Account
📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾 ➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ። 📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️ B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር 100K ይደርስ ነበር ። For any comment @Meki3

Username
@ethioleboled
Category
Books
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers2,318
Avg views per post, 7d170−62.9% vs prev 7d
ERR7.34%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 5, 2026356
Nov 7, 2026318
Nov 10, 2026339
Nov 12, 2026507
Nov 18, 2026459
Nov 22, 2026312
Nov 25, 2026182
Nov 27, 202668

Most viewed this month

  1. 01

    ❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 4⃣0⃣ የመጨረሻ ክፍል አንድ ቀይ ቀለም የበዛበት ማስታወቂያ የተለጠፈበት ቢሮ ውስጥ ገባች፡፡ እጇን ከጠረጴዛው ወዲያ ተቀምጣ ስትቦዝን ለነበረችው ነርስ ዘረጋችላት፡፡ ደሟን ወስዳ ጥቂት ደቂቃዎችን እንድትታገሳት ጠየቀቻት፡፡ ናርዶስ ተስፋ መቁረጧ ፊቷ ላይ እየተነበበ ከቢሮው ወጥታ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተች፡፡ የማዋለጃ ክፍሉ በር ላይ ወላጆቿ እና ጎረቤቶቿ ሲቁነጠነጡ ተመለከተች፡፡ ሁሉም የሂባን መውለድ በተስፋ እንደ  ሚጠብቁ ገመተች፡፡ የሂባ ልጅ የመጣው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ የናርዶስም ስብራት የተፈጠረው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን በጋብቻ እና በዝሙት መሀል ነው፡፡ ከጋብቻው ልጅ ….. ከዝሙቱ ደግሞ በሽታ! ጋብቻ ምንም ያህል የተመቻቸ ባይሆን እንኳ ፍሬው እንደዝሙት አይከፋም ስትል አሰበች፡፡ ጋብቻ ያስከተለው ህይወትን ….. ዝሙቷ የሸለማት ሞትን እንደሆነ ስታስብ እንባዋ ቀደማት፡፡ ናርዶስን የመረመረቻት ነርስ ከላብራቶሪ የመጣላትን ውጤት ከተመለከተች በኋላ ወደ ተረኛው የስነ ልቦና ባለሙያ ደወለች፡፡ ካፌ ውስጥ እያውደለደለ ነበር፡፡ እየሮጠ መጥቶ ወደ ቢሮው ገባ፡፡ ነርሷ ወደ ውጪ ወጥታ ናርዶስን ጠራቻት፡፡ ናርዶስ ቢሮው ውስጥ እንደገባች ነርሷ ቢሮውን ዘግታ ወጣች፡፡ ቀጫጫው የስነ ልቦና ባለሙያ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ ለምን መመርመር እንደፈለገች ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ከጅምሩ ምክር ማብዛት ሲጀምር ሰለቻት፡፡ ‹‹ቫይረሱ ቢኖርብሽ እንኳ በህይወት መኖር አትችይም ማለት አይደለም! ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖር ይቻላል …..›› ወሬው ሰለቻት፡፡ ‹‹ይቅርታ …… የምትለውን ሁሉ አውቀዋለሁ፡፡ አሁን ውጤቴን ብቻ ንገረኝ!›› ተበሳጨች፡፡ ‹‹ካልሽ መልካም ….. ውጤቱ የሚያሳየው ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ማለት ግን ….›› ‹‹እልልልልልልልል›› የሚል የደስታ ጩኸት ጤና ጣቢያውን አናጋው፡፡ ሂባ በሰላም የመገላገሏን ብስራት የሰሙ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶቿ ያወጡት ድምፅ ነበር፡፡ ናርዶስ የስነ ልቦና ባለሙያውን ሳታስጨርሰው ትታው ወጣች፡፡ የጠበቀችውን ውጤት መስማቷ ብዙም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ ከመተላለፊያው ላይ ቆማ ማዋለጃ ክፍል በር ላይ እየተካሄደ ያለውን የደስታ ትዕይንት ተመልክታ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለሂባ ….. ፈገግ ለጓደኛዋ ደስታ …. ፈገግ ለአብሮአደጓ የአብራክ ክፋይ ….. ፈገግ! የቤተሰቡን …. የራሷንም እናት ደስታ ስታይ ለቤተሰቧ ውርደት መሆንን ፈራች፡፡ ከረፈደ በኋላ መንቃቷ እያመማት ቀስ ብላ በሌላኛው የፎቁ መውረጃ በኩል ወርዳ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም …. ቦርሳዋን ብቻ እንደያዘች ….. ማንም ወደ ማያውቃት ….. ማንንም ወደማታሰድብበት ቦታ ለመሰደድ ወሰነች፡፡ ታክሲ ውስጥ ….. ከዛም መናኸሪያ …… ከዛም አንድ አባዱላ መኪና ውስጥ እንዱ ደላላ ጎትቶ ሲያስገባት …. መኪናው ወዴት እንደሚሄድ እንኳ አታውቅም! ብቻ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ብቻ ነው የፈለገችው …… ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ….. ናርዶስ አዲስ አበባን ለቅቃ ወደማታውቀው ስፍራ ተጓዘች፡፡ ሂባ ከሆስፒታል ከወጣች ጀምሮ ጥያቄ የሆነባት ናርዶስን አለማየቷ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿ ተጨንቀው ስልክ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ….. ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሳምንት … ናርዶስ የሌለችበት ባዶ ቤት ውስጥ አለፈ፡፡ ዚያድ ልጁን ለማየት ብቅ ባለበት እግረ መንገዱን አባቷ ባዘዙት መሰረት ‹‹ፈትቼሻለሁ›› ብሏት አዲስ የሰርግ ጥሪ ካርድ ሰጥቷቸው ሄደ፡፡ ተፈላጊ ነኝ ለማለት ይመስላል፡፡ ገንዘብ አለው …… ሴት ለእርሱ የምትገዛ እቃ ናት፡፡ * ቀመር የነበራት ተስፋ ሲሟጠጥ ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን አገኘችው፡፡ ሻንጣዋን ይዛ ነበር፡፡ በጣም ደንግጧል፡፡ ‹‹ወዴት ነው?›› ‹‹ወደ ቤት …. በቃኝ ባክህ እዛው የግል እማራለሁ … ወንጀል ከለመድኩበት ቦታ ልሽሽ!›› ‹‹እንዴ ቀመር ጎበዝ ተማሪ እኮ ነሽ …›› ‹‹እሱን ተወው ለማንኛውም አሁን ላገኝህ የፈለግኩት ባለፈው ሂባ ያማከረችህ ጉዳይ ስለራሷ እንደሆነ ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ፈትታለች … ሲመስለኝ ልጅም አርግዛለች … አግባት›› ‹‹ጓደኛዋ ደውላ ስትነግረኝ ወዲያው ነው የነገረችኝ ስለራሷ እንደነበር የገባኝ …. ግን ለእማማ ስነግራት የወለደች ሴት አታገባም … ያኔ እንደዛ አድርጋህ ምናምን አለች …. እዛው ደሴ ቤተሰብ የሚያመጣውን  ለማግባት ወስኛለሁ ባክሽ!›› ‹‹እሷ የወለደችው እኮ አግብታ ነው አይደል እንዴ ….. አንተ ሳታገባ በዝሙት የረከስክ መሆንህን እንደውም ለሂባ ንፅህና የማትመጥን መሆኑን አትነግራቸውም ነበር? …… ያው ለነገሩ ፍርዳችን ሁሌም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ወንድ እንዳሻው ቢቆሽሽ አይታወቅበትም …. አይታወቅበትም ብቻ ሳይሆን ቢታወቅም እሱ ወንድ ስለሆነ ችግር የለውም አይደል? …. ሴት አግብታ ስትወልድ ግን ….. ›› ንግግሯን መጨረስ ከበዳት፡፡ ‹‹እንዴ ጥብቅና መቆም›› ሳቀ፡፡ ‹‹በቃ ቻው የምትመጥንህን ይስጥህ ብያለሁ!›› ‹‹ይቅርታ ለዚህ ውሳኔሽ ምክንያት ስለሆንኩ!›› የፌዝ ፈገግታ ፈገግ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ትታው ሄደች፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ለቅቃ እስክትወጣ በአይኑ ሸኛት፡፡ የሂባን በደል ቀመር ላይ የተወጣ መሰለው፡፡ በልቡ ‹‹ሁሉም ዕድሉን ሲያገኝ በደለኛ ነው!›› ሲል አሰበ፡፡ ዋናው በር ላይ በእርሱ አነሳሽነት የተመሰረተው የሴቶች መብት ላይ የሚሰራው ቢሮ ክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ ወጪያቸውን ለመሸፈን በማሰብ ላሰናዳው የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ምክረ ሀሳብ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ የመጥሪያ ባነር ተሰቅሎ ነበር፡፡ *            ✋ ተፈፀመ፡✋ ታሪኩ በዚሁ ተጠናቋል ሀሳብ አስተያየታችሁን አድርሱን በቅርቡ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ሰላም ቆዩኝ                  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

