Account
Ethiopia Check

Ethiopia Check

Verified

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Username
@ethiopiacheck
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers24,694
Avg views per post, 7d3,440−28% vs prev 7d
ERR13.93%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 16, 20265,540
Nov 18, 20264,020
Nov 20, 20263,440

Most viewed this month

  1. 01
    Views5.54K
    Forwards—
    Reactions5
    Comments—
  2. 02
    Views4.02K
    Forwards—
    Reactions5
    Comments—
  3. 03

    #FactCheck ይህ ምስል ሰሞኑን በአዲግራት አቅራቢያ እንዲሁም ባድመ አከባቢ የወደሙ ታንኮችን አያሳይም /ኢትዮጵያ ቼክ/- በስክሪን ቅጂው ላይ የሚታየውና በአዲግራት አቅራቢያ ወይም ባድመ አካባቢ የወደሙ ታንኮችን እንደሚያሳይ የተገለጸ ምስል ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። ምስሉን ከሁለት ቀናት በፊት ያጋራው ‘Digital TDF’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ምስሉ የወደሙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታንኮችን እንደሚያሳይ ጠቁሟል። ገጹ “ከአዲግራት ትንሽ ወጥተው ወደ መቀሌ ሊሸሹ የነበሩ የብልጽግና ታጣቂዎች ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል” የሚል ጽሁፍ ከምስሉ ጋር አጋርቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ምስሉ ትላንት ለሊት ባድመ አካባቢ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የወደሙ የኤርትራ ሠራዊት ታንኮችን እንደሚያሳይ በመግለጽም እየተጋራ ይገኛል። ይህን ምስል እና የጽሁፍ መረጃ ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች መካከል ‘Kusse Gelebo’ የሚል አካውንት አንዱ ሲሆን “ባድመን መልሶ ለመቆጣጠር ከትናንት ጀምሮ ያለውን አቅምና ኃይል አሰባስቦ የተንቀሳቀሰው የሻዕቢያ ሠራዊት በጀግናው የኢትዮጵያ አየር ኃይል መብረቃዊ ምትና በስትራቴጂክና ካሚካዚ ድሮኖች ከባድ ውድመት ደርሶበታል፤ አከርካሪው ተሰብሯል” የሚል ጽሁፍ አጋርቷል። በዚህ አካውንት የተጋራውን መረጃም ከ30 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው አጋርተውታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ከሰሞኑ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አከባቢ ወይም አዲግራት አቅራቢያ የተነሳ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ምስሉ ከሶስተ አመታት በፊት እኤአ 2023 ከተቀረጸ ቪዲዮ ስክሪን ቅጂ (screenshot) የተወሰደ ሲሆን በሩስያ ጦር የወደሙ የዩክሬን ታንኮች እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን እንደሚያሳይ በወቅቱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ተዘግቦ ነበር። በወቅቱ ጉዳዩን ከዘገቡ የዜና አውታሮች መካከል ሮይተርስ አንዱ ሲሆን ዘገባውም በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://www.reuters.com/world/europe/russia-awards-medals-after-claiming-hits-leopard-tanks-us-bradleys-ukraine-2023-06-11/ ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ

    Photo
    Views3.44K
    Forwards—
    Reactions15
    Comments—

Latest posts

#2647Photo

Open in Telegram
Views3,440−21%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#2646Link preview
Views4,020−7%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#2645Link preview
Views5,540+28%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#2644Link preview
Views9,670+123%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#2643Photo
Views12,500+188%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#2642Photo

#FactCheck እነዚህ ምስሎች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ያረጉትን ንግግር እና የተመድ ዋና ፀሐፊ ምላሽ አያሳይም /ኢትዮጵያ ቼክ/ -- ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ እየተካሄደ ባለው የ81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሰናባቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር አደረጉ የተባለው ቃላት ምልልስ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ ቪዲዮ በዚህ ሳምንት በርካታ ተከታዮች ባላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እየተጋራ እና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገደ ይገኛል። ይህን ቪዲዮ መረጃ ካጋሩ መካከል Umut Cagri Sari የተባለ ኤክስ ላይ ከ10 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ ይገኛል: https://x.com/umutcagrisariii/status/2104160684313383191 በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ወደ 91 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 14 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። በተመሳሳይ 1991 የተባለ ከ 1,700 በላይ ተከታዮች ያሉት የኤክስ ገፅ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 198 የሚሆኑ የኤክስ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 32 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። https://x.com/Meconneno/status/2104085168596070750 በተጨማሪም በርካታ የኤርትራ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ የሚጠቁሙ አካውንቶች መልዕክቱን በስፋት አሰራጭተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በቪዲዮ ምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከሰሞኑ የተደረገ ምልልስ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት በመፈለግ ባደረግነው ማጣራት ቪዲዮው ፕሬዝደንት ታዬ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእከተኛ በነበሩበት ጊዜ መስከረም 26 2014 የተደረገ የቃላት ምልልስ መሆኑን አረጋግጧል: https://youtu.be/Sy3zq422Gj4?si=adIWo17TibZQlq_d በዚህ ሰሞን ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ ኒው ዮርክ ያደረጉትን ንግግር ቪዲዮ በተለያዩ ተቋማት ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል: https://youtu.be/d0ekOP-ts_Y?si=wDwm2xg84qslLGMs በዚህም መሰረት ስለዚህ እነዚህ ቪዲዮች ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል። በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck

Open in Telegram
Views10,500+142%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#2641Photo

