Account
ገድለ ቅዱሳን ዘእለታት

ገድለ ቅዱሳን ዘእለታት

ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Username
@gedlekdusan
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers1,248
Avg views per post, 7d89last 7 days
ERR7.10%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 25, 2026124
Nov 26, 2026101
Nov 27, 202688
Nov 28, 202648

Most viewed this month

  1. 01
    Views145
    Forwards—
    Reactions9
    Comments—
  2. 02
    Views138
    Forwards—
    Reactions6
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photo
    Views126
    Forwards—
    Reactions2
    Comments—
  4. 04
    Views124
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—

Latest posts

#13976Link preview
Views27−70%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h19
4 h27
  1. After 1 hour19
  2. Total to date27
#13974Photo
Views22−75%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h16
4 h22
  1. After 1 hour16
  2. Total to date22
#13973Text

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት +"+ =>በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች:: +ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ (የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው) በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት: ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው:: +ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ: ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር:: +በዛው ልክ ደግሞ ገና በ20 ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል: በውበቱም ደመ ግቡ: በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል:: +ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን (የጠላት) ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል:: +የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው:: +አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ: በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት 24 ክንድ ነበር:: +ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ: ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ: ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው:: +ክርስቶስ ተክዶ: ጣዖት ቁሞ: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው: የክርስቲያኖች ደም ፈሶ: ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ: ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ:: +ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ:- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ: ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ: ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት:: +በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ:: +በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን (ዜናህን) የጻፈ: ያጻፈ: ያነበበ: ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: +በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል:: +"+ ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ +"+ =>ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ: በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ50ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: +እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል:: +ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ (አንያኑ) ይባላል:: ጣዖት አምላኪ: ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው (መስፊያው) ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ (አታኦስ)" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር:: +ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ: ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው:: +ወዲያውም ደሙ ቁሞ: ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም: ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው:: +አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው:: +ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ60 ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) አድርጐ ሾመው:: +ቅዱስ አንያኖስም ለ12 ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ:: +የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ 118ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ 117ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት:: =>አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: =>ኅዳር 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት 2.ቅዱስ አንያኖስ (አንያኑ) =>ወርኀዊ በዓላት 1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ 3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና 5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት =>+"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: +"+ (1ዼጥ. 3:13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Open in Telegram
Views24−73%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h17
4 h24
  1. After 1 hour17
  2. Total to date24
#13971Link preview

