘን በዛው ምሽት ያደርነውን አዳር እንደአዳር ላስታውሰው እንዴ?" "ለምንድን ነው የምታስታውሽው ያኛው በደረቁ ስለሆነ ነው" "ኪኪኪኪ አቦ ያድርቅህ ወደዛ ሞዛዛ" አለችኝ። ቃልዬ አፈረች። "እኔማ ሀረርን የረሳሻት መስሎኝ ገርሞኝ ነበር" "እንዴት ይረሳል ኤፍዬ ያኔ ስታወራ የነበረውን ወሬ ባስታወስኩት ቁጥር እስቃለሁ አይ ኤፍዬ ግልፅነትህ እኮ ደስ ይላል!! ስትለኝ ሀረር እያለን ከግልፅነቴ ውጪ የምትወጁልኝ ምንድን ነው ስላት ሌላ ግዜ ነግርሀለሁ ያለችኝ ትዝ አለኝ። ጠየኳት። " ኤፍዬ ሙት ሁሉ ነገርህን እወድልሀለሁ ብቻ አንዳንዴ•••" ብላ እያየችኝ ዝም ብላ ቆየችና "በቃ አሁን ቡናውን እንጠጣ አታስለፍልፈኝ " አለች። "ቃልዬ ደሞ አንዴ ጀመርነው እኮ ቆይ ከኔ ባህሪ የማይመችሽ ወይ የማትወጂው አለ ? እሱን ንገሪኝ እስቲ" "ኤፍዬ ሙት ብዙ የለም ብቻ አንዳንዴ ድንገት የሚቀይርህ ነገር አለ ዝም ብሎ የሚከፋህ ነገር ያኔ እጨነቃለሁ" "ሌላስ?" "ሌላው ደሞ ቶሎ ግንፍል የምትለው ነገር ያስፈራል ኤፍዬ እኔ ላይ አይደለም ግን በቀደም ያንን ሰካራም ሰውዬ ልታንቀው ስትንደረደር ላየህ ሁኔታህ በጣም ያስፈራ ነበር እኔ እራሴ ፈራሁህ። እንዴ ኤፍዬ እንዲህ አይነትም ባህሪ አለው እንዴ ነው ያልኩት። ሀረር እያለንም እየደንነስን አንዱ ሳያውቅ ገፋ አድርጎኝ እንዴት እንዳሽቀነጠርከው ትዝ ይልሀል ? ደስ አይልም ቶሎ ወደ ፀብ የምትገባ ሰው እንድትሆን አልፈልግም" "እሺ ቃልዬ አስተካክላለሁ" አልኳት። ቃልዬ እንዳለችው ቶሎ ወደ ፀብ የመግባት ድክመቴን አምኜ እቀበላለሁ። በርግጥ ከድሮው አንፃር አሁን እሻላለሁ። ቃልዬ ድሮ ብታውቀኝ ደንብራ ካጠገቤ ትጠፋ ነበር አልኩ በውስጤ። ድንገት የሚቀይር ድንገት የሚከፋህ ያለችው ነገር ግን በሷና በዛኪ ድፍንፍን ባለ ግኑኝነት ምክንያት የመጣብኝ አዲስ ህመም ነው። ምን ላድርግ ተናግሬም የማይወጣልኝ ትቼም የማልተወው ህመም ሆነብኝ።እኔማ ግዜ እውነቱን ያውጣው ብዬ ትቼው ነበር እድሜ ለኪያ የቃልዬን እና የዛኪን ዱካ እየተከታተለ አልፈልግም ብለውም በግድ ወሬ እያቀበለኝ ወዳሉበት ሁሉ ይልከኛል። ካየሁዋቸው ደግሞ መረበሼ አይቀርም። ምንሽ ነው አልላት ነግራኛለች ። ለምን ከሱ ጋር እንዲህ ትሆኛለሽ እንዳልላት የምከታተላት፣ የማላምናት፣ የምጠረጥራት ይመስላታል ትጣላኛለች ብዬ እፈራለሀ። የጨነቀ ነገር ሆኖብኝ እንጂ የምቀየረው እሄስ ባህሪ የኔ አልነበረም። አቦሉን እንደጠጣን•• "ኤፍዬ" "ወዬ ቃል" "እስቲ ስለኔም እናውራ" ስትለኝ ደነገጥኩ። "ስላንቺ ምን ቃሌ?" "አንተስ የምትወድልኝን እና የምትጠላብኝን ባህሪ አትነግረኝም?" "ቃልዬ የምወድልሽን ነገር መናገር ብጀምር እየደለም እሄ ምሽት ነገ ቀኑም ቢጨመር መሽቶ እስኪነጋ አውርቼ የምጨርስ የሚበቃኝ ይመስልሻል?" "እሺ በቃ የምትጠላብኝን ባህሪ ንገረኝ" "ቃሌ የምጠላው ሳይሆን ብትሆኝልኝ ወይ ብትለምጂልኝ ብዬ የምመኘውን አንድ ሁለት ነገር ልንገርሽ አንደኛው ቃልዬ ውሎ እንዴት ነበር ? የሚባል ነገር አለማወቋ ያበሽቀኛል" ስላት "ማለት?" አለችኝ። "ማለትማ በፍቅር ሂወት መሀል አንዱ ወሳኝ ነገር ውሎ እንዴት ነበር ብሎ ማውራት ነዋ፣ አንቺ ደሞ አልፈጠረብሽም " "አልገባኝም ኤፍዬ" "እኔ ስንገናኝ ከመገናኘታችን በፊት ባሳለፍነው ቀን የነበርንበትን ሁኔታ ብናወራ ደስ ይለኛል ፣ አንቺ ግን እንኳንስ ሳልጠይቅሽ ልትነግሪኝ ስጠይቅሽም ደምሽ ይፈላል" ስላት ትን እስኪላት ሳቀች። "ወይ ኤፍዬ እና አንተ እምትፈልገው ልክ ስንገናኝ ዛሬ ጥዋት ልክ አስራ ሁለት ሰአት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ከእንቅልፌ ነቃሁ፣ ሁለት ተኩል ላይ ቁርስ በላሁ፣ አራት ሰአት ክላስ ገባሁ፣ ስድስት ሰአት ከክላስ ወጣሁ፣ መንገድ ላይ አንድ ለከፈኝ፣ ግቢ ውስጥ አንዱ ወደድኩሽ አለኝ፣ ከግቢ ውጪ አንዱ ሰደበኝ እያልኩ ሪፖርት እንዳቀርብልህ ነው ኪኪኪ"
Open in Telegramትግስቴ አለቀ። አንቄ ላወርደው ገና ያዝ ሳደርገው••• "ኤፍዬ ኤፍዬ ለኔ ስትል ስሞትልህ ኤፍዬ ልቀቀው እራሱ ይወርዳል!" አለች ቃል ግብግብ ብላ። " አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ? እራሱ ድብን ይበል አንቺ ለምን ብለሽ ነው የምትሞችው? እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር! ምኑ ዳይኖሰር ነገር ነው በሚስቴ ሞት ተከመረብኝ እኮ" "እሺ አሁን ትወርዳለህ አትወርድም?" አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ "እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !" "ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ! "ታድያ ለማን ነው የቆምከው?" "ለሷ!" "ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው አሃሃሃ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ ! ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!" ሲላት••• ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል••• "እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው። "ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ልጠጣ እየሄድኩ ነው ። ያቺ ግሮሰሪ አትዘጋም። ሙች እውነቴን ነው ያቺ ግሮሰሪ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው. ዝግ ከሆነች ወደ ከተማ እመለሰላሁ"ሲላት "በናትህ ኤፍዬ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለችኝ። ብስጭት እንዳልኩ ባጃጇን አስነስቼ ከነፍኩ። "ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት••• "ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ እሺ በይኝ ?" "ምን ?" "አንዴ ብቻ የቅድሟን ሳቅ ድገሚልኝ " አላት ቃልዬስ ሳቂልኝ የሚላት አግኝታ ነው ለቀቀችው። ደስ አለው። በናትሽ ይህን ሹፌር እናቃጥለው አሁንም ድገሚው ሲላት እኔ እራሴ ሳልፈልግ ሳቄ መጣ። "ግን ምን ሆነሽ ነው ከዚህ ባለ አስፈሪ ፊት ሹፌር ጋር በጭለማ ብቻሽን የምትሄጂው ?" ሲላት አልቻልኩም። ሳቄን ለቀቅኩት። "ግሮሰሪዋ ዝግ ነች ምን ይሻልሀል?" " ዉ ይ ዝግ ነው እንደውም ባንተ ባጃጅ መሄድ አልፈልግን እዛው የጫንከኝ ቦታ መልሰኝ " "ምን ?" አልኩት እያቆምኩ። "ኪኪኪኪ ኤፍዬ በናትህ በቃ አድርሰኸኝ ስትመለስ ጣል