Посты канала አል–ዒምራን (CMC) የቁርኣንና ኢስላማዊ ት/ት ተቋም
🌿 ዝምድናን መቀጠል – صِلَةُ الرَّحِمِ ዝምድናን መቀጠል በእስልምና ከፍተኛ ቦታ ያለው የኢባዳ አካል ነው። ዘመዶቻችንን መጠየቅ፣ መርዳት፣ መጎብኘትና ከእነሱ ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር የእምነታችን መገለጫ ነው። 📖 ከቁርአን 1️⃣ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا﴾ [النساء: 1] «አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተቆጣጣሪ ነው።» 2️⃣ ﴿فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَعَنَهُمُ اللَّهُ﴾ [محمد: 22-23] «እናንተ ከእውነት ብትመለሱ በምድር ላይ ብልሹነትን ታስፋፋላችሁን? ዝምድናችሁንስ ትቆርጣላችሁን? እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው።» 3️⃣ ﴿وَالَّذِينَ يَصِلُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَنْ يُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ﴾ [الرعد: 21] «እነዚያ አላህ እንዲቀጠል ያዘዘውን የሚያቀጥሉና ጌታቸውን የሚፈሩ ናቸው።» 🌙 ከነቢዩ ﷺ ሐዲሶች 1️⃣ የሪዝቅና የዕድሜ በረከት قال رسول الله ﷺ: «مَنْ أَحَبَّ أَنْ يُبْسَطَ لَهُ فِي رِزْقِهِ، وَيُنْسَأَ لَهُ فِي أَثَرِهِ، فَلْيَصِلْ رَحِمَهُ» «ሪዝቁ እንዲሰፋለትና ዕድሜው እንዲረዝምለት የሚወድ ዝምድናውን ያቀጥል።» 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 2️⃣ እውነተኛው ዝምድናን የሚያቀጥል قال رسول الله ﷺ: «لَيْسَ الْوَاصِلُ بِالْمُكَافِئِ، وَلَكِنِ الْوَاصِلُ الَّذِي إِذَا قُطِعَتْ رَحِمُهُ وَصَلَهَا» «ዝምድናን የሚያቀጥል ማለት በመልካም ላደረገለት በመልካም የሚመልስ ብቻ አይደለም፤ እውነተኛው ዝምድናን የሚያቀጥል ዘመዶቹ ሲቆርጡትም እሱ የሚያቀጥላቸው ነው።» 📚 ሶሒሕ አል-ቡኻሪ 3️⃣ ዝምድናን መቁረጥ ከባድ ኃጢአት ነው። قال رسول الله ﷺ: «لَا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ قَاطِعٌ» «ዝምድናን የሚቆርጥ ጀነት አይገባም።» 📚 ቡኻሪና ሙስሊም 🤲 የመጨረሻ መልእክት ዘመድህ ካልጠየቀህ አንተ ጠይቀው፤ ካልጎበኘህ አንተ ጎብኘው፤ ካልረዳህ አንተ እርዳው። ዝምድና በተመሳሳይ መልካም ምላሽ ብቻ ሳይሆን በአላህ ፊት ያለን ኃላፊነት ነው። አላህ ዝምድናችንን ከሚያቀጥሉና ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን። አሚን! 🤲 https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegramአራት የሰው ልጅ ጠላቶች! 1️⃣ الشَّيْطَانُ – ሸይጧን። ﴿إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ﴾ [فاطر: 6] 2️⃣ النَّفْسُ – ክፉ የሚያዝዝ ነፍስ። ﴿إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ﴾ [يوسف: 53] 3️⃣ الدُّنْيَا – የዱንያ ማታለያ። ﴿فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا﴾ [لقمان: 33] 4️⃣ الْهَوَى – የስሜት ፍላጎት። ﴿وَلَا تَتَّبِعِ الْهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ﴾ [ص: 26] ! የሰው ልጅ ትልቁ ትግል ከራሱ ነፍስና ከሚያሳስቱት ነገሮች ጋር የሚያደርገው ትግል ነው።
Открыть в Telegramበቁርአን የተጠቀሱ ሦስት ዓይነት ልቦች! 1️⃣ قَلْبٌ سَلِيمٌ – ንጹሕ ልብ ከሽርክ፣ ከጥላቻና ከምቀኝነት የጠራ። ﴿إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ﴾ [الشعراء: 89] 2️⃣ قَلْبٌ مُنِيبٌ – ወደ አላህ የሚመለስ ልብ። ﴿مَنْ خَشِيَ الرَّحْمَٰنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُنِيبٍ﴾ [ق: 33] 3️⃣ قَلْبٌ مَرِيضٌ – የታመመ ልብ። ﴿فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ فَزَادَهُمُ اللَّهُ مَرَضًا﴾ [البقرة: 10] አስተውሉ! የሰው ትልቁ ሀብት ንጹሕ ልብ ነው። ጁሙዓቹ የተባረከ ይሁን!! اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد
Открыть в Telegramበቁርአን የተጠቀሱ አራት ዓይነት ጉዞዎች! 1️⃣ فَامْشُوا – ተራመዱ ወደ ሪዝቅ ፍለጋ። ﴿فَامْشُوا فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُوا مِن رِّزْقِهِ﴾ [الملك: 15] 2️⃣ فَاسْعَوْا – በትጋት አቅኑ ወደ አላህ ዚክርና የጁሙዓ ሶላት። ﴿فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ﴾ [الجمعة: 9] 3️⃣ سَارِعُوا – ተሽቀዳደሙ ወደ አላህ ምህረትና ገነት። ﴿وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ﴾ [آل عمران: 133] 4️⃣ فَفِرُّوا – ሽሹ ወደ አላህ። ﴿فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ﴾ [الذاريات: 50] አስተውሉ! ሪዝቅን ለማግኘት ተራመዱ፤ ወደ ዒባዳ በትጋት አቅኑ፤ ምህረትን ለማግኘት ተሽቀዳደሙ፤ ከኃጢአትና ከጥመት ወደ አላህ ሽሹ! አላህ ከሚወዳቸው በመልካም ሥራ የሚቻኮሉና ወደ እርሱ የሚመለሱ ባሮች ያድርገን።
Открыть в Telegramሴቶች በእስልምና !! በኡስታዝ አስለም ዩሱፍ ኢማም ሀሰን መድረሳ ምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegramጁሙዓቹ የተባረከ ይሁን ባለፉት ሳምንታት ልጥፎቻችን ተደራሽ እንዲሆን ስላደረጋችሁት አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን ። I got over 10,000 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉 https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegram#ኡስታዝ ዓዲል አህመድ 13ኛ ዙር የአል ዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም ምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ ። https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegramአላህ ያቆመህ ቦታ ሀላፊነትህን በሚገባ ተወጣ። #ኡስታዝ ዓዲል አህመድ 13ኛ ዙር የአል ዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም ምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ ። https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegram4ነገሮች ብቻ ተናገር ህይወትህ እንዲያምር ኡስታዝ ዓዲል አህመድ 13ኛ ዙር የአል ዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም ምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ ። https://t.me/Alimrancmc
Открыть в Telegram