⭕️ወላይታ ድቻ በክለቡ ደጋፊዎች ለፈጸሙት የዲሲፕሊን ጥፋት 75000/ሰባ አምስት ሺህ/ ብር እንዲከፍል ተወሰነ ! ወላይታ ድቻ ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ሁለተኛዋ ግብ መቆጠር በኋላ ከ66ኛው ደቂቃ ጀምሮ የክለቡ ደጋፊዎች ውሃ የያዙ ፕላስቲክ ኮዳዎች ወደ ሜዳ ሲወረውሩ እንደነበር የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦታል። ስለሆነም ደጋፊዎች ለፈጸሙት ጥፋት ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት ፈጽመው የተለለፈባቸው ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻሉ ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 66 በተራ ቁጥር 3ሀ መሠረት ብር 75000/ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል። ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች 2 ወንበሮች ስለመሰብሰፋቸው ሪፖርት ቀርቦታል። ስለሆነም ክለቡ የተሰበሩትን ወንበሮች እንዲያሰራ ወይም የስታደየሙ ባለቤት የሚያቀርበውን ውጪ እንዲከፍል ወስኗል። ወላይታ ድቻ ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች 1 ወንበር ስለመሰብሰፋቸው ሪፖርት ቀርቦታል። ስለሆነም ክለቡ የተሰበረውን ወንበር እንዲያሰራ ወይም ያስታደየሙ ባለቤት አካርዮ የሚያቀርበውን ውጪ እንዲከፍል ወስኗል። @Ethiopian_Coffee_Sc @Ethiopian_Coffee_Sc
Open in Telegramቡናችን 👆
💛 ቡናችን | የቡናማውያን ድምፅ ☕️ የ12 ለባሹ እውነተኛ መኖሪያ! 💛🤎 ቡናውያን በአንድነት የሚደምቁበት፣ የክለባችንን እውነተኛ የድልና የታሪክ ጉዞ በየደቂቃው የሚከታተሉበት ታማኝ የመረጃ ማዕከል! ስለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና የሚወጡ ትኩስ ታማኝ እና ፈጣን መረጃዎችን በየደቂቃው ያግኙ! ለአስተያየት @EthiopianCoffeeScBot
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 11, 2026 | 1,800 |
| Nov 12, 2026 | 1,640 |
| Nov 13, 2026 | 2,010 |
| Nov 14, 2026 | 1,805 |
| Nov 17, 2026 | 1,470 |
| Nov 18, 2026 | 856 |
| Nov 20, 2026 | 1,130 |
| Nov 21, 2026 | 1,139 |
| Nov 22, 2026 | 1,320 |
| Nov 25, 2026 | 786 |
| Nov 26, 2026 | 612 |
Most viewed this month
- 01Views2.01KForwards—Reactions19Comments—
- 02Views1.89KForwards—Reactions8Comments—
- 03Views1.8KForwards—Reactions9Comments—
- 04Views1.72KForwards—Reactions18Comments—
Latest posts
የጨዋታው ኮከብ ሽልማቱን ከተረከበ በኋላ በሰጠው አስተያየት በሁለተኛው 45 ደቂቃ ተቀይሮ የገባው አብዱልከሪም ወርቁ የጨዋታውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መቀየሩን ገልጿል። "አብዱልከሪም ወደ ሜዳ መግባቱ ጨዋታውን ለእኛ ይበልጥ ቀላል እንዲሆንልን አድርጎታል፤ እሱ በጣም ምርጥ ተጫዋች ነው" ሲል ተይባ የቡድን አጋሩን አድናቆት ችሮታል። አክሎም ቡድኑ በሁለተኛው አጋማሽ መስመሩን ወደፊት አስጠግቶ በመጫወትና የተፈጠሩትን አጋጣሚዎች በመጠቀም ከአስቸጋሪ የውጤት ማጣት በኋላ ወሳኙን 3 ነጥብ ማሳካት መቻሉን ገልጿል @Ethiopian_Coffee_Sc @Ethiopian_Coffee_Sc
Open in Telegram"ኢትዮጵያ ቡና ቤቴ ነው፤ ያለኝን አቅም ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ አብዱልከሪም ወርቁ @Ethiopian_Coffee_Sc @Ethiopian_Coffee_Sc