አድርገው" "አንቺ ደሞ አበዛሽው!" ቃልዬን ግቢ በር ላይ አድርሻት እንደወረደች ። "ኬት ጠብ አደረካት ይቺን የመሰለች ልጅ እባክህ አንባሳ ነህ አባቴ ይሙት ኮራሁብህ ጀግና " ሲለኝ አሁን ገላጋይ የለም ብሎ እያባበለኝ መሆኑ ገባኝና ፈገግ አልኩ። "አለች እንጂ የኔዋ ያፈር ገንፎ የመሰለች ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ አፈር የመስልኩት። እቺ እኮ ጣፋጭ ጠረኗ ሁሉ እስካሁን እስካሁን ባጃጁ ውስጥ አለ ። አለች እንጂ የኔዋ የላብ ገንቦ ወድጄ መሰለህ እንዴ አፍንጫዬ ላይ ማድያት ያወጠሁት። ያንተ እኮ ሀፒታይዘር በላት ሽንኩርት የሆነች ልጅ አለች እንጂ የኔ ዘጊ ምግብ ስነላ ፊቴ ተቀምጣ ካፈጠጠች ምግቡ ይዘጋኛል ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ ባጥንቴ የቀረሁት።" ወድጄ መሰለህ እያለ ሁሉንም የሱን እንከን በሚስቱ ላይ ሲለድፍ ግራ ገብቶኝ ከሳቄ መልስ "ቆይ ጠልፋህ ነው እንዴ ያገባሀት?" አልኩት "እንዴት? "ፈልገህ አደል እንዴ ያገባሀት?" አልኩት። "መጀመሪያ እማ ያገባሁዋት ላባቷ አንድ ልጅ ነች ብቸኛ ወራሽ እሷ ነች ብዬ ነበር። አባቷ ሲሞት ለካ በየቀበሌው ሁለት ሁለት ወልዷል ተጠራርተው ስምንት ሆነው መጡ ከኔዋ ጉድ ጋር ዘጠኝ አትልም አንዷን ውርስ ለዘጠኝ በጣጥሰው ሲካፈሏት ክው አልኩ። ለሚስቴ የደረሳት ብር አመትም አልቆየ አለቀ፣ ከዛ በኋላ በሰላም ውለንም አድረንም አናውቅም ጭራሽ ያባቷን ፈለግ ተከትላ ስምንት ልጅ በየቀበሌው ልትወልድ ነው መሰለኝ አርፋ አትቀመጥም ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ የምጠጣው ?" ብሎኝ ወረደ። የቃልዬ ዳንስ አይኔ ላይ እየተርገበገበ፣ የኪያ ንግግር ጆሮዬ ላይ እያቃጨለ አልጠፋ አለኝ። ለሶስት ቀን ያህል ከገባሁበት ድባቴ አልወጣሁም። ከቃልዬ ጋር በስልክ እንደነገሩ ከማውራት ውጩ ሶስቱንም ቀን አልተገናኘንም።ቃልዬ በደወልኩም በደወለችም ቁጥር ምን ያህል እንደምታፈቅረኝ ሳትነግረኝ ስልኩን አትዘጋም። ናፍቆት ፀናብኝ። የቃልዬ ናፍቆት ዳንሱንም ከአይኔ ላይ የኪያን ንግግርም ከጆሮዬ ላይ ጠራርጎ ድራሹን አጠፋው። ሶስት ቀን ያላየኋት ቃልዬ በብርቱ ናፈቀችኝ። ንዴቴም ፣ ብሶቴም፣ ኩርፊያዬም በቃልዬ ናፍቆት ታጥቦ ገደል ገባ። እሷን ከማግኘት ረሀብ ውጪ የሚሰማኝም የሚታየኝም ነገር ጠፋ። በሶስተኛው ቀን ማታ ወደቃልዬ ስልክ ስደወል። "ሄሎ" አለኝ የወንድ ድምፅ ነው ። ክፉኛ ደንግጬ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አወናጭፌ አወረድኩትና አፈጠጥኩበት ። አልተሳሳትኩም ቃልዬ ላይ ነው የደወልኩት• ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
Open in Telegram#ተማሪዋ! ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን ፡ ፡ "ትናንት የዛሬው ጭፈራ ቤት አየሁሽ ልበላት እንዴ?" ጭንቅላቴ ከመፈንዳቱ በፊት ተንፍሸው ልገላገል የምትለውን ትበል። በቃ ለኔ ሁለቱም ያው ነው ፣ እኔ በጭንቀት ከመፈንዳቴ በፊት ጭንቀቴን ተንፍሸው ያበጠው ይፈንዳ። ምን ብዬ ልጠይቃት••• "ቃልዬ ከአንድ ቀን በፊት ዛሬ የሄድንበት ጭፈራ ቤት አየሁሽ ልበል?" ስላት ቃልዬ ብስጭት ንጭንጭ እያለች " አዎን