Account

Posts of ትምህርት መረጃ( academic info)

newest first

#3142Text

በ28 ሺህ ዶላር ይሸጥ የነበረው የኤችአይቪ መከላከያ መርፌ በ40 ዶላር ወደ አፍሪካ ገባ‼️ ኤችአይቪን ለመከላከል የሚያስችለውና በዝቅተኛ ዋጋ የሚቀርበው «ሌናካፓቪር» የተሰኘ ፈር ቀዳጅ መድኃኒት ወደ አፍሪካ መግባት መጀመሩን ዓለም አቀፉ የጤና ፈንድ (ግሎባል ፈንድ) አስታውቋል። የመድኃኒቱ የመጀመሪያ ዙር ጭነት ዛምቢያ መድረሱን ተቋሙ ገልጿል። ዩጋንዳ በመጪዎቹ ቀናት እንዲሁም ዚምባብዌ በመጪው ዓመት መጀመሪያ ላይ መድኃኒቱን ይረከባሉ። የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ደረጃ በሚገኝባት አፍሪካ ውስጥ የዚህ መድኃኒት መግባት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች መከላከያውን እንዲያገኙ ትልቅ ተስፋ ፈጥሯል። በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመርፌ መልክ የሚሰጠው ይህ መድኃኒት ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ ወደ 100 በመቶ የሚጠጋ ውጤታማነት አለው። ቀደም ሲል በአሜሪካው «ጊሊያድ ሳይንስስ» ኩባንያ ተዘጋጅቶ የነበረው ዋናው መድኃኒት በዓመት እስከ 28 ሺህ ዶላር ይጠየቅበት ነበር። አሁን ግን በህንዱ «ሄቴሮ» ኩባንያ ተመርቶ የቀረበው ተመሳሳይ መድኃኒት ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ለአንድ ሰው በዓመት 40 ዶላር አካባቢ ብቻ ሆኗል። ሌናካፓቪር የኤችአይቪ ቫይረስን መከላከያ ሽፋን በማጥቃት ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይባዛና ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር ያደርጋል። እ.ኤ.አ. በ2024 በዩጋንዳና በደቡብ አፍሪካ ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ ታዳጊ ልጃገረዶችና ወጣት ሴቶች ላይ በተደረገ ክሊኒካዊ ሙከራ መርፌውን ከወሰዱት መካከል አንዳቸውም በኤችአይቪ አልተያዙም። በዚህም መሠረት የዓለም ጤና ድርጅት መድኃኒቱ ለኤችአይቪ መከላከያነት ጥቅም ላይ እንዲውል ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። በየዕለቱ ከሚዋጡ እንክብሎች ይልቅ ይህ መርፌ ለተጠቃሚዎች እጅግ ምቹ አማራጭ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች አብራርተዋል። ግሎባል ፈንድ የዚህ ርካሽ መድኃኒት ወደ አፍሪካ መግባት በኤችአይቪ ላይ በሚደረገው ጦርነት ትልቅ እመርታ መሆኑን አስታውቋል። ጥራቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት በፍጥነት እንዲዳረስም ያስችላል። እስካሁን በ10 አገራት ውስጥ ከ189 ሺህ በላይ ሰዎች የመጀመሪያውን ዙር መርፌ ወስደዋል። በቀጣይም እ.ኤ.አ. እስከ 2028 መጨረሻ ድረስ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር በመተባበር ቢያንስ ለሦስት ሚሊዮን ሰዎች መድኃኒቱን ለማድረስ ታቅዷል። በሂደትም በ120 ታዳጊ አገራት ተደራሽ ይሆናል።

Open in Telegram
Views1,210−72%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3141Text
Views1,540−64%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3140Text
Views1,740−59%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3138Link preview
Views4,120−4%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3137Photo

አሳዛኝ ዜና በወልቂጤ መድረክ ላይ «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ገልጾ ወዲያው ህይወቱ አልፏል💔😭 አመለ ሸጋው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል። ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል። ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል። በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል። በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር። ለባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን ይሁን

Open in Telegram
Views4,050−6%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3133Photo