Open in Telegram«የአብዱልከሪም ወደ ሜዳ መግባት ጨዋታውን አቅልሎልናል» — የጨዋታው ኮከብ ታይባ @Ethiopian_Coffee_Sc @Ethiopian_Coffee_Sc
Open in Telegram"በአስፈላጊ ሰዓት የምንፈልገውን ሶስት ነጥብ አግኝተናል!" - አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ☕️⚽️ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከጨዋታ በኋላ የሰጡት አስተያየት፡ "በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ተጋጣሚያችን ዝቅ ብሎ (Low block) ስለሚጫወት ኳሱን ተቆጣጥረን አደጋ ለመፍጠር ሞክረናል፤ ነገር ግን እንደታሰበው አልሄደም። በሁለተኛው አጋማሽ አብዱልከሪም ወርቁን ካስገባን በኋላ የቡድናችን የማጥቃት ፍላጎትና የጎል አፒታይት ተስተካክሏል። ዛሬ ሶስት ነጥብ ያስፈልገን ስለነበረ በአስፈላጊ ሰዓት ማግኘታችን በጣም ጥሩ ነው። አጥቂዎች ጎል ባገኙና ቡድኑ ባሸነፈ ቁጥር ለቀጣይ ጨዋታዎች ያለው አዎንታዊ ተፅዕኖ ቀላል ስላልሆነ ቡድኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ያሸጋግረዋል። ምስል ከሶከር ኢትዮጵያ የተወሰደ @Ethiopian_Coffee_Sc @Ethiopian_Coffee_Sc
Open in Telegramከድል ጋር ታርቀናል 💪 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል። ቡናማዎቹን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ታይባ ምቦኑዩምዋኒ እና ዩቪ ዮሴፍ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።
Open in Telegram📢 የጨዋታ ቀን! ⚽ ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ 📅 ዛሬ፡ ቅዳሜ (12/03/2019) 🕤 ሰዓት፡ 9:30 📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ ስታዲየም በብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ሊግ የተመለሰ ሲሆን፣ ዛሬ በ9:30 ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ከወላይታ ድቻ ጋር ይጫወታል። #ኢትዮጵያ_ቡና_ከእኛ_የሚፈልገው! «ቡና ካለ እኛም አለን!» ብለን ቃላችንን የሰጠነው እኛ፣ ኢትዮጵያ ቡና በሜዳ ውስጥ እየተጫወተ ከጎኑ መገኘታችን ግድ ይለናል። ልጆቻችን ከመቼውም በላይ ወደ አሸናፊነት እንዲመለሱ የእኛን የማያቋርጥ ድጋፍ ይፈልጋሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ከእኛ የሚፈልገው የሚስማርን ፤...ሜዳውን የሚያናጋና ተጋጣሚን የሚያንበረክክ ድጋፍ፣ የጥላ ፎቅን ዕረፍት የለሽ ጩኸት፣ የካማን አንሼ ልብ የሚያሞቅ ዝማሬ — በአጠቃላይ የካምቦሎጆን ደም የሚያሞቅ ዝማሬ ከእኛ ይጠበቃል። ስለዚህ ሁሉም ደጋፊዎች እና አስጨፍሪዎችን በየቦታቸው ካምቦሎጆን በማድመቅ ተጫዋቾችን በማበረታታት ኢትዮጵያ ቡናን ወደ አሸናፊነት የምንመልስበት ቀን ይሆናል። ድል ለኢትዮጵያ ቡና
Open in Telegram✔ቀጣይ ጨዋታ ⚽️ ኢትዮጵያ ቡና 🆚 ወላይታ ድቻ 📆ነገ ቅዳሜ - ህዳር 12/2019 🕘 9:30 🏟️ አዲስ አበባ ስታድየም 🎫 http://ticket.ethiosport.pro
Open in TelegramConnections
Similar channels
ኢትዮ ባርሴሎና በኢትዮጵያ ™@ethio_barcelona_fcSport1.26K
ኢትዮ ሪያል ማድሪድ Troll 😁⚽️@ethio_real_madrid_trollSport1.58K
Dire Soccer@diresoccerSport1.59K
ኢትዮ ቼልሲ Troll ቻናል@troll_chelseaSport1.7K
Ethio liverpool troll channel@troll115Sport1.99K
BISRAT TROLL 🥇@bisrat_trollSport2.5K
ከእግር ኳስ ማህደር ⚽️@soccer_talksSport2.71K
TROLL ማንችስተር ሲቲ ኢትዮ FANS™@man_city_ethiofans_trollSport3.08K