በ28 ሺህ ዶላር ይሸጥ የነበረው የኤችአይቪ መከላከያ መርፌ በ40 ዶላር ወደ አፍሪካ ገባ‼️ ኤችአይቪን ለመከላከል የሚያስችለውና በዝቅተኛ ዋጋ የሚቀርበው «ሌናካፓቪር» የተሰኘ ፈር ቀዳጅ መድኃኒት ወደ አፍሪካ መግባት መጀመሩን ዓለም አቀፉ የጤና ፈንድ (ግሎባል ፈንድ) አስታውቋል። የመድኃኒቱ የመጀመሪያ ዙር ጭነት ዛምቢያ መድረሱን ተቋሙ ገልጿል። ዩጋንዳ በመጪዎቹ ቀናት እንዲሁም ዚምባብዌ በመጪው ዓመት መጀመሪያ ላይ መድኃኒቱን ይረከባሉ። የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ደረጃ በሚገኝባት አፍሪካ ውስጥ የዚህ መድኃኒት መግባት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች መከላከያውን እንዲያገኙ ትልቅ ተስፋ ፈጥሯል። በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመርፌ መልክ የሚሰጠው ይህ መድኃኒት ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ ወደ 100 በመቶ የሚጠጋ ውጤታማነት አለው። ቀደም ሲል በአሜሪካው «ጊሊያድ ሳይንስስ» ኩባንያ ተዘጋጅቶ የነበረው ዋናው መድኃኒት በዓመት እስከ 28 ሺህ ዶላር ይጠየቅበት ነበር። አሁን ግን በህንዱ «ሄቴሮ» ኩባንያ ተመርቶ የቀረበው ተመሳሳይ መድኃኒት ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ለአንድ ሰው በዓመት 40 ዶላር አካባቢ ብቻ ሆኗል። ሌናካፓቪር የኤችአይቪ ቫይረስን መከላከያ ሽፋን በማጥቃት ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይባዛና ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር ያደርጋል። እ.ኤ.አ. በ2024 በዩጋንዳና በደቡብ አፍሪካ ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ ታዳጊ ልጃገረዶችና ወጣት ሴቶች ላይ በተደረገ ክሊኒካዊ ሙከራ መርፌውን ከወሰዱት መካከል አንዳቸውም በኤችአይቪ አልተያዙም። በዚህም መሠረት የዓለም ጤና ድርጅት መድኃኒቱ ለኤችአይቪ መከላከያነት ጥቅም ላይ እንዲውል ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። በየዕለቱ ከሚዋጡ እንክብሎች ይልቅ ይህ መርፌ ለተጠቃሚዎች እጅግ ምቹ አማራጭ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች አብራርተዋል። ግሎባል ፈንድ የዚህ ርካሽ መድኃኒት ወደ አፍሪካ መግባት በኤችአይቪ ላይ በሚደረገው ጦርነት ትልቅ እመርታ መሆኑን አስታውቋል። ጥራቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት በፍጥነት እንዲዳረስም ያስችላል። እስካሁን በ10 አገራት ውስጥ ከ189 ሺህ በላይ ሰዎች የመጀመሪያውን ዙር መርፌ ወስደዋል። በቀጣይም እ.ኤ.አ. እስከ 2028 መጨረሻ ድረስ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር በመተባበር ቢያንስ ለሦስት ሚሊዮን ሰዎች መድኃኒቱን ለማድረስ ታቅዷል። በሂደትም በ120 ታዳጊ አገራት ተደራሽ ይሆናል።
Open in Telegramትምህርት መረጃ( academic info)
@ትምህርት መረጃ( academic info) Telegram: https://t.me/academic_info Facebook: https://www.facebook.com/share/1EqNsbE4CN/ email: [email protected] Instagram:https://www.instagram.com/academicinfor?igsh=ZW8xc2J0MXdxdDVj Mobile 09725443......
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 2, 2026 | 7,160 |
| Nov 6, 2026 | 6,300 |
| Nov 8, 2026 | 6,220 |
| Nov 11, 2026 | 6,800 |
| Nov 16, 2026 | 4,750 |
| Nov 18, 2026 | 4,220 |
| Nov 19, 2026 | 4,330 |
| Nov 20, 2026 | 3,370 |
| Nov 21, 2026 | 4,050 |
| Nov 22, 2026 | 4,120 |
| Nov 23, 2026 | 3,820 |
| Nov 27, 2026 | 1,740 |
| Nov 28, 2026 | 1,375 |
Most viewed this month
- Views7.16KForwards—Reactions9Comments—
- Views6.8KForwards—Reactions12Comments—
- Views6.3KForwards—Reactions2Comments—
- Views6.22KForwards—Reactions6Comments—
Latest posts
የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና! ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ ወር 2019 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በመሆኑም መረጃችሁን ከዚህ ቀደም ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከህዳር 21-30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ይህ መረጃን የማስተሳሰር ሒደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሒደት እንደሚቀጥል ተገልጿል። የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁና ስማችሁ ወደ ሲስተም ያልገባላችሁ ተመዛኞች ስማችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን ይጠበቅባችኋል ተብሏል። @tikvahuniversity
Open in Telegramበአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የገጠመንን ችግር ልናካፍላችሁ እንወዳለን። ወደ ሀገራችን ተመልሰን ቤተሰብን ለመጠየቅ እና የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለማውጣት ከፍተኛ ወጪ እየጠየቀን ይገኛል። ይህ ደግሞ በኢኮኖሚያችን ላይ ከፍተኛ ጫና ስለሚፈጥር፣ መንግስት ጉዳዩን ተመልክቶ ሂደቱን በአቅራቢያችን ባሉ ኤምባሲዎች በኩል በማቃለል መፍትሄ እንዲሰጠን በአክብሮት እንጠይቃለን።" ይህ መልክት በቂ ነው ወይስ የተወሰነ ማስተካከያ ይደረግበት?
Open in Telegramየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT - master's & PhD) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ከትላንት ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ምዝገባ መከፈቱን አመልክቶ ምዝገባው እስከ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ገልጿል። በተሻሻለው ተመን መሠረት ለፈተናውን የሚከፈለው 3,500 ብር መሆኑን ክፍያው የሚፈጸመው በቴሌብር እንደሆነ አሳውቋል። የመመዝገቢያ አድራሻው https://exam.ethernet.edu.et ነው። የፈተና ጣቢያ (ዩኒቨርሲቲና ካምፓስ) በተመዝጋቢዎች ምርጫ የሚወሰን ሲሆን እያንዳንዱ ካምፓስ የተወሰነ የመቀመጫ ብዛት ያለው በመሆኑ መቀመጫ የሞላባቸው ካምፓሶች በምርጫ ዝርዝሩ ውስጥ አይታዩም።
Open in Telegramአሳዛኝ ዜና በወልቂጤ መድረክ ላይ «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ገልጾ ወዲያው ህይወቱ አልፏል💔😭 አመለ ሸጋው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል። ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል። ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል። በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል። በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር። ለባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን ይሁን
Open in Telegram#ETA ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተምረው በ2019 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ ዕጩ ተፈታኝ ለመሆን ሊያጣሯቸው የሚገቡ መስፈርቶችን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስቀምጧል፡፡ ● የተማሩብት ተቋም የተሰጠውን የፈቃድ ጊዜ፣ የትምህርት መስክ እና ካምፓስ ማረጋገጥ፣ ● በትምህርት ላይ ቆይታቸው አራት፣ አምስት እና ስድስት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች በየመርሐግብራቸው ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን ማረጋገጥ፣ ● የተፈታኝ ሙሉ ስም እስከ አያት መኖሩን ማረጋገጥ፣ ● ወደ ተቋሙ በዝውውር የመጡ ተማሪዎች የዝውውር ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ● ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀረቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በትምህርት መስኮችና በካምፓሶች የስነ-ስርዓት ጥሰት የሌላቸው መሆኑ ማረጋገጥ፣ … የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በቀን 09/03/2019 ዓ.ም ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጻፈው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል፡፡ (ሊያጣሯቸው የሚገቡ ሙሉ መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
Open in Telegramህፃናት በአንድ ዓመት ሁለት ክፍል እንዲያልፉ የሚፈቅድ መመሪያ አወጣ‼ ትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ ለቀሩ ህፃናት ሁለተኛ ዕድል የሚሰጥ «መደበኛ ያልሆነ የተፋጠነ ትምህርት መመሪያ ቁጥር 1160/2019» አወጣ። መመሪያው ዕድሜያቸው ከ12-14 ዓመት የሆኑና ከ1ኛ-3ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለ2 ዓመትና ከዚያ በላይ ያቋረጡ ልጆችን (ተፈናቃዮችንና ስደተኞችን ጨምሮ) ተጠቃሚ ያደርጋል።ለሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ወላጅ አልባ ልጆች ቅድሚያ ይሰጣል። በዚህ ፕሮግራም የ4 ዓመቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት በ2 ዓመት ይጠቃለላል (1ኛና 2ኛ ክፍል በአንድ ዓመት ተጨምቆ ወደ 3ኛ፤ 3ኛና 4ኛ ክፍል በአንድ ዓመት ተጨምቆ ወደ 5ኛ ክፍል ያሸጋግራል)። ተማሪዎቹ 5 ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶችን በዓመት ለ650 ሰዓታት የሚማሩ ሲሆን፣ የትምህርት ቤት ምገባና መሠረተ ልማቶችንም በእኩልነት ይጠቀማሉ ነው የተባለው።
Open in TelegramConnections
Mentions
Tikvah-University@tikvahuniversity1 mention