ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል የኡስታዞች የጋራ የስራ ግምገማ ስብሰባ አካሄደ! አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ል ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ያሰማራቸውን ኡስታዞች በማሰባሰብ የማዕከሉን አጠቃላይ የትምህርት አፈጻጸም ለመገምገምና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ የጋራ ስብሰባ አካሄደ። ከጠቅላላ የማዕከሉ መምህራን 50% ያህሉ በተገኙበት የሚከተሉት ዋና ዋና ውሳኔዎች ተላልፈዋል፦ የተማሪዎች የቂርአት ግምገማና የወላጆች ተሳትፎ፦ በተደረገው የተማሪዎች የቂርአት ደረጃ ግምገማ የወላጆች ክትትልና ተሳትፎ 25% ብቻ መሆኑ ተለይቷል። ይህንን ክፍተት ለመሙላትና የወላጆችን ኃላፊነት ለማሳደግ በቀጣይ ከወላጆች ጋር በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የጋራ የምክክር መድረክ እንዲካሄድ ተወስኗል። በተጨማሪም የሁሉም ተማሪዎች የህዳር ወር የትምህርት እቅድ ተዘጋጅቷል። የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ፦ የማዕከሉን አስተዳደራዊ አሰራር የሚያዘምን እንዲሁም የኡስታዞችን መብት፣ ግዴታና ኃላፊነት በግልጽ የሚደነግገው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የማሻሻያ ሃሳቦች ቀርበዋል። ደንቡ በማዕከሉ አስተዳደር ተገምግሞ ከጸደቀ በኋላ ለሁሉም ኡስታዞች ተደራሽ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደርሷል። የኡስታዞች የአቅም ግንባታ ስልጠና፦ የመምህራንን ሙያዊ እውቀትና የማስተማር ክህሎት ይበልጥ ለማሳደግ በያዝነው ወር ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ተወስኗል። ስብሰባው የማዕከሉን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የወላጆችን ተሳትፎ ለማጠናከርና የኡስታዞችን ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት ወሳኝ ውሳኔዎች የተላለፉበት ስኬታማ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል። ሂላል ኪድስ ቤት ለቤት የቁርአን ማዕከል #HilalKids#የቁርአን_ማዕከል #ቤት_ለቤት_ቁርአት #
Open in TelegramPosts of ሂላል ኪድስ Hilal Kids
🎓 ሂላል ኪድስ ኢስላማዊ ድርጅት የክረምት ተማሪዎቹን አስመረቀ 🌟✨ በህፃናትና ታዳጊዎች አእምሮ ውስጥ የዲን እውቀትንና ኢስላማዊ እሴቶችን በመቅረፅ 6 ዓመታትን ያስቆጠረው ሂላል ኪድስ፤ በ2016 የክረምት ወቅት በመርየም አካዳሚ ሲያሰተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል! 👉ተማሪዎቻችን በሁለት ወራት ቆይታቸው ከቃኢዳና ቁርአን በተጨማሪ ተርቢያ፣ አረብኛ፣ ሲራ፣ ሀዲስ፣ አዝካር፣ ፊቂህ፣ ተጅዊድ እና አዳብን ጨምሮ በድርጅቱ በራሱ በተዘጋጁ መጻሕፍትና የትምህርት ስርዓት አጠቃላይ የዲን እውቀት ሲቀስሙ ቆይተዋል። ✨ 🥰ተማሪዎቻችን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ያሳዩት የመማር ፍላጎት፣ የቁርኣን እና የኢስላማዊ እውቀት እድገት ለሁላችንም ትልቅ ኩራት ነው። የተማሪዎቻችንን ጥረት እውን ለማድረግ ከጎናችን ለነበራችሁ ውድ ወላጆች እና መምህራን በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው። 