    Text
    Views662
    Forwards—
    Reactions13
    Comments—
  2. 02
    Views644
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  3. 03
    Views459
    Forwards—
    Reactions13
    Comments—
  4. 04

    ❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣0⃣ ዚያድ ሲወጣ ሂባ የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ እየሮጠች አባቷ ላይ ተጠምጥማ ማልቀስ ጀመረች፡፡ በአባቷ እንደዛሬ የተደሰተችበት ቀን በህይወቷ ገጥሟት የሚያውቅ አልመሰላትም፡፡ አባቷም እንባ ተናነቃቸው፡፡ ግንባሯን ሳሟት እና ‹‹ልጄ አላህ ያክብርሽ እስከዛሬ አንድም ቀን አስከፍተሸኝ አታውቂም! ከዚህ በኋላ አንቺ የምትፈልጊውን ሰው አምጪ አይተን ጥሩ ከሆነ እንድርሻለን! እኛም የምናመጣውን ካልፈለ ግሽው ይቀራል!›› አሉ፡፡ ምንም ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ ቢሆንም አባቷ ስለተረዷት ደስ አላት፡፡ ግን ከዚህ በኋላ ዳሩኝ ብላ የምታመጣው ሰው ያለ አልመስል አላት፡፡ ኢምራን ነበር! እሱን አሁን ላይ ለማግባት የምትመጥን አይመስላትም! ‹‹ጠምቶት ሲማፀነኝ ከልክዬው ፣ ያልደፈረሰውን ለሌላ ሰጥቼ ፣ ያጠጣሁት ሲገፋኝ ጠርቼ ፣ ቅራሪዬን ጠጣ አልለውም!›› ትላለች፡፡ የኢምራን መሆን ብትፈልግም አሁን ላይ ያንተ ልሁን ማለት ለሱ አለማሰብ ይመስላታል፡፡ *** ‹‹አራቱንም ፈተና የነገርከኝ ቦታዎችን ነበር focus አድርጌ ያጠናሁት! እንዳለ የመጣውም እሱ part ነው፡፡›› ቀመር ፍራሹ ላይ ተቀምጣ ከስራ መጥቶ ጃኬቱን የሚያወልቀውን ኢምራንን እያየች ቀጠለች ‹‹እና አሪፍ ውጤት እንደሚኖረኝ አትጠራጠር!›› ‹‹እሱን ሲመጣ እናየው የለ የምን ፕሮፖጋንዳ ማብዛት ነው?!›› ‹‹እኔማ ላመስግንህ ብዬ ነው!›› ‹‹እና አሁን ስንት ፈተና ቀራችሁ?›› ‹‹ሁለት መሰለኝ! በዚህ ሳምንት እንጨርሳለን!›› ‹‹ከዛስ?›› ‹‹ከዛማ ጉዞ ወደ ቁሌታሟ ሀላባ ነዋ!›› ተሳሳቁ! ‹‹የማጥኛ ክፍልሽ አትናፍቅሽም?›› ለማለት የፈለገውን ተረዳችና ፈገግ አለች፡፡ ‹‹በጣም ትናፍቀኛለህ ኢምሩዬ! አንተ ወደ ደሴ አትሄድም እንዴ?›› ‹‹ለሳምንት ደርሼ መምጣቴ አይቀርም!›› ‹‹በቃ ታዲያ ስትመለስ ደውልልኝና እመጣለኋ!›› ‹‹የምርሽን ነው?›› ‹‹አዎ እኛ ቶሎ ስለምንሄድ አንተ ውጤት አስገብተህ ከመሄድህ በፊት ራሱ እኔ እዛ ሄጄ ሳምንት አሳልፋለሁ፡፡ ከዛ አንተ ሄደህ አንድ ሳምንት! በድምሩ አስራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ቤት ደግሞ ከዚህ በላይ የምናርፍ ስለማይመስላቸው አይባንኑም! so ከች እላለሁ፡፡ ታዲያ ፈታ የምታደርገኝ ከሆነ ነው! ታስደብረኝና አለቀልህ!›› ‹‹ውይ እኔ ፈታ ማድረግ አልችልበትም! ያው ባይሆን አንቺ እንሂድ የምትይው ቦታ ለመሄድ ከተስማማሁ አይበቃም?›› ‹‹ይበቃል! የምልህን ሁሉ እሺ ካልክማ በቃ የሚገርም ጊዜ ነው የምናሳልፈው!›› ተሳሳቁ፡፡ ለማለት የፈለገችውን እሱም ተረድቶታል፡፡ በፊት በፊት ቶሎ አይገባውም ነበር፡፡ ሰዓቱ ለመምሸት እየቀረበ ስለነበር ጓደኞቿ መደወል አበዙ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ለመሄድ ተነሳች፡፡ ሁሌም ልትሄድ ስትል ደስ አይለውም፡፡ ከብቸኝነቱ የሚያተርፈው ትዝታ ነው፡፡ ትዝታው ደግሞ መሪር ነው፡፡ በቀመር ውስጥ ትዝታውን ለመርሳት ይታገላል፡፡ የሀይማኖቱን ክልከላ ይዘነጋው ጀምሯል፡፡ በራሱ በጣም ተማመነ መሰል ቤት ውስጥ ብቻቸውን መቀመጣቸው የሚያመጣው መዘዝ መኖሩን ረስቷል፡፡ ግን ባትሄድ ደስ ይለዋል፡፡ ለሊቱንም አብራው ሆና ከትዝታው ብታስጥለው ይመኛል፡፡ ምኞት ብቻ! ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ! እግረ መንገዱን የቆይታቸውን ጊዜ ሊያራዝም! ግቢ መግባቷ ላይቀር! . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣1⃣ 