#FactCheck አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል የተባል ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ እንደሚገኝ ተመልክተናል። በምስሉ ‘የኢትዮጵያ አየር ኃይል ETHIOPIAN AIR FORCE’ የሚል ጽሁፍ ያለበት ድሮን ኮረብታማ አካባቢ ወድቆ ይታያል። ከበስተኋላው ደግሞ ሚሊተሪ እና ሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች እየጨሰ ወደሚገኘው ድሮን ሲራመዱ ይታያሉ። ይህን ምስል ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Zelalem Hailu (One Amhara fano)’ የሚል ስም እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ይገኝበታል። ገጹ “አንድ በሉ!….” ከሚል ጽሁፍ ጋር ምስሉን ያጋራ ሲሆን ልጥፉ በርከት ያሉ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል። የጉግል ምርት የሆነውንና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ምስሎች፤ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለመለየት የሚረዳው ሲንት አይዲ ዲቴክተርን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ በከፍተኛ እርግጠኛነት (very high confidence) በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ተመልክተናል። በሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተፈብርከው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየታዩ ሲሆን በርካቶችን ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሲዳርጉም ይስተዋላል። በመሆኑም በማህመራዊ ትስስር ገጾች የሚጋሩ አጠራጣሪ የሆኑና ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠ ምስሎችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck

Open in Telegram
Views9,820+127%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#2639Photo

#FactCheck እነዚህ ምስሎች ሰሞኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂዎች የወደመ የአርሶ አደር ቡና ማሳን አያሳዩም /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በመንግስት ጸጥታ አካላት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መከሰቱ ሲዘገብ ሰንብቷል፣ በግጭቱ ምክንያትም በርካታ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸው እንዲሁ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዞኑ በፋኖ ታጣቂዎች የወደመን የአርሶ አደር ቡና ማሳ ያሳያሉ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። እነዚህ ከትላንት ረቡዕ ነሀሴ 27፣ 2018 ጀምሮ እየተዘዋወሩ የሚገኙ ምስሎች በርካታ ተከታዮች ባላቸው የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች ጭምር እየተጋሩ አና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገዱ ይገኛሉ። ይህን መረጃ ካጋሩ መካከል ‘Alex Taye’ የሚል ስምና ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አካውንት አንዱ ሲሆን “ይህ የፋኖ ጽንፈኞች ያወደሙት የወለጋ አርሶ አደር ቡና ነው” ከሚል ፍሁፍ ጋር ምስሎቹን አጋርቷል። በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ከ300 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን ከ700 በላይ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ከሰሞኑ የተነሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት በመፈለግ (Reverese image search) ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከአመት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው የነበሩ እንደሆኑ ተመልክተናል። በወቅቱ ምስሎቹን ያጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችም ምስሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ውስጥ የተነሱ እንደሆኑ በመጥቀስ ነበር ምስሎቹን ያጋሩት፡ https://www.facebook.com/share/p/18N8Jj6eDj/?mibextid=wwXIfr የቆዩና ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ

Open in Telegram
Views13,600+214%vs avg
Forwards—
Reactions60
Comments—
#2638Photo

#FactCheck የሳውዲው 'Al Riyadh' ጋዜጣ ያወጣው ነው በሚል ተቀናብሮ የተሰራጨው ፅሁፍ እና ምስል ሀሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- የሳውዲው Al Riyadh ጋዜጣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን እግር ሲስሙ ያሳያል የሚል ዜና ሰርቷል በሚል አንድ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ምስሉንና አርእስተ ዜናውን ካጋሩት መሀል ፋሲል የኔአለም 'Fasil Yenealem' የተባለ በፌስቡክ ላይ ከ269 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ ይገኛል። በተጨማሪም ኤክስ ላይ ወደ 23ሺህ የሚጠጋ ተከታዮች ያሉት @Joe የሚባል የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ መረጃውን አጋርቷል። ይሁንና ኢትዮጽያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ምስሉም፣ ዜናውም Al Riyadh ጋዜጣ ላይ እንዳልወጣ አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቼክ Google Lens የተባለ የድህረ ገፅ መረጃ ማጣሪያ በመጠቀም ባረገው ማጣረት የ Al Riyadh አርእስተ ዜና ርእስ የሚጠቀማቸው የአረብኛ ቃላቶች ልዩ ደማቅ ጥቁር የአረብኛ ፅሁፍ ጥበብ እንደሚጠቀም እና አረንጓዴ ቀለም ያለው የቴምር ዛፍ መለያው እንደሆነ አረጋግጧል: https://www.alriyadh.com/ በተጨማሪም Al Riyadh ጋዜጣ አመተ ምህረቱን የሚያስገባው ከአርእስቱ በታች በግልፅ በአውሮፓውያን አመተ ምህረት አቆጣጠር ተጠቅሞ በአግድም መልክ እንደሚያስቀምጥ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን ያሳያል የተባለው ምስል የAl Riyadh ጋዜጣ መለያ የሆነውን አረንጓዴ የቴምር ዛፍ ሳይሆን የተባበሩት አረብ ኤምሬቴስ መለያ የሆነውን የወርቅ ቀለም ያለው መለያ ምስል በጉልህ ይታያል። በተጨማሪም የAl Riyadh ጋዜጣ ሌላ መለያው የሆነውን አመተ ምህረት አገባብ፣ ፊደልና የአውሮፓውያን አመት አቆጣጠር አያሳይም። የሰው-ሰራሽ አስተውሎት በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ወጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ

Open in Telegram
Views10,700+147%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—

All posts

Connections