Account

Posts of 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

newest first

#7359Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 6   የልጇ መክሳት ክፉኛ ሲያስለቅሳቸው ከቆየ በኋላ ማልቀሳቸውን ማቆማቸውን ሲያውቅ ። " እራት ገዝቼ መጣሁ " አላቸውና ሰለሞን ከቤት ወጣ ። ነገር ግን እራት መግዛት ሳይሆን ወደ ጎረቤት ቤት ነበር የሄደ ። የጎረቤታቸውን የወ/ሮ ዝናሽን ግቢ አልፎ ቤት ከገባ በኋላ ወ/ሮ ዝናሽን ወጥ እየሰራች አገኛት ። ከማብሰየዋ ተከታትሏት ገባና እማማ ነው የሚላት " እማማ እባክሽ እናቴን አሞብኝ ነው የማሳክምበት ብር ካለሽ አበድሪኝ " አላት እየፈራ አንገቱን እንዳቀረቀረ ብድር ሲጠይቅ የመጀመሪያው ነው ። " አመማት እንዴ ምንቴን ? " አለችው እማማ ም ቢሆን ደንግጣ ነበር " ምንትዋብን " አቆላምጣ ስጠራት " ምንቴ " ነው የምትላት " አዎ ውጋት ነገር አሟታል " አላት ። እማማ ወሬ ማብዛት አልፈለገችም ወደ ሳሎን ከገባች በኋላ ከጥቁር ቦርሳ ውስጥ ብር እያወጣች ተመለሰች 2000 ብር ቆጥራ ሰጠችውና ። " ካነሰህ ጠይቀኝ " ። ሰለሞን በጣም አመስግኖ ከማብሰያዋ ወጣና አንዴ ፈጣሪውን አንዴ እማማን እያመሰገነ ለእናቱ እራት ሊገዛ ወደ አንድ ካፌ አቀና ። ወ/ሮ ምንትዋብ እና እማማ የልጅነት ጓደኛሞች ብቻ ሳይሆኑ እህትማማቾችም ማለት ናቸው ። በተቸገሩ ጊዜ አንዷ ከአንዷ ተበዳድረዋል ። ዛሬ ድህነት ቤት ሰራባቸው እንጂ ወ/ሮ ምንትዋብም ለእማማ አንዴ ከገንዘቡ ፣ አንዴ ከሚበላው አበድረዋት ያውቃሉ ። ዛሬ ግን የሰው እጅ እያዩ መኖር እጣ ፈንታቸው ሆኗል ። ሰለሞን እራት ገዝቶ ከመጣ በኋላ አብረው ከእናቱ ጋር መብላት ጀመሩ ። ልጃቸው አብሯቸው በመብላቱ ደስ ብሏቸዋል ። አንዴ እሱ አንዴ እሷ እየተጎራረሱ ይበላሉ ። ወ/ሮ ምንትዋብ ልጃቸውን ሊያጎርሱ የጠቀለሉትን ጉርሻ እንጀራ በተመተማ አፉ እየመሰላት አንዴ አፍንጫው ላይ አንዴ ደሞ አገጩ ላይ ይጨምሩታል ፡ ያኔ ሰለሞን በእናቱ ድርጊት ትን እስኪለው ይስቃል ። የልጃቸው መሳቅ ፈገግ አስባላቸው ደስተኛ ሆነዋል የታመሙ አይመስሉም ። አይናቸውን ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ የሚስቀውን ልጃቸውን ሲስቅ ለማየት ቢያንከባልሉትም ሊያዩት አልቻሉም ከመስማት ውጭ ። . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 7

Open in Telegram
Views80−75%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#7358Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 5 ይቅር እንዳላት ነግሯት ሊሸኛት ወደ ቤቷ አመሩ ሂሩት ፊቷ በደስታ ፈክቷል ። አሁን ይቅር ስላላት ውስጧን ሰላም ተሰምቷታል ነፃ ሁናለች ። ሰለሞንም ቢሆን በደስታ ሰክሯል በተለይ ስላቀፈችው ፡ ከእናቱ ውጭ ማንም አቅፎት አያውቅም ወደ ቤቷ በመሸኘት ላይ እያለ በመንገዳቸው ሰው ከሌለ እጁን ትክሻዋ ላይ ጣል ሲያደርገው የተመቻት ይመስል ፈገግ ከማለት ውጭ ምንም አላለችውም ። ከፊታቸው ሰው ከመጣ ወይም ደግሞ ከኋላቸው ሰው ከተከተላቸው እጁን ከትክሻዋ ላይ ያወርደዋል ። አስቆጣታለሁ ብሎ ስላሰበ ነበር ። ቤት ልትደርስ ትንሽ ሲቀራት ቤታቸውን ከርቀት አሳየችውና ቻው ተባብለው ነገ ዛሬ ከጠበቃት ቦታ ላይ እንደሚጠብቃት ነግሯት ተለያዩ ። ልቡ በሀይለኛው ይመታ ነበር ። ....ድው......ድው ይላል ። ቆሞ ቤት እስክትገባ በአይኑ ሸኛት ቤቷ ስትገባ ተመለከተና ፊቱን አዙሮ ወደ ቤቱ በፈገግታ መሄድ ጀመረ ። በደስታ እየተፍለቀለቀ ቤቱ ሲደርስ እናቱ ከቤት ውስጥ ሆነው " አሟቸው ነው መሠል እህ .....እህ እያሉ ሲሰማ ዘሎ ወደ ቤት ገባ ። እንደገባ እናቱ እያቃሰቱ ነበር ። የሰው ኮቴ ሲሰሙ ማቃሰታቸውን አቆሙና " ማነው ? " አሉ ። አይናቸው እንደሚያይ ሁሉ ወደ በሩ ልከው ። " አማየ " አመመሽ እንዴ ? አላት ሰለሞን ወደ አልጋው እየተጠጋ " ሰለሞኔ አንተ ነህ እንዴ ? " " አዎ ዛሬስ ልቤን ውጋት ደሞ ያመኝ ጀመር " አሉት ። ቅስማቸው ተሰብሯል የእናቱ ቅስም ተሰብሯል ። ሰለሞን የሚያደርገው ጠፋው በጣም ፈርቷል " አይዞሽ እማየ ነገ እንደምንም አሳክምሻለሁ " አላት ከጎኗ እየተቀመጠ ። ምንም ገንዘብ እንደሌለው ያውቃል ግን የሚላቸው ጠፍቶት ነበር አሳክምሻለሁ ያላት ። አቀፉትና ወደ ደረታቸው አስጠግተው የጎደለው አካል እንዳለ ሁሉ ከላይ ከፀጉሩ ጀምረው መዳበስ ጀመሩ ። " ምነው ሰለሞኔ ፀጉርህ እንደዚህ ዱር እስኪመስል ድረስ የማትቆረጥ ? " አሉት ፀጉሩን ሲዳብሱት ከቆዩ በኋላ ። " እሽ እማየ ነገ እቆርጣለሁ " አላቸው ። ብዙ ጊዜ የምትጠይቀውን ሁሉ እሽ አደርገዋለሁ ይላቸዋል ። ብዙ ጊዜ አደርገዋለሁ ያለውን ግን ያደርጋል ፡ እናቱ ፈገግ እንዳሉ መዳበሳቸውን ቀጠሉና ግንባሩን አልፈው ወደ ታች ሲወርዱ ፊቱ አካባቢ " የሰለሞን " እንባ እጃቸውን ፈጃቸው ፡ ፈገግታቸው ወዲያው ድርግም አለና ግንባራቸውን ቋጠሩ ። " ሰለሞኔ ለምን ታለቅሳለህ " አሉት " ም...ም....ምንም እማየ " አላት እንባውን እና ንፍጡን እየጠረገ ። እናቱ የልጃቸውን አንገት እና ደረት ከዳበሱት በኋላ ግን እንባቸው ይገነፍል ጀመር ። የደረቱ አጥንት መግጠጡን በእጃቸው ዳብሰው ልጃቸው እንደ ከሳ አውቀውታል ። " ምነው ልጄ ከስተሀል ምግብ አትበላም ? " አሉት እንባቸውን እንዳያይ ፊታቸውን እየዞሩ ። " አልከሳሁም እኮ እማየ ደህና ነኝ " አላቸው ። እንዳታዝን እና እንዳታለቅስ ፈልጎ እንጂ ለእሱም መክሳቱ አልጠፋውም ። ብዙውን ጊዜ ምሳም ሆነ እራት አይበላም ። በቀን የሰራው ብር ትንሽ ከሆነ ለእናቱ የሚሆን ምግብ ብቻ ይገዛና ይመለሳል ። " ና አብረን እንብላ " ያለችው እንደሆነ ጠጋ ብሎ አንዴ ይጎርስና " እዛው ምግብ ቤቱ በልቼ ነው የመጣሁ ይልቅ አንቺ መብይላት አለብሽ " ይላታል ። ነገር ግን ውሸቱን ነበር " እናቱ እንዳታስብና የገዛው ምግብ ለሁለት ስለማይበቃ ነበር " ሁሌም በልቼ ነው የመጣሁ " የሚላት.............          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 6

Open in Telegram
Views61−81%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#7357Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 4 አባቷ አቶ መኮንን ነጋዴ ሲሆኑ በሀብት ደረጃ በከተማዋ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ሶስት ቢላ ቤት እና ሁለት ሰፋፊ ሱቆች አሏቸው አንዱ የመኪና መለዋወጫ ሱቅ ሲሆን አንዱ ደግሞ የፈርኒቸር ሱቅ ነው ። ነገር ግን በፀባያቸው ብዙም ከሰው ጋር የማይግባባ ኮስታራ እንዲሁም በአካባቢው ክፉ ተብለው የሚታማ ሰው ነው ። ለሂሩት ልዩ ፍቅር ነው ያለው ከሌሎች ልጆቹ እሷን ያስበልጣል ። ይንከባከባታል ስለ ህይወት ይመክራታል ። ሁሌም አንድ ምክር አላቸው " ማንም ወንድ ውበትሽን አይቶ እንዲያፈቅርሽ አትፍቀጂለት ምክንያቱም አንቺን ሳይሆን ውበትሽን ነው ያፈቀረ ውበት ደግሞ ጤዛ ነው ይረግፋል " ። ቆንጆ ስለመሆኗ እንኳን አባቷ ማንም አይጠራጠርም ሂሩትም ቢሆን የአባቷ ነገር ብርቋ ነው በጣም ትወደዋለች ። በትምህርቷ ጎበዝ ስትሆን ትምህርት ቤቱ ከቤታቸው ብዙም ስለማይርቅ በእግሯ ነው የምትመላለስ ። ..... አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስትመለስ ከጓደኞቿ ጋር ተለያይተው ወደ ቤቷ የሚወስደውን መንገድ ስትይዝ ጠብቆ እየሮጠ ተከተላት ፡ ራቅ ብሎ ቆሞ ስለነበር ቤቷ ከመግባቷ በፊት ሊያናግራት ስለፈለገ በፍጥነት ነበር እየሮጠ የደረሰባት ። አጠገቧ መድረሱን ሲያውቅ ቁና ቁና እየተነፈሰ " ሂሩት....ብሎ ተጣራ ድንግጥ ብላ ስትዞር ሰለሞን ነበር ዛሬም ፈርታዋለች ግን እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ቆማ ጠበቀችው ። ፈገግ ብሎ አንዴ እሷን አንዴ ደግሞ መሬት መሬቱን እያየ ተጠጋት ፡ እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት ስትፈራ ስትችር እጁን ጨበጠችውና ቶሎ ብላ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ እጇን ከእጁ መነጨቀችው ። አንገቱን ቀብሮ እየተንተባተበ መናገር ጀመረ " ባ...ባ...ለፈው ስለ..ተፈጠረው ነገር ይ....ቅርታ ልጠይቅሽ ነው የጠራሁሽ " አላትና ቀና ብሎ ሲያያት ትኩረት ሰጥታ እያዳመጠችው እንደሆነ ሲያውቅ መናገሩን ቀጠለ ። " ማለት ማስደንገጥም ሆነ ማስፈራራት የ...ለብኝም ነበር በዛ ላይ ልክ ነበራቹ እ...ብድ እመስላለሁ " አላት ተናግሮ ሲጨርስ ወደ መሬት የደፋውን ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ይቅርታዋን ለመቀበል ሲያያት ግን እሷም እራሷን አቀርቅራለች ። ሰለሞን ግራ ገባውና እጁን ትክሻዋ ላይ አድርጎ ቀና ሲያደርጋት ፡ ሎሚ በመሰለው ጉንጯ ላይ እንባዋ እየተንከባለለ ጡቷ ላይ ይንጠባጠብ ጀመር ። ሰለሞን ይበልጥ ግራ ተጋብቶ " ዛሬም ፈርታኝ ይሆን የምታለቅስ " ሲል አሰበ ። " ለምንድን ነው የምታለቅሺ " አላት እንባዋን በመዳፏ ከጠራረገች በኋላ " ሁሌም ይፀፀተኝ ነበር አንተ እብድ አይደለህም ስራ ባቆሸሸው ልብስህ ተሳለቅንብህ እብድ አልንህ ፣ ሰደብንህ ሰሞኑን ደግሞ እኛ ቤት የመጣህ ቀን የቤተሰብህን ችግር ስትነግረን ይበልጥ በራሴ ላይ አዘንኩ እራሴንም በጣም ጠልቼው ነበር ። አንተ ምንም አላጠፋክም ጥፋተኛ እኔ ነኝ ስለዚህ እባክህ ይቅርታ በለኝ " አለችው ። በመለመን አይነት ቅላፄ አይን አይኑን እያየች ። እንባዋ ግን ብትጠርገውም አሁንም እንደ አባይ ወንዝ መፍሰሱን አላቆመም ነበር ። ሰለሞን እንደ እንባ የሚፈራው ነገር የለም ። በትኩረት ተመለከታትና እንባዋን ቀስ ብሎ በእጁ መዳፍ ከጠራረገላት እቅፍ አደረጋት ። እሷም እጇን ቀስ እያደረገች አንስታ ጀርባው ላይ ካደረገች በኋላ አቀፈችው ። ሁለቱም መተቃቀፍ የመጀመሪያቸው ነው ይቅር እንዳላት ነግሯት ሊሸኛት ወደ ቤቷ አመሩ ሂሩት ፊቷ በደስታ ፈክቷል......          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 5