#ETA ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተምረው በ2019 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ ዕጩ ተፈታኝ ለመሆን ሊያጣሯቸው የሚገቡ መስፈርቶችን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስቀምጧል፡፡ ● የተማሩብት ተቋም የተሰጠውን የፈቃድ ጊዜ፣ የትምህርት መስክ እና ካምፓስ ማረጋገጥ፣ ● በትምህርት ላይ ቆይታቸው አራት፣ አምስት እና ስድስት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች በየመርሐግብራቸው ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን ማረጋገጥ፣ ● የተፈታኝ ሙሉ ስም እስከ አያት መኖሩን ማረጋገጥ፣ ● ወደ ተቋሙ በዝውውር የመጡ ተማሪዎች የዝውውር ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ● ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀረቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በትምህርት መስኮችና በካምፓሶች የስነ-ስርዓት ጥሰት የሌላቸው መሆኑ ማረጋገጥ፣ … የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በቀን 09/03/2019 ዓ.ም ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጻፈው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል፡፡ (ሊያጣሯቸው የሚገቡ ሙሉ መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)

Open in Telegram
Views4,190−2%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3132Text
Views4,220−2%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#3131Text

የመንግስት ሠራተኞች የፈተና አወቃቀርና ክብደት፦ 1. የባህሪ ብቃቶች (30%) ይህ ክፍል 12 የባህሪ ብቃቶች ተቀምጠዋል፦ 1. ታማኝነትና ሥነ-ምግባር 2. የህዝብ አገልግሎት ቁርጠኝነት 3. የመግባቢያ ክህሎት 4. የቡድን ሥራና ትብብር 5. ችግር የመፍታት ችሎታ 6. በውጤት ላይ ያተኮረ አስተሳሰብ 7. በደንበኛ/ዜጋ ላይ ያተኮረ አገልግሎት 8. የለውጥ አስተዳደር 9. የመሪነት ችሎታ 10. የውሳኔ አሰጣጥ 11. የግጭት አስተዳደር 12. ሙያዊነትና ተግሣጽ 2. የቴክኒክ ብቃቶች (50%) ይህ ክፍል 15 የቴክኒክ ብቃቶች ተዘርዝረዋል፦ 1. የፖሊሲ ልማትና ትንተና 2. ዕቅድና ፕሮግራም አስተዳደር 3. ክትትልና ግምገማ 4. የውሂብ ትንተናና ተጨባጭ ማስረጃ አጠቃቀም 5. የቁጥጥርና ፍተሻ ክህሎት 6. የፕሮጀክት አስተዳደር 7. የአደጋ አስተዳደር 8. ሪፖርት አጻጻፍና ሰነድ አዘጋጅነት 9. የመረጃ አስተዳደር 10. አይሲቲና ዲጂታል ክህሎት 11. የፋይናንስ አስተዳደር መሠረታዊ ዕውቀት 12. የምርምርና ትንተና ክህሎት 13. የጥራት አስተዳደር 14. የግዥና ውል አስተዳደር 15. ከዘርፉ ጋር የተያያዘ ልዩ የቴክኒክ ሙያዊ ዕውቀት 3. የሁኔታ ግምገማና የጉዳይ ትንተና (20%) ይህ ክፍል አመልካቹ በሥራ ላይ በሚያጋጥሙ እውነተኛ የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት እንደሚወስን የሚገመግም ነው። በተለምዶ ሠራተኛው ለሚያጋጥመው ሁኔታ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ የሚጠየቅበት ወይም የተሰጠውን የሥራ ጉዳይ በመተንተን መፍትሔ እንዲያቀርብ የሚጠየቅበት ክፍል ነው። ዓላማው የአመልካቹን የትንተና ችሎታ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ብቃትና በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ የመላመድ አቅም መመዘን ነው። ከሦስቱ ዋና ክፍሎች በተጨማሪ፣ ማዕቀፉ የብቃት ደረጃዎችን (Beginner, Intermediate, Advanced, Expert) እና ለዳይሬክተር ደረጃ ሠራተኞች የሚጠበቁ ልዩ ብቃቶችን (እንደ ስትራቴጂካዊ መሪነት፣ የፖሊሲ ትርጓሜና ትግበራ፣ በአደጋ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የተቋም አስተዳደር፣ የአፈጻጸም አስተዳደር እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ) ይዘረዝራል።

Open in Telegram
Views5,240+22%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#3130Text
Views4,260−1%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3129Text

