Account

Posts of ❤እግዚአብሔርን አመስግኑ❤

newest first

#20828Text
Views106−92%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#19865Audio

Forwarded from የተዋሕዶ ቃልና ዜማ ☦️☦️

🌼 ምን ብትወደኝነው 🌼 ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ/2/ ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/   አዝ 🌼 🌼 🌼 ? አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ እቀኛለሁ ስለአዳኜ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/    አዝ 🌼 🌼 ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/        አዝ 🌼 🌼 ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት አዝማናቱ ስራህን እያሳየ ልሁንልህ ከዓለም የተለየ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/  አዝ 🌼 🌼 ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/          መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ  ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇     @OrthoMezmur16     ╰═══❖•🌺•❖═══╯

Open in Telegram
Views8,530+553%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#19771Audio
Views5,880+350%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#19523Text

የበዓሉ መጠሪያ ስሞች 1. ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል። 2. ቡሔ ይባላል ፦ ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውንየጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡ 3. ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡ 4. "ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›" እንደሚባል ወቅቱበሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት ፤ በዶፉና በጎርፉ ተሸፍና የነበረች መሬት የምትገለጥበት በመሆኑ ነው፡፡ 5.  ቡሔ (ቡሔእየ) ተብሎ ይተረጎማል ይኸውም የደብረታቦር እለት እርሾ ሳይገባበት ተቦክቶ የሚጋገረውን ኅብስት ያሳያል፡፡ 6. ችቦ የመብራቱ ፣ የሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት መብራት የሚበራው 12 ለ13 ዋዜማ ሌሊት በ3 ሰዓት ነው የጌታችን ክብሩ በተገለጠበት ጊዜ ብርሃኑ የሌሊቱን ጨለማ ገፍቶት እስከ አርሞንዔም ደርሶ ነበርና በዚያ አካባቢ የነበሩ እረኞች በሁኔታው ተገርመው ቀንም መስሎኣቸው ሌሊቱም ተዘንግቷቸው በዚያው ቆይተው ነበርና ቤተሰቦቻቸው ምን አግኝቷቸው ይሆን በማለት መብራት አብርተው (ችቦ ይዘው)፣ የሚመገቡትን ይዘው/ሙልሙል/ልጆቻቸውን ፍለጋ ወጥተዋል እረኞችም ያሉበትን ቦታ ለቤተሰቦቻቸው ጅራፍን በማጮኸ አመልክተዋቸዋልና ይህን ለማሰብ ነው፡፡ ዋናው ምሥጢሩ ግን፡- የችቦው ብርሃን የጌታ ክብር መገለጡን፣ የጅራፋ ጩኸት ሐዋርያትን ያስደነገጣቸው የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ሲሆን፣ ኅብስቱ ጌታችን በመስቀል ላይ መሥዋዕት የመሆኑ (የሥጋወደሙ) ምሳሌ ነው፡፡ •  ከላይ እናዳየነው ጅራፋ መጮኹ የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ነው ይኸውም በታቦር ተራራ ላይ እንደሆነም ተገልጧል ስለዚህ ዛሬም ምሳሌነቱን ለማጉላት ጅራፍ የማጮኹን ሥርዓት በተራራ ማድረግ የተሻለ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን  ሥርዓቱን ባልጠበቀ መልኩ ማክበሩ ሃይማኖታዊ ትውፊት የለውም ይልቁንም ሰውን ለማስደንገጥ ተብሎ በአስደንጋጭ ነገሮች  ሰውን ማስደንገጥ የበዓሉን ሥርዓት ማሳደፍም ከመሆኑም በላይ ከሃይማኖተኛ ሰው የማይጠበቅ የሰውን መብትና ክብር መንካት ነው ጌታችን በብርሃን ንስሓ እንመላለስ ዘንድ ዓይነ ልቡናችንን ብሩህ ያድርግልን፡፡                         

Open in Telegram
Views5,280+304%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#19049Audio
Views7,150+447%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—