Open in Telegram
Views63−80%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#7356Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 3 ወ/ሮ ሙሉነሽ እንባ ያቆረው አይናቸውን እዬጠራረጉ * አይዞህ የኔ ልጅ * ሁሉም ለበጎ ነው ብለው ለማፅናናት ሞከሩ ። ሂሩትም ቢሆን አታልቅስ እንጂ እንዳዘነች አይኗን አይቶ መገመት ይቻላል .....ወ/ሮ ሙሉነሽ ሰለሞንን እስከ በሩ እያወሩ ሸኝተውት ሲመለሱ " እኔን አፈር በበላሁ አይ ወንድ ልጅ እኔን ይቸግረኝ ወንድ ልጅ አይጣ " እያሉ ከልባቸው እያዘኑ ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ። ሂሩት ግን ተከትላቸው አልገባችም ። ቁጭ እንዳለች በሆነ ሀሳብ ውስጥ ተጠምዳለች ። ሰለሞን ተሸክሞ ባገኛት 50 ብር ለእናቱ ቀለል ያለ ምሳ ገዝቶላት ወደ ቤቱ ገባ ። ሂሩትን ሲያያት የደነገጠው ድንጋጤ ግን አሁንም አለቀቀውም ሲያስበው በድጋሜ ይደነግጣል ። አንድ ቀን ምሽት ...... ስራ ያደከመውን አካሉን ለማሳረፍ በጥድፊያ ወደ ቤቱ በመሄድ ላይ እያለ ሂሩትና የሴት ጓደኛዋ ትዕግሥት ፊት ለፊት ተገናኙት ። የልብሱ ቀዳዳ መሆን እና መቆሸሽ እንዲሁም የፀጉሩ መንጨብረር ያስፈራቸው ሂሩትና ጓደኛዋ ትዕግሥት ያበደ ሰው መሰላቸው ። በፍርሀት እየተንቀጠቀጡ ካለፉት በኋላ "እብድ ነው ?" ብላ ጠየቀቻት ሂሩት ጓደኛዋን "አዎ እብድ ነው መሠለኝ " አለች ጓደኛዋ ። በዚህ ሰዓት ሰለሞን ሰማቸውና ዘወር ብሎ ሊያናግራቸው ሲል እየጮሁ ይሮጡ ጀመር ። በንዴት ቱግ አለና ሰለሞንም ያሯሩጣቸው ጀመር አጣደፈና ጓደኛዋ ሮጣ ስታመልጥ ሂሩትን ያዛት ። ሁለቱም ከላይ ከላይ ይተነፍሳሉ በጣም አሯሩጣው ነበር ። ልታመልጥ ብትሞክርም አአልተሳካላትም ሁለት እጇን አጣምሮ ያዘና ወደ እሱ አዙሮ ጮኸባት ። " ልብስ የቆሸሸ ሁሉ እብድ ነው ? ' " ድህነት እብድ ያስብላል ? " ንገሪኝ እንጂ ? እያለ ቢጮህባትም መላ አካሏ እየተንቀጠቀጠ አይን አይኑን እያየች ከማልቀስ ውጭ ምንም ልትመልስለት አልቻለችም ። እንባዋን ካየ በኋላ ግን አሳዘነችውና ቁጡ ስሜቱ በርዶ በቆመችበት ጥሏት ሄደ ። ሂሩት ይደበድበኛል ወይም ይደፍረኛል ብላ ነበር የጠበቀች በዛ ላይ እብድ እንዳልነበረ አወቀች ። በቆመችበት ከአይኗ እስኪጠፋ ተመለከተችው እሱ ግን ወደ ቤቱ ከመጣደፍ ውጭ አንዴም ዞሮ አላያትም ነበር ። ከዛን ቀን ጀምሮ ሂሩት የሰለሞን አስፈራ ፀጉር ፣ እጇን አጣብቆ የያዛት ፣ ስሜታዊነቱ ፣ ቁጡነቱ ፣ ያሯሯጣት ከአይነ ህሊናዋ ጠፍቶ አያውቅም ። ዛሬ ግን ሰለሞን ቤቷ ድረስ ቢመጣም ከመበቀል ይልቅ ለራበው ሆዱ ምግብ ሰጠችው ። የሰለሞን ህይወት አሳዝኗታል ። ሰሞኑን ደግሞ ሀሳቧን ሁሉ ሰለሞን ተቆጣጠረው ብቻ ስለእሱ ሁሌም ታስባለች ። ሂሩት የ10 ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ገና የ18 አመት ልጅ ናት ። መካከለኛ ቁመት ያላት ሲሆን የአይኖቿ ጎላጎላ ማለት ፣ የከንፈሯ ልስላሴ ፣ የሰውነቷ ጥራት ፣ የአንገቷ ርዝማኔ ብቻ በውበቷ ልዩ የምትባል ሴት ናት ። ገና በዚሁ እድሜዋ የገጿን አቦል የውበቷን አፍላ ለመቅመስ በከተማው ውስጥ የፍቅር ጥያቄ ያልጠየቃት ወንድ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ከተማሪ እስከ መምህር ፣ ከቀን ሰራተኛ እስከ መንግስት ሰራተኛ ፣ ከሌባ እስከ ፖሊስ የማይጠይቃት የለም ነበር ። የሷ መልስ ግን " አሁን ለማፍቀር ዝግጁ አይደለሁም " ትላቸዋለች ብዙ ቀንም ተማራ ታውቃለች ። የቤቱ የመጨረሻ ልጅ ስትሆን ውጭ ሀገር በመማር ላይ የሚገኙ ሁለት ትላልቅ ወንድሞች አሏት ። አባቷ አቶ መኮንን ነጋዴ ሲሆኑ በሀብት ደረጃ በከተማዋ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ሶስት ቢላ ቤት እና ሁለት ሰፋፊ ሱቆች አሏቸው.....          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 4

Open in Telegram
Views192−40%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7355Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 2 ሰለሞን ቁጭ እንዳለ ግቢውን ይቃኝ ጀመር መዋኛ ገንዳው ፣ የተለያየ ቀለም ያላቸው አበቦች ፣ ልዩ ውበት ተሰጥተውታል ። እንደዚህ አይነት ግቢ አይቶ አያውቅም ። ተመስጦ ግቢውን በማየት ላይ እያለ ወ/ሮ ሙሉነሽ ቦርሳቸውን ይዘው ወጡ ። የሰለሞን አይን ከቦርሳው ላይ ነበር * ስንት ትከፍለኝ ይሆን አለ በውስጡ * ዝርዝር ያጡ ይመስል ብዙ ከፈለጉ በኋላ ድፍን ሀምሳ ብር አውጥተው ሲሰጡት ሰለሞን ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ዋጠ ። ያ ላበት ሲፈስበት የቆየው እርሾ የመሠለዉ ፊቱ በአንዴ ፈካ ከመቀመጫው ተነስቶ አመስግኖ ሊሄድ ሲል ። * ቆይ የኔ ልጅ የሚበላ ነገር ቅመስ አሉትና ፡ እዛው በረንዳው ላይ ካለው ወንበር እየተቀመጡ * ሂሩት የሚበላ ነገር ለልጁ አምጭለት * አሏት ሳሎን ውስጥ ቁጭ ብላ የምታነበውን ልጇን ሰለሞን ለመግደርደር ቢሞክርም በርሀብ የተሰቃየው ሆዱ እሽ አልለው ስላለ ቁጭ አለ ። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ የሚበላ ነገር ይዛ የመጣችውን ሂሩትን ሲያያት ክው ብሎ ደነገጠ ። ያውቃት ነበር ፡ ሲያያት የሀፍረት ስሜት ተሰማው ሂሩት የያዘችውን ምግብ ከሰጠችው በኋላ ወደ ሳሎን ከመግባት ይልቅ እዛው በረንዳው ላይ ካለው ወንበር ላይ ከእናቷ አጠገብ ቁጭ አለችና በትኩረት ትመለከተው ጀመር ። የሰጠችውን እንጀራ በምስር ወጥ አንገቱን ደፍቶ ምንም ሳይናገር በፍጥነት በልቶ ሊሄድ ሲል * የኔ ልጅ * አሉት አቤት ማዘር ... : : ስምህ ማነው ? ሰለሞን.... አላት ፊቱን ሳያዞር እዚሁ ነው የምትኖረው ?....ቀጠለች አዎ ቀበሌ 3 ነው የምኖረው አላቸው ሂሩት በዚህ ሰዓት ዝም ብላ ነበር የምታዳምጥ ስራስ የለህም ? ምንም ልትለቀው አልፈለገችም * አዎ የለኝም የእለት ጉርሳችንን በቀን በምሰራው ነው በልተን የምናድር ኑሯችን ከእጅ ወደ አፍ ነው * አላት ወ/ሮ ሙሉነሽ አሳዘናቸው መሠል ፊታቸው ከመቅፅበት ተቀያየረ ከማን ጋር ነው የምትኖረው ? ቤተሰብ አለህ ? አለችው ። እሷ ስትጠይቅ እሱ ሲመልስ ከቤተሰቡ ደረሱ ስለ ቤተሰቡ አንድ በአንድ ይነግራት ጀመር ። * አባቱ ሻምበል ምትኩ ይባል የነበረ ሲሆን ወታደር ነው እናቱ ወ/ሮ ምንትዋብ ደግሞ የቤት እመቤት ናቸው ። አንድ ልጅ ብቻ ወልደው ያቆሙ ሲሆን ከሰለሞን ውጭ ሌላ ልጅ አልታደሉም ። ድህነት የሚባል ነገር ከአጠገባቸው ድርሽ የማይል ለራሳቸው የማያንሱ ቤተሰቦች ነበሩ ። ሰለሞን ገና የ16 አመት ልጅ የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ አባቱ ሻ/ል ምትኩ ግዳጅ ላይ እንዳለ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ያለፈች ሲሆን ። የዚያን ቀን እናቱ ወ/ሮ ምንትዋብ በድንጋጤ ምክንያት ራሳቸውን ስተው ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ ሲነቁ ሁለቱም አይናቸው ማየት ተሳነው ። ወዲያው ህክምና ቢደረግላቸውም ሊሻላቸው አልቻለም ነበር ። ሰለሞን ታዲያ በ16 አመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ የቀን ስራ ተሰማራ ። ያ ከአጠገባቸው ርቆ የነበረው ድህነት ዛሬ ቤታቸውን ቤቱ አደረገ ቤታቸው የቀበሌ ቤት ቢሆንም ቤተሰቡ ሙሉ እያለ የሚያምረው ቤት ዛሬ ቴሌቭዥኑ ተሽጦ ፣ ሶፋዎች ለችግር ማስወገጃ ተሽጠው ቤቱ ጥርስ የሌለው አፍ መስሏል ። ሰለሞን ቀን ሰርቶ በሚያገኘው ብር ለእናቱ ምሳ ፣ እራት እየያዘ መግባት ከጀመረ 5 አመታትን አለፈ ። እናቱ ከአይናቸው በተጨማሪ ሌላ በሽታም ያማቸዋል ። የሰለሞን እድሜ ዛሬ 21 ነው ወ/ሮ ሙሉነሽ እና ልጇ ሂሩት በጥሞና ካዳመጡት በኋላ......          . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3

Open in Telegram
Views171−46%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#7354Photo
Views3180%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#7353Text

❤️ ለፍቅር❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️                        ክፍል 1 ፀሀይዋ በከተማዋ ላይ ቂም የቋጠረች ይመስል ገና 3 ሰዓት ሳይሆን ሙቀቷን ትረጫለች ። ሰለሞን ግን የፀሀይዋን ሙቀት ከምንም ሳይቆጥር በሰው መሀል እየተሹለከለከ ወደፊት ያመራል ሲያዩት ቀጠሮ ያለበት ነበር የሚመስል ቢጠሩትም አይሰማም ። በጣም ከመቸኮሉ የተነሳ ወደ ኋላው እንኳን ዞሮ አያይም ። ቀጥ ብሎ ነበር የሚሄድ መናሀሪያውን ካለፈ በኋላ ወደ አደባባዩ የሚወስደውን መንገድ ተያያዘው ። የለበሰው አሮጌ ጅንስ ሱሪ ከማለቁ የተነሳ ተቀዳዷል ከላይ የለበሳት ቢጫ ቲሸርት በጣም ከመቆሸሿ የተነሳ ውሃ ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም ። የፀጉሩ ነገርማ አይነገርም በጣም ከመንጨፍረሩ የተነሳ የጃርት እሾህ መስሎ ቆሟል ። አደባባዩ ከደረሰ በኋላ ወደ ቀኝ ታጠፈና ወደ ገበያው ገባ ። የህዝቡ ብዛትና ጫጫታ ግራ ያጋባው ሰለሞን መሀል ላይ ቆሞ ከወዲያ ወዲህ ቢያማትር ተሸካሚ ( ወዛደር ) የሚፈልግ ሰው በአይኑ ቢያስስ አጣ ። “ በቃ ዛሬም ሳልሰራ ልውል ነው ? " አለ በውስጡ ። ትንሽ ከጠበቀ በኋላ ወደ ጤፍ መሸጫው መካዘን አመራ እዛም ወዛደር የሚፈልግ ሰው አጣ ። አንድ ከተዘጋ ሱቅ ገደፍ ብሎ እንደቆመ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ ። ከእጅ ወደ አፍ የሆነው ኑሮው ይበልጥ ያስጨንቀው ጀመር ። ሰው ሁሉ በሰው ከማሸከም ይልቅ ለፍጥነቱ እያለ በእሽኩኒታ ማስጫኑ የወዛደሮች ኑሮ ወደፊት ምን ሊመስል እንደሚችል እያሰበ እያለ ነበር ድንገት “ የኔ ልጅ " የሚል ድምፅ ብዙ ርቀት ከሄደበት ሀሳቡ ያነቃው ። ገና ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው አይኑን እያጨላሞሰ ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ ሲዞር ከአንድ እናት ጋር አይን ለአይን ተጋጩ ። ትሸከማለህ ? አለችው በማዳበሪያ የሞላውን ጤፍ በአገጯ እየጠቆመች ። አዎ...ብሎ ጣድፎ ስለ ክፍያ ሳይነጋገሩ ተወተርትሮ አንስቶ ተሸከመው ። በክፍያ አለመስማማት ይመጣል ብሎ ስላሰበ ነበር ስለ ክፍያ ሳይጠይቅ ለመሸከም የተገደደው ። ሰሞኑን ሳይሰራ በመሰንበቱ ነበር የሰጠችውን ክፍያ ለመቀበል የወሰነ ። የህዝቡን ጋጋቴ ቀስ እያለ ካለፈ በኋላ ። ከፊት ሆና ሴትዮዋ በምትመራው ወደ ዋናው ንግድ ባንክ ከሄዱ በኋላ እንደገና ወደ ስታዲየሙ በሚወስደው መንገድ ጉዞውን ጀመረ ። ሴትዮዋን ከዚህ በፊት አይቷት የማያውቅ ቢሆንም ከተማው ውስጥ በደግነት አንቱታን ያተረፉ የቤት እመቤት ናቸው ። ወ/ሮ ሙሉነሽ ይባላሉ ። ከጨፍራራ ፀጉሩ የሚፈሰው ላበት ፊቱን አልብሶ ወደ አንገቱ መፍሰስ ጀምሯል ። ከፀጉሩ ላይ ላበት እያጠበ የሚያመጣው እድፍ አይኑን ስለሚቆጠቁጠው ቆም ይልና ፡ በአንድ እጁ ዣዱ ላይ የተሸከመውን ጤፍ እንዳይወድቅበት ይይዝና በሌላኛው እጁ ደግሞ ሁለቱንም አይኑን ጠራርጎ ፡ እንደ ወጣት በፍጥነት የሚጓዙትን ወ/ሮ ሙሉነሽን በፍጥነት ጉልበቱ ከጉልበቱ እየተጋጨ እና እየተወላገደ አሊያም በማቸልቸል ይደርስባቸዋል ። ቀጥ ያለውን የስታዲየሙን መንገድ ጨርሰው የመጨረሻ መታጠፊያ ሲቀር ወ/ሮ ሙሉነሽ ቆማ ጠበቁትና " አይዞህ የኔ ልጅ ደርሰናል " አሉትና ወደ መታጠፊያው ገቡ ። ልምድ ሆኖባቸው ወጣቱን በሙሉ " የኔ ልጅ " ማለት ይቀናቸዋል ። ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ሰፊ በር ያለውን ግቢ ሲያንኳኩ ጥበቃቸው እየተጣደፈ በሩን ከፈተላቸው ። ሰለሞን ጤፉን በረንዳው ላይ ካወረደ በኋላ " ደከመህ የኔ ልጅ ? አልደከመኝም.... አላቸው ቁና ቁና እየተነፈሰ ። በዚህ ሰዓት ወ/ሮ ሙሉነሽ ወደ ውስጥ ገቡ ። ሰለሞን ቁጭ እንዳለ አጥር ግቢውን ይቃኝ ጀመር ። . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 2

