Account

Posts of ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]

newest first

#3932Text
Views448−22%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#3929Text

የወርሃዊ የዳዕዋ ፕሮግራም ጥሪ! ወደ አላህ የሚያቀርብህን ዕውቀት ለመቅሰም፣ ልብህን በኢማን ለማደስና ከመልካም ሰዎች ጋር ለመሰብሰብ ተዘጋጅተሃልን? እነሆ! የወርሃዊ የዳዕዋ ፕሮግራማችን የዚህ ወር ተራ ደርሷል። በቀደሙት ወራት በተለያዩ መስጂዶች የተካሄዱትን የዳዕዋ ፕሮግራሞች በመቀጠል፣ በዚህ ወር የምንገናኘው በ ዓኢሻ መስጂድ ይሆናል። 📖 የአላህን ቃል ለመስማት፣ 🌱 የዲን ዕውቀትን ለመጨመር፣ 🤝 የወንድማማችነትን ትስስር ለማጠናከር፣ ❤️ ልቦችን በኢስላማዊ እሴቶች ለማቀራረብ። 🗓 ቀን፦ መጪው እሁድ 6/3/2019 ዓ.ል. 📍 ቦታ፦ ዓኢሻ መስጂድ 🔺ውድ የወራቤና አካባቢዋ ሙስሊሞች! ይህን ፕሮግራም የሌላው ሰው ጥሪ ብቻ አድርጋችሁ አትመልከቱት፤ ለራሳችሁ የዲን ዕድል አድርጉት። በእውቀት የተገነባ ማኅበረሰብ በአንድ ቀን አይፈጠርም፤ እንዲህ ባሉ የዕውቀትና የኢማን ስብሰባዎች ይገነባል። እንገናኝ! እንማር! እንተሳሰብ! በዲናችንም አብረን እንጠናከር! የአላህ ፈቃድ ከሆነ በዚህ የተባረከ ስብሰባ እንገናኛለን። https://t.me/fewaidworabe

Open in Telegram
Views934+63%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#3927Text

Forwarded from አቡ ሱለይማን ኻሊድ ሙሀመድ ዲናዊ ጥያቄዎች መመለሻ

تركناهم لله …      ለአላህ ተውናቸው በክፉ ጥርጣሬ ለተመለከቱን፣ ባልሠራነው ለከሰሱን፣ በእኛ ውስጥ የሌለውን ባሕርይ በእኛ ላይ ለለጠፉት፣ ልባቸውንም በሐሰት ግምት ሞልተው እስከሚያምኑበት ድረስ ለደረሱት… ለአላህ ተውናቸው። ያነወሩንን፣ የበደሉንን፣ ውለታችንን የረሱትን፣ ልባችንን ያቆሰሉትንና የሰበሩትን፣ በሐሰት የከሰሱንንና ያልተናገርነውን የቀጠፉብንን፣ ስማችንን ያጎደፉትን፣ ንግግራችንን ያጣመሙትን፣ በበደል ላይ በደል የጨመሩትን ሁሉ… ለአላህ ተውናቸው። መልስ ማጣት ሳይሆን ከከንቱ ክርክር ራሳችንን ለማራቅ፣ የማይጠቅም ሙግትን ንቀን፣ ከቂምና ከበቀል ስሜት በላይ ሆነን፣ ፍርዳችንን በአላህ ፍትሕና ሚዛን ላይ በመተው… ለአላህ ተውናቸው። እርሱ ስለ እኛ ከራሳችንም በላይ ዐዋቂ ስለሆነ፣ የእኛን እውነታ ከእነርሱ ጥርጣሬ በላይ በሚገባ ስለሚያውቅ፣ የተደበቀውን ሁሉ ስለሚመለከት፣ በስሜትና በግል ጥቅም ከሚነዱ ሰዎች ሁሉ በላይ በፍርዱ ፍትሐዊ ስለሆነ… ለአላህ ተውናቸው። https://t.me/ibnmuha2

Open in Telegram
Views722+26%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#3924Text
Views702+22%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—