    Text
    Views428
    Forwards—
    Reactions9
    Comments—

Latest posts

#7359Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 6   የልጇ መክሳት ክፉኛ ሲያስለቅሳቸው ከቆየ በኋላ ማልቀሳቸውን ማቆማቸውን ሲያውቅ ። " እራት ገዝቼ መጣሁ " አላቸውና ሰለሞን ከቤት ወጣ ። ነገር ግን እራት መግዛት ሳይሆን ወደ ጎረቤት ቤት ነበር የሄደ ። የጎረቤታቸውን የወ/ሮ ዝናሽን ግቢ አልፎ ቤት ከገባ በኋላ ወ/ሮ ዝናሽን ወጥ እየሰራች አገኛት ። ከማብሰየዋ ተከታትሏት ገባና እማማ ነው የሚላት " እማማ እባክሽ እናቴን አሞብኝ ነው የማሳክምበት ብር ካለሽ አበድሪኝ " አላት እየፈራ አንገቱን እንዳቀረቀረ ብድር ሲጠይቅ የመጀመሪያው ነው ። " አመማት እንዴ ምንቴን ? " አለችው እማማ ም ቢሆን ደንግጣ ነበር " ምንትዋብን " አቆላምጣ ስጠራት " ምንቴ " ነው የምትላት " አዎ ውጋት ነገር አሟታል " አላት ። እማማ ወሬ ማብዛት አልፈለገችም ወደ ሳሎን ከገባች በኋላ ከጥቁር ቦርሳ ውስጥ ብር እያወጣች ተመለሰች 2000 ብር ቆጥራ ሰጠችውና ። " ካነሰህ ጠይቀኝ " ። ሰለሞን በጣም አመስግኖ ከማብሰያዋ ወጣና አንዴ ፈጣሪውን አንዴ እማማን እያመሰገነ ለእናቱ እራት ሊገዛ ወደ አንድ ካፌ አቀና ። ወ/ሮ ምንትዋብ እና እማማ የልጅነት ጓደኛሞች ብቻ ሳይሆኑ እህትማማቾችም ማለት ናቸው ። በተቸገሩ ጊዜ አንዷ ከአንዷ ተበዳድረዋል ። ዛሬ ድህነት ቤት ሰራባቸው እንጂ ወ/ሮ ምንትዋብም ለእማማ አንዴ ከገንዘቡ ፣ አንዴ ከሚበላው አበድረዋት ያውቃሉ ። ዛሬ ግን የሰው እጅ እያዩ መኖር እጣ ፈንታቸው ሆኗል ። ሰለሞን እራት ገዝቶ ከመጣ በኋላ አብረው ከእናቱ ጋር መብላት ጀመሩ ። ልጃቸው አብሯቸው በመብላቱ ደስ ብሏቸዋል ። አንዴ እሱ አንዴ እሷ እየተጎራረሱ ይበላሉ ። ወ/ሮ ምንትዋብ ልጃቸውን ሊያጎርሱ የጠቀለሉትን ጉርሻ እንጀራ በተመተማ አፉ እየመሰላት አንዴ አፍንጫው ላይ አንዴ ደሞ አገጩ ላይ ይጨምሩታል ፡ ያኔ ሰለሞን በእናቱ ድርጊት ትን እስኪለው ይስቃል ። የልጃቸው መሳቅ ፈገግ አስባላቸው ደስተኛ ሆነዋል የታመሙ አይመስሉም ። አይናቸውን ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ የሚስቀውን ልጃቸውን ሲስቅ ለማየት ቢያንከባልሉትም ሊያዩት አልቻሉም ከመስማት ውጭ ። . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 7

Open in Telegram
Views80−75%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#7358Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 5 ይቅር እንዳላት ነግሯት ሊሸኛት ወደ ቤቷ አመሩ ሂሩት ፊቷ በደስታ ፈክቷል ። አሁን ይቅር ስላላት ውስጧን ሰላም ተሰምቷታል ነፃ ሁናለች ። ሰለሞንም ቢሆን በደስታ ሰክሯል በተለይ ስላቀፈችው ፡ ከእናቱ ውጭ ማንም አቅፎት አያውቅም ወደ ቤቷ በመሸኘት ላይ እያለ በመንገዳቸው ሰው ከሌለ እጁን ትክሻዋ ላይ ጣል ሲያደርገው የተመቻት ይመስል ፈገግ ከማለት ውጭ ምንም አላለችውም ። ከፊታቸው ሰው ከመጣ ወይም ደግሞ ከኋላቸው ሰው ከተከተላቸው እጁን ከትክሻዋ ላይ ያወርደዋል ። አስቆጣታለሁ ብሎ ስላሰበ ነበር ። ቤት ልትደርስ ትንሽ ሲቀራት ቤታቸውን ከርቀት አሳየችውና ቻው ተባብለው ነገ ዛሬ ከጠበቃት ቦታ ላይ እንደሚጠብቃት ነግሯት ተለያዩ ። ልቡ በሀይለኛው ይመታ ነበር ። ....ድው......ድው ይላል ። ቆሞ ቤት እስክትገባ በአይኑ ሸኛት ቤቷ ስትገባ ተመለከተና ፊቱን አዙሮ ወደ ቤቱ በፈገግታ መሄድ ጀመረ ። በደስታ እየተፍለቀለቀ ቤቱ ሲደርስ እናቱ ከቤት ውስጥ ሆነው " አሟቸው ነው መሠል እህ .....እህ እያሉ ሲሰማ ዘሎ ወደ ቤት ገባ ። እንደገባ እናቱ እያቃሰቱ ነበር ። የሰው ኮቴ ሲሰሙ ማቃሰታቸውን አቆሙና " ማነው ? " አሉ ። አይናቸው እንደሚያይ ሁሉ ወደ በሩ ልከው ። " አማየ " አመመሽ እንዴ ? አላት ሰለሞን ወደ አልጋው እየተጠጋ " ሰለሞኔ አንተ ነህ እንዴ ? " " አዎ ዛሬስ ልቤን ውጋት ደሞ ያመኝ ጀመር " አሉት ። ቅስማቸው ተሰብሯል የእናቱ ቅስም ተሰብሯል ። ሰለሞን የሚያደርገው ጠፋው በጣም ፈርቷል " አይዞሽ እማየ ነገ እንደምንም አሳክምሻለሁ " አላት ከጎኗ እየተቀመጠ ። ምንም ገንዘብ እንደሌለው ያውቃል ግን የሚላቸው ጠፍቶት ነበር አሳክምሻለሁ ያላት ። አቀፉትና ወደ ደረታቸው አስጠግተው የጎደለው አካል እንዳለ ሁሉ ከላይ ከፀጉሩ ጀምረው መዳበስ ጀመሩ ። " ምነው ሰለሞኔ ፀጉርህ እንደዚህ ዱር እስኪመስል ድረስ የማትቆረጥ ? " አሉት ፀጉሩን ሲዳብሱት ከቆዩ በኋላ ። " እሽ እማየ ነገ እቆርጣለሁ " አላቸው ። ብዙ ጊዜ የምትጠይቀውን ሁሉ እሽ አደርገዋለሁ ይላቸዋል ። ብዙ ጊዜ አደርገዋለሁ ያለውን ግን ያደርጋል ፡ እናቱ ፈገግ እንዳሉ መዳበሳቸውን ቀጠሉና ግንባሩን አልፈው ወደ ታች ሲወርዱ ፊቱ አካባቢ " የሰለሞን " እንባ እጃቸውን ፈጃቸው ፡ ፈገግታቸው ወዲያው ድርግም አለና ግንባራቸውን ቋጠሩ ። " ሰለሞኔ ለምን ታለቅሳለህ " አሉት " ም...ም....ምንም እማየ " አላት እንባውን እና ንፍጡን እየጠረገ ። እናቱ የልጃቸውን አንገት እና ደረት ከዳበሱት በኋላ ግን እንባቸው ይገነፍል ጀመር ። የደረቱ አጥንት መግጠጡን በእጃቸው ዳብሰው ልጃቸው እንደ ከሳ አውቀውታል ። " ምነው ልጄ ከስተሀል ምግብ አትበላም ? " አሉት እንባቸውን እንዳያይ ፊታቸውን እየዞሩ ። " አልከሳሁም እኮ እማየ ደህና ነኝ " አላቸው ። እንዳታዝን እና እንዳታለቅስ ፈልጎ እንጂ ለእሱም መክሳቱ አልጠፋውም ። ብዙውን ጊዜ ምሳም ሆነ እራት አይበላም ። በቀን የሰራው ብር ትንሽ ከሆነ ለእናቱ የሚሆን ምግብ ብቻ ይገዛና ይመለሳል ። " ና አብረን እንብላ " ያለችው እንደሆነ ጠጋ ብሎ አንዴ ይጎርስና " እዛው ምግብ ቤቱ በልቼ ነው የመጣሁ ይልቅ አንቺ መብይላት አለብሽ " ይላታል ። ነገር ግን ውሸቱን ነበር " እናቱ እንዳታስብና የገዛው ምግብ ለሁለት ስለማይበቃ ነበር " ሁሌም በልቼ ነው የመጣሁ " የሚላት.............          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 6

Open in Telegram
Views61−81%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#7357Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 4 አባቷ አቶ መኮንን ነጋዴ ሲሆኑ በሀብት ደረጃ በከተማዋ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ሶስት ቢላ ቤት እና ሁለት ሰፋፊ ሱቆች አሏቸው አንዱ የመኪና መለዋወጫ ሱቅ ሲሆን አንዱ ደግሞ የፈርኒቸር ሱቅ ነው ። ነገር ግን በፀባያቸው ብዙም ከሰው ጋር የማይግባባ ኮስታራ እንዲሁም በአካባቢው ክፉ ተብለው የሚታማ ሰው ነው ። ለሂሩት ልዩ ፍቅር ነው ያለው ከሌሎች ልጆቹ እሷን ያስበልጣል ። ይንከባከባታል ስለ ህይወት ይመክራታል ። ሁሌም አንድ ምክር አላቸው " ማንም ወንድ ውበትሽን አይቶ እንዲያፈቅርሽ አትፍቀጂለት ምክንያቱም አንቺን ሳይሆን ውበትሽን ነው ያፈቀረ ውበት ደግሞ ጤዛ ነው ይረግፋል " ። ቆንጆ ስለመሆኗ እንኳን አባቷ ማንም አይጠራጠርም ሂሩትም ቢሆን የአባቷ ነገር ብርቋ ነው በጣም ትወደዋለች ። በትምህርቷ ጎበዝ ስትሆን ትምህርት ቤቱ ከቤታቸው ብዙም ስለማይርቅ በእግሯ ነው የምትመላለስ ። ..... አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስትመለስ ከጓደኞቿ ጋር ተለያይተው ወደ ቤቷ የሚወስደውን መንገድ ስትይዝ ጠብቆ እየሮጠ ተከተላት ፡ ራቅ ብሎ ቆሞ ስለነበር ቤቷ ከመግባቷ በፊት ሊያናግራት ስለፈለገ በፍጥነት ነበር እየሮጠ የደረሰባት ። አጠገቧ መድረሱን ሲያውቅ ቁና ቁና እየተነፈሰ " ሂሩት....ብሎ ተጣራ ድንግጥ ብላ ስትዞር ሰለሞን ነበር ዛሬም ፈርታዋለች ግን እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ቆማ ጠበቀችው ። ፈገግ ብሎ አንዴ እሷን አንዴ ደግሞ መሬት መሬቱን እያየ ተጠጋት ፡ እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት ስትፈራ ስትችር እጁን ጨበጠችውና ቶሎ ብላ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ እጇን ከእጁ መነጨቀችው ። አንገቱን ቀብሮ እየተንተባተበ መናገር ጀመረ " ባ...ባ...ለፈው ስለ..ተፈጠረው ነገር ይ....ቅርታ ልጠይቅሽ ነው የጠራሁሽ " አላትና ቀና ብሎ ሲያያት ትኩረት ሰጥታ እያዳመጠችው እንደሆነ ሲያውቅ መናገሩን ቀጠለ ። " ማለት ማስደንገጥም ሆነ ማስፈራራት የ...ለብኝም ነበር በዛ ላይ ልክ ነበራቹ እ...ብድ እመስላለሁ " አላት ተናግሮ ሲጨርስ ወደ መሬት የደፋውን ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ይቅርታዋን ለመቀበል ሲያያት ግን እሷም እራሷን አቀርቅራለች ። ሰለሞን ግራ ገባውና እጁን ትክሻዋ ላይ አድርጎ ቀና ሲያደርጋት ፡ ሎሚ በመሰለው ጉንጯ ላይ እንባዋ እየተንከባለለ ጡቷ ላይ ይንጠባጠብ ጀመር ። ሰለሞን ይበልጥ ግራ ተጋብቶ " ዛሬም ፈርታኝ ይሆን የምታለቅስ " ሲል አሰበ ። " ለምንድን ነው የምታለቅሺ " አላት እንባዋን በመዳፏ ከጠራረገች በኋላ " ሁሌም ይፀፀተኝ ነበር አንተ እብድ አይደለህም ስራ ባቆሸሸው ልብስህ ተሳለቅንብህ እብድ አልንህ ፣ ሰደብንህ ሰሞኑን ደግሞ እኛ ቤት የመጣህ ቀን የቤተሰብህን ችግር ስትነግረን ይበልጥ በራሴ ላይ አዘንኩ እራሴንም በጣም ጠልቼው ነበር ። አንተ ምንም አላጠፋክም ጥፋተኛ እኔ ነኝ ስለዚህ እባክህ ይቅርታ በለኝ " አለችው ። በመለመን አይነት ቅላፄ አይን አይኑን እያየች ። እንባዋ ግን ብትጠርገውም አሁንም እንደ አባይ ወንዝ መፍሰሱን አላቆመም ነበር ። ሰለሞን እንደ እንባ የሚፈራው ነገር የለም ። በትኩረት ተመለከታትና እንባዋን ቀስ ብሎ በእጁ መዳፍ ከጠራረገላት እቅፍ አደረጋት ። እሷም እጇን ቀስ እያደረገች አንስታ ጀርባው ላይ ካደረገች በኋላ አቀፈችው ። ሁለቱም መተቃቀፍ የመጀመሪያቸው ነው ይቅር እንዳላት ነግሯት ሊሸኛት ወደ ቤቷ አመሩ ሂሩት ፊቷ በደስታ ፈክቷል......          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 5