Open in Telegram
Views306−4%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#7350Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 4⃣0⃣ የመጨረሻ ክፍል አንድ ቀይ ቀለም የበዛበት ማስታወቂያ የተለጠፈበት ቢሮ ውስጥ ገባች፡፡ እጇን ከጠረጴዛው ወዲያ ተቀምጣ ስትቦዝን ለነበረችው ነርስ ዘረጋችላት፡፡ ደሟን ወስዳ ጥቂት ደቂቃዎችን እንድትታገሳት ጠየቀቻት፡፡ ናርዶስ ተስፋ መቁረጧ ፊቷ ላይ እየተነበበ ከቢሮው ወጥታ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተች፡፡ የማዋለጃ ክፍሉ በር ላይ ወላጆቿ እና ጎረቤቶቿ ሲቁነጠነጡ ተመለከተች፡፡ ሁሉም የሂባን መውለድ በተስፋ እንደ  ሚጠብቁ ገመተች፡፡ የሂባ ልጅ የመጣው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ የናርዶስም ስብራት የተፈጠረው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን በጋብቻ እና በዝሙት መሀል ነው፡፡ ከጋብቻው ልጅ ….. ከዝሙቱ ደግሞ በሽታ! ጋብቻ ምንም ያህል የተመቻቸ ባይሆን እንኳ ፍሬው እንደዝሙት አይከፋም ስትል አሰበች፡፡ ጋብቻ ያስከተለው ህይወትን ….. ዝሙቷ የሸለማት ሞትን እንደሆነ ስታስብ እንባዋ ቀደማት፡፡ ናርዶስን የመረመረቻት ነርስ ከላብራቶሪ የመጣላትን ውጤት ከተመለከተች በኋላ ወደ ተረኛው የስነ ልቦና ባለሙያ ደወለች፡፡ ካፌ ውስጥ እያውደለደለ ነበር፡፡ እየሮጠ መጥቶ ወደ ቢሮው ገባ፡፡ ነርሷ ወደ ውጪ ወጥታ ናርዶስን ጠራቻት፡፡ ናርዶስ ቢሮው ውስጥ እንደገባች ነርሷ ቢሮውን ዘግታ ወጣች፡፡ ቀጫጫው የስነ ልቦና ባለሙያ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ ለምን መመርመር እንደፈለገች ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ከጅምሩ ምክር ማብዛት ሲጀምር ሰለቻት፡፡ ‹‹ቫይረሱ ቢኖርብሽ እንኳ በህይወት መኖር አትችይም ማለት አይደለም! ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖር ይቻላል …..›› ወሬው ሰለቻት፡፡ ‹‹ይቅርታ …… የምትለውን ሁሉ አውቀዋለሁ፡፡ አሁን ውጤቴን ብቻ ንገረኝ!›› ተበሳጨች፡፡ ‹‹ካልሽ መልካም ….. ውጤቱ የሚያሳየው ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ማለት ግን ….›› ‹‹እልልልልልልልል›› የሚል የደስታ ጩኸት ጤና ጣቢያውን አናጋው፡፡ ሂባ በሰላም የመገላገሏን ብስራት የሰሙ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶቿ ያወጡት ድምፅ ነበር፡፡ ናርዶስ የስነ ልቦና ባለሙያውን ሳታስጨርሰው ትታው ወጣች፡፡ የጠበቀችውን ውጤት መስማቷ ብዙም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ ከመተላለፊያው ላይ ቆማ ማዋለጃ ክፍል በር ላይ እየተካሄደ ያለውን የደስታ ትዕይንት ተመልክታ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለሂባ ….. ፈገግ ለጓደኛዋ ደስታ …. ፈገግ ለአብሮአደጓ የአብራክ ክፋይ ….. ፈገግ! የቤተሰቡን …. የራሷንም እናት ደስታ ስታይ ለቤተሰቧ ውርደት መሆንን ፈራች፡፡ ከረፈደ በኋላ መንቃቷ እያመማት ቀስ ብላ በሌላኛው የፎቁ መውረጃ በኩል ወርዳ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም …. ቦርሳዋን ብቻ እንደያዘች ….. ማንም ወደ ማያውቃት ….. ማንንም ወደማታሰድብበት ቦታ ለመሰደድ ወሰነች፡፡ ታክሲ ውስጥ ….. ከዛም መናኸሪያ …… ከዛም አንድ አባዱላ መኪና ውስጥ እንዱ ደላላ ጎትቶ ሲያስገባት …. መኪናው ወዴት እንደሚሄድ እንኳ አታውቅም! ብቻ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ብቻ ነው የፈለገችው …… ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ….. ናርዶስ አዲስ አበባን ለቅቃ ወደማታውቀው ስፍራ ተጓዘች፡፡ ሂባ ከሆስፒታል ከወጣች ጀምሮ ጥያቄ የሆነባት ናርዶስን አለማየቷ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿ ተጨንቀው ስልክ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ….. ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሳምንት … ናርዶስ የሌለችበት ባዶ ቤት ውስጥ አለፈ፡፡ ዚያድ ልጁን ለማየት ብቅ ባለበት እግረ መንገዱን አባቷ ባዘዙት መሰረት ‹‹ፈትቼሻለሁ›› ብሏት አዲስ የሰርግ ጥሪ ካርድ ሰጥቷቸው ሄደ፡፡ ተፈላጊ ነኝ ለማለት ይመስላል፡፡ ገንዘብ አለው …… ሴት ለእርሱ የምትገዛ እቃ ናት፡፡ * ቀመር የነበራት ተስፋ ሲሟጠጥ ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን አገኘችው፡፡ ሻንጣዋን ይዛ ነበር፡፡ በጣም ደንግጧል፡፡ ‹‹ወዴት ነው?›› ‹‹ወደ ቤት …. በቃኝ ባክህ እዛው የግል እማራለሁ … ወንጀል ከለመድኩበት ቦታ ልሽሽ!›› ‹‹እንዴ ቀመር ጎበዝ ተማሪ እኮ ነሽ …›› ‹‹እሱን ተወው ለማንኛውም አሁን ላገኝህ የፈለግኩት ባለፈው ሂባ ያማከረችህ ጉዳይ ስለራሷ እንደሆነ ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ፈትታለች … ሲመስለኝ ልጅም አርግዛለች … አግባት›› ‹‹ጓደኛዋ ደውላ ስትነግረኝ ወዲያው ነው የነገረችኝ ስለራሷ እንደነበር የገባኝ …. ግን ለእማማ ስነግራት የወለደች ሴት አታገባም … ያኔ እንደዛ አድርጋህ ምናምን አለች …. እዛው ደሴ ቤተሰብ የሚያመጣውን  ለማግባት ወስኛለሁ ባክሽ!›› ‹‹እሷ የወለደችው እኮ አግብታ ነው አይደል እንዴ ….. አንተ ሳታገባ በዝሙት የረከስክ መሆንህን እንደውም ለሂባ ንፅህና የማትመጥን መሆኑን አትነግራቸውም ነበር? …… ያው ለነገሩ ፍርዳችን ሁሌም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ወንድ እንዳሻው ቢቆሽሽ አይታወቅበትም …. አይታወቅበትም ብቻ ሳይሆን ቢታወቅም እሱ ወንድ ስለሆነ ችግር የለውም አይደል? …. ሴት አግብታ ስትወልድ ግን ….. ›› ንግግሯን መጨረስ ከበዳት፡፡ ‹‹እንዴ ጥብቅና መቆም›› ሳቀ፡፡ ‹‹በቃ ቻው የምትመጥንህን ይስጥህ ብያለሁ!›› ‹‹ይቅርታ ለዚህ ውሳኔሽ ምክንያት ስለሆንኩ!›› የፌዝ ፈገግታ ፈገግ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ትታው ሄደች፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ለቅቃ እስክትወጣ በአይኑ ሸኛት፡፡ የሂባን በደል ቀመር ላይ የተወጣ መሰለው፡፡ በልቡ ‹‹ሁሉም ዕድሉን ሲያገኝ በደለኛ ነው!›› ሲል አሰበ፡፡ ዋናው በር ላይ በእርሱ አነሳሽነት የተመሰረተው የሴቶች መብት ላይ የሚሰራው ቢሮ ክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ ወጪያቸውን ለመሸፈን በማሰብ ላሰናዳው የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ምክረ ሀሳብ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ የመጥሪያ ባነር ተሰቅሎ ነበር፡፡ *            ✋ ተፈፀመ፡✋ ታሪኩ በዚሁ ተጠናቋል ሀሳብ አስተያየታችሁን አድርሱን በቅርቡ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ሰላም ቆዩኝ                  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!

Open in Telegram
Views662+108%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#7349Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣9⃣ ቀመር የኢምራን ነገር ተስፋ እያስቆረጣት የመጣ ይመስላል፡፡ ከሱ የጠበቀችውን ክብር እያገኘች አይደለም፡፡ ዶርም ውስጥ ተኝታ በደንብ ስታሰላስለው የነበረው ኢምራንን የምታስገድድበትን አዲስ መንገድ ነበር፡፡ ምንም አይነት አዲስ መንገድ አላገኘችም፡፡ ከዶርም ወጥታ በቀጥታ እየተንደረደረች ወደ ኢምራን ቢሮ ሄደች፡፡ ኢምራን ቢሮው ውስጥ ተቀምጦ እያነበበ ነበር፡፡ ሳታንኳኳ ቢሮውን በርግዳው ገባች፡፡ ኢምራን ሁኔታዋ በጣሙን አስደንግጦታል፡፡ ጠረጴዛውን አልፋ ሄዳ ጭኖቹ ላይ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ደህና ነሽ ግን?›› በግርምት እያየ ጠየቃት፡፡ ‹‹ኢምሩ በአላህ ይሁንብህ አግባኝ! ካንተ ሌላ ጥብቅ የነበርኩ መሆኔን የሚያውቅ የለም! አዲስ ሰው መልመድ አልችልም እባክህ!›› ‹‹ቀመር ይኼ እኮ በልመና የሚሆን አይደለም! ውስጤ ላይ ላንቺ ያለኝ ፍላጎት ተንኗል፡፡ ተረጂኝ!›› ‹‹የመጨረሻ ውሳኔህ ነው?›› ‹‹አዎ አዝናለሁ!›› ‹‹በቃ መጥጠህ ወረወርከኝ? ስሜትህን አረካህብኝ በቃ?›› ቀመር ማልቀስ ጀመረች፡፡ ኢምራን ለቅሶዋ ሰልችቶታል፡፡ ‹‹ለሰራሽው ስራ ሀላፊነቱን ራስሽ ውሰጂ! አስገድደሽኝ እንጂ አስገድጄሽ ያደረግኩት ነገር የለም!›› ቀመር ተፈናጥራ ቢሮውን ለቅቃ ወጣች፡፡ ልቧ ውስጥ የነበረው ተስፋ ሙሉ ለሙሉ ሲተንን ተሰማት፡፡ * ልክ እንደ ፅጌረዳ አበባ …. የፍካቷ ቀን በመጣ ጊዜ አይኖች እንደሚቃብዙባት …. ብዙዎች እንደሚመኟት ….. አዎን ልክ እንደ አበባዋ ፍካት አክሳሚ እጆች እንደሚሽቀዳደሙባት ….. የተቀጠፈች ቀን ከቀናት የዘለለ እድሜ እንደማይኖራት …. እንደምትሟሽሸው እንደሷ እንደአበባዋ ….. ናርዶስም ፈክታ ፣ ሂባም አብረቅርቃ ነበር፡፡ የሂባ ትዳር ጎርባጣ መሆን ሁለቱንም ሲያሳዝናቸው ፣ ማምለጫ ሲያስፈልጋቸው …. ስሜቱን እኩል ሲጋሩት ያኔ የመጀመሪያው ስብራታቸው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ከብዶ የሚከብድ …. እንዲሁ በቃኝ ተብሎ የማይመለጥበት የጭንቀት አጥር ውስጥ ታጭቀዋል፡፡ ዛሬ ማንንም ለመውቀስ የማይመች ሁኔታ ላይ ወድቀዋል፡፡ ‹‹እና ምርመራውን ምን አሰብሽ?›› ሂባ የናርዶስ አልጋ ላይ እግሮቿን በልቅጣ ትራሷን ተደግፋ አልጋው ላይ በፊቷ ተደፍታ የደነዘዘችውን ናርዶስን ጠየቀቻት፡፡ ‹‹አላውቅም›› ‹‹ናርዲዬ እንዲሁ ክፍልሽ ውስጥ ታሽገሽ ሳምንት ሊያልፍ እኮ ነው! ቢያንስ ለመፍትሄ ይረዳናል ተመርመሪ!›› ‹‹ለየቱ መፍትሄ? ቀን ከሌት ክኒን ለመዋጥ? ንገሪኛ ለምኑ ነው የሚረዳን?›› ናርዶስ ለቅሶዋን ቀጠለች፡፡ የናርዶስ ፊት ጠውልጓል፡፡ በለቅሶ ብዛት አይኖቿ አባብጠዋል፡፡ ለቤተሰቦቿ ስራዋን እርግፍ አድርጋ ትታ መኝታ ቤቷ መታሸጓ ትልቅ ዱብዳ ሆኖባቸዋል፡፡ ምግብም በብዙ ልመና ጥቂት ብትወስድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በአንድ ቀን ተገለባብጧል፡፡ ሳቂታዋ ናርዶስ ለቅሶ ቤት ሆናለች፡፡ ሂባ ሁኔታዋ እጅጉን እያሸበራት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለች አቅም አንሷት መሞቷ ነው፡፡ ሂባ ልመናዋን ቀጥላለች፡፡ ‹‹ናርዲዬ አሁን እኮ እሱ ስላለበት ነው ይዞሽ ሊሆን ይችላል ብለን ያሰብነው! ምን ይታወቃል ይዞሽ ባይሆንስ? መመርመሩ ይሻላል ተይ!?›› ‹‹ሂባ ለምን አጉል ተስፋ ትሰጪኛለሽ? በየቀኑ ያለምንም መከላከያ ነበር እኮ ስንፋተግ የነበረው! ……ምናለ ቢያንስ እንኳ ትንሽ ቢያስብልኝ? ደደብ! ….. ራስ ወዳድ ነው!›› ሂባ የናርዶስን ስልክ ከአጠገቧ አንስታ ልታስነሳው ሞከረች፡፡ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ተዘግቶ ነበር፡፡ ቻርጅ ከሰካችው በኋላ ድጋሚ አስነሳችው፡፡ ስልኩ በርቶ ትንሽ እንደቆየ በርካታ መልዕክቶች ገቡ፡፡ የኤርሚያስን መልዕክት ከፈተችው፡፡ ‹‹ለተፈጠረው ነገር አዝናለሁ፡፡ እኔም ለራሴ ማሰብ ስለነበረብኝ ነው፡፡ መከላከያ ለምን እንድንጠቀም አላደረግክም ላልሽኝ ….. ሎሊፖፕ ከነልጣጩ መምጠጥ እንደማለት ነው፡፡ ስሜት አይሰጠኝም! አዝናለሁ!›› ይላል፡፡ ሂባ ማንበብ የፈለገችውን ስላገኘች ስልኩን መልሳ አጠፋችው፡፡ ‹‹እና ናርዲዬ እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምትቀጥይው?›› ‹‹እስከምሞት ነዋ! ከዚህ የአታላዮች አለም እስክገላገል!›› ብላ ወደ ሂባ ፊቷን መለሰችና ንግግሯን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሂባዬ ታውቂያለሽ አይደል? እኔ ያላንቺ … አንቺ ያለኔ ደካማ እንደሆንን? …. እ ሂቡ ታውቂያለሽ አይደል ከልጅነታችን ጀምሮ በሁሉም የህይወታችን ጉዳዮች ላይ በጋራ ተማክረን ስንወስን በራሳችን መወሰን እንዳልለመድን? ….. አየሽ ያኔ ሳይረፍድ በፊት ስለ ኤርሚያስ ላማክርሽ ስፈልግ አንቺ በዚያድ ምክንያት ጊዜ አልነበረሽም፡፡ ስንገናኝም ስለ ዚያድ በደል እንጂ ስለ አዲስ ፍቅር ለማውራት ሁኔታዎች ምቹ አልነበሩም፡፡ ያኔ አንቺን አማክሬሽ ቢሆን ኖሮ እንዲህ አልሆንም ነበር፡፡ …. ሂቡዬ ያኔ ብነግርሽ ኖሮ…›› ለቅሶዋ በርትቶ ከንግግሯ ገታት፡፡   ሂባ በናርዶስ ተስፋ መቁረጥ ውስጧ ተረበሸ፡፡ ዳግም ወደ ተወችው መነፋረቋ ተመለሰች፡፡ * በእንባ እና በጭንቅ እንደተሞሉ በርካታ ቀናት ነጎዱ …. ሂባ ለእርግዝና ክትትሏ ወደ ህክምና ተቋም በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ ናርዶስን እንድትመረመር ብትለምናትም ልትሰማት አልቻለችም፡፡ ምርመራ የሚባለው ቃል እጅጉን ቀፏታል፡፡ ስራዋን ትታ ቤቷ ውስጥ ከታሸገች ወር አለፈ፡፡ ቤተሰቦቿ መጨነቃቸው ሲበረታ ሂባ ‹‹ፍቅረኛዋ ከድቷት ነው›› በሚል ምክንያት ልባቸውን ለማሳረፍ ትሞክራለች፡፡ አሁን አሁን ግን እነሱም አልመስል እያላቸው ነው፡፡ የሚያዚያ ወር ገብቶ ጥቂት ቀናት ሄደዋል፡፡ ሂባ እና ናርዶስ የሂባ መኝታ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ስለኢምራን እያወሩ ነበር፡፡ ናርዶስ ስልኳን አንስታ ኢምራን ጋር ደወለችለት፡፡ ‹‹ምን እያደረግሽ ነው?›› ሂባ ደንግጣለች፡፡ ‹‹አታካብጂ ባክሽ የምን መንቀጥቀጥ ነው!›› ስልኩ ተነሳ፡፡ ኢምራን የቀድሞ ጓደኛውን ስልክ ከረዥም ጊዜ በኋላ ሲያይ ተገርሟል፡፡ ‹‹ናርዲ ቀውሷ!››  ‹‹ትሰማለህ ኢምራን! ሂባ ከባሏ ጋር ተፋታለች፡፡ ከአንድ ልጇ ጋር ተቀብለህ ልታገባት ከፈለግክ ፈቃደኛ ስለሆነች ደውልላት! ቻው!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችው፡፡ ‹‹ናርዲ ምንድነው ያደረግሽው?›› ‹‹በቃ ከፈለገሽ ይደውላል፡፡ አለቀ!›› እየተጨዋወቱ ብዙም ሳይቆይ ሂባ ማቃሰት ጀመረች፡፡ ምጧ መጥቶ ነበር፡፡ ናርዶስ ሮጥ ብላ ወ/ሮ ዘምዘምን ጠራቻቸው፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ፡፡ እናቷ እንደደገፏት ናርዶስ የምታውቀው ባለላዳ ጋር ደውላ ይዘዋት ወደ ጤና ጣቢያ ሄዱ፡፡ ጤና ጣቢያ ደርሰው ሂባን ለነርሶቹ ካስረከቡ በኋላ ውጪ ላይ ቆመው እየተቁነጠነጡ የመውለዷን ብስራት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሂባ አባት ስለተደወለላቸው ከስራ ቦታቸው መጡ፡፡ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው የሂባን ልጅ በሰላም ወደዚህ አለም መቀላቀል ነው፡፡ ናርዶስ በሩ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀከል ተነጥላ ወደ ፎቅ ወጣች፡፡ የላይኛው ፎቅ ከታች ወደ ላይ እስከጣራው ድረስ ደረጃው ዙሪያውን ክፍት ነው፡፡ ታች ሆና የላይኛው ፎቅ ላይ ያየችው ነገር አለ፡፡ ራመድ ….. ራመድ ….  አንደኛ ፎቅ ….. ሁለተኛ ፎቅ ….. ሶስተኛ ፎቅ …..

Open in Telegram
Views407+28%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#7348Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣8⃣ ሜላት ስልኳ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ ‹‹ባሌ ጋ ልደውልለት አንዴ!›› አለችና ስልኳን አንስታ እየደወለች ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ናርዶስ ይኼን ጭንቅ ለማን እንደምታዋየው ግራ ገብቷት ስታሰላስል ብትቆይም ከሂባ ውጪ የመጣላት ሰው አልነበረም፡፡ እንባዋን ለመጥረግ እየሞከረች ሂባ ጋር ለመደወል ስልኳን ስታነሳ ኤርሚያስ ደወለ፡፡ ውስጧ እልህ እየተንቀለቀለ ስልኩን አነሳችው፡፡ ‹‹ሄሎ የኔ ማር ሰላም ዋልሽልኝ?›› ኤርሚያስ እንደሁሌው እየተቅለሰለሰ ንግግሩን ጀመረ፡፡ ‹‹ምን በድዬህ ነው ግን ኤርሚ? እንዴት ይኼን ያህል ራስ ወዳድ ትሆናለህ? ትንሽ እንኳ አላሳዝንህም?›› ተነፋረቀች፡፡ ‹‹ናርዲዬ ምንድነው የምትዪው? የምን ራስ ወዳድነት ነው? ምን ሆንሽብኝ?›› ‹‹ቢያንስ እንኳ ምናለ በኮንዶም እንድንወጣ ብታደረግ? እህት ባይኖርህ እንኳ እናት የለህም?›› ‹‹ናርዲ እባክሽ ግራ አታጋቢኝ! ምንድነው አረገዝሽ እንዴ?›› ‹‹እሱማ በምን እድሌ! ስማ! ዛሬ የሄድክበት ሀኪም ቤት እኔም ክትትል ስጀምር እንገናኝ ይሆናል! አንተ ግን ሰብዓዊነት የማይሰማህ …… ደደብ ነህ እሺ!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት፡፡ ትንሽ ካነባች በኋላ ሂባ ጋር ልትደውል እንደነበር ትዝ አላት፡፡ ሂባ ጋር ስትደውል ሜላት ወደ መቀመጫዋ እየተመለሰች ነበር፡፡ ሜላት ወንበሯ ላይ እንደተመቻቸች ስልኳን ጆሮዋ ላይ የለጠፈችውን ናርዶስን እየተመለከተች ‹‹ናርዲዬ ይኼ ማለት እኮ አንቺን ይዞሻል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ አይታወቅም እኮ የፈጣሪ ነገር ላይዝሽ ይችላል ብዙ አትረበሺ!›› አለች፡፡ ናርዶስ የደወለችው ስልክ ተነስቶ ስለነበር ምላሽ ሳትሰጣት እያለቀሰች ‹‹ሂባዬ …. ›› አለች፡፡ ‹‹ወዬ ናርዲዬ ምንድነው ድምፅሽ? ምን ሆነሻል?›› ‹‹ጉድ ሆንኩልሽ ሂባዬ! ጉድ ሆንኩልሽ!›› ‹‹የት ነሽ? ምን ተፈጠረ?›› ድንጋጤዋ ንግግሯን የመርበትበት ወዘና አልብሶታል፡፡ ያለችበትን ቦታ ነገረቻት፡፡ የአብሮ አደግ ጓደኛዋ ጭንቅ ላይ መሆን ሆዷ በጣሙን መግፋቱንና በታክሲ ለመሳፈር በጣሙን የሚከብዳት መሆኑን አስረስቷታል፡፡ ከቤቷ ወጥታ ታክሲ ጋር እስከምትደርስ የሆዷን መግፋት ረስታው ነበር፡፡ ሰዓቱ መምሸቱ ደግሞ ታክሲ እንደልብ እንደማታገኝ ሲያረዳት ኮንትራት ታክሲ አናገረች፡፡ የናርዶስ መስሪያ ቤት አቅራቢያ ስትደርስ ደወለችላት፡፡ ከካፌው በር ላይ ወጥታ ተቀበለቻት፡፡ ሜላት ናርዶስን ለሂባ አስረክባ በተደጋጋሚ ሲደውል ወደነበረው ባሏ ሄደች፡፡ ናርዶስ ሂባን ስታይ ለቅሶዋ ቅጥ አጣ፡፡ ክፉኛ አነባች፡፡ ከልብ ለማንባት ምቹ መደገፊያ ያሻል የሚባለው እውነት ለመሆኑ ምስክር ይመስላሉ፡፡ ሂባ ምን እንደሆነች እንኳ ሳታውቅ ደረቷ ላይ አስደግፋት አብራት ታለቅሳለች፡፡ በቃ ዝም ብሎ ማልቀስ! ዝም ብሎ ማንባት!  ‹‹የኔ ቆንጆ ምንድነው የሆንሽብኝ?›› ሂባ ፊቷ በእንባ እንደታጠበ የናርዶስን እንባ ለመጥረግ እየሞከረች ጠየቀቻት፡፡ ከንፈሮቿ እየተንቀጠቀጡ ፣ ሳግ ባጎረበጠው ድምፅ ‹‹ኤርሚ ኤች አይ ቪ አለበት›› አለች፡፡ ሂባ የሰማችውን ለማመን አልቻለችም፡፡ በቀጥታ አዕምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ምስል የናርዶስ ሞት ነው፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ከደነዘዘች በኋላ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ለቅሶዋ ናርዶስን ይበልጥ እያስለቀሳት ነው፡፡ አፅናኝ የለም፡፡ ሁለቱም ህመሙን እኩል የቀመሱት ይመስላሉ፡፡ ያነባሉ …. እንባ ግን አይፈውስም፡፡ . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣9⃣

Open in Telegram
Views315−1%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#7347Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣7⃣ ናርዶስ ከቢሮዋ ወጥታ በፍጥነት ደረጃውን ስትወርድ የኤርሚያስ ባልደረባ ተከተለቻት፡፡ ባለፈው ሰፈር ውስጥ አብረው አግኝታቸው ነበር፡፡ ናርዶስ ዛሬ ኤርሚያስ ለስብሰባ ወደ ሰበታ ሄጃለሁ ስላላት ከነጋ አላገኘችውም፡፡ እድሜዋ ከሀያ አራት የማይበልጠው አጠር ያለችው የኤርሚያስ ባልደረባ እየተፍለቀለቀች ቀረበቻት፡፡ ‹‹hey ናርዲ እንዴት ነሽ?›› ‹‹አለሁልሽ ሜላትዬ ሁሉ አማን ነው!›› ‹‹ኤርሚ ዛሬ የለም ብቻሽን ነሽ!›› ‹‹አዎ ስብሰባ ነው አይደል? እናንተም ዛሬ ብቻችሁን ዋላችሁ!›› ‹‹ስብሰባ? የምን ስብሰባ?›› ‹‹የቀረው ስብሰባ ሄዶ አይደለም እንዴ?›› ‹‹ምናልባት አዲስ ነገር መጥቶ በዛው ከላኩት አላውቅም እንጂ ዛሬ የቀረው ለህክምና አስፈቅዶ ነው!››  ‹‹የምን ህክምና ነው? አሞታል እንዴ?›› ‹‹ ናርዲ ግር እያልሽኝ ነው! ይቅርታና ፍቅረኛው ነሽ አይደል?›› ‹‹አዎ እንደዛ ነገር ነኝ፡፡ ምነው?›› ‹‹ምንም አይነት የሚከታተለው ህክምና እንዳለ አታውቂም?›› ‹‹እኔ አንድም ቀን አሞት አይቼው አላውቅም!›› ሜላት ነገሩ ግራ ስለገባት ረጋ ብላ ልታወራት ፈለገች፡፡ ደረጃውን ወርደው ወደ ውጪ ከወጡ በኋላ ወደ ቀኝ ታጥፈው ትንሽ እንደተራመዱ ያገኟት ትንሽዬ ካፌ ገብተው ተቀመጡ፡፡ አስተናጋጁ ከመቅፅበት ከፊታቸው መጥቶ ተገተረ፡፡ ማስተናገድ ናፍቆት የነበረ ይመስላል፡፡ ትኩስ ነገር ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ ‹‹ናርዲዬ ከኤርሚ ጋር ምን ያህል ጊዜ ሆናችኋል?›› ‹‹በቃ እዚህ ከተቀጠርኩ በኋላ ነው እንደ ጓደኛ ቀረበኝ ቀስ በቀስ ወደዛ ቀየርነው፡፡›› ‹‹እኔ እኮ ከዛም በፊት የምትተዋወቁ ነበር የሚመስለኝ! እንደውም በሱ ጥረት ነው የተቀጠረችው ምናምን ይባል ነበር እኮ!›› ‹‹አጎቴ ነው ያስቀጠረኝ! ኤርሚያስን ከመቀጠሬ በፊት እንኳን ልግባባው አይቼውም አላውቅም!›› ሜላት አቀረቀረች፡፡ እንባ አይኗን ታገለው፡፡ በውሸት ፈገግታ እንባዋን ለማባረር እየሞከረች ቀና አለች፡፡ ‹‹መስሪያ ቤት ውስጥ ስለናንተ የሚወራውን ሰምተሽ አታውቂም?›› ‹‹ስለኛ ይወራል?›› ናርዶስ ቢሮ ውስጥ ያደረጉት ነገር የታወቀ መስሏት ልቧ በፍርሀት ራደ፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚወራው!›› ‹‹ምን ተብሎ?›› ‹‹በብዛት የሚወራው ከድሮም እንደምትተዋወቁ ፣ በጣም ራሳችሁን ስለምትጠብቁ እንደማያስታውቅባችሁ ምናምን ነው፡፡›› ‹‹ምኑ ነው የማያስታውቅብን? ፍቅረኛ መሆናችን?›› ሜላት ራሷን ለማደፋፈር ሞከረችና ቀጠለች፡፡ ‹‹የእድሜ ማራዘሚያ ትወስጂያለሽ አይደል?›› ‹‹ፈጣሪ ራሱ ያርዝምልኝ እንጂ እኔ ምን እወስዳለሁ?›› ካለች በኋላ ሳቋን ለቀቀችው፡፡ ‹‹ግልፅ አድርጌ ልጠይቅሽ! አንቺ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ካወቅሽ ምን ያህል ጊዜ ነው?›› ‹‹የምን ቫይረስ?›› ናርዶስ ሳታስበው ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡ ‹‹አረ ቁጭ በይ ተረጋግተን እናውራ! እኔም ይሄን ስለገመትኩ እኮ ነው ላወራሽ የፈለግኩት!›› ናርዶስ በዝግታ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ይኸውልሽ ናርዶስ ታውቂ ይሆን አይሆን ለማረጋገጥ ነበር ዙሪያ ጥምጥም እየሄድኩ ጥያቄዎችን ስጠይቅሽ የነበረው፡፡ አሁን እንደገባኝ ከሆነ ምንም የምታውቂው ነገር የለም፡፡ በአጭሩ ልልሽ የፈለግኩት ኤርሚያስ HIV career ነው፡፡ ይኼን ሳታውቂ ከሆነ የገባሽበት ከአሁኑ መንገድሽን እንድታስተካክዪ ነው፡፡ ያው ግንኙነታችሁ የአጭር ጊዜ ስለሆነ ሌላ ነገር ውስጥ የገባችሁ አይመስለኝም፡፡›› ‹‹ቆይ ግን አንቺ እንዴት አወቅሽ? ማለቴ እሱ እንደዛ እንደሆነ!›› ‹‹ይኸውልሽ እሱ እዚህ መስሪያ ቤት ወጣት ሆና የገባች ሴት አንድም አታልፈውም ነበር፡፡ ሲበዛ ሴሰኛ ነገር ነው፡፡ እኔም ስቀጠር እንደዚሁ ሊያሰምጠኝ ሞክሮ ነበር፡፡ ግን እኔ የዛኔም ቀለበት አስሬ ለማግባት የቀረኝ ጥቂት ቀን ስለነበር ፊት አልሰጠሁትም፡፡ እሱም ቀለበት እንዳሰርኩ ሲያውቅ ተፋታኝ! እና የገባውን ሰራተኛ ሁሉ በአጉል ጀብደኝነት ካልቀመስኩ ሲል ውጪም ጠጥቶ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ሲልከሰከስ ነው የያዘው! አንዷን ከኔ በፊት የገባች ፋይናንስ ክፍል የምትሰራ ልጅ እንደዚሁ አሰማምጦ ቤቱ ወስዷት ቤቱ ውስጥ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ምናምን አየች፡፡ ከዛ ደግሞ ስትበረብር የኤች አይ ቪ ህሙማን ማህበር የአባልነት መታወቂያውን አገኘች፡፡ ከዛ መታወቂያውን ፎቶ አነሳችና ለግቢው ሰራተኞች ለምታውቃቸው ላከችላቸው፡፡ እያለ እያለ ሙሉ ግቢው አወቀ፡፡ እሱም ከዛ በኋላ በግልጽ የኤች አይ ቪ ቀን እዚህ ግቢ ሲከበር ምናምን ያስተምራል ነገር! አሁን አሁን እየቆየ ሲመጣ ሰዉ ተላመደውና ተረሳ እንጂ የገባ ሰራተኛ ቀድሞ የሚነገረው ይኼ ነበር፡፡ ያንቺን ግን ገና እንደገባሽ ፍቅረኛዬን አስቀጠርኳት ብሎ ቀድሞ ነበር ያስወራው፡፡ ደግሞም ትመስሉ ነበር፡፡››  ናርዶስ ሰማይ ከአናቷ ላይ የተደፋባት ያህል አዘመመች፡፡ ዝም ፣ ጭጭ! አስር ደቂቃ ፣ አስራ አምስት ደቂቃ ፣ ሀያ ደቂቃ! ዝም እንዳሉ ነጎደ፡፡ በእነዚህ ደቂቃዎች ላለፉት ስድስት ወራት የተካሄደውን ሁሉ እየተመለከተችው ነበር፡፡ ሜላት ትዕግስቷ ሲያልቅ ዝምታውን ለመስበር ሞከረች፡፡ ወንበሯን ወደ ናርዶስ በደንብ አስጠግታ አይኖቿን እያየች ማውራት ጀመረች፡፡ ‹‹ናርዲዬ አብራችሁ ተኝታችኋል እንዴ?›› ‹‹በጣም ብዙ ጊዜ!›› ናርዶስ ፊቷ ፍም መስሏል፡፡ እንባ እንኳን ማፍሰስ አልቻለችም፡፡ ‹‹በጣም ቸኮልሽ ናርዲዬ! Whatever ግን በኮንዶም ነበር የምትወጡት አይደል?›› ‹‹አይደለም ሁሉንም ቀን በባዶ ነበር ያደረግነው!›› አሁን ፊቷ በእንባ መራስ ሰውነቷ መንዘፍዘፍ ጀምሯል፡፡ ሜላትም አቅፋት ማንባት ጀመረች፡፡ ‹‹አንቺ የተማርሽ አይደለሽ እንዴ ናርዲዬ እንዴት ሳትመረመሩ ያለኮንዶም አብረሽው ትወጪያለሽ?›› ‹‹እኔ  …… (ተንሰቀሰቀች) ….. HIV? ….  የጠፋ ነበር የሚመስለኝ! አንድም ቀን ትዝ ብሎኝ አያውቅም!›› ‹‹ከሚዲያ ላይ ጠፋ እንጂ እኮ ሀገራችን ውስጥ ወረርሽኝ በሚመስል መልኩ እየተስፋፋ ነው፡፡ ለማንኛውም ቶሎ ብትመረመሪ ነው የሚሻለው!›› ‹‹እና ምን በድዬው ነው እኔን ማስያዝ የፈለገው? እንዴት ያለ ራስወዳድነት ነው ይኼ?›› ረዥም ሰዓት ናርዶስ እየተንሰቀሰቀች ሜላት ስታባብላት ከቆየች በኋላ ናርዶስ አልቅሳ ሲደክማት ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡ ‹‹እናንተ ታዲያ ለምን እስካሁን አልነገራችሁኝም?›› ‹‹አንቺም እንዳለብሽ ነው የነገረን ደግሞ ገና መቀጠርሽን ሳናውቅ ማውራት ስለጀመረ አመንነው፡፡ እንጂ እንዲሁ ከገበያ ጥናት ክፍል ተነስቶ ኢንጅነሪንግ ሴክሽን ድረስ የሄደ አልመሰለንም ነበር፡፡›› ‹‹እና አሁን ምንድነው የሚሻለኝ?›› እንባዋን በመዳፏ በጠረገችበት ቅፅበት ተመልሶ ይፈስሳል፡፡ ‹‹መተኛት ከጀመራችሁ ሶስት ወር ይሆናል?›› ናርዶስ ጥቂት እንደማሰብ ካለች በኋላ ‹‹ይሆናል!›› አለች፡፡ ‹‹ይኼን ያህል ጊዜ ከሆነው ብትመረመሪ ጥሩ ነው፡፡ ከጅምሩ የሆነ እርምጃ መውሰድ ትችያለሽ!››

