Account
ሂላል ኪድስ Hilal Kids

ሂላል ኪድስ Hilal Kids

ህፃናትን የሚመጥኑ ኢስላማዊ ትምህርቶችና ጠቃሚ መልዕክቶች የሚተላለፉበት አንዲሁም ልጆችን የሚያዝናኑ የተለያዩ ውድድሮች የሚካሄድበት ቻናል ነው። 👉 መጪውን ትውልድ በመገንባት ጉዞ ላይ አብረውን ይሁኑ!! ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @hilalederbot

Username
@hilaleder
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers1,649
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR23.35%30-day average

Latest posts

#2402Photo

ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል የኡስታዞች የጋራ የስራ ግምገማ ስብሰባ አካሄደ! ​አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ል ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ያሰማራቸውን ኡስታዞች በማሰባሰብ የማዕከሉን አጠቃላይ የትምህርት አፈጻጸም ለመገምገምና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ የጋራ ስብሰባ አካሄደ። ​ከጠቅላላ የማዕከሉ መምህራን 50% ያህሉ በተገኙበት የሚከተሉት ዋና ዋና ውሳኔዎች ተላልፈዋል፦ ​የተማሪዎች የቂርአት ግምገማና የወላጆች ተሳትፎ፦ በተደረገው የተማሪዎች የቂርአት ደረጃ ግምገማ የወላጆች ክትትልና ተሳትፎ 25% ብቻ መሆኑ ተለይቷል። ይህንን ክፍተት ለመሙላትና የወላጆችን ኃላፊነት ለማሳደግ በቀጣይ ከወላጆች ጋር በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የጋራ የምክክር መድረክ እንዲካሄድ ተወስኗል። በተጨማሪም የሁሉም ተማሪዎች የህዳር ወር የትምህርት እቅድ ተዘጋጅቷል። ​የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ፦ የማዕከሉን አስተዳደራዊ አሰራር የሚያዘምን እንዲሁም የኡስታዞችን መብት፣ ግዴታና ኃላፊነት በግልጽ የሚደነግገው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የማሻሻያ ሃሳቦች ቀርበዋል። ደንቡ በማዕከሉ አስተዳደር ተገምግሞ ከጸደቀ በኋላ ለሁሉም ኡስታዞች ተደራሽ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደርሷል። ​የኡስታዞች የአቅም ግንባታ ስልጠና፦ የመምህራንን ሙያዊ እውቀትና የማስተማር ክህሎት ይበልጥ ለማሳደግ በያዝነው ወር ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ተወስኗል። ​ስብሰባው የማዕከሉን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የወላጆችን ተሳትፎ ለማጠናከርና የኡስታዞችን ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት ወሳኝ ውሳኔዎች የተላለፉበት ስኬታማ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል። ​ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል ​#HilalKids#የቁርአን_ማዕከል #ቤት_ለቤት_ቁርአት #

Open in Telegram
Views3850%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#2397Photo

🎓 ሂላል ኪድስ ኢስላማዊ ድርጅት የክረምት ተማሪዎቹን አስመረቀ 🌟✨ በህፃናትና ታዳጊዎች አእምሮ ውስጥ የዲን እውቀትንና ኢስላማዊ እሴቶችን በመቅረፅ 6 ዓመታትን ያስቆጠረው ሂላል ኪድስ፤ በ2016 የክረምት ወቅት በመርየም አካዳሚ ሲያሰተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል! 👉ተማሪዎቻችን በሁለት ወራት ቆይታቸው ከቃኢዳና ቁርአን በተጨማሪ ተርቢያ፣ አረብኛ፣ ሲራ፣ ሀዲስ፣ አዝካር፣ ፊቂህ፣ ተጅዊድ እና አዳብን ጨምሮ በድርጅቱ በራሱ በተዘጋጁ መጻሕፍትና የትምህርት ስርዓት አጠቃላይ የዲን እውቀት ሲቀስሙ ቆይተዋል። ✨ 🥰ተማሪዎቻችን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ያሳዩት የመማር ፍላጎት፣ የቁርኣን እና የኢስላማዊ እውቀት እድገት ለሁላችንም ትልቅ ኩራት ነው። የተማሪዎቻችንን ጥረት እውን ለማድረግ ከጎናችን ለነበራችሁ ውድ ወላጆች እና መምህራን በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው። 👉ውድ ቤተሰቦቻችን በቤት ለቤት የቂርአት አገልግሎታችን ልጆቻችሁን በማስመዝገብ በጋውንም ከሂላል ኪድስ ጋር ታሳልፉ ዘንድ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለተመራቂ ተማሪዎች ብሩህ ተስፋ እንመኛለን! ሂላል ኪድስ ኢስላማዊ ድርጅት

Open in Telegram
Views886+130%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#2395Text
Views929+141%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#2394Photo
Views1,100+186%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#2393Photo
Views997+159%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections