Account
ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan Official page

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan Official page

ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ወንጌልን በመላው አለም ለማስፋፋት በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እየሰራ ይገኛ። እርሶም ለወገኖ በማጋራት ወንጌልን በመላው አለም እንዲሰበክ የድርሻዎትን ይወጡ .. የሰማነውን እንናገራልርን ያየነውን እንመሰክራለን! ማህበረ ቅዱሳን https://t.me/mahbere_kidusan

Username
@mahbere_kidusan
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers15,316
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR28.34%30-day average

Latest posts

#2204Photo

በማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት 88 የበገኛ ሠልጣኞች ተመረቁ። ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ከሚያከናውናቸው መንፈሳዊ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የበገና ዝማሬ ትውፊትን ማስጠበቅና ማስቀጠል አንዱ ሲሆን። የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትውፊትና ሥርዓተ እና ያሬዳዊ ዝማሬን ጠብቆ ከሕፃናት ጀምሮ ሁሉንም የዕድሜ ክልል በአማከለ መልኩ በገና አሰልጥኖ በማስመረቅ ለአገልግሎት በማሰማራት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰርት በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል 9ኛ እና 10ኛ ዙር 53 የበገና ሰልጣኞችን በሮቤ ፈለገ ብርሃን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም አስመርቋል። ማእከሉ እስካሁን ከ290 በላይ የበገና ደርዳሪዎችን አሠልጥኖ ለአገልግሎት አሰማርቷል። በዚህም የምርቃት መርሐ ግብር ላይ የሮቤ ከተማ እና አካባቢዋ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ጸሓፊ ቀሲስ ዮሐንስ ካሣ፣የቤተ ክህነቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ዲያቆን ይትባረክ ስሜ፣ ተመራቂዎች፣የተመራቂ ቤተሰቦች እና የደብሩ ምእመናን ተገኝተዋል። በዕለቱ ስብከተ ወንጌል ሥነ ግጥም፣ ያሬዳዊ ዝማሬ በማእከሉ መዘምራን እና የበገና ዝማሬ በተመራቂ ተማሪዎች ቀርቧል። ለተማራቂዎች የአደራ መስቀል በአባቶች ቡራኬ የተደረገላቸው ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ከማእከሉ የማበረታቻ ስጦታ ተበርክቷል። ተመራቂዎች ለቀጣይ ሠልጣኞች ለበገና ማስተማሪያ የሚውሉ የበገና አውታር እና ላስተማሯቸው መምህራን ስጦታ አብርክተዋል። በመጨረሻም የማእከሉ ምክትል ተጠሪ አቶ ዘገየ ዲሪባ የእንኳን አደረሳቹሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የበገና ሥልጠና የምትፈልጉ ማእከሉ 11ኛ ዙር ሥልጠና ስለጀምረ ተመዝግባችሁ እንድትማሩ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

Open in Telegram
Views4,3400%vs avg
Forwards—
Reactions66
Comments—
#2203Photo
Views10,600+144%vs avg
Forwards—
Reactions64
Comments—
#2202Text