+++#ከላይ_የሚመጣ_ፈተና#+++ (Temptation From Above) አረጋዊው አባ ቀልዮጳ በክርስትና ሕይወት ስንኖር ከስምንት አቅጣጫ ፈተና ሊመጣብን ይችላል ይላሉ። ሌሎቹን ትቼ አንዷንም ከፍዬ አጭር ነገር ላቀርብ ወደድኹ። ከስምንቱ ዝርዝር ውስጥ አንዱ ከላይ የሚመጣ ፈተና (Temptation from above) የምንለው ነው። ይህ የፈተና ዓይነት በውስጡ ኹለት ክፍል አለው። አንደኛው በአጭሩ ከአቅም በላይ መጋደልን ማዕከል ያደረገ ነው። በአንዴ ፍጹማን የሚያደርጉትን ለማድረግ መሞከር፣ በአንዴ ብዙ ዓመት እንደ ተጋደሉ ቅዱሳን ተጋድሎ ካልተጋደልኹ ማለት፣ ወይም በሕማም ውስጥ ኾነው ሳለ ለረጅም ጊዜ ካልጾምኩ፣ ገና ከዓለም የመጡ ኾነው ሳለ እንደ አባ እንጦንስ ካልጸለይኹ ... የማለት ፈተና ነው። መንፈሳዊነት የማይቋረጥ ዕድገት እንጄ በአንዴ ከኹሉ ተደርሶ የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም። ...! ኹለተኛው መንፈሳዊ ብስለትንና ዕድገትን ያላገናዘበ የቅዱሳት መጻሕፍት መረዳት ፍላጎት ወይም ከአቅም በላይ የኾነ የመንፈስ ቅዱስን ምሥጢር ወይም ጠቅለል ሲል የእግዚአብሔርን ምሥጢር የመመርመርና የመረዳት ፍላጎት ፈተና ነው። ቅዱሳን በቅድስና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተገልጦላቸው የተረዱትን የመንፈስ ቅዱስ ምሥጢር እንዲሁ መንፈሳዊ ዕድገት ላይ ሳይደርሱ በጥልቀት የመረዳትና የማስረዳት ፍላጎት ፈተና ነው። ያለ አቅም እንደ ቄርሎስ፣ እንደ አትናቴዎስ፣ እንደ ሄሬኔዎስ ራስን አድርጎ የማሰብ ወይም የማሳሰብ ፈተና ነው። ጥልቅ የኾነውን የእግዚአብሔርን ምሥጢር በራስ የመረዳት መጠን የማድረግና የማስረዳት ፈተና ከላይ የሚመጣ ፈተና ነው። እንግዲህ ይህን ዘመን በእርጋታ ካየነው በአብዛኛው በኔ ዕድሜና ከኔም አነስ ያልን ጀማሪዎች በጣም የመራቀቅ፣ የራስን መረዳት ያለቀለት አድርጎ የማሰብ፣ በአጭር ንባብ ብዙ የመናገር፣ ረጋ ብሎ ሕይወቱ ያላቸውን ከማማከር ይልቅ በለብ ለብ ንባብ የተገኘችን ዕውቀት እንደ ልዩ መረዳት አድርጎ በማሳሰብ ራስን የማግነን ወይም ራስን የማስወደድ ፍላጎት ያለብን ይመስለኛል። ከባድ ፈተና ላይ ነን። በአንዴ ከላይ ያሉትን ታላላቅ አባቶች ለመምከር፣ ለማረም፣ በኔ መረዳት በኩል እለፉ ብሎ ለመለካት፣ እንደኔ ተቀባይነት የላችሁም የሚል የሚመስል reaction የማሳየት እጅግ ፈተና ውስጥ ነን። ፍጹም የማንሰማና የምንቸኩል፣ ቶሎ ቶሎ እያልን ረቂቁን ምሥጢረ እግዚአብሔር አእምሯዊ ብቻ አድርገን በመፈላሰፍ አጀንዳ የመኾን ... ፈተናችን ጥልቅ ነው። የኾነች ንባብ ካገኘን አንረጋጋም፣ አንመረምርም፣ አናብሰለስልም፣ በአግባቡ ጊዜ ወስደን ለመረዳት አንሞክርም ይልቁን ወዲያው ማጯጯህና በማይኾን አገላለጽ መግለጽ ልማድ እየኾነብን ይመስላል። ትንሽ ንባብ ይዘን ወዲያው መካሪ ዘካሪ፣ የክርስትና አስተማሪ ለመኾን እንጥራለን። በተለይ ይህ ሚዲያ ማንንም እንዳንፈራ፣ ውስጣችን ጻፍ ያለንን እንዲሁ ዝም ብሎ የመጻፍ ፍላጎት ላይ አድርሶናል። ሌላው ቀርቶ አንዳንዴ የምንጽፈውና የምንናገረው ስለ እግዚአብሔር መኾኑን እንኳን ልብ የምንል አይመስልም። በኹሉም ዐዋቂ የመምሰል አደገኛ ፈተና ውስጥ ከመኾናችን የተነሣ፣ በአጭር ዕድሜያችን በመገለጥ እናግኝ ወይስ በምን እንጃ! ነገረ ሃይማኖትን፣ ታሪክን፣ ፍልስፍናን፣ ሳይንስን፣ ... ኹሉንም ነገር ካላብራራው፣ ካልተነተንኩ፣ በኹሉም አለኹኝ ማለት ጀምረናል። በኹሉም ረገድ የበዛ ተራቃቂነት፣ ከመጠን ያለፈ መርማሪነት፣ ከመጠን ያለፈ አመክንዮአዊነት፣ እጅግ ጠርጣሪነት፣ ... ይታይብናል። እንግዲህ በጊዜ ብንስተካከል አይሻልምን? እግዚአብሔር ከክፉ ፈተና በቸርነቱ ይጠብቀን። https://t.me/gedlekdusan

Open in Telegram
Views67−24%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h44
8 h67
  1. After 6 hours67
  2. Total to date67
#13970Text
Views65−27%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h33
8 h65
  1. Total to date65
#13969Photo
Views65−27%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h32
8 h65
  1. Total to date65
#13967Photo
Views93+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
11 h57
26 h93
  1. After 24 hours93
  2. Total to date93
#13966Link preview

✞✞✞✝ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ ✞✞✞✝ ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል:: እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ (ሰርግዮስ) ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር:: ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና:: በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው:: ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ:: ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ:: ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ:: በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት:: መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት:: ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት:: ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ6 ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል:: ✞✞✞✝ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ ✞✞✞✝ ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል:: በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት:: ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና 5 ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን (መታሠሩን) ሰማች:: ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ:: ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው:: ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ5 ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ:: ††† አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ኅዳር 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት 3.ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ (የቅዱሱ ሚስትና ልጅ) 4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ (ልደቱ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 4.አቡነ ስነ ኢየሱስ 5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም 6.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ††† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" ††† (ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Open in Telegram
Views93+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
11 h56
26 h93
  1. After 24 hours93
  2. Total to date93
#13965Link preview
Views890%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—

All posts

Connections