👉ውድ ቤተሰቦቻችን በቤት ለቤት የቂርአት አገልግሎታችን ልጆቻችሁን በማስመዝገብ በጋውንም ከሂላል ኪድስ ጋር ታሳልፉ ዘንድ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለተመራቂ ተማሪዎች ብሩህ ተስፋ እንመኛለን! ሂላል ኪድስ ኢስላማዊ ድርጅት
Open in Telegramእንኳን ደስ አላችሁ😍 የ2018 መድረሳችንን እንዲ ሙቅ አድርገን ከፍተናል🎉🎉 👉ምዝገባ አለመጠናቀቁን እየገለጽን የዚህ ወርቃማ ዕድል ተጠቃሚ በመሆን የልጅዎን የክረምት ግዜያት ያስውቡ ዘንድ እናስታውሰዎታለን! አድራሻ፡- ቤተል ዶ) ር ሃድራና አባስ ክሊኒክ 100 ሜትር ገባ ብሎ ስልክ 0940912291 ቀድሞ ለደወለ ሰው በተማሪ የ10% ቅናሽ ያገኛል።
Open in Telegram🥰🥰ጁምአ ሙባረክ 🌱🌱የልጆችዎን ክረምት በሂላል ኪድስ መድረሳ ያስዉቡ !! 🎉 አሁንም ዕድል አሎት ፈጥነው በ0940912291 አልያም በ0970979393 በመደወል ቦታ ያስይዙ!! 👉 በአካል ለመመዝገብ በሚቀርብዎ የመድረሳው ቅርንጫፎች ቤተል ዶ/ር ሃድራና አባስ ክሊንክ 100 ሜ ገባ ብሎ አልያም ጀሞ ሚካኢል መስታውት ክሊኒክ ጀርባ በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ!! ሂላል ኪድስ የክረምት መድረሳ 😍እነሆ የማይረሳ የዕረፍት ግዜ ለልጆቻችን🍀
Open in Telegramበድጋሚ ለወላጆችና ልጆች የቀረበ የክረምት ስጦታ! ስመ ጥሩ ሂላል መድረሳ ለ2018 ክረምት የልጆች የተርቢያ፣ የእስላማዊ የእውቀት ዘርፎች እና የመዝናኛ መርሃግብሮች ምዝገባ ጀምሯል። የምናቀርበው አገልግሎት 👉ሂፍዝ 👉ቃኢዳ 👉 ቁርአን በተጅዊድ 👉 ሂፍዝ 👉 በልጆች አይምሮ ተመጥነው በተዘጋጁ የማእከሉ መማሪያ መፅሀፍ የፊቅህ፣ ሲራ፣ አዳብ፣ አዝካር፣ አረብኛና የሀዲስ ትምህርቶች 👉 ትምህርታዊ ጉዞዎች ከጣፋጯ ሀላ እና ከሸይኽ ሉቅማን ጋር 👉 የልጅዎን እድገትና ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉበት ኮሚኒኬሽን ቡክ 📍 አድራሻ ቁጥር 1 ቤተል፣ ከዶክተር ሀድራና አባስ ክሊኒክ 100 ሜትር ገባ ብሎ፣ በመርየም አካዳሚ ጊቢ ውስጥ 📍 ቁጥር 2 ጀሞ ሚካኤል፣ ከመስታወት ሆስፒታል ጀርባ፣ በኡማ ቪዥን አካዳሚ ጊቢ ውስጥ 🕒 ከሰኞ እስከ ጁመዓ ከ3:00 ሰዓት እስከ 9:30 ሰዓት 📞 በ0940912291 ይደውሉ 📌 ምዝገባ ሰኔ 25 ይጠናቀቃል።
Open in Telegram🌙እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ 🥰በአሉ ከልጆቻችሁ ጋር አስደሳች ቆይታ የምታደርጉበት ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን!! ✨ሂላል ኪድስ ኢስላማዊ ድርጅት
Open in Telegramላይክ ፎሎ እና ሼር በማድረግ ተደራሽ ያድርጉልን🙏 https://vm.tiktok.com/ZS912SDHhcmE9-4uOFz/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
Open in Telegram