እኔና ጓደኞቼ እና የአክስቴ ልጅ ሆነን ወጣ ብለን ነበር " "ኡፍፍፍ••• እና ያክስትሽ ልጅ ከሆነ ከሱ ጋር እንደዛ እየተሻሹ መደነሱ ለምን አስፈለገ?" ስላት••• •••• " ምን ? ምናልክ እንኳንም በግዜ አወቅኩህ ለካ እንደዚህ አይነት ሰው ነህ?" "እንዴት" "ኦኦኦ ተደብቀህ እኔን መከታተል ጀመርክ ገና ፍቅረኛህ ሆኜ እንዲህ እየተደበቅክ የምትከታተለኝ ብታገባኝማ እቤት ውስጥ ቆልፈህብኝ ነው የምትወጣው እንኳንም በጊዜ አወቅኩህ ። እንኳንም ወደፊት ምን አይነት የቅናት ዛር የሚያንዘረዝርህ ቅናታም ባል እንደምትሆን በግዜ እንድነቃ አደረከኝ። ከዚህ ቀደም ዛኪ ማነው አልከኝ፣ ማንነቱን በግልፅ ነገርኩህ ፣ ከዚህ በላይ ምን ፈለክ ? ተሻሸሽ ይላል እንዴ እንኳን ተሻሸሁ ደግ አደረኩ በራሴ ገላ ምን አገባህ። ሆ•••• አንሶላ ስጋፈፍ የያዘኝ አይመስልም በጌታ፣ ምን ውስጥ ነው የገባሁ ትገርማለህ ግን ከማንም ጋር ያሻኝን የመሆን መብት አለኝ እሺ፣ ምንም ነገር የማደርገውም የማላደርገውን አንተን ፈርቼ ከመሰለህ ለራስህ የሰጠኸው ቦታ የተሳሳተ መሆኑን እወቀው። ሰማንያ ቆርጠህ፣ ሽማግሌ ልከህ ፣ ደግሰህ ያገባኸኝ መሰለህ እንዴ? ያኔማ በየመንገዱ ምንድን ነው ለሰውየው ፈገግ አልሽለት እንዴ ? ለምንድን ነው ትኩር ብሎ ያየሽ ? ታውቂዋለሽ እንዴ? እና ካላወቅሽው በየመንገዱ ምን ያስገለፍጥሻል? እያልክ መሳቅ ስፈልግ በናትህ ሳቅ አፈነኝ ልሳቅ እንዴ ኤፍዬ እያልኩ እንዳስፈቅድህ ሳታስገድደኝ አትቀርም። ተሻሸሽ ይለኛል እንዴ እንኳን ተሻሸሁ ፣ ታድያ አሁንስ ከኔ ጋር ምን ታደርጋለህ አንተም አንዷን ፈልገህ አትተሸሽም?። ይሄው አንድ አመት ሊሞላን ነው ካንተ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ጭቅጭቅ ብቻ ነው። እኔ ነፃነቴን እፈልገዋለሁ። ቤት ገባሽ ቤት ወጣሽ ? ማንን አገኘሽ? ከማን ነሽ? እሚለኝ ፍቅረኛ አይደለም እንዲኖረኝ በጭራሽ አልፈልግም!። ካሁን በሁዋላ እንዳትደርስብኝ አልደርስብህም። ድርሽ እንዳትልብኝ። ዞር በልልኝ አትጠጋኝ ኤፍሬም ። እንዳትጠጋኝ እኔ ጮኻለሁ ኤፍሬም!" እያለች ኤፍዬ ስትለኝ እንዳልነበር ስሜን ከነአሰስ ገሰሱ እየጠራች ፣ እንደአብድ እያደረጋት ፣ ንፋስ ላይ እንደተሰጠ ጨርቅ እየተወናጨፈች ሜዳ ላይ ገትራኝ ስትሄድ በአይነ ህሊናዬ ታየኝ ፣ ከዚህ ጭለማ በላይ የኔ ሂወት ሲጨልም ታየኝ እውን የሆነ ያህል ደንግጬ ••• "ኧረ ቃልዬ!" አልኩ ሳይታወቀኝ በደመነፍስ ። "ምንድን ነው የምትለኝ ኤፍዬ ግባና ንዳ እንጂ ቀስ እያልክ ንዳ ማለት ይህን ያህል ያናድዳል?" ስትለኝ ከሄድኩበት የሀሳብ አለም ባንኜ። "ምናልኩሽ?" አልኳት ደንግጬ። ግባና ንዳ እራስሽ ንጂው አልነዳም እየተባባልን ስንጨቃጨቅ አንድ ስካር ጢንቢራውን ያጠናገረው ሰካራም ከየት እንደመጣ እንጃ ጎንበስ ቀና እያለ መጣና ድንገት ባጃጇ ውስጥ ጥልቅ አለ። "ወይኔ ኤፍዬ ድረስ !!" ብላ ጮኸች ቃልዬ ደንግጣ። ዛኪዬ ድረስ አለማለቷም ተመስገን ነው። "እሰይ እኔን እብድ ስትይ የለየለት መጣልሽ " አልኩ በውስጤ ሰውየውን እያየሁት። "የየየየየ የምን ኤፍዬ ነው ? የኔ ስም ገረመው ነው ቆንጅት ኤፍዬ ትያለሽ እንዴ ገረመውብለሽ ጥሪኝ ህቅ•••እስቲ ገረመው በይ?" አላት ። ከመስከሩ የተነሳ ቁጭብ ሎም መሸከም ያቃተው ጭንቅላቱ ብቻውን ይንገዳገዳል። "አሁን ትወርዳለህ አትወርድም ገረመው