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራር ቦታዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች እንዲሸፈኑ ተደነገገ። • የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች የአገልግሎት ዘመን በአምስት ዓመት እንዲገደብ የተወሰነሲሆን ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ያላለፉ አመራሮች የመምህርነት ደረጃ ዕድገትና ጥቅማጥቅማቸው ተጠብቆ ወደ ማስተማር ይመለሳሉ። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) የትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተከትሎ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የሚመረጡበትንና የሚመደቡበትን አዲስ አገር አቀፍ መመሪያ አውጥቷል። መመሪያው የሥራ ተነሳሽነት፣ ብቃትና ልምድ ያላቸው አመራሮች ትምህርት ቤቶችን እንዲመሩ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ የምልመላ ሂደቱ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በዞን ወይም በክልልና ከተማ አስተዳደር የትምህርት መዋቅሮች እንደሚከናወን ደንግጓል። በተጨማሪም በትምህርት ቤት አመራርነት ተመልምሎ የተመደበ ማንኛውም አመራር የአገልግሎት ዘመኑ 5 ዓመት እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ከ5 ዓመት ቆይታ በኋላ ለተመሳሳይ መደብ በድጋሚ ተወዳድሮ ማለፍ ካልቻለ ወደ መምህርነት ተመድቦ አቻዎቹ የደረሱበት የደረጃ ዕድገትና ጥቅማጥቅም እንደሚጠበቅለት ተመላክቷል። እንደ አዲሱ መመሪያ ድንጋጌ ለርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር በቅድመ አንደኛ ደረጃ ቢያንስ ዲፕሎማ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) በትምህርት አመራር ወይም በመምህርነት የትምህርት መስክ ማግኘት ግዴታ ተደርጓል። በደረጃ ዕድገት በኩልም አመልካቾች በመምህራን የደረጃ መሰላል መሠረት "ከፍተኛ መሪ መምህር" ደረጃ የደረሱ መሆን የሚጠበቅባቸው ሲሆን ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች፣ በልማት ወደኋላ በቀሩ ወይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች ግን ዝቅተኛው መስፈርት "ተባባሪ መሪ መምህር" እንዲሆን ተወስኗል። በምክትል ርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር በዲሲፕሊን ያልተቀጣ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ እና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት፣ በፈረቃ፣ በሥርዓተ ትምህርት ወይም በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) አስተባባሪነት ቢያንስ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ማሟላት ይጠበቃል። የደረጃ ዕድገትን በተመለከተም መደበኛ ተወዳዳሪዎች "መሪ መምህር" በአስቸጋሪና አርብቶ አደር አካባቢዎች ደግሞ ቢያንስ "ከፍተኛ መምህር" ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባቸው በመመሪያው ተደንግጓል። በሱፐርቫይዘርነት እና በከፍተኛ ሱፐርቫይዘርነት የሥራ መደቦች ላይ ለመመደብ በርዕሰ መምህርነት ወይም በምክትል ርዕሰ መምህርነት ያገለገሉ ባለሙያዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፤ ለከፍተኛ ሱፐርቫይዘርነት በሱፐርቫይዘርነት ቢያንስ የሁለት ዓመት ወይም በርዕሰ መምህርነት የአራት ዓመት አገልግሎት ማሳየት የግድ ይላል። የዕጩ አመራሮች የውድድር ሂደት የመጨረሻዎቹ ሁለት ተከታታይ ዓመታት (የአራት ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ቢያንስ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል። የውድድር ነጥብ አያያዙም የቴክኒክና የባሕርይ ብቃት ምዘና 60 በመቶ (በቅድሚያ ከፈተናው 80% እና ከዚያ በላይ ያመጡ ብቻ የሚያልፉበት)፣ የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ ዝግጅት 20 በመቶ እንዲሁም የዕቅድ ገለጻና ቃለ-መጠይቅ 20 በመቶ ሆኖ በአጠቃላይ ከ100 በመቶ እንደሚሰላ ተደንግጓል። ከነዚህ ሂደቶች በኋላ ከአጠቃላይ ውጤት 70 በመቶ እና ከዚያ በላይ ካስመዘገቡት መካከል አብላጫ ነጥብ ያመጣው ተመድቦ ወደ ሥራ ይሰማራል። መመሪያው የሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማበረታታት ልዩ ድጋፍ ያካተተ ሲሆን፤ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአመራር ቦታዎች (ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህር) ሙሉ በሙሉ በሴቶች እንዲሸፈኑ ወስኗል፤ ሴቶች በማይገኙበት ሁኔታ ብቻ ወንዶች እንዲሳተፉ ይደረጋል። በተጨማሪም ወንድና ሴት ተወዳዳሪዎች በእኩል ውጤት ካጠናቀቁ ቅድሚያው ለሴት ተወዳዳሪ እንደሚሰጥ በግልጽ ሰፍሯል። የአመራር ምልመላና ምደባውን በበላይነት የሚመራና ሰባት አባላት ያሉት "የምልመላና ምደባ ኮሚቴ" በየደረጃው እንዲቋቋም የተወሰነ ሲሆን፣ የመምህራን ማኅበር ሁለት ተወካዮች (አንዷ ሴት የሆነች) በኮሚቴው ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል። በውድድሩ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አመልካች ውሳኔውን ባወቀ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለሲቪል ሰርቪስ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በጽሑፍ የማቅረብ መብት የተሰጠው ሲሆን የተሰጠውን አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተቀበለ አካል ጉዳዩን ለሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት በይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል ተመልክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ/ም