Open in Telegram
Views63−80%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#7356Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 3 ወ/ሮ ሙሉነሽ እንባ ያቆረው አይናቸውን እዬጠራረጉ * አይዞህ የኔ ልጅ * ሁሉም ለበጎ ነው ብለው ለማፅናናት ሞከሩ ። ሂሩትም ቢሆን አታልቅስ እንጂ እንዳዘነች አይኗን አይቶ መገመት ይቻላል .....ወ/ሮ ሙሉነሽ ሰለሞንን እስከ በሩ እያወሩ ሸኝተውት ሲመለሱ " እኔን አፈር በበላሁ አይ ወንድ ልጅ እኔን ይቸግረኝ ወንድ ልጅ አይጣ " እያሉ ከልባቸው እያዘኑ ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ። ሂሩት ግን ተከትላቸው አልገባችም ። ቁጭ እንዳለች በሆነ ሀሳብ ውስጥ ተጠምዳለች ። ሰለሞን ተሸክሞ ባገኛት 50 ብር ለእናቱ ቀለል ያለ ምሳ ገዝቶላት ወደ ቤቱ ገባ ። ሂሩትን ሲያያት የደነገጠው ድንጋጤ ግን አሁንም አለቀቀውም ሲያስበው በድጋሜ ይደነግጣል ። አንድ ቀን ምሽት ...... ስራ ያደከመውን አካሉን ለማሳረፍ በጥድፊያ ወደ ቤቱ በመሄድ ላይ እያለ ሂሩትና የሴት ጓደኛዋ ትዕግሥት ፊት ለፊት ተገናኙት ። የልብሱ ቀዳዳ መሆን እና መቆሸሽ እንዲሁም የፀጉሩ መንጨብረር ያስፈራቸው ሂሩትና ጓደኛዋ ትዕግሥት ያበደ ሰው መሰላቸው ። በፍርሀት እየተንቀጠቀጡ ካለፉት በኋላ "እብድ ነው ?" ብላ ጠየቀቻት ሂሩት ጓደኛዋን "አዎ እብድ ነው መሠለኝ " አለች ጓደኛዋ ። በዚህ ሰዓት ሰለሞን ሰማቸውና ዘወር ብሎ ሊያናግራቸው ሲል እየጮሁ ይሮጡ ጀመር ። በንዴት ቱግ አለና ሰለሞንም ያሯሩጣቸው ጀመር አጣደፈና ጓደኛዋ ሮጣ ስታመልጥ ሂሩትን ያዛት ። ሁለቱም ከላይ ከላይ ይተነፍሳሉ በጣም አሯሩጣው ነበር ። ልታመልጥ ብትሞክርም አአልተሳካላትም ሁለት እጇን አጣምሮ ያዘና ወደ እሱ አዙሮ ጮኸባት ። " ልብስ የቆሸሸ ሁሉ እብድ ነው ? ' " ድህነት እብድ ያስብላል ? " ንገሪኝ እንጂ ? እያለ ቢጮህባትም መላ አካሏ እየተንቀጠቀጠ አይን አይኑን እያየች ከማልቀስ ውጭ ምንም ልትመልስለት አልቻለችም ። እንባዋን ካየ በኋላ ግን አሳዘነችውና ቁጡ ስሜቱ በርዶ በቆመችበት ጥሏት ሄደ ። ሂሩት ይደበድበኛል ወይም ይደፍረኛል ብላ ነበር የጠበቀች በዛ ላይ እብድ እንዳልነበረ አወቀች ። በቆመችበት ከአይኗ እስኪጠፋ ተመለከተችው እሱ ግን ወደ ቤቱ ከመጣደፍ ውጭ አንዴም ዞሮ አላያትም ነበር ። ከዛን ቀን ጀምሮ ሂሩት የሰለሞን አስፈራ ፀጉር ፣ እጇን አጣብቆ የያዛት ፣ ስሜታዊነቱ ፣ ቁጡነቱ ፣ ያሯሯጣት ከአይነ ህሊናዋ ጠፍቶ አያውቅም ። ዛሬ ግን ሰለሞን ቤቷ ድረስ ቢመጣም ከመበቀል ይልቅ ለራበው ሆዱ ምግብ ሰጠችው ። የሰለሞን ህይወት አሳዝኗታል ። ሰሞኑን ደግሞ ሀሳቧን ሁሉ ሰለሞን ተቆጣጠረው ብቻ ስለእሱ ሁሌም ታስባለች ። ሂሩት የ10 ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ገና የ18 አመት ልጅ ናት ። መካከለኛ ቁመት ያላት ሲሆን የአይኖቿ ጎላጎላ ማለት ፣ የከንፈሯ ልስላሴ ፣ የሰውነቷ ጥራት ፣ የአንገቷ ርዝማኔ ብቻ በውበቷ ልዩ የምትባል ሴት ናት ። ገና በዚሁ እድሜዋ የገጿን አቦል የውበቷን አፍላ ለመቅመስ በከተማው ውስጥ የፍቅር ጥያቄ ያልጠየቃት ወንድ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ከተማሪ እስከ መምህር ፣ ከቀን ሰራተኛ እስከ መንግስት ሰራተኛ ፣ ከሌባ እስከ ፖሊስ የማይጠይቃት የለም ነበር ። የሷ መልስ ግን " አሁን ለማፍቀር ዝግጁ አይደለሁም " ትላቸዋለች ብዙ ቀንም ተማራ ታውቃለች ። የቤቱ የመጨረሻ ልጅ ስትሆን ውጭ ሀገር በመማር ላይ የሚገኙ ሁለት ትላልቅ ወንድሞች አሏት ። አባቷ አቶ መኮንን ነጋዴ ሲሆኑ በሀብት ደረጃ በከተማዋ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ሶስት ቢላ ቤት እና ሁለት ሰፋፊ ሱቆች አሏቸው.....          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 4