እኔ ሰው አልጭንም " አልኩት። "ምናልክ ሹፌሩ ሰው አልጭንም እና ኩንታል ልትጭን ነው እንዴ የቆምከው በባጃጅ ኩንታል ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው የሚለውን ዘፈን ጨርሰህ ዝፈነው እሺ ያኔ አቅምህን ታውቃለህ። እኔ እዚህ ጨለማ ውስጥ ባጃጅ ጥበቃ ስንት ሰአት እንደቆምኩ ታውቃለህ ሰው አልጭንም ይላል እንዴ እና ይቺ ከጎኔ የተቀመጠችው ኩንታል ነች እንዴ ? እሄው በደንብ አየኃት አይደለችም " እያለ ወደ ፉቷ ጠጋ ብሎ ሲመለከታት ቃልዬ ሽምቅቅ ብላ ባጇጇ ላይ ተጣበቀች። "አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ ። አይገርምሽም ታምሪያለሽ አይገልፅሽም። አለች እንጂ የኔ ሚስት በጨለማ አትታይ በፀሀይ አትታይ ምኗን አይቼ እንዳገባሁዋት ግራ ገብቶኛል። ወድጄ መሰለሽ የምጠጣው ምናልባት ምኗን አይቼ እንደወደድኳት ስጠጣ ቢገለጥልኝ ብዬኮነው። ሴት መሰለችሽ ሰላቢ በያት እሄው እሷን ስከታተል ስንት አመት ሆነኝ እሳን እጅ ከፍንጅ እይዛለሁ ብዬ ስከተላት ስንት ቦታ ፈንጅ ረገጥኩ መሰለሽ። እኔና ሚስቴኮ አብረን እየኖርን የተፋቷን ብቸኛ ባለትዳሮች ነን ። አብረን እየኖርን አብረን እያደርን ነው አሁንም ድረስ ግን ተፋተናል። ብዙ ወሬ ሰማሁ ወሬ ሰምቼ ከምወስን በገዛ አይኔ አይቼ ቢለያኝ ይሻላል ብዬ ምንም እንዳልሰማ ባል ሆኜ በድብቅ እከታተላት ጀመር እኔ እሷን ተደብቄ ልከታተል እሷው ተደብቃ እኔን ትከታተለኝ እስከሚምታታብኝ ድረስ እንኳንስ በማታ በቀንም ላገኛት አልቻልኩም ቀን ከስራ እቤት መጥቼ የለሽም የት ነበርሽ ስላት አጠገብህ ትለኛለች ። በቃ ሁሌ ያለሁበት ቦታ ሁሉ ያለች ይመስለኛል ወድጄ መሰለሽ ድምፄን ቀንሼ የማወራው የምትሰማኝ እየመሰለኝ እኮ ነው ። " ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ!" አልኩት በንዴት!። "ስማ ሹፌሩ አንተም ወንድ ነህ ነገ ማግባትህ መውለድህ አይቀርም የጀመርኩትን ወሬ ልጨርስበት አታቋርጠኝ ምን ይመስላል በሚስቴ ሞት። ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ? እኔን እኮ ነኝ እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ሲል ቃልዬ ሳቀች። አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና••• "ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው የምትመስይው ! ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !" አላት ። ተበሳጨሁ። "ስማ ሰውዬ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ የሚደገመው አሁን የምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት። "ጠጅ አልጠጣሁም አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? እኔ ጠጅ አልጠጣሁም አረቄ ነው ነው የጠጣሀት ዝም ብለህ በመላ ምት ጠጅ ትላለህ እንዴ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ "እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
Open in Telegram