Open in Telegram
Views350+10%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7346Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣6⃣ ‹‹ከዚህ በፊት ለነበረው እኔ ተጠያቂ ልሆን እችላለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ላለው ግን ተጠያቂው አንተ ነህ! ህጋዊ እንድናደርገው እየለመንኩህ ነው፡፡›› ‹‹ታውቂያለሽ ….. ድሮ እንደ ትዳር የሚያጓጓኝ ነገር አልነበረም፡፡ አሁን ግን ያስፈራኛል፡፡ ደግሞ …….. መሰረቱ ወንጀል የሆነ ትዳር እንዲኖረኝ አልፈልግም፡፡›› ‹‹ገብቶኛል የትም መሄጃ እንደሌለኝ ስለምታውቅ ነው እንደዚህ የምትንጠባረርብኝ! …………. አዎ አጥፍቻለሁ አልኩኝ እኮ! …… የኔ ላደርግህ ጓጉቼ መሄድ ባልነበረብኝ መንገድ ሄጃለሁ! ለሱይቅርታ! ግን አሁን የተሻለ ነገር እንገንባ! ተረዳኝ! አፈቅርሀለሁ!›› ‹‹ብረዳሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም!›› ‹‹ማለት?›› ከእቅፉ ተመንጭቃ ወጣችና አፈጠጠችበት፡፡ ‹‹ማለት ማለት?›› ‹‹አታገባኝም?›› ‹‹ውስጤ አልተረጋጋም በዚህ ሰዓት ምንም ልልሽ አልችልም!›› ቀመር እንባዋ ፊቷ ላይ እየተንዠቀዠቀ ቀጠለች፡፡ ‹‹ወንድ ሁሉ አንድ ነው ሲባል ውሸት ይመስለኝ ነበር፡፡ አንተም ከሌሎቹ በምንም አትሻልም፡፡ ስሜትህን ካረካህብኝ በኋላ ልትወረውረኝ ነው ፍላጎትህ!›› ‹‹እኔ ከጅምሩ ስሜቴን ላረካ አልቀረብኩሽም! ከገባሽ አንቺው ነሽ የደፈርሽኝ! ማልቀስ ደግሞ መፍትሄ አይሆንም!›› ‹‹በጣም ጥሩ ስህተታችንን እንድናርም ፈቃደኛ ካልሆንክ ሌላ ስህተት እንቀጥላለን! አየህ አይደል በፍቅር እጅ አትሰጥም ሀይል ብቻ ነው የሚገዛህ! እኔማ የፍቅር ሰው ትመስለኝ ነበር፡፡›› ‹‹እሱን ለመመስከር ካንቺ ይልቅ ሂባ ትሻላለች! ሳፈቅር የምታውቀኝ እሷ ናት!›› የተፈጠረውን የመካረር ስሜት ለማብረድ ፈለገች፡፡ ተመልሳ ወደ እቅፉ ገባች፡፡ ‹‹ስለማፈቅርህ እኮ ነው! እሺ በለኝ እና ደስተኛ ሆነን እንኑር!›› ‹‹ቀመር እኔ አብረን እንድንተኛ እንኳ አልፈልግም እኮ! ግን አንቺ ስትመጪ እምቢ ማለት አይሆንልኝም! ራሴን እንደዚህ ያለ ቆሻሻ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም! ለዚህ ደግሞ ምክንያቷ አንቺ ነሽ! ልንገርሽ አይደል እንደውም ከዚህ በኋላ ቤቴ እንድትመጪ አልፈልግም! ከዚህ በላይ መቆሸሽ አልፈልግም በቃኝ! በቃኝ!›› ለመጀመሪያ ጊዜ ስትስመውም ሆነ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ስትገፋፋው ወዲያው ተፀፅቶ ያገባኛል የሚል እሳቤ ነበራት፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ እየሆነ ፣ ኢምራን ትዳርን እየሸሸ ፣ ለሷ የነበረው መውደድ እንኳ ተሸርሽሮ ቤቴ ድርሽ እንዳትይ ማለት ጀመረ፡፡ በፈጣሪዋ ዘንድ ድንበር አልፋ ልታገኝ ያሰበችው የደስታ ህይወት ገና ከጅምሩ እየራቃት ነው፡፡ እቅፉ ውስጥ እንዳለች ከዚህ ቀደም የሰማችው የነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ንግግር ትዝ አላት፡፡ ‹‹አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው ለጅብሪል ጅብሪል ሆይ እኔ ይኼን ባሪያዬን ወድጄዋለሁ አንተም ውደደው ይለዋል፡፡ ጅብሪል ደግሞ ለመልዓክቱ ጌታችሁ ይኼን ባሪያ ወዶታል እናንተም ውደዱት ይላል፡፡ ከዚያም አላህ በምድር ያሉ ሁሉ እንዲወዱት ያደርጋል፡፡ ሲጠላም በተመሳሳዩ ነው›› እናም ምናልባት በነበረችበት ጌታዋን የማስደሰትና ወንጀልን የመራቅ መንገድ ላይ ቀጥላ ቢሆን ለሷ ያለውን ጊዜው ሲደርስ ታገኝ ነበር፡፡ ጌታዋን አስከፍታ ከኢምራን ልታገኝ የፈለገችው ፍቅር በጌታዋ ይሁንታን ያገኘ አይመስልም! ‹‹እሺ ጥሩ …. (እንባዋ አይኗን እየሞላ ይፈሳል) … እስኪ ኢምሩ ንገረኝ ከኔ ምኔን ነው የጠላኸው?›› ውስጧ ላይ የርካሽነት ንፋስ ይነፍሳል፡፡ ‹‹አንቺን በአንቺነትሽ አልጠላሽም፡፡ አንቺን የምጠላሽ የወንጀለኛው እኔነቴ አካል በመሆንሽ ብቻ ነው፡፡›› ‹‹አተርፍ ባይ አጉዳይ ነዋ የሆንኩት!›› እንባዋ ፊቷን ማርጠቡን ቀጠለ፡፡ ድሮ ገና ፊቷ ሲቀየር እንኳ ይደነግጥ ነበር፡፡ አሁን ግን እንባዋ ሲንዠቀዠቅ እንኳ ግድ አይሰጠው ጀምሯል፡፡ . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣7⃣

Open in Telegram
Views331+4%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#7345Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣5⃣ ናርዶስ የወሲብ ፊልም የማየት ሱሷን ለመግታት እጅጉን ከራሷ ጋር ትግል እየገጠመች ነው፡፡ ሂባ ፊልም በፍላሽ የሚጭኑ ቤቶች እየሄደች የሆሊዉድ ኮሜዲ ፊልሞችን እያስጫነች ታመጣላታለች፡፡ ናርዶስ ብትጨክን ብትጨክን በሳቅ አትጨክንምና የወሲብ ቪዲዮ በምታይባቸው ጊዜዎች ኮሜዲ ፊልሞችን ማየት ጀምራለች፡፡ ግን እንዲሁ በአንዴ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ከብዷታል፡፡ ሂባ ሁሉንም ነገር ችላ ብላ ናርዶስን መልሶ በመስራቱ ጉዳይ ላይ ትኩረቷን አድርጋለች፡፡ የናርዶስ ስልክ እና ላፕቶፕ ላይ የነበሩትን የወሲብ ፊልሞች ሂባ ሙሉ ለሙሉ ስላጠፋቻቸውና በየቀኑም ስልኳን ስለምትፈትሽባት ማየት ብትፈልግ እንኳ ቢሮ ስትሄድ በኤርሚያስ ስልክ የማየት እድል ብቻ ነው ያላት፡፡ እጅጉን ከብዶ የከበዳት ከኤርሚያስ ጋር ያላትን የአልጋ ግንኙነት የመቋጨቱ ጉዳይ ነው፡፡ ልትጠላው አልቻለችም፡፡ ወንዳ ወንድ ቁመናውን ….. ያስለመዳትን አጓጉል ነገር … ብቻ በቃኸኝ ለማለት ብትፈልግም አልቻለችም፡፡ ቢሮ እየመጣ ከአንገት በላይ ሰርቷት ይሄዳል፡፡ በእርግጥ እንደድሮው ፊልሞችን አያመጣላትም፡፡ ምክንያቱም ፊልሞቹ እንዲያደርሷት የፈለገበት ቦታ ደርሳለታለች፡፡ እንደቀድሞው በየቀኑ ባይሆንም በሳምንት ሁለት ቀን እሱ ቤት ሄዳ የለመዱትን ይፈፅማሉ፡፡ ለሂባ ግን እሱ ቤት እንደምትሄድ አትነግራትም፡፡ ዛሬ ከስራ እንደወጣች ከኤርሚያስ ጋር ተያይዘው እሱ ቤት ሄዱ፡፡ ሰዓቱ መሸት ወደማለቱ እየተጠጋ ነበር፡፡ መንፈራገጡ ሲያበቃ አልጋው ላይ እንደተጋደሙ ማውራታቸውን ቀጠሉ፡፡ እሷ በጊዜ መሄድ አለባት፡፡ ‹‹ስማ postpill አላለቀም አይደል?›› ‹‹እስኪ እሱ መሳቢያ ውስጥ ፈልጊ!›› ማርገዝን እጅጉን ትፈራዋለች፡፡ አረገዘች ማለት ጉዷ ሁሉ ተዘረገፈ ማለት ነው፡፡ የአልጋውን ኮመዲኖ ስትከፍተው ብዙ አይነት ክኒኖች ተመለከተች፡፡ ጫፍ ላይ pospill ስላገኘች ኮመዲኖውን ዘጋችና የመኝታ ክፍሉ በር አካባቢ መሬት ላይ ከተቀመጡት የታሸጉ ውሀዎች አንዱን አንስታ ክኒኑን ዋጠች፡፡ ‹‹አንተም የወሊድ መቆጣጠሪያ ትወስዳለህ እንዴ? ምንድነው ይሄ ሁሉ ክኒን?›› ‹‹ባክሽ የቆዩ ናቸው፡፡ ዛሬ ለምን እዚህ አታድሪም?›› ‹‹ያምሀል እንዴ! አሁን ራሱ ላመሸሁበት ሰበብ መፈለግ አለብኝ!›› ‹‹አንቺ ደግሞ ስታካብጂ ነው እንጂ አሁን እኮ ብዙ አልቆየሽም፡፡ ሰበብ የሚያስፈልገው አይነት አይደለም፡፡›› ልብሷን ለባብሳ ስትጨርስ ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዱን ጨርሰው ሜክሲኮ ጋር ሲደርሱ አንድ የስራ ባልደረባቸውን አገኙ፡፡ የኤርሚያስ ቢሮ ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ ከልጅቷ ጋር ሰላም ተባብለው ከተሰነባበቱ በኋላ የፒያሳ ታክሲ ተሰለፉ፡፡ ሰልፉ ረዥም ነበር፡፡ ግን ማለቁ አይቀርም፡፡ ህይወትም እንደዛው ናት፡፡ ረዥም ብትመስልም ማለቋ አይቀርም፡፡ * ሂባ የናርዶስ ነገር ራስምታት እየሆነባት ነው፡፡ ቀን ከሌት የቀድሞዋ ናርዶስን ለመገንባት የሚያስችሏትን መንገዶች ታሰላስላለች፡፡ ናርዶስ አብዛኛውን ሰዓቷን መስሪያ ቤት ማሳለፏ ደግሞ ለሂባ ትልቅ እንቅፋት እየሆነባት ነው፡፡ በሂባ እጅ ትነፃና እዛ ሄዳ በኤርሚያስ እጅ ትጨቀያለች፡፡ ሂባ ቤት ተቀምጣ ቴሌቪዥን እያየች ነበር፡፡ ከእነርሱ ቤት ፊት ለፊት ያለው ቤት የሚኖሩት ጎረቤታቸው ወ/ሮ ገነት መጡ፡፡ የሂባን ለመፋታት መንገድ ላይ መሆን ከራሷ እና ከናርዶስ ቤተሰቦች በቀር የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ገና እንደገቡ ሰላምታ እንኳ ሳያስቀድሙ ‹‹ወይኔ ሂባዬ ለካ ከባልሽ ጋር ተጣልተሽ ነው የመጣሽው! እኔ እኮ ስለደረስሽ ልትታረሺ መስሎኝ ነበር፡፡›› አሉ፡፡ ሂባ ከየት እንደሰሙ ግራ ገባት፡፡  ‹‹ማነው እንደዛ ያለው?›› ‹‹ውይ አሁንማ ሁሉም አውቆ የለ እንዴ! አንቺ ግን ምነው ከኛ ይደበቃል ይኼ? እኔስ ብሆን እናትሽ አይደለሁ!›› ‹‹ይኼ እኮ ደስ የሚል ነገር አይደለም! ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ማወቅዎ አይቀርም ነበር፡፡›› ‹‹ይሁን እስኪ! እና መች ነው የፍርድ ቤት ቀጠሮው? ያለውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ነው አይደል የሚያካፍሏችሁ?›› ‹‹ኧረ ገንዬ የምን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ፣ የምን ንብረት ነው?›› ‹‹እንዴ የሰፈሩ ሴት ሁሉ ቤተሰቦቿን ልታስከብራቸው ነው ስላረገዘች የመኪና መሸጫው ለሷ ሊፈረድ ይችላል እያለ አይደል እንዴ?›› ‹‹እንደሱ ብሎ ነገር የለም፡፡ ወሬ ነው፡፡›› ሂባ ውስጧ እያረረ ነው፡፡ ‹‹አዪ ተይው ተይው! ገና ለገና የሆነ ገንዘብ ትጠይቀኛለች ብለሽ ነው አይደል? ድሮም ሰው እኮ ገንዘብ ሲያገኝ መቀየሩ አዲስ አይደለም!›› ወ/ሮ ገነት ከተቀመጡበት ተነስተው ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡ ሂባ የወሬው መናፈስ ግርም እያላት ትኩረቷን እየተመለከተችው ወደነበረው የቴሌቪዥን ዝግጅት ለመመለስ ሞከረች ግን አልቻለችም፡፡ ገንዘቡን ፈልጋ ተፋታች ይሉኛል የሚለው ስጋት ውስጧን ይረብሸው ነበር፡፡ ሰው የራሱን ህይወት ትቶ በሌሎች ሰዎች ህይወት ዙሪያ የማያውቀውን ሲቀባጥር ስትመለከት ቀፈፋት፡፡ * ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሁለተኛው መንፈቅ አመት የትምህርት መርሀ ግብር ተጀምሯል፡፡ ቀመር ቀደም ብላ ለኢምራን ገብታው በነበረው ቃል መሰረት civil engeenering ከመግባት ተቆጥባ biomedical engeeneringን መርጣ ተመድባለች፡፡ የየካቲት ወር ተጠናቆ የመጋቢት ወር ስለተጋመሰ ትምህርቱም በአግባቡ እየተሰጠ ነው፡፡ ቀመር እና ኢምራን ሳያስቡት የወደቁበት የስሜት አረር በዘላቂነት እየተንቀለቀለ ነው፡፡ አብረው ከተኙ በኋላ በጣሙን ተፀፅቶ ነበር፡፡ እሷም ያጠፋችው ጥፋት አሟታል፡፡ ግን ሁለቱም ሲገናኙ ፀፀታቸውን ረስተው ድጋሚ ስሜታቸውን ይከተላሉ፡፡ ኢምራን የማያውቀውን መጥፎ ነገር ለምዶ ያቅበጠብጠዋል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ፀፀቱ መፈጠሩን እስኪጠላ ድረስ ያይልበታል፡፡ ከመጀመሪያዋ መንፈራገጥ ወዲያ ቀመር አብዛኛውን ቀን እሱ ጋር ማደር ጀምራለች፡፡ ዛሬም ምሽቱን አብረው ናቸው፡፡ ትግሉ በሁለቱም አሸናፊነት ሲጠናቀቅ እቅፉ ውስጥ እንዳለች አንሾካሾከች፡፡ ‹‹ኢምሩዬ!›› ‹‹ወዬ›› ‹‹ትወደኛለህ?›› ‹‹እኔንጃ! ይመስለኛል!›› ‹‹ጉረኛ እኮ ነህ!›› ‹‹አይመስለኝም!›› ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው? ለምን ኒካህ አናስርም?›› ‹‹ለምንድነው የምናስረው?›› ‹‹እንዴ! እኔ የማውቀው ኢምራን እንደዚህ አይልም! አሁን የምንሰራው እኮ ወንጀል ሆኖ ይመዘገብብናል፡፡ ሚስትህ ስሆን ግን እንደውም ምንዳ እናገኝበታለን፡፡ ደግሞ ልጅም እወልድልሀለሁ፡፡›› ‹‹ተይ ይሄ ባንቺ አፍ አያምርም፡፡ ራሴን ከዝሙት በብዙ ርቀት ጠብቄ የነበርኩትን ልጅ ገፍትረሽ ካሰመጥሽኝ በኋላ እጅሽን ተጣጥበሽ ልትሰብኪኝ አትሞክሪ!›› ‹‹ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ? ተፀፅተን መንገዳችንን ካረምን እኮ አላህ ይቅር ይለናል!›› ‹‹ወንጀል ውስጥ ሆነ ብለሽ እንድንገባ ካደረግሽ በኋላ ይምረናል ስትዪ ትንሽ አይሸክክሽም? ይምረኛል ብሎ ወንጀል መስራት በጣም ያስቃል፡፡››