Open in Telegram
Views6,800+58%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#3128Text
Views6,220+45%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#3127Text

ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድን የሚከለክል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለአስተያየት ክፍት ተደርጓል። • በመመሪያው መሰረት ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን ፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከልም አይቻልም። አአ ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትንና ተገቢነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወጥ የሆነ አሰራርና ተጠያቂነትን ለመዘርጋት ያስችላል ያለውን "የአጠቃላይ ትምህርት የእውቅና ፍቃድና እድሳት አሰጣጥ መመሪያ (ረቂቅ)" አዘጋጅቶ በትምህርት ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ክፍት አድርጓል። ረቂቅ መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በሚገኙ የመንግሥት፣ የግል እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይወሰን በርቀት ትምህርት፣ በማጠናከሪያ ትምህርት (ቲቶሪያል)፣ በመሰረታዊ ቋንቋ ማሰልጠኛዎች እና በማማከር አገልግሎት ላይም የሚተገበር ነው። እንደ ረቂቅ መመሪያው ድንጋጌ፣ የትምህርት ተቋማት እውቅና ፈቃድ ለ2 ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እድሳቱም በየሁለት ዓመቱ የሚከናወን ይሆናል። አዲስ ለሚቋቋሙ ተቋማት የሚሰጠው የቅድመ እውቅና ፈቃድ ደግሞ የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ይኖረዋል። የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ (1ኛ-6ኛ ክፍል)፣ የመካከለኛ ደረጃ (7ኛ-8ኛ ክፍል) እና የማጠናከሪያ ትምህርት ፈቃድና እድሳት በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች በኩል ይሰጣል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (9ኛ-12ኛ ክፍል)፣ የቋንቋ ማሰልጠኛዎች፣ የርቀት ትምህርት እና የማማከር አገልግሎቶች እውቅና ፈቃድና እድሳት ደግሞ በማዕከል በትምህርት ቢሮው ደረጃ ይሰጣል። የትምህርት ተቋማት እንደ አገልግሎት ዘርፋቸው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ብቻ ማመልከት እንዳለባቸው ረቂቁ ደንግጓል። በዚህም መሠረት ለአዲስ አጠቃላይ ትምህርት ተቋም የቅድመ እውቅና ማመልከቻ ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዝያ 30፣ ለእውቅና እድሳትና እርከን ማሳደግ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 30 ድረስ ብቻ በአካል ወይም በበይነ-መረብ ማመልከት ይቻላል። የርቀት ትምህርት ለአንደኛ ወሰነ ትምህርት ከግንቦት 1 እስከ ሰኔ 30፣ እንዲሁም ለሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ከኅዳር 1 እስከ ታኅሣሥ 30 ድረስ ማመልከቻዎችን ይቀበላል። የቋንቋ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ደግሞ አገልግሎቱን ከመጀመራቸው 1 ወር አስቀድመው ማመልከት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያላመለከተ ተቋም አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችል ተመላክቷል። አዲስ የሚቋቋሙ ተቋማት የቅድመ እውቅና ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 85 በመቶ ማሟላት አለባቸው፤ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ቀሪውን 15 በመቶ አሟልተው 100 በመቶ ሲደርሱ ሙሉ እውቅና ያገኛሉ። በመጀመሪያው ዙር ምዘና 100 በመቶ ያሟላ ተቋም ግን በቀጥታ ሙሉ እውቅና ይሰጠዋል። በረቂቁ ድንጋጌ መሰረት የተሟላ እውቅና ፈቃድ እና እድሳት የሚሰጠው መመዘኛዎቹን 100 በመቶ ለሚያሟሉ ተቋማት ብቻ ነው። ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ብቻ የተቋቋሙ ማዕከላት ግን የእውቅና እና የእድሳት ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 65 በመቶ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው በረቂቁ ተመላክቷል። ምዘና ተካሂዶ ውጤቱ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚገለጽ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር ያላሟሉ ተቋማት በ30 ቀናት ውስጥ ክፍተታቸውን አርመው ለአንድ ጊዜ ብቻ ዳግም እንዲመዘኑ ይደረጋል። እንዲሁም ተቋማት ባስመዘገቡት ግብዓት መሠረት እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከኅዳር 1 ጀምሮ ድህረ-እውቅና ምዘና ይካሄዳል። የትምህርት ተቋማት ስለሚሰሩበት ግቢ እና ሰነዶች በተመለከተም ተቋማቱ በራሳቸው ግቢ የሚሰሩ ከሆነ የተረጋገጠ የይዞታ ካርታ ማቅረብ አለባቸው። የራሳቸው ሕንፃ የሌላቸው ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የትምህርት ዘመን የሚቆይ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ውል እና የይዞታ ካርታ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይዞታቸው ካርታ የሌለው ከሆነ ለአንድ ጊዜ እድሳት ብቻ የሚያገለግል የባለቤትነት የመሬት ይዞታ ደብተር ወይም ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ባለሙያዎች በመምህርነት ሙያ ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና ቢያንስ የአምስት ዓመት የማስተማር ልምድ ሊኖራቸው ይገባል። የርቀት ትምህርት ተቋማትም የተማሪዎች የፊት ለፊት ገለጻና የቤተ-ሙከራ አገልግሎት የሚሰጡበትን ቦታ ከትምህርት ቤቶች ጋር ውል ገብተው ማቅረብ እንዳለባቸው ተደንግጓል። ተቋማት ተማሪዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመቀበል ግዴታ ያለባቸው ሲሆን አማካይ ውጤትን፣ የባህሪ ሪፖርትን፣ ደረጃን ወይም የቅድመ ቅበላ ፈተናን መሠረት በማድረግ በተማሪዎች ላይ ቅድመ ሁኔታ መጣል አይቻልም። ፆታን፣ ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ ማህበራዊ መሠረትን፣ ፖለቲካዊ አመለካከትን ወይም የልዩ ፍላጎት ሁኔታዎችን (አካላዊ፣ አእምሯዊና ስነ-ልቦናዊ) መነሻ በማድረግ መከልከልም ሆነ አድሎ መፈጸም በጥብቅ የተከለከለ ነው። ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድ አይችልም ይህን ጥሶ የተገኘ ተቋም ምክርና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ካላስተካከለ ለ1 ዓመት እውቅና ፈቃዱ ይታገዳል። ማጠናከሪያ ትምህርት በወላጆችና ተማሪዎች ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆን አለበት ተብሏል። ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከል እንደማይቻል መመሪያው አስቀምጧል። ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ/ም

Open in Telegram
Views6,300+47%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#3124Text
Views12,200+184%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3123Text