Open in Telegram
Views192−40%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7355Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 2 ሰለሞን ቁጭ እንዳለ ግቢውን ይቃኝ ጀመር መዋኛ ገንዳው ፣ የተለያየ ቀለም ያላቸው አበቦች ፣ ልዩ ውበት ተሰጥተውታል ። እንደዚህ አይነት ግቢ አይቶ አያውቅም ። ተመስጦ ግቢውን በማየት ላይ እያለ ወ/ሮ ሙሉነሽ ቦርሳቸውን ይዘው ወጡ ። የሰለሞን አይን ከቦርሳው ላይ ነበር * ስንት ትከፍለኝ ይሆን አለ በውስጡ * ዝርዝር ያጡ ይመስል ብዙ ከፈለጉ በኋላ ድፍን ሀምሳ ብር አውጥተው ሲሰጡት ሰለሞን ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ዋጠ ። ያ ላበት ሲፈስበት የቆየው እርሾ የመሠለዉ ፊቱ በአንዴ ፈካ ከመቀመጫው ተነስቶ አመስግኖ ሊሄድ ሲል ። * ቆይ የኔ ልጅ የሚበላ ነገር ቅመስ አሉትና ፡ እዛው በረንዳው ላይ ካለው ወንበር እየተቀመጡ * ሂሩት የሚበላ ነገር ለልጁ አምጭለት * አሏት ሳሎን ውስጥ ቁጭ ብላ የምታነበውን ልጇን ሰለሞን ለመግደርደር ቢሞክርም በርሀብ የተሰቃየው ሆዱ እሽ አልለው ስላለ ቁጭ አለ ። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ የሚበላ ነገር ይዛ የመጣችውን ሂሩትን ሲያያት ክው ብሎ ደነገጠ ። ያውቃት ነበር ፡ ሲያያት የሀፍረት ስሜት ተሰማው ሂሩት የያዘችውን ምግብ ከሰጠችው በኋላ ወደ ሳሎን ከመግባት ይልቅ እዛው በረንዳው ላይ ካለው ወንበር ላይ ከእናቷ አጠገብ ቁጭ አለችና በትኩረት ትመለከተው ጀመር ። የሰጠችውን እንጀራ በምስር ወጥ አንገቱን ደፍቶ ምንም ሳይናገር በፍጥነት በልቶ ሊሄድ ሲል * የኔ ልጅ * አሉት አቤት ማዘር ... : : ስምህ ማነው ? ሰለሞን.... አላት ፊቱን ሳያዞር እዚሁ ነው የምትኖረው ?....ቀጠለች አዎ ቀበሌ 3 ነው የምኖረው አላቸው ሂሩት በዚህ ሰዓት ዝም ብላ ነበር የምታዳምጥ ስራስ የለህም ? ምንም ልትለቀው አልፈለገችም * አዎ የለኝም የእለት ጉርሳችንን በቀን በምሰራው ነው በልተን የምናድር ኑሯችን ከእጅ ወደ አፍ ነው * አላት ወ/ሮ ሙሉነሽ አሳዘናቸው መሠል ፊታቸው ከመቅፅበት ተቀያየረ ከማን ጋር ነው የምትኖረው ? ቤተሰብ አለህ ? አለችው ። እሷ ስትጠይቅ እሱ ሲመልስ ከቤተሰቡ ደረሱ ስለ ቤተሰቡ አንድ በአንድ ይነግራት ጀመር ። * አባቱ ሻምበል ምትኩ ይባል የነበረ ሲሆን ወታደር ነው እናቱ ወ/ሮ ምንትዋብ ደግሞ የቤት እመቤት ናቸው ። አንድ ልጅ ብቻ ወልደው ያቆሙ ሲሆን ከሰለሞን ውጭ ሌላ ልጅ አልታደሉም ። ድህነት የሚባል ነገር ከአጠገባቸው ድርሽ የማይል ለራሳቸው የማያንሱ ቤተሰቦች ነበሩ ። ሰለሞን ገና የ16 አመት ልጅ የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ አባቱ ሻ/ል ምትኩ ግዳጅ ላይ እንዳለ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ያለፈች ሲሆን ። የዚያን ቀን እናቱ ወ/ሮ ምንትዋብ በድንጋጤ ምክንያት ራሳቸውን ስተው ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ ሲነቁ ሁለቱም አይናቸው ማየት ተሳነው ። ወዲያው ህክምና ቢደረግላቸውም ሊሻላቸው አልቻለም ነበር ። ሰለሞን ታዲያ በ16 አመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ የቀን ስራ ተሰማራ ። ያ ከአጠገባቸው ርቆ የነበረው ድህነት ዛሬ ቤታቸውን ቤቱ አደረገ ቤታቸው የቀበሌ ቤት ቢሆንም ቤተሰቡ ሙሉ እያለ የሚያምረው ቤት ዛሬ ቴሌቭዥኑ ተሽጦ ፣ ሶፋዎች ለችግር ማስወገጃ ተሽጠው ቤቱ ጥርስ የሌለው አፍ መስሏል ። ሰለሞን ቀን ሰርቶ በሚያገኘው ብር ለእናቱ ምሳ ፣ እራት እየያዘ መግባት ከጀመረ 5 አመታትን አለፈ ። እናቱ ከአይናቸው በተጨማሪ ሌላ በሽታም ያማቸዋል ። የሰለሞን እድሜ ዛሬ 21 ነው ወ/ሮ ሙሉነሽ እና ልጇ ሂሩት በጥሞና ካዳመጡት በኋላ......          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3