Open in Telegram
Views335+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#7344Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣4⃣ ከዛ ደግሞ ድካም አለ …. ፍራሹ ላይ ጎን ለጎን ተዘረሩ፡፡ ሀፍረት ሁለቱንም ከመተያየት ቆጥቧቸዋል፡፡ ቀመር ከፍራሹ ራስጌ የቆሻሻ ልብስ ማስቀመጫ ቅርጫቱ ላይ የተቀመጠውን አንሶላ አንስታ ለበሰች፡፡ ሙሉ ለሙሉ ራቁቷን ነበረች፡፡ አንሶላውን ተጋራት፡፡ ዝም እንዳሉ መሸ፡፡ አስር የለ፣ መግሪብ የለ ፣ ኢሻ የለ ….. ዝም! ሁለቱም ልብ ውስጥ በዚህ ሁኔታ ፈጣሪ ፊት የመቆም ድፍረት የለም፡፡ ዝምታው ሲደክማት ተጠግታ ተለጠፈችበት፡፡ አቀፋት፡፡ ‹‹ኢምሩዬ አፈቅርሀለሁ እሺ!›› ‹‹እኔም እወድሻለሁ!›› ‹‹የምርህን ነው?›› ‹‹ይመስለኛል! ባልወድሽ ይህን ያህል አልቀርብሽም ነበር፡፡›› ፊቷ ላይ የደስታ ብርሀን በራ፡፡ እንዳታልፈው እስኪሰጋ ድረስ ተለጠፈችበት፡፡ የወደደችውን ስላገኘች ….. ህይወቷን ልትሰጠው የምትፈልገው ሰው ስለተቀበላት ….. ደስ ብሏታል፡፡ ‹‹ግን ቀሙ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ አይደል?›› ‹‹የቱ?›› ‹‹አሁን ካንቺ ጋር መተኛቴ!›› ‹‹በጣም ይቅርታ ኢምሩዬ! አማራጭ የነበረኝ አልመሰለኝም!›› ቀና ብላ ከንፈሩን ሳመችው፡፡ መፀፀት የጀመረው ያገኘው እርካታ አልቆበት ከሆነ ብላ ማደንዘዣዋን ደገመችው ….. ሳመችው፡፡ በጣም ደካማ ነበር፡፡ ስትስመው ተመልሶ ስሜቱ ውስጥ ሰጠመ፡፡ የፍራሿ ስቃይ ቀጠለ፡፡ እሱም ሆነ እሷ በፍፁም ራሳቸውን በዚህ አይነት ወራዳ ተግባር ውስጥ እናገኛለን ብለው አስበው አያውቁም፡፡ ጭንቅላቷን ተጠቅማ እያሸነፈች ነበር፡፡ አሁን ግን በአቋራጭ ለማሸነፍ ብላ ሴትነቷን ተጠቀመች፡፡ ሴት ልጅ መሸነፍ የምትጀምረው ሴትነቷን መጠቀም ስትጀምር ነው፡፡ ዛሬ ኢምራን ተደፈረ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መድፈር በጉልበት ማነቅ ብቻ አይደለም፡፡ እንዲህ በውበት ሀይል …. እንዲህ በስሜት ሀይል አስገድዶ እጅ እንዲሰጥ ማድረግም መድፈር ነው፡፡ ጠዋቱን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ ቀመር የወር አበባ ላይ ሆና ሰላት የማትሰግድባቸው ቀናትን እንኳ ልምድ ሆኖባት በንጋት ስግደት ሰዓት ትባንን ነበር፡፡ ኢምራንም የሷው ቢጤ ነው፡፡ ወንጀል ፤ ሰሪውን ከመልካም ስራ እንደምትከለክል ለመረዳት የሻ ሰው ሁለቱን መመልከት ይበቃዋል፡፡ የትናንትናው ወንጀላቸው ከስግደት ሲከለክላቸው … ደነገጡ፡፡ ‹‹ሁለት ሰዓት ሆኖ ነው?›› ቀመር ሰውነቷን በአንሶላው እንደጠቀለለች ስልኳን ፈልጋ ስትመለከት ማመን ከብዷት የጠየቀችው ነበር፡፡ ‹‹ማለት ነዋ እንግዲህ! ምነው ደነገጥሽ?›› ‹‹ፈጅር ሳንሰግድ ብዬ ነዋ!›› ፈጅር ጎህ ሲቀድ የሚሰገደው የንጋት ስግደት መሆኑ ነው፡፡ ‹‹ትናንት አስር ፣ መግሪብ እና ኢሻም አልሰገድንም ከረሳሽው ላስታውስሽ!›› ቅስሟ ስብር እንዳለ ወደ ፍራሹ ተመለሰች፡፡ ገና ለስግደት ብቁ ለመሆን ጀናባ ማውረድ የሚባለው መስፈርት ይቀራቸዋል፡፡ ገላቸውን መታጠብ አለባቸው፡፡ ያኔ ጀናባቸው ወረደ ይባላል፡፡ ኢምራን ከወ/ሮ አርሴ መዘፍዘፊያ ተውሶ ቀመር ቤቱ ውስጥ ገላዋን እንድትታጠብ እሱ ደግሞ ግቢው ውስጥ እንደነገሩ በቆርቆሮ የታጠረችው ክፍል ውሀ ይዞ ሄዶ ለመታጠብ አሰበ፡፡ ቱታውን ለብሶ ወደ ወ/ሮ አርሴ ቤት ሲሄድ ወ/ሮ አርሴ እና ሌሎች ተከራዮች ቤቱ ውስጥ ሲሰራ የነበረውን ወንጀል ያወቁ ፣ ያወቁ እየመሰለው ያፍር ነበር …. እነሱ ግድ ይሰጣቸው ይመስል ይጠራጠራቸዋል! የሚመለከተው ….. ከመመልከት ምንም የማይጋርደው ጌታው ግን ያልተፈቀደለትን ቀለበት በማህተሙ ሲዘጋ እየተመለከተው ነበር፡፡ እሱ ያውቃል …. እሱ ተወንጅሏል ….. ግን ምንም አላለም! አይቸኩልማ! . . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣5⃣

Open in Telegram
Views369+16%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#7343Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣3⃣  ቀመር ለአስራ አምስት ቀናት ያህል የትውልድ ከተማዋ ሀላባ ላይ ከቤተሰቦቿ ጋር ከቆየች በኋላ ውዷን ለማግኘት በናፍቆት እየተሳከረች ወደ ሀዋሳ አቀናች፡፡ ኢምራን ለአንድ ሳምንት ያህል ደሴ ደረስ ብሎ እንደተመለሰ መጀመሪያ ያሳወቃት ለቀመር ነበር፡፡ እሷም በተነጋገሩት መሰረት ይኸው ከተፍ አለች፡፡ ለሁለተኛው የትምህርት መንፈቅ አመት የሚያስፈልጓትን እንደ በሶ እና ሌሎች መሰል ግብዓቶችን ሳትይዝ ነበር  የመጣችው፡፡ ገና በመጀመሪያው ሴሚስተር የፍሬሽነት ካባው ሙሉ ለሙሉ ከላይዋ ላይ ተገሽልጦ ሳይወርድ አልቀረም፡፡ ልጅቷ በጣም ፈጣን ናት፡፡ አውቶብስ ተራ ስትደርስ ኢምራን ቀድሞ ደርሶ መምጣቷን እየተጠባበቀ ነበር፡፡ ለኢምራን የራሱ ለውጥ በጣም እየገረመው ነው፡፡ በቻለው መጠን ይገፋት እንዳልነበር አሁን በሷ የፍጥነት መጠን እሱም እየተጠጋት ያለ እየመሰለው ነው፡፡ አውቶብስ ተራው ጋ ያለች ትንሽዬ ሻይ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ቡና እየጠጣ ደሴ ሲሄድ እናቱ የተማፀኑት ተማፅኖ አይኑ ላይ ድቅን አለበት፡፡ የሂባ ክህደት በጣም እንደጎዳው ያውቃሉና ቢያንስ እሷን የምታስረሳ ሴት ፈልጎ እንዲያገባ ካልሆነም እሳቸው የሚያመጡለትን እንዲቀበል ተማፅነውት ነበር፡፡ እንደምንም ‹‹እኔው ያሰብኳት አለች!›› ብሎ ተፋታቸው እንጂ በእርሳቸው አያያዝ እዛው ተድሮ መምጣቱ ነበር፡፡ ከሚኒባሱ እንደወረደች ደወለችለት፡፡ ሂሳቡን ከፍሎ ፈጠን ፈጠን እያለ ወደ መናኸሪያው ገባ፡፡ ወደሷ ሲመጣ ስታየው ፊቷ በብርሀን ፈገግታ ተሞላ፡፡ ወገቧ ላይ የተሸከመችው ተለቅ ያለ ቦርሳ ፣ በእጇ ያንጠለጠለችውን ፌስታል ሲያይ … እንዲሁ በብርሀን እንደተጠመቀች ወደ ህዋ ልትመጥቅ መሰለው፡፡ ፈገግ ለማለት ሞከረ፡፡ ወደሷ ተጠግቶ በእጇ የያዘችውን ፌስታል ተቀበላትና ቦርሳዋን ከወገቧ ላይ አንስቶ አዘለው፡፡ ‹‹ቢያንስ ፌስታሉን እኔ ልያዘው!›› ‹‹ቀላል ነው እኮ! ቦርሳውም ፌስታሉም አይከብድም! ይኼ ብቻ ነው ልብስሽ?›› ‹‹ውይ አንተ ደግሞ ልብሴማ ዶርም ነው ያለው! ይህቺ ለአስራአምስት ቀን ይበቃኛል ብዬ ይዣት የሄድኩት ናት!›› ‹‹በለው አሰብኩት እኮ ዶርም ያለው ሻንጣ ደግሞ ምን እንደሚያክል!›› ከመናኸሪያው ከወጡ በኋላ ኢምራን ሰረቅ አድርጎ አያትና ‹‹አሁን የት ነው የምንሄደው?›› አለ፡፡ ‹‹ኮተቴን ዶርም ላስቀምጥ እና ምሳ እንብላ!›› ‹‹ምሳ አሪፍ ድንች ወጥ ሰርቻለሁ ቤት እንበላለና?›› ‹‹መችስ ድንቹ ተበጥብጧል አይደል?›› ተሳሳቁ፡፡ እየተቀላለዱ የቴክኖ ግቢ በር ጋ ሲደርሱ ኮተቷን ይዛ ገባች፡፡ ዶርም አስገብታ እስክትመለስ እሱ በር ጋር ቆሞ ጠበቃት፡፡ ከዶርሟ ልጆች ውስጥ ማንም የተመለሰ አልነበረም፡፡ ገና ለምዝገባ አንድ ሳምንት ይቀራል፡፡ ኮተቷን አስቀምጣ ከተመለሰች በኋላ ተያይዘው ወደ እሱ ቤት አቀኑ፡፡ ቤት ደርሰው ወጡን እያሞቀ ‹‹ታውቂያለሻ ግን እኔ ድሮ ረጋ ያለች ሴት ነበር የምወደው!›› አለ፡፡ ቀመር እየሳቀች አየችው፡፡ ‹‹እና አሁን ምን አይነት ሴት ወደድክ?›› ‹‹ማለቴ አሁን እንዳንቺ ፈጠን ፈጠን የሚሉ ሴቶች አልወድም ነበር፡፡ የሆነ ዱርዬ ምናምን ነበር የሚመስሉኝ!›› ‹‹እና አሁንስ?›› ‹‹አሁንማ ላይሆኑ እንደሚችሉ ባንቺ እያየሁ ነው፡፡›› ‹‹ታውቃለህ ቤት በጣም ነው የሚፈሩኝ! ከሰው ጋር መቀራረብ ስለማበዛ ምናምን በተለይ ከወንድ ጋር ስለምቀራረብ መጥፎ ነገር ላይ እንዳልወድቅ ይፈራሉ፡፡ ለዛ ነው ሁሌ ሊድሩኝ የሚፈልጉት፡፡ አሁን ራሱ ለክረምት ስመለስ ወይ እኔ ያመጣሁትን ወይ እነሱ የመረጡትን ለማግባት ቃል አስገብተውኝ ነው የመጣሁት!›› ‹‹እና ክረምቱን ሰርግ ልታበይኝ ነዋ!›› ‹‹ታዋጣለህ እንጂ አዎ!›› ሳቀች፡፡ ‹‹ስሚ ደግሞ ሳልነግርሽ ሂባዬ ደውላ ረዥም ሰዓት አወራን እኮ!›› ‹‹ከባለፈው በኋላ?›› ውስጧ እየተቃጠለ ነው፡፡ ‹‹አዎ!›› ‹‹እና ስለልጇ ምን አለችህ? ባሏ ነው ወይስ አንተ ስም የምታወጡለት?›› ‹‹ስለሱ እንኳ አላወራንም ግን ለጓደኛዋ ምክር ቢጤ ፈልጋ አማከርኳት!›› ‹‹ጓደኛዋ ምን ገጥሟት?›› ሂባ የነገረችውን አንድም ሳያዛንፍ ነገራት፡፡ ፊቷ ተቀያየረ፡፡ የነገረችው የሁለቱን ታሪክ እንደሆነ ለመረዳት ቅፅበት አልወሰደባትም፡፡ ‹‹ምነው ቀመር? አመመሽ እንዴ?›› የፊቷ መቀያየር አስደንግጦታል፡፡ ‹‹አይ ደህና ነኝ! እና እጮኛ ይዘሀል ወይ አላለችህም?›› ‹‹ብላኛለች እንዴት አወቅሽ?›› ‹‹ያው ሴት አይደለሁ! ልትልህ የምትችለው አይጠፋኝም!›› ‹‹በለው ጉራ!›› ‹‹ከዛ በኋላ ሌላ ምንም ነገር አልነገረችህም አይደል?›› ‹‹አዎ በቃ የነገርኩሽን ብቻ ነው ያወራነው፡፡›› ወጡን ጨልፎ ያዘጋጀውን ምሳ አቀረበ፡፡ ቀመር በልቧ ሂባን እንዴት መቅደም እንዳለባት ታሰላስላለች፡፡ ምግብ የመብላት ፍላጎቷ ትቷት ተነነ፡፡ ‹‹ቀሙ ሰላም ነሽ ግን? እየበላሽ እኮ አይደለም!›› ‹‹ሰላም ነኝ …. አንተ ግን ለኔ ….›› የጀመረችውን መጨረስ አቃታት፡፡ ጭንቅላቷ ውስጥ የሊዲያ ምክር አቃጨለ፡፡ ‹‹እወድሀለሁ እንዳትይው ዝም ብለሽ ከንፈሩን ሳሚው!›› የሷ እቅድ በዚህ መልኩ የነበረ ባይሆንም የሂባ ፍጥነት እጅጉን ስላስፈራት የማታምንበትን ነገር ለማድረግ አሰበች፡፡ ‹‹ብስመው ምን ይለኛል? ከቤት ያባርረኛል? ወይስ መልሶ ይስመኛል?›› ከራሷ ጋር ሙግት ገጠመች፡፡ ‹‹ቀሙ የተፈጠረ ነገር ካለ ንገሪኝ አታስጨንቂኝ! ምግቡ አልተመቸሽም?›› ‹‹አጉርሰኝ!›› ቁጣ የቀላቀለ ትዕዛዝ ነበር፡፡ ኢምራን ደንግጧል፡፡ እጁ ላይ ይዞት የነበረውን አጎረሳት፡፡ እያጎረሳት ለራሱም እየጎረሰ ምግቡን በልተው ሲጨርሱ እጇን አስታጥቧት እቃውን አነሳሳና ፍራሹ ላይ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ከዚህ በፊት እንዲህ ከጎኗ ተቀምጦ አያውቅም፡፡ ልቧ በፍጥነት መምታቱን ቀጥሏል፡፡ ‹‹ልሳመው ፣ አልሳመው›› አመነታች፡፡ ‹‹ቀሙ ዝም አልሽ እኮ! ዝም ስትዪ በጣም ነው የምትጨንቂው!›› ሳታስበው እንባዋ ከአይኖቿ ሞልቶ ፈሰሰ፡፡ ‹‹ቀሙ!›› ኢምራን ደነገጠ፡፡ እንዴት እንደሚያባብላት ግራ ገባው፡፡ ደረቱ ላይ ተለጥፋ ማልቀስ ጀመረች፡፡ እንባዋን ለመጥረግ እጁን ወደ ፊቷ ሲልክ ያዘችውና ቀና አለች፡፡ በፊቶቻቸው መካከል የህጻን ልጅ ስንዝር ያህል እንኳ ርቀት የለም፡፡ የኢምራን ልብ ቀጥ አለ፡፡ አይኗን ጨፍና ተጠጋችው፡፡ አንዴ ስትስመው የተፈጥሮ ህግ ትዝ አለው፡፡ እሱ ወንድ ነው፡፡ ራሱን ያጠረባቸውን የመርህ ሰንሰለቶች ሁሉ ዘነጋቸው፡፡ ደገመችው፡፡ ንዝረቱ ጋመ፡፡ ደጋገመችው፡፡ ወንድ ሆነ፡፡ መሳሙ ወደ መሳሳም ተቀየረ፡፡ የኢምራን ጾመኛ ቤት ሳታስበው አፈጠረች፡፡ ባልታሰበ ….. ፀጋ ለማለት በሚከብድ መና ጾሟን ገደፈች፡፡ ይህቺን እሳት በአግባቡ ካልሞቋት ማቃጠሏ እንደማይቀር ግልፅ ነበር፡፡ የአሟሟቁ አግባብ በትዳር መተሳሰር ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡ አቅላቸውን ስተው ደመ ነፍሳቸው የሰጣቸውን ፈረስ ቼ ቼ ቼ እያሉ ጋለቡ፡፡ ትንሿ ቤት ሰምታው የማታውቀውን የሲቃ ድምፅ ሰማች …. ፍራሿም ተጭኗት የማያውቅ ሀይል ሲፈትጋት ተጨንቃለች፡፡ የእሳቱ ማጥፊያ የነበረው እሷ ጋ ነው፡፡ እሳት አደጋ መከላከያ የለኮሰውን እሳት ደግሞ መብራት ሀይል ሊያባብሰው እንጂ ሊያጠፋው አይችልም፡፡ የተፈጥሮን ሚዛን እንድትጠብቅበት የተሰጣትን አደራ በላች፡፡ ደካማውን ፍጥረት አስጎነበሰችው፡፡ 