...እስኪ ንገረኝ በዚህ ምድር የምታጣጥመው ደስታ ምን ዓይነት ነው? እኔ ያስተማርኩህንስ ደስታ በዚህ ዓለም ሳለን ማጣጣም አይቻለንምን? ምን ዓይነት ነፃነትን እንደምታገኝ ልብ በል፤ በጽድቅ የምትመላለስ ከሆነ የትኛውም ሰው ቢሆን አያስፈራህም ወይም አያሸብርህም፤ ጠላትም ቢሆን ወይም በአንተ ላይ የሚሸምቍትም ቢሆኑ ወይም ነገር ሰሪም ቢሆን አበዳሪም ቢሆን ፆታዊ ፍቅርም ቢሆን ክፉ ሰዎችም ቢሆኑ ድህነትም ቢሆን በሽታም ቢሆን ሌሎችም በሰው ላይ የሚመጡ ሁሉ አያስፈሩህም። ነገር ግን እንደ ልብህ ምኞት ሀብትህ እንደ ጅረት ሆኖ ቢፈስ በዚህ ምክንያት በአንተ ላይ ከሚመጡት ሁከቶች፤ ዓመፃዎችና እንቅፋቶች እንዲሁም ጠቦች ሕይወታቸው በጋለሞታ ከሚመሰቃቀልባቸው ሰዎች ይልቅ የታወከ ነው፡፡ በጋለሞታይቱ ሕይወቱ የተመሰቃቀለበት ያ ሰው ራሱን በከንቱ የሚያስታብይ ክብረ ቢስ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ እርሷን ለመማረክ ሲል የፋመ ጠብ ውስጥ ይገባል፡፡ ይህ በብዙ ሺህ እጥፍ ከሞት ይልቅ የከፋ ነው፡፡ ቅጣቱም የሚቋቋሙት አይደለም፡፡ በመንፈሳዊነት ውስጥ ግን እነዚህን የመሰሉ ነገሮች ፈጽሞ የሉም፡፡ ፍሬዎቹም መጽሐፍ እንደሚነግረን፡-“ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም” ናቸው፡፡ በመንፈሳዊው ሕይወት ውስጥ ይህን የመሰለ ሁከት የለም፤ ወይም ያለ ምክንያት የሚባክን ገንዘብ ወይም ያለአግባብ የሚወጣ ወጪ የለም፤ እንዲሁም ጥቂት ሳንቲም ወይም ቁራሽ እንጀራ ወይም ቀዝቃዛ ውኃ ብትስጥ እርሱ በዝቶ ይሰጥሃል፡፡ እርሱም ቢሆን አንተን የሚያስጨንቅ የሚጎዳ ነገር አያመጣብህም፤ ነገርን በሁሉ ትከብር ዘንድ ይፈልጋል፤ ከሚያዋርድ ነገር ሁሉ ነፃ ያወጣሃል፡፡ የክፋት ሥራዎችን ካልተውናቸው ግን ስለመተላለፋችን ምን መከላከያ ልናቀርብ ይቻለናል? ምን ዓይነት ይቅርታስ እናገኛለን? እኛ ከተፈጥሮአችን በተቃራኒ ለሆነ ሥራ ራሳችንን አሳልፈን ሰጥተናልና ከሚንቀለቀል ዘለዓለማዊ እሳት ውስጥ እንጣላለን፡፡ ስለዚህም በዚህ ደዌ የተያዙ ወገኖች ከዚህ ክፉ ሕማም ራሳቸውን እንዲያርቁ ወደ ጤናቸውም እንዲመለሱና ራሳቸውን ለጥፋት አጋልጠው እንዳይሰጡ እመክራቸዋለሁ:: ያ የጠፋው ልጅ በጣም በተጎሳቆለ ሕይወት ውስጥ ይኖር ነበር፤ ወደ አባቱ ቤት በተመለሰ ጊዜ ግን የቀደመ ክብሩ ተመለሰለት፡፡ ከወንድሙ በላይ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ታይቶ በማይታወቅ ፍጹም ደስታ ደስ ተሰኘ፡፡ እኛም እርሱን እንምሰለው፤ ከመንፈሳዊው ሕይወት ርቀን ከሆነ ወደ አባታችን ቤት ለመመለስ እንፋጠን፤ በመንግሥቱ በደስታ መኖርን ገንዘብ ለማድረግ ለኀጢአት ባሪያ ከመሆን እንለይ፤ ራሳችንንም ነፃ እናውጣ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅጽ 2 ገጽ 321-322 በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

Open in Telegram
Views10,100+133%vs avg
Forwards—
Reactions48
Comments—
#2196Photo
Views7,500+73%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#2190Photo
Views6,420+48%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#2184Photo
Views7,030+62%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—

All posts

Connections