Open in Telegram
Views171−46%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#7354Photo
Views3180%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#7353Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 1 ፀሀይዋ በከተማዋ ላይ ቂም የቋጠረች ይመስል ገና 3 ሰዓት ሳይሆን ሙቀቷን ትረጫለች ። ሰለሞን ግን የፀሀይዋን ሙቀት ከምንም ሳይቆጥር በሰው መሀል እየተሹለከለከ ወደፊት ያመራል ሲያዩት ቀጠሮ ያለበት ነበር የሚመስል ቢጠሩትም አይሰማም ። በጣም ከመቸኮሉ የተነሳ ወደ ኋላው እንኳን ዞሮ አያይም ። ቀጥ ብሎ ነበር የሚሄድ መናሀሪያውን ካለፈ በኋላ ወደ አደባባዩ የሚወስደውን መንገድ ተያያዘው ። የለበሰው አሮጌ ጅንስ ሱሪ ከማለቁ የተነሳ ተቀዳዷል ከላይ የለበሳት ቢጫ ቲሸርት በጣም ከመቆሸሿ የተነሳ ውሃ ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም ። የፀጉሩ ነገርማ አይነገርም በጣም ከመንጨፍረሩ የተነሳ የጃርት እሾህ መስሎ ቆሟል ። አደባባዩ ከደረሰ በኋላ ወደ ቀኝ ታጠፈና ወደ ገበያው ገባ ። የህዝቡ ብዛትና ጫጫታ ግራ ያጋባው ሰለሞን መሀል ላይ ቆሞ ከወዲያ ወዲህ ቢያማትር ተሸካሚ ( ወዛደር ) የሚፈልግ ሰው በአይኑ ቢያስስ አጣ ። “ በቃ ዛሬም ሳልሰራ ልውል ነው ? " አለ በውስጡ ። ትንሽ ከጠበቀ በኋላ ወደ ጤፍ መሸጫው መካዘን አመራ እዛም ወዛደር የሚፈልግ ሰው አጣ ። አንድ ከተዘጋ ሱቅ ገደፍ ብሎ እንደቆመ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ ። ከእጅ ወደ አፍ የሆነው ኑሮው ይበልጥ ያስጨንቀው ጀመር ። ሰው ሁሉ በሰው ከማሸከም ይልቅ ለፍጥነቱ እያለ በእሽኩኒታ ማስጫኑ የወዛደሮች ኑሮ ወደፊት ምን ሊመስል እንደሚችል እያሰበ እያለ ነበር ድንገት “ የኔ ልጅ " የሚል ድምፅ ብዙ ርቀት ከሄደበት ሀሳቡ ያነቃው ። ገና ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው አይኑን እያጨላሞሰ ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ ሲዞር ከአንድ እናት ጋር አይን ለአይን ተጋጩ ። ትሸከማለህ ? አለችው በማዳበሪያ የሞላውን ጤፍ በአገጯ እየጠቆመች ። አዎ...ብሎ ጣድፎ ስለ ክፍያ ሳይነጋገሩ ተወተርትሮ አንስቶ ተሸከመው ። በክፍያ አለመስማማት ይመጣል ብሎ ስላሰበ ነበር ስለ ክፍያ ሳይጠይቅ ለመሸከም የተገደደው ። ሰሞኑን ሳይሰራ በመሰንበቱ ነበር የሰጠችውን ክፍያ ለመቀበል የወሰነ ። የህዝቡን ጋጋቴ ቀስ እያለ ካለፈ በኋላ ። ከፊት ሆና ሴትዮዋ በምትመራው ወደ ዋናው ንግድ ባንክ ከሄዱ በኋላ እንደገና ወደ ስታዲየሙ በሚወስደው መንገድ ጉዞውን ጀመረ ። ሴትዮዋን ከዚህ በፊት አይቷት የማያውቅ ቢሆንም ከተማው ውስጥ በደግነት አንቱታን ያተረፉ የቤት እመቤት ናቸው ። ወ/ሮ ሙሉነሽ ይባላሉ ። ከጨፍራራ ፀጉሩ የሚፈሰው ላበት ፊቱን አልብሶ ወደ አንገቱ መፍሰስ ጀምሯል ። ከፀጉሩ ላይ ላበት እያጠበ የሚያመጣው እድፍ አይኑን ስለሚቆጠቁጠው ቆም ይልና ፡ በአንድ እጁ ዣዱ ላይ የተሸከመውን ጤፍ እንዳይወድቅበት ይይዝና በሌላኛው እጁ ደግሞ ሁለቱንም አይኑን ጠራርጎ ፡ እንደ ወጣት በፍጥነት የሚጓዙትን ወ/ሮ ሙሉነሽን በፍጥነት ጉልበቱ ከጉልበቱ እየተጋጨ እና እየተወላገደ አሊያም በማቸልቸል ይደርስባቸዋል ። ቀጥ ያለውን የስታዲየሙን መንገድ ጨርሰው የመጨረሻ መታጠፊያ ሲቀር ወ/ሮ ሙሉነሽ ቆማ ጠበቁትና " አይዞህ የኔ ልጅ ደርሰናል " አሉትና ወደ መታጠፊያው ገቡ ። ልምድ ሆኖባቸው ወጣቱን በሙሉ " የኔ ልጅ " ማለት ይቀናቸዋል ። ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ሰፊ በር ያለውን ግቢ ሲያንኳኩ ጥበቃቸው እየተጣደፈ በሩን ከፈተላቸው ። ሰለሞን ጤፉን በረንዳው ላይ ካወረደ በኋላ " ደከመህ የኔ ልጅ ? አልደከመኝም.... አላቸው ቁና ቁና እየተነፈሰ ። በዚህ ሰዓት ወ/ሮ ሙሉነሽ ወደ ውስጥ ገቡ ። ሰለሞን ቁጭ እንዳለ አጥር ግቢውን ይቃኝ ጀመር ። . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 2