Open in Telegram
Views305−4%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#7342Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣1⃣ አርብ ከከሰዓት በኋላ ኤርሚያስ እና ናርዶስ የመስሪያ ቤቱ ክበብ ውስጥ ተቀምጠው ስለፊልሞቹ እየተወያዩ ነው፡፡ ‹‹የመጀመሪያው አሪፍ ነበር ያው ታሪኩን ወድጄዋለሁ! ሁለተኛው እስከዚህም ነው ግን እሱም ደስ የሚል ነገር አለው፡፡ those pornography videos ግን …. ለምናባህ ነው የላክልኝ?!›› ኤርሚያስ እየሳቀ ወደ አፉ ያስጠጋውን ማኪያቶ ፉት ብሎ ወደ ጠረጴዛው መለሰና ቀጠለ፡፡ ‹‹ያው ለወደፊቱ እውቀት ይሆንሻል ብዬ ነዋ! ግን አሪፍ ናቸው እኮ አልወደድሻቸውም?›› ‹‹ሂድ እዛ ሙት እሺ! ዘጊ!›› ‹‹ቆይ እንደውም ላሳይሽ አዲስ የተቀበልኩትን!›› ስልኩን አውጥቶ መነካካት ጀመረ፡፡ ‹‹እንዴ አንተ እብድ! ሰው አለ እኮ!›› ጨነቃት፡፡ ‹‹ነይ እሺ አንቺ ቢሮ እንሂድ!›› ስልኩን እየነካካ ተነሳ፡፡ ተከተለችው፡፡ ሂሳብ ከፍለው ወደ ቢሮዋ ሄዱ፡፡ ቪዲዮውን የማየት ፍላጎቱ ቢኖራትም ከሱ ጋር ለማየት ፈቃደኛ መሆኗ ርካሽ እንዳያስብላት ፈርታለች፡፡ በሩን ከውስጥ ከቆለፈው በኋላ ቀድሟት ወንበሯ ላይ ተቀመጠ እና ጎትቶ ጭኑ ላይ አስቀመጣት፡፡ የጆሮ ማዳመጫውን ካደረጉ በኋላ ቪዲዮውን ከፈተው፡፡ ከእስከዛሬዎቹ እጅጉን የከፋ ነበር፡፡ የናርዶስ ሰውነት መንዘፍዘፍ ጀመረ፡፡ እግሯ እግሩን ሲታከከው ይታወቀዋል፡፡ እሱ ላይ ቪዲዮው ብዙም ተፅዕኖ አያሳድርበትም ፣ የለመደው ነው፡፡ የናርዶስን መቅለጥ ሲመለከት እጆቹን ወደ ሰውነቷ ልኮ ይደባብሳት ጀመር፡፡ እጅግ ቀስቃሽ የሆኑ የሰውነት ክፍሎቿን በእጆቹ አዋራቸው፡፡ ናርዶስ አቅሏን ለመሳት እየተቃረበች ነው፡፡ ስልኩን ጠረጴዛው ላይ ወርውሮ ወደ ራሱ አዞራት፡፡  ከዛማ … የሚቆራረጥ ትንፋሽ!  ከዛማ …. የሚወዛወዝ ጠረጴዛ! ስልኩ ከጠረጴዛው ስር መሬት ላይ ወድቆ ተሰበረ፡፡ ከጠረጴዛው በላይም የተሰበረ ውድ ነገር ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ማብቂያ አለውና መንፈራገጡ ሲያበቃ ተፋፈሩ፡፡ ናርዶስ ጭንቅላት ውስጥ ብዙ ጥያቄ ይመላለሳል፡፡ ክብሯን በዚህ መልኩ ማጣቷ ፣ ነገስ የሚለው ጥያቄ ፣ ብዙ ብዙ ታስባለች፡፡ ‹‹ሁሉ ነገርሽ ምርጥ …. ጣፋጭ ነሽ!›› የወለቀውን ቀሚሷን እየለበሰች ያለችውን ናርዶስን እያየ ቀጠለ ‹‹ዛሬ ነው አይደል እራት የምትጋብዢኝ?›› እሱ ሱሪውን ለብሶ ከረባቱን እያስተካከለ ነበር፡፡ ‹‹አንተ ውጪ ሰምተውን ይሆን እንዴ? በጣም ጮህኩ?›› ከቢሮ  ስትወጣ ቀና ብሎ የመሄድ ድፍረት ውስጧ ላይ የለም፡፡ ‹‹ይኼ እኮ አርማታ ነው ድምፅ አያስወጣም! ፈታ በይ ባክሽ!›› ‹‹ባረግዝስ?›› ‹‹አሁን የሚወሰድ ክኒን አለ ቆይ ስንወጣ እገዛልሻለሁ!›› ‹‹አውቀዋለሁ እሺ! አሁን እንሂድ በቃ ከዚህ እንጥፋ!›› የምትናገረው ለራሷም ግራ እየገባት ነው፡፡ ተያይዘው ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ * ሂባ ቅዳሜ ከሰዓቱን ናርዶስ ጋር ስልክ ስትደውል አይነሳም፡፡ በአካል ከተገናኙ ሶስት ቀን ሊያልፍ ነው፡፡ ከሰዓቱን ስራ ስለሌላት በጊዜ ትመጣለች ብላ ብትጠብቃት በጣም ዘገየች፡፡ ደጋግማ የሞከረችው ስልክ ተስፋ ሲያስቆርጣት አልጋ ላይ ጋደም እንዳለች  ኢምራን ጋር ስለመደወል አሰበች፡፡ ‹‹ደውዬ ምን እለዋለሁ?›› ፈራች፡፡ ልትተወው ስትል ባለፈው ‹‹የምታማክሪኝ ነገር ሲኖር ከጎንሽ ነኝ!›› ማለቱ ትዝ አላት፡፡ ደወለች፡፡ ጥቂት ከጠራ በኋላ ተነሳ፡፡ ኢምራን ቶሎ ለመመለስ ብላ ፈተና እንዳለቀ የሄደችውን ቀመርን አውቶብስ ተራ ሸኝቶ መመለሱ ነበር፡፡ ስልኩ ላይ የሂባን ስልክ ሲመለከት ውስጡ በደስታ ተሳከረ፡፡ ‹‹ሂባዬ!›› ‹‹ኢምሩ እንዴት ነህ?›› ‹‹አለሁልሽ አንቺ እንዴት ነሽ?›› ‹‹አለሁ አልሀምዱሊላህ!›› ሰላምታቸውን እንደቋጩ የተፈጠረ አዲስ ነገር ካለ ከተጠያየቁና እሱ ከነገራት እሷ ከደበቀችው በኋላ ወደ ደወለችበት ጉዳይ ገቡ፡፡ ‹‹አንድ ነገር ላማክርህ ብዬ እኮ ነው!›› ‹‹ምን?›› ‹‹አንድ ጓደኛዬ ናት እና አንድ ወዳጇ በጣም ቤቷን ወዶት ቤቷ ውስጥ አንድ ክፍል ልትሰጠው ተስማምተው ነበር፡፡ ኋላ ላይ እሷ ቤት ለመኖር እቃውን ሸክፎ ሲመጣ የቤተሰቦቼ ዘመዶች ስለመጡ እነሱ ሊያርፉበት ነው ብላ ከለከለችው፡፡ እሱም እንደሷ ቤት ልቡ ወዶ የሚያርፍበት ቦታ ስላልነበረው በጣም ተጉላላ፡፡ ኋላ ላይ እሱ ተጉላልቶ ተጉላልቶ ሲረጋጋ ፣ የቤተሰቦቿ ዘመዶች ሁሌ እየረበሹ አስቸገሯትና አባረረቻቸው፡፡ እነሱ ሲኖሩበት የሰጠቻቸውን ክፍል በር ሰብረውት ነበር፡፡ ኮርኒሱም ውሀ አዝሎ ጠቁሯል፡፡ አሁን ያንን ወዳጇን ጠርታ ቤቱን ልትሰጠው ትፈልጋለች ግን አዲስ እያለ ቃሏን አጥፋ ስለነበር አሁን በሩ ከተሰበረ እና ኮርኒሱ ውሀ ካዘለ በኋላ ብጠራው ሌላ የተሻለ ቤት እንዳያገኝ መመቅኘት ይሆናል ብላ ፈራች፡፡ እና ምን ልበላት?›› ‹‹እሱ ቆይ አቅም የለውም ነው? ለምን እሷ ቤት ማረፍ ፈለገ?›› ‹‹ቤቷን ስለወደደው ነው እንጂ አቅም እንኳ አለው!›› ‹‹ታዲያ አቅም ካለው በሩንም ፣ ኮርኒሱንም አሰርቶ መኖር ይችላል አይደል! ያለውን ሁኔታ ለምን አትነግረውም?›› ‹‹በሩም ሆነ ኮርኒሱ የተሰሩት በጣም ድሮ ከውጪ ሀገር በመጡ ግብዓቶች ነበር፡፡ አሁን ምርቱ ስለቆመ ገበያ ላይ የሚገኙ አይነት አይደሉም!›› ‹‹ታዲያ የዘመኑን አዲስ በር እና ኮርኒስ ያስገጥማ ምንድነው እንዲህ መጨናነቅ?›› ‹‹እንደዛ መሆን አይችልም! እቃው ላይቀየር ከአያቶቿ አደራ አለባት፡፡›› ‹‹በቃ ወይ አሁን እሱ ያለበትን ሁኔታ ታጣራና የተሻለ ቤት ካገኘ ትተወው! ካላገኘ ደግሞ ትንገረውና እሱ የፈለገውን ይምረጥ! አይታወቅም እኮ ቤቱን ከወደደው በሩ ቢሰበርም ሊኖርበት ሊፈልግ ይችላል›› ‹‹እሺ ይኼ ጥሩ አማራጭ ነው!›› ‹‹አዲስ አበባ ቤት እንዲህ ችግር ሆነ ማለት ነው? የሚወደድ ቤት እንዲህ ጥቂት እስኪሆን?›› ‹‹አይገርምህም!›› የምታወራው ወሬ ምንም እንዳልገባው በመረዳቷ በጣም ደስ ብሏታል፡፡ እንደልቧ የማውራት ነፃነት አግኝታለች፡፡ የመከራትን ምክር ዛሬውኑ ተግባራዊ ለማድረግ አሰበች፡፡ ‹‹በቃ የጓደኛዬን ጉዳይ ያልከኝን እነግራታለሁ፡፡ እስኪ ወደራሳችን እንመለስ ኢምሩዬ ግን እስካሁን እንዴት አላገባህም?›› ‹‹እንዴ ገና እኮ ስምንት ወር አልሞላም ቁርጤን ካወቅኩ፡፡ በዚህ ጊዜ ሌላ ከየት ይመጣል?›› ‹‹ፍቅረኛም አልያዝክም? እንደው ያሰብካትም የለችም?›› ‹‹አንቺ ደግሞ ኧረ ማንም የለም ባክሽ!›› የቀመርን ጉዳይ ሊነግራት አስቦ ነበር ግን በቅጡ መስመር ውስጥ ያልገባ ጉዳይ ማውራት ከበደውና ተወው፡፡ ‹‹ማስተማሩ busy አድርጎሀል ማለት ነው፡፡›› ‹‹በይው›› ሂባ በሱ ምክር መሰረት ቀጣዩ ስራ የተፈጠረውን ሁሉ ነግራ ምርጫውን ለሱ መስጠት መሆኑን አውቃለች ግን ደግሞ ከየት ድፍረት አምጥታ እንደምትነግረው ግራ ገብቷታል፡፡ * ቀናት  የጊዜ ጓዛቸውን እየጠቀለሉ ከመጓዝ አልቦዘኑም፡፡ እሽጉ ከተፈታ ወዲያ ኤርሚያስ ቤት ጎራ ተብሎ በቪዲዮ የተመለከቱትን መተግበር የናርዶስ ቋሚ ስራ ሆኗል፡፡ ከሂባ ጋር በቅጡ ተገናኝተው የሚያወሩበት ፣ እንደድሮው ስለሁሉም ነገር የሚማከሩበት ጊዜ ጠፍቷል፡፡ አምሽታ ትመጣለች …..

