የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጩ ! በኢትዮጵያ ሽንፈት የገጠማቸው ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጭተዋል። አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ከጋዜጠኞች ጋር ወደ ፀብ መግባታቸው ተገልጿል። ፀቡ ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ ከጋዜጠኞች በቀረበ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በኋላም ወደ አካላዊ ግጭት አምርቷል። አስተያየት ለመስጠት በቦታው የተገኘው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጣልቃ ገብቶ ግጭቱን ማረጋጋቱ ተገልጿል። አሰልጣኙ ጋዜጠኛውን “ እሰብርሀለሁ “ እያሉ ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል። የብሔራዊ ቡድኑ የድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ በሁከት መጠናቀቁን የሞዛምቢክ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። @DireSoccr
Open in Telegram
Dire Soccer
The Voice of Ethiopian Football Telegram : https://t.me/DireSoccer Facebook : https://m.facebook.com/diresoccer
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 27, 2026 | 437 |
| Nov 6, 2026 | 346 |
| Nov 7, 2026 | 413 |
| Nov 9, 2026 | 309 |
| Nov 10, 2026 | 265 |
| Nov 12, 2026 | 207 |
| Nov 13, 2026 | 204 |
Most viewed this month
- 01Views456Forwards—Reactions1Comments—
- 02Views439Forwards—Reactions—Comments—
- 03Views416Forwards—Reactions—Comments—
- 04Views413Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
“ ዩናይትድን አለመቀበል ከባድ ነው “ ፖቼቲኖ ማንችስተር ዩናይትድን የተረከቡት አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኙ ዛሬ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ " አሜሪካን ለመልቀቅ መወሰን የህይወቴ ከባዱ ውሳኔ ነው “ ሲሉ በእንባ ተናግረዋል። አክለውም " እንደ ማንችስተር ዩናይትድ ያለ ትልቅ ክለብ ሲጠይቅ እድሉን ማሳለፍ ከባድ ነው “ብለዋል። “ እንደዚህ አይነት እድሎች በህይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ የማይፈጠሩ ናቸው “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። “ ማንችስተር ዩናይትድን በመቀላቀሌ በጣም ተደስቻለሁ ነገርግን አሁን ስለእሱ ለማውራት ጊዜው አይደለም “ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ. @DireSoccer
Open in Telegramየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞዛምቢክ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ ! በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ ግብር ማፑቶ ላይ በዚምፔቶ ስታዲየም ሞዛምቢክን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 አሸንፏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ48 የማጣሪያው ተሳታፊ ቡድኖች ብቸኛ ያደረገውን ግብ ያለማስቆጠር ችግር በቀረፈበት ጨዋታ፣ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ 87ኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ አስቆጥሯል። የማጣሪያውን የመጀመሪያ ግብ እና የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ያገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ደረጃውን ወደ 3ኛ አሻሽሏል። ምድቡን ሴኔጋል በሰባት ነጥብ ስትመራ፣ ሞዛምቢክ በአራት ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሶስት ነጥብ ይዛ ከኢትዮጵያ በግብ ክፍያ ያነሰችው ሱዳን ግርጌ ላይ ተቀምጣለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በባህርዳር ስታዲየም ያደርጋል። @DireSoccer
