Account

Posts of አል–ዒምራን (CMC) የቁርኣንና ኢስላማዊ ት/ት ተቋም

newest first

#3195Text

🌿 ዝምድናን መቀጠል – صِلَةُ الرَّحِمِ ዝምድናን መቀጠል በእስልምና ከፍተኛ ቦታ ያለው የኢባዳ አካል ነው። ዘመዶቻችንን መጠየቅ፣ መርዳት፣ መጎብኘትና ከእነሱ ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር የእምነታችን መገለጫ ነው። 📖 ከቁርአን 1️⃣ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا﴾ [النساء: 1] «አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተቆጣጣሪ ነው።» 2️⃣ ﴿فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ ۝ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَعَنَهُمُ اللَّهُ﴾ [محمد: 22-23] «እናንተ ከእውነት ብትመለሱ በምድር ላይ ብልሹነትን ታስፋፋላችሁን? ዝምድናችሁንስ ትቆርጣላችሁን? እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው።» 3️⃣ ﴿وَالَّذِينَ يَصِلُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَنْ يُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ﴾ [الرعد: 21] «እነዚያ አላህ እንዲቀጠል ያዘዘውን የሚያቀጥሉና ጌታቸውን የሚፈሩ ናቸው።» 🌙 ከነቢዩ ﷺ ሐዲሶች 1️⃣ የሪዝቅና የዕድሜ በረከት قال رسول الله ﷺ: «مَنْ أَحَبَّ أَنْ يُبْسَطَ لَهُ فِي رِزْقِهِ، وَيُنْسَأَ لَهُ فِي أَثَرِهِ، فَلْيَصِلْ رَحِمَهُ» «ሪዝቁ እንዲሰፋለትና ዕድሜው እንዲረዝምለት የሚወድ ዝምድናውን ያቀጥል።» 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 2️⃣ እውነተኛው ዝምድናን የሚያቀጥል قال رسول الله ﷺ: «لَيْسَ الْوَاصِلُ بِالْمُكَافِئِ، وَلَكِنِ الْوَاصِلُ الَّذِي إِذَا قُطِعَتْ رَحِمُهُ وَصَلَهَا» «ዝምድናን የሚያቀጥል ማለት በመልካም ላደረገለት በመልካም የሚመልስ ብቻ አይደለም፤ እውነተኛው ዝምድናን የሚያቀጥል ዘመዶቹ ሲቆርጡትም እሱ የሚያቀጥላቸው ነው።» 📚 ሶሒሕ አል-ቡኻሪ 3️⃣ ዝምድናን መቁረጥ ከባድ ኃጢአት ነው። قال رسول الله ﷺ: «لَا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ قَاطِعٌ» «ዝምድናን የሚቆርጥ ጀነት አይገባም።» 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 🤲 የመጨረሻ መልእክት ዘመድህ ካልጠየቀህ አንተ ጠይቀው፤ ካልጎበኘህ አንተ ጎብኘው፤ ካልረዳህ አንተ እርዳው። ዝምድና በተመሳሳይ መልካም ምላሽ ብቻ ሳይሆን በአላህ ፊት ያለን ኃላፊነት ነው። አላህ ዝምድናችንን ከሚያቀጥሉና ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን። አሚን! 🤲 https://t.me/Alimrancmc

Open in Telegram
Views5,050−13%vs avg
Forwards—
Reactions85
Comments—
#3191Photo
Views7,060+21%vs avg
Forwards—
Reactions104
Comments—
#3190Photo
Views7,100+22%vs avg
Forwards—
Reactions94
Comments—
#3189Photo
Views7,560+30%vs avg
Forwards—
Reactions140
Comments—