Open in Telegram
Views281−12%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#7341Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 3⃣0⃣ ዚያድ ሲወጣ ሂባ የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ እየሮጠች አባቷ ላይ ተጠምጥማ ማልቀስ ጀመረች፡፡ በአባቷ እንደዛሬ የተደሰተችበት ቀን በህይወቷ ገጥሟት የሚያውቅ አልመሰላትም፡፡ አባቷም እንባ ተናነቃቸው፡፡ ግንባሯን ሳሟት እና ‹‹ልጄ አላህ ያክብርሽ እስከዛሬ አንድም ቀን አስከፍተሸኝ አታውቂም! ከዚህ በኋላ አንቺ የምትፈልጊውን ሰው አምጪ አይተን ጥሩ ከሆነ እንድርሻለን! እኛም የምናመጣውን ካልፈለ ግሽው ይቀራል!›› አሉ፡፡ ምንም ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ ቢሆንም አባቷ ስለተረዷት ደስ አላት፡፡ ግን ከዚህ በኋላ ዳሩኝ ብላ የምታመጣው ሰው ያለ አልመስል አላት፡፡ ኢምራን ነበር! እሱን አሁን ላይ ለማግባት የምትመጥን አይመስላትም! ‹‹ጠምቶት ሲማፀነኝ ከልክዬው ፣ ያልደፈረሰውን ለሌላ ሰጥቼ ፣ ያጠጣሁት ሲገፋኝ ጠርቼ ፣ ቅራሪዬን ጠጣ አልለውም!›› ትላለች፡፡ የኢምራን መሆን ብትፈልግም አሁን ላይ ያንተ ልሁን ማለት ለሱ አለማሰብ ይመስላታል፡፡ *** ‹‹አራቱንም ፈተና የነገርከኝ ቦታዎችን ነበር focus አድርጌ ያጠናሁት! እንዳለ የመጣውም እሱ part ነው፡፡›› ቀመር ፍራሹ ላይ ተቀምጣ ከስራ መጥቶ ጃኬቱን የሚያወልቀውን ኢምራንን እያየች ቀጠለች ‹‹እና አሪፍ ውጤት እንደሚኖረኝ አትጠራጠር!›› ‹‹እሱን ሲመጣ እናየው የለ የምን ፕሮፖጋንዳ ማብዛት ነው?!›› ‹‹እኔማ ላመስግንህ ብዬ ነው!›› ‹‹እና አሁን ስንት ፈተና ቀራችሁ?›› ‹‹ሁለት መሰለኝ! በዚህ ሳምንት እንጨርሳለን!›› ‹‹ከዛስ?›› ‹‹ከዛማ ጉዞ ወደ ቁሌታሟ ሀላባ ነዋ!›› ተሳሳቁ! ‹‹የማጥኛ ክፍልሽ አትናፍቅሽም?›› ለማለት የፈለገውን ተረዳችና ፈገግ አለች፡፡ ‹‹በጣም ትናፍቀኛለህ ኢምሩዬ! አንተ ወደ ደሴ አትሄድም እንዴ?›› ‹‹ለሳምንት ደርሼ መምጣቴ አይቀርም!›› ‹‹በቃ ታዲያ ስትመለስ ደውልልኝና እመጣለኋ!›› ‹‹የምርሽን ነው?›› ‹‹አዎ እኛ ቶሎ ስለምንሄድ አንተ ውጤት አስገብተህ ከመሄድህ በፊት ራሱ እኔ እዛ ሄጄ ሳምንት አሳልፋለሁ፡፡ ከዛ አንተ ሄደህ አንድ ሳምንት! በድምሩ አስራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ቤት ደግሞ ከዚህ በላይ የምናርፍ ስለማይመስላቸው አይባንኑም! so ከች እላለሁ፡፡ ታዲያ ፈታ የምታደርገኝ ከሆነ ነው! ታስደብረኝና አለቀልህ!›› ‹‹ውይ እኔ ፈታ ማድረግ አልችልበትም! ያው ባይሆን አንቺ እንሂድ የምትይው ቦታ ለመሄድ ከተስማማሁ አይበቃም?›› ‹‹ይበቃል! የምልህን ሁሉ እሺ ካልክማ በቃ የሚገርም ጊዜ ነው የምናሳልፈው!›› ተሳሳቁ፡፡ ለማለት የፈለገችውን እሱም ተረድቶታል፡፡ በፊት በፊት ቶሎ አይገባውም ነበር፡፡ ሰዓቱ ለመምሸት እየቀረበ ስለነበር ጓደኞቿ መደወል አበዙ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ለመሄድ ተነሳች፡፡ ሁሌም ልትሄድ ስትል ደስ አይለውም፡፡ ከብቸኝነቱ የሚያተርፈው ትዝታ ነው፡፡ ትዝታው ደግሞ መሪር ነው፡፡ በቀመር ውስጥ ትዝታውን ለመርሳት ይታገላል፡፡ የሀይማኖቱን ክልከላ ይዘነጋው ጀምሯል፡፡ በራሱ በጣም ተማመነ መሰል ቤት ውስጥ ብቻቸውን መቀመጣቸው የሚያመጣው መዘዝ መኖሩን ረስቷል፡፡ ግን ባትሄድ ደስ ይለዋል፡፡ ለሊቱንም አብራው ሆና ከትዝታው ብታስጥለው ይመኛል፡፡ ምኞት ብቻ! ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ! እግረ መንገዱን የቆይታቸውን ጊዜ ሊያራዝም! ግቢ መግባቷ ላይቀር! . . . . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣1⃣ 

Open in Telegram
Views428+35%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7340Text

❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️ ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና                        ክፍል 2⃣9⃣ በእግሮቿ መንፈራገጥ የአልጋው አንሶላ ተሰብስቦ ከአልጋው መሀል ላይ ደርሷል፡፡ ልክ ምጥ ላይ ያለች እናት ህመሟን ለመቋቋም ፍራሹን አሊያም ትራሱን ጨምድዳ እንደምትይዘው የግራ እጇ ከላይ የለበሰችውን ብርድ ልብስ በሀይል እየጨመደደ ይለቃል፡፡ ከንፈሮቿ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የመኝታ ክፍሏ ጭልም ብሎ ከስልኳ የሚወጣው ጨረር ብቻውን ይንቦገቦግበታል፡፡ የስልኳ ስክሪን ላይ ሁለት ራቁታቸውን ያሉ ሴቶች ከአንድ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ካለ ወንድ ጋር የተለያየ መጠሪያ ያላቸውን የወሲብ አይነቶች ሲፈፅሙ ይታያል፡፡ የድርጊቱ አካል የሆነች እስኪመስል ገፅታዋ ላይ ተፅዕኖው እየታየ ኤርሚያስ የሰጣትን ተከታታይ የወሲብ ፊልም ተመልከታ ጨረሰች፡፡ ሌላ አይነት ፊልም የማየት ፍላጎቷ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሞቷል፡፡  በነጋታው ቢሮ ስትገባ ኤርሚያስን የህንፃው ደረጃ ላይ አገኘችው፡፡ ተያይዘው ወደ እሷ ቢሮ ገቡ፡፡ ኤርሚያስ እንደተለመደው ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሷል፡፡ ‹‹ሱፍ ላንተ ነው! የሌለ እኮ ነው የሚያምርብህ!›› ቢሮ ገብተው ወንበሯ ላይ እየተቀመጠች ነበር፡፡ ‹‹እንዳንቺ ሁሉም ነገር አያምርብኝም እንጂ በሱፍ አልታማም!›› ተሟዘዘ፡፡ በልቧ የሰጣትን ፊልም ተመልክታ እንደጨረሰችና ቀጣዩን ክፍል እንዲልክላት ለመጠየቅ ፈልጋለች ግን አፈረች፡፡ እሱ ስለፊልሙ እንዲያስታውስ ለማድረግ መላ ዘየደች፡፡ ‹‹የአማርኛ ፊልሞች ግን አይደብሩም? ታሪካቸው ሁሉ ተመሳሳይ ነው እኮ!›› ፈገግ አለ፡፡ ስለላከላት ፊልም ለማውራት ፈልጋ እንጂ ስለአማርኛ ፊልም የሚያስቀባጥር ምንም ምክንያት እንደሌላት ገብቶታል፡፡ ሀፍረቷን ጠብቆ ፍላጎቱ የሆነውን ፍላጎቷን ሊሰጣት ፈለገ፡፡ ‹‹እንዴ ረስቼው የሰጠሁሽን ፊልም ጨረስሽው?›› ‹‹አዎ ጨረስኩት እኮ ትንሽ ግን ይደብራል ነገር!›› ወደደች ላለመባል መታገሏ ነው፡፡ ‹‹እሱን ለመፍረድ አጨራረሱን ማየት ያስፈልጋል! የመጨረሻው ክፍል ተልኮልኛል፡፡ እዪው እና እናወራበታለን፡፡››  የተከታታዩን የወሲብ ፊልም የመጨረሻ ክፍል እና ሌላ ምንም ታሪክ የሌላቸው የወሲብ ቪዲዮዎችን አብሮ ላከላት፡፡ ‹‹እና ደሞ ስሚ እራቱን አልረሳሁትም! በዚህ ሳምንት ትጋብዢኛለሽ!›› ‹‹ውይ ስፕራይት ምናምን እሽኮለሌ ስትል አልነበር እንዴ ባለፈው?›› ‹‹አይ እንግዲህ ሰበብ አትፈልጊ! ትጋብዢኝ እንደው መጋበዝ ነው!›› ‹‹አታለቃቅስ በቃ እጋብዝሀለሁ!››  ተሰናብቷት ወደ ቢሮው ሄደ፡፡ ፊልሞቹ ላይ እንዳየችው ቢነካካት ፣ ቢስማት …. ውስጧ ይመኝ ነበር፡፡ መልሳ በራሷ ታፍራለች፡፡ የቀድሞዋን ናርዶስ ውስጧ ላይ እያጣቻት መሆኑ ያስፈራታል፡፡ ‹‹ይሄን ነገር ልተው? አልተው?›› በሀሳብ ትዋልላለች፡፡ ገና ከቢሮዋ እግሩ ሲወጣ በሩን ቆልፋ የሰጣትን ፊልም መመልከት ጀመረች፡፡ ጠዋቱን ለወጉ ስራ ገባች እንጂ የምትሰራው ስራ አልነበረም፡፡ ከገፀ-ባህሪያቱ ጋር አብራ በስሜት ነደደች፡፡ ከሁሉም የምትጠላው የፊልሙን ማለቅ ነው፡፡ ፊልሙ ሲያልቅ የሷን ንዳድ የሚያበርድ ምንም ነገር አጠገቧ አለመኖሩ ያማታል፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ፣ አንዳንዴም በራስ የማፈር ስሜት ይሰማታል፡፡ የራሷን ስሜት ራሷ ስለማብረድ ታስባለች፡፡ ሀይማኖቷ ትዝ ይላትና ሌላ ወንጀል መጨመርን ትፈራለች፡፡ በዚህ ከቀጠለች ሰው መሆኗ እየጠበበ ሴት ብቻ እንደምትሆን ታውቀዋለች፡፡ አካሏ ሁሉ ቀርቶ ሀፍረተ ስጋ ብቻ ወደ መሆን ስነ ልቦና እንደምትሸጋገር ትረዳለች፡፡ መፍትሄው ግን ማወቅ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህ ጉድ ጎትቶ የሚያወጣ ጠንካራ አቋም ይፈልጋል፡፡ አሁንም ፊቷ በላብ እየተጠመቀ ፣ እግሮቿ መሬቱን እያስቸገሩ ነው፡፡ ቆንጅዬዋ እና በስነ ምግባሯ የማትታማው ናርዶስ የወሲብ ፊልም እያየች ነው፡፡ *** ዚያድ ሂባ ከቤት ከወጣች ከአራት ቀናት በኋላ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት መጣ፡፡ እጅ መንሻ የሚሆን ኮተት አስከትሏል፡፡ አመሻሽ ላይ ስለነበር ጋሽ ጀሚልም ወደ ቤት ተመልሰው ነበር፡፡ ሂባ ወንድሟ የዚያድን መምጣት ሲነግራት የእናትና አባቷ መኝታ ክፍል ገብታ በሩን ቆለፈችው፡፡ አስገድዶ ይዟት የሚሄድ ይመስል ትፈራለች፡፡ ያንን የጨለማ ጊዜ መድገም አትፈልግም፡፡ በስነ ስርዓቱ ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ጋሽ ጀሚል ቁጣቸው እጅጉን ጣራ ቢነካም ዋጥ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ ወ/ሮ ዘምዘም የእጅ ውሀ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ መብላት እንደማይፈልግ ደጋግሞ ማለ፡፡ ‹‹እሺ ጋሼ ዛሬ ያው በዚህ ሰዓት የመጣሁት ለእርቅ ነው፡፡ ሰው ነን አለመስማማት ያለ ነው፡፡ ግን ትዳርን ያክል ነገር ትቶ መውጣት እጅጉን አሳፋሪ ነው፡፡ እኔም ያው ልጅነቷ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ነው እናንተ የሚበጀውን እንድታሳይዩዋት ለመጠየቅ መምጣቴ!››  ሂባ የሚለውን ሁሉ ግድግዳው ላይ ተለጥፋ እያደመጠች ነው፡፡ ጋሽ ጀሚል ቁጣቸው ገነፈለ፡፡ ‹‹ልጄን አክብሬ ስሰጥህ ዘር እንድታስቀጥሉ ፣ ተሳስባችሁ እንድትኖሩ እንጂ! እንደ ባሪያ እንድትደበድባት ፣ እንድታስራት ነበር እንዴ!?›› ‹‹እንዴ ጋሼ የምን መደባደብ ፣ የምን እስር ነው? እንዴት ተንከባክቤ እንደያዝኳት እማማ ሲመጡ ተመልክተዋል እኮ! ይኼ እልም ያለ ቅጥፈት ነው፡፡›› ሂባ ምን ያህል የመዋሸት ድፍረት እንዳለው እየታዘበች ውስጧ በብስጭት አረረ፡፡ ‹‹ስማ ዚያድ ከምንም በላይ ደሜ ያንገበግበኛል፡፡ ስጋዬን ቆርጬ ስሰጥህ እሷን አስገድደን እንጂ ወዳ አልነበረም! ከድሮም ስርዓት ያላት ልጅ ስለሆነች ፍላጎቷ ሳይሆን እንኳ ፣ ሌላ የምትወደውን ሰው ትታ ፣ የአባቷን ትዕዛዝ አክብራ ፣ ፍላጎቷን ተጭና ነው የዳርኩልህ! ይህን ሁሉ አድርጋ ስታበቃ በፍፁም ባለፈው ደውለህ ያልከውን መሸርሞጥም ሆነ አንተን አለመታዘዝ የምታስብ ልጅ ናት ብትለኝ ልሰማህ አልችልም!›› ሂባ አንጀቷ ራሰ፡፡   ‹‹እንዴ ጋሼ እኔም እኮ ልጅዎት ነኝ! በዛ ላይ ልጃችንን አርግዛለች፡፡ የሚበጀው ተስማምተን ብንኖር ነው፡፡›› ‹‹ከሽምግልናው በፊት ተገናኝተን ስናወራ ጫት አልቅምም ብለኸኝ ነበር እኮ! አንተ ግን በየቀኑ ተጥደህበት ነው የምትውለው! ስለሷ ሳይሆን ስለጫት ብቻ ነው የምታስበው! ጫት እኔም እቅማለሁ ግን እኔ አልቅምም ብዬ አልቀጥፍም! ያመጣብኝንም ጉዳት እኔ አውቀዋለሁ!›› ‹‹ጋሼ እንዲህማ ጥሩ ነገር የሌለኝ አያስመስሉ! እኔ ለሷም ለቤተሰቡም ጥሩ ለመሆን ሞክሬያለሁ!›› ስለከፈለላቸው ገንዘብ ማስታወሱ እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡  ‹‹የዋልከውን የዋልከው በፍላጎትህ እንጂ ማንም አስገድዶህ አይደለም! ለማንኛውም አሁን በሰላሙ የምልህ ልጁ ከተወለደ በኋላ አርፈህ ኒካህን አውርድ! ከዚህ በኋላ ልጄን ድጋሚ አስገድጄ ህይወቷን አላበላሽም!›› ‹‹ኧረ እማማ የሆነ ነገር በሉ!›› ወደ ወ/ሮ ዘምዘም ዞሮ በአይኑ ተለማመጠ፡፡ ወ/ሮ ዘምዘም ከዝምታ በቀር ሌላ ምላሽ አልነበራቸውም፡፡ ሂባ የአባቷ ይህን ያህል መቆጣትና ለሷ ዘብ መቆም ፍፁም ያልጠበቀችው ነበር፡፡ ያለፉት ምሽቶች ላይ ያወሩት ያሳለፈችው መከራ እጅጉን እንደቆረቆራቸው ገባት፡፡ በሳቸው አስገዳጅነት መዳሯ ደግሞ የስቃይዋ ምንጭ እንደሆኑ እንዲያስቡ ሳያደርጋቸው አይቀርም፡፡

Open in Telegram
Views284−11%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—