Open in Telegramፈተናውን በእንግሊዝኛ አንፈተንም! አሰልጣኞች ጥያቄ አነሱ! የCAF A ላይሰንስ ለመውሰድ ከተዘጋጁ 35 ሰልጣኞች 2ቱ ጥያቄ አነሱ! «ፈተናውን በእንግሊዝኛ አንፈተንም!» በፋስት ትራክ የB ዲፕሎማቸውን ወስደው በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እግር ኳስ ላይ በማሰልጠን ላይ ለሚገኙ የቀድሞ አንጋፋ ተጫዋቾችና የአሁን አሰልጣኞች የCAF A ላይሰንስ ስልጠና የመውሰድ አዲስ ዕድል መፈጠሩ ይታወሳል። ለዚህ ስልጠና የመግቢያ ፈተናው ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የፋስት ትራክ የB ዲፕሎማ ወስደው ለCAF A ላይሰንስ ስልጠና ለመግባት የተዘጋጁ አንዳንድ አሰልጣኞች ፈተናው በእንግሊዝኛ መሰጠቱን በመቃወም ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ። አሰልጣኞቹ እንደሚሉት፣ «በእንግሊዝኛ አንፈተንም። በዚህ ቋንቋ ከተፈተንን ውጤት ማምጣት ይከብደናል። እኛ የምናሰለጥነው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፤ ተጫዋቾቻችንም የሚናገሩትና የሚያነቡት አማርኛ ነው» የሚል ነው። ነገር ግን የCAF A ላይሰንስ ስልጠና በCAF ከሚጠቀምባቸው የመግባቢያ ቋንቋዎች አንዱ በሆነው እንግሊዝኛ የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህንን ላይሰንስ የያዘ አሰልጣኝ በመላው አፍሪካ የማሰልጠን ዕድል ይኖረዋል። ከዚህም ባለፈ፣ ይህንን ላይሰንስ የያዘ አሰልጣኝ ወደፊት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድንም ሆነ የሌሎች ሀገራትን ብሔራዊ ቡድኖች የማሰልጠን ዕድል ሊያገኝ ይችላል። ጥያቄው ግን ይህ ነው፦ በአፍሪካ ደረጃ የማሰልጠን ዕድል የሚከፍትላቸውን ላይሰንስ ለመያዝ የሚፈልጉ አሰልጣኞች፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ቡድኖች ወይም ብሔራዊ ቡድኖች የማሰልጠን ዕድል ሲያገኙ በምን ቋንቋ ይግባባሉ? እንዴት ነው ብሔራዊ ቡድንስ ለማሰልጠን ጥያቄዎችን የሚያስቀርቡት? ይህ ጉዳይ ከፈተና ቋንቋ በላይ የአሰልጣኞችን ዓለም አቀፍ ብቃትና የሙያ ዝግጁነት የሚያነሳ ጥያቄ ነው። [ ምንጭ :- ብሩክ ተስፋዬ ] @DireSoccer
Open in Telegramየሮናልዶ ክፍል ለሌላ ተጨዋች አይሰጥም ! የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ የሚገኘውን 201 ክፍል ለሌላ ተጨዋች ላለመስጠት መወሰኑ ተገልጿል። ክፍሉ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች ወቅት ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑ ተነግሯል። ፌዴሬሽኑ ሮናልዶ በብሔራዊ ቡድኑ ያሳረፈውን አሻራ ክብር ለመስጠት በማለም ይህንን ማድረጉ ተዘግቧል። የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች እና አሰልጣኝ አባላት ለእውቅናው ድጋፍ መስጠታቸው ተዘግቧል። የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ ከሁለት አስርት አመታትን በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉ አይዘነጋም። @DireSoccer
Open in Telegramከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ አቻው ተሸነፈ ህዳር 03፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቀዳሚ ጨዋታ የሞሮኮ አቻውን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 ተሸንፏል። በድሬዳዋ ስታድየም በተደረገው ጨዋታ ዩኑስ ኤል ባህራዊ የሞሮኮን ብቸኛ ግብ በ29ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚ ሳጥን መድረስ ቢችልም ግብ ማስቆር ተስኖት ጨዋታውን አጠናቋል። የመልሱ ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ በራባት በሙላይ ኤል ሀሰን ስታድየም ከቀን 09:30 ጀምሮ ይደረጋል ። @DireSoccer
Open in Telegramሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ገቢ ይጠብቃል ! ሪያል ማድሪድ በዘንድሮው የውድድር አመት ሪከርድ የሚሰብር ከፍተኛ ገቢ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ በዚህ አመት 1.4 ቢልዮን ዩሮ ገቢ እናገኛለን ብለው እንደሚጠብቁ ተነግሯል። ገቢው ባለፈው የውድድር አመት በ 1.2 ቢልዮን ዩሮ ይዞ የነበረውን የክለቡ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል። ክለቡ ከስታዲየሙ አጠቃላይ ገቢ 420 ሚልዮን ዩሮ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ባለፉት አመታት ትልቅ ዋንጫዎችን ያላሳካው ሪያል ማድሪድ ከሜዳ ውጪ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል። @DireSoccer
Open in TelegramConnections
Similar channels
ኢትዮ ሪያል ማድሪድ Troll 😁⚽️@ethio_real_madrid_trollSport1.58K
ኢትዮ ቼልሲ Troll ቻናል@troll_chelseaSport1.7K
Ethio liverpool troll channel@troll115Sport1.99K
ኢትዮ ባርሴሎና በኢትዮጵያ ™@ethio_barcelona_fcSport1.26K
BISRAT TROLL 🥇@bisrat_trollSport2.49K
ከእግር ኳስ ማህደር ⚽️@soccer_talksSport2.72K
TROLL ማንችስተር ሲቲ ኢትዮ FANS™@man_city_ethiofans_trollSport3.08K
Chelsea Fc fan goal@chelseaa_goalSport4.42K