Open in Telegram
Views306−4%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#7350Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 4⃣0⃣ የመጨረሻ ክፍል አንድ ቀይ ቀለም የበዛበት ማስታወቂያ የተለጠፈበት ቢሮ ውስጥ ገባች፡፡ እጇን ከጠረጴዛው ወዲያ ተቀምጣ ስትቦዝን ለነበረችው ነርስ ዘረጋችላት፡፡ ደሟን ወስዳ ጥቂት ደቂቃዎችን እንድትታገሳት ጠየቀቻት፡፡ ናርዶስ ተስፋ መቁረጧ ፊቷ ላይ እየተነበበ ከቢሮው ወጥታ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተች፡፡ የማዋለጃ ክፍሉ በር ላይ ወላጆቿ እና ጎረቤቶቿ ሲቁነጠነጡ ተመለከተች፡፡ ሁሉም የሂባን መውለድ በተስፋ እንደ  ሚጠብቁ ገመተች፡፡ የሂባ ልጅ የመጣው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ የናርዶስም ስብራት የተፈጠረው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን በጋብቻ እና በዝሙት መሀል ነው፡፡ ከጋብቻው ልጅ ….. ከዝሙቱ ደግሞ በሽታ! ጋብቻ ምንም ያህል የተመቻቸ ባይሆን እንኳ ፍሬው እንደዝሙት አይከፋም ስትል አሰበች፡፡ ጋብቻ ያስከተለው ህይወትን ….. ዝሙቷ የሸለማት ሞትን እንደሆነ ስታስብ እንባዋ ቀደማት፡፡ ናርዶስን የመረመረቻት ነርስ ከላብራቶሪ የመጣላትን ውጤት ከተመለከተች በኋላ ወደ ተረኛው የስነ ልቦና ባለሙያ ደወለች፡፡ ካፌ ውስጥ እያውደለደለ ነበር፡፡ እየሮጠ መጥቶ ወደ ቢሮው ገባ፡፡ ነርሷ ወደ ውጪ ወጥታ ናርዶስን ጠራቻት፡፡ ናርዶስ ቢሮው ውስጥ እንደገባች ነርሷ ቢሮውን ዘግታ ወጣች፡፡ ቀጫጫው የስነ ልቦና ባለሙያ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ ለምን መመርመር እንደፈለገች ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ከጅምሩ ምክር ማብዛት ሲጀምር ሰለቻት፡፡ ‹‹ቫይረሱ ቢኖርብሽ እንኳ በህይወት መኖር አትችይም ማለት አይደለም! ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖር ይቻላል …..›› ወሬው ሰለቻት፡፡ ‹‹ይቅርታ …… የምትለውን ሁሉ አውቀዋለሁ፡፡ አሁን ውጤቴን ብቻ ንገረኝ!›› ተበሳጨች፡፡ ‹‹ካልሽ መልካም ….. ውጤቱ የሚያሳየው ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ማለት ግን ….›› ‹‹እልልልልልልልል›› የሚል የደስታ ጩኸት ጤና ጣቢያውን አናጋው፡፡ ሂባ በሰላም የመገላገሏን ብስራት የሰሙ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶቿ ያወጡት ድምፅ ነበር፡፡ ናርዶስ የስነ ልቦና ባለሙያውን ሳታስጨርሰው ትታው ወጣች፡፡ የጠበቀችውን ውጤት መስማቷ ብዙም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ ከመተላለፊያው ላይ ቆማ ማዋለጃ ክፍል በር ላይ እየተካሄደ ያለውን የደስታ ትዕይንት ተመልክታ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለሂባ ….. ፈገግ ለጓደኛዋ ደስታ …. ፈገግ ለአብሮአደጓ የአብራክ ክፋይ ….. ፈገግ! የቤተሰቡን …. የራሷንም እናት ደስታ ስታይ ለቤተሰቧ ውርደት መሆንን ፈራች፡፡ ከረፈደ በኋላ መንቃቷ እያመማት ቀስ ብላ በሌላኛው የፎቁ መውረጃ በኩል ወርዳ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም …. ቦርሳዋን ብቻ እንደያዘች ….. ማንም ወደ ማያውቃት ….. ማንንም ወደማታሰድብበት ቦታ ለመሰደድ ወሰነች፡፡ ታክሲ ውስጥ ….. ከዛም መናኸሪያ …… ከዛም አንድ አባዱላ መኪና ውስጥ እንዱ ደላላ ጎትቶ ሲያስገባት …. መኪናው ወዴት እንደሚሄድ እንኳ አታውቅም! ብቻ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ብቻ ነው የፈለገችው …… ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ….. ናርዶስ አዲስ አበባን ለቅቃ ወደማታውቀው ስፍራ ተጓዘች፡፡ ሂባ ከሆስፒታል ከወጣች ጀምሮ ጥያቄ የሆነባት ናርዶስን አለማየቷ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿ ተጨንቀው ስልክ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ….. ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሳምንት … ናርዶስ የሌለችበት ባዶ ቤት ውስጥ አለፈ፡፡ ዚያድ ልጁን ለማየት ብቅ ባለበት እግረ መንገዱን አባቷ ባዘዙት መሰረት ‹‹ፈትቼሻለሁ›› ብሏት አዲስ የሰርግ ጥሪ ካርድ ሰጥቷቸው ሄደ፡፡ ተፈላጊ ነኝ ለማለት ይመስላል፡፡ ገንዘብ አለው …… ሴት ለእርሱ የምትገዛ እቃ ናት፡፡ * ቀመር የነበራት ተስፋ ሲሟጠጥ ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን አገኘችው፡፡ ሻንጣዋን ይዛ ነበር፡፡ በጣም ደንግጧል፡፡ ‹‹ወዴት ነው?›› ‹‹ወደ ቤት …. በቃኝ ባክህ እዛው የግል እማራለሁ … ወንጀል ከለመድኩበት ቦታ ልሽሽ!›› ‹‹እንዴ ቀመር ጎበዝ ተማሪ እኮ ነሽ …›› ‹‹እሱን ተወው ለማንኛውም አሁን ላገኝህ የፈለግኩት ባለፈው ሂባ ያማከረችህ ጉዳይ ስለራሷ እንደሆነ ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ፈትታለች … ሲመስለኝ ልጅም አርግዛለች … አግባት›› ‹‹ጓደኛዋ ደውላ ስትነግረኝ ወዲያው ነው የነገረችኝ ስለራሷ እንደነበር የገባኝ …. ግን ለእማማ ስነግራት የወለደች ሴት አታገባም … ያኔ እንደዛ አድርጋህ ምናምን አለች …. እዛው ደሴ ቤተሰብ የሚያመጣውን  ለማግባት ወስኛለሁ ባክሽ!›› ‹‹እሷ የወለደችው እኮ አግብታ ነው አይደል እንዴ ….. አንተ ሳታገባ በዝሙት የረከስክ መሆንህን እንደውም ለሂባ ንፅህና የማትመጥን መሆኑን አትነግራቸውም ነበር? …… ያው ለነገሩ ፍርዳችን ሁሌም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ወንድ እንዳሻው ቢቆሽሽ አይታወቅበትም …. አይታወቅበትም ብቻ ሳይሆን ቢታወቅም እሱ ወንድ ስለሆነ ችግር የለውም አይደል? …. ሴት አግብታ ስትወልድ ግን ….. ›› ንግግሯን መጨረስ ከበዳት፡፡ ‹‹እንዴ ጥብቅና መቆም›› ሳቀ፡፡ ‹‹በቃ ቻው የምትመጥንህን ይስጥህ ብያለሁ!›› ‹‹ይቅርታ ለዚህ ውሳኔሽ ምክንያት ስለሆንኩ!›› የፌዝ ፈገግታ ፈገግ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ትታው ሄደች፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ለቅቃ እስክትወጣ በአይኑ ሸኛት፡፡ የሂባን በደል ቀመር ላይ የተወጣ መሰለው፡፡ በልቡ ‹‹ሁሉም ዕድሉን ሲያገኝ በደለኛ ነው!›› ሲል አሰበ፡፡ ዋናው በር ላይ በእርሱ አነሳሽነት የተመሰረተው የሴቶች መብት ላይ የሚሰራው ቢሮ ክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ ወጪያቸውን ለመሸፈን በማሰብ ላሰናዳው የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ምክረ ሀሳብ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ የመጥሪያ ባነር ተሰቅሎ ነበር፡፡ *            ✋ ተፈፀመ፡✋ ታሪኩ በዚሁ ተጠናቋል ሀሳብ አስተያየታችሁን አድርሱን በቅርቡ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ሰላም ቆዩኝ                  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

Open in Telegram
Views662+108%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—

All posts

Connections