#ግስ (#Verb) 1. ትርጉም (Definition): ግስ ማለት ድርጊትን (action)፣ ሁኔታን (state)፣ ክስተትን (occurrence) ወይም ባለቤትነትን (possession) የሚገልጽ ቃል ነው። · ምሳሌ፦ She writes a letter. (ድርጊት) · ምሳሌ፦ He seems happy. (ሁኔታ) · ምሳሌ፦ An accident happened yesterday. (ክስተት) · ምሳሌ፦ She has a car. (ባለቤትነት) 2. የግስ ዓይነቶች (Types of Verbs): · ዋና ግስ (Main Verb / Principal Verb): የዓረፍተ ነገሩን ዋና ትርጉም የሚሸከም። · ምሳሌ፦ He plays cricket. / She knows the answer. / They built a house. · ረዳት ግስ (Helping Verb / Auxiliary Verb): ዋናው ግስ ጊዜ (tense)፣ ጥያቄ (question)፣ አሉታዊ (negative) ወዘተ እንዲፈጥር የሚረዳ። · ምሳሌ፦ She is reading. / They have finished. / Do you understand? 3. ረዳት ግሶች (Auxiliary Verbs): · ቀዳሚ ረዳቶች (Primary Auxiliaries): · be: am, is, are, was, were, be, being, been · have: have, has, had · do: do, does, did · አጠቃቀሞች፦ be (ቀጣይ ጊዜ፣ ተገብሮ ድምጽ)፣ have (ፍጹም ጊዜያት)፣ do (ጥያቄዎች፣ አሉታዊነት፣ አፅንዖት)። · ሞዳል ረዳቶች (Modal Auxiliaries): · can, could, may, might, shall, should, will, would, must, ought to · ምሳሌ፦ You must obey the rules. / She can swim. / We should help others. 4. ተሻጋሪ እና ተሻጋሪ ያልሆኑ ግሶች (Transitive and Intransitive Verbs): · ተሻጋሪ ግስ (Transitive Verb): ቀጥተኛ ተሳቢ (direct object) ይወስዳል። "ምን?" ወይም "ማን?" ብለን መጠየቅ እንችላለን። · ምሳሌ፦ She bought a book. / He kicked the ball. · ተሻጋሪ ያልሆነ ግስ (Intransitive Verb): ቀጥተኛ ተሳቢ አይወስድም። · ምሳሌ፦ The baby cried. / Birds fly. / He slept peacefully. · አንዳንድ ግሶች ሁለቱም ሊሆኑ ይችላሉ፦ · She runs every morning. (ተሻጋሪ ያልሆነ) · She runs a business. (ተሻጋሪ) 5. የተወሰኑ እና ያልተወሰኑ ግሶች (Finite and Non-finite Verbs): · የተወሰነ ግስ (Finite Verb): ጊዜን ያሳያል እና ከርዕሰ ጉዳይ (subject) ጋር ይስማማል። · ምሳሌ፦ He works hard. / They work hard. / She went home. · ያልተወሰነ ግስ (Non-finite Verb): ጊዜን በተናጥል አያሳይም ወይም ከርዕሰ ጉዳይ ጋር አይስማማም። ሦስት ዓይነት ናቸው፦ 1. Infinitive (የቃል መሠረት): to read, to write 2. Gerund (የግስ ስም): Reading is useful. 3. Participle (ተሳቢ): a broken chair. 6. መደበኛ እና ያልተለመዱ ግሶች (Regular and Irregular Verbs): · መደበኛ ግሶች (Regular verbs): -ed ወይም -d ይጨምራሉ። · work - worked - worked · play - played - played · ያልተለመዱ ግሶች (Irregular verbs): የተለያዩ ቅርጾችን ይከተላሉ። · go - went - gone · write - wrote - written · speak - spoke - spoken · take - took - taken · see - saw - seen · eat - ate - eaten 7. አገናኝ እና የድርጊት ግሶች (Linking and Action Verbs): · የድርጊት ግሶች (Action Verbs): ድርጊትን ይገልጻሉ። · ምሳሌ፦ She dances beautifully. / He opened the door. · አገናኝ ግሶች (Linking Verbs): ርዕሰ ጉዳዩን ከመግለጫ (description) ወይም ከማንነት (identity) ጋር ያገናኛሉ። · ምሳሌ፦ She is intelligent. / The soup tastes delicious. / He became a doctor. · የተለመዱ አገናኝ ግሶች፦ be, seem, become, appear, remain, feel, look, smell, sound, taste. 8. ጠቃሚ የግስ ቅርጾች (Important Verb Forms): · V1 (write): Base form (የቃል መሠረት) · V2 (wrote): Simple past (ቀላል ያለፈ ጊዜ) · V3 (written): Perfect tenses, passive voice (ፍጹም ጊዜያት፣ ተገብሮ ድምጽ) · V4 (writing): Continuous forms, gerund (ቀጣይ ቅርጾች፣ የግስ ስም) · V5 (writes): Third-person singular present (የሦስተኛ ሰው ነጠላ የአሁን ጊዜ) 9. ርዕሰ-ግስ ስምምነት (Subject-Verb Agreement): · ግሱ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በቁጥር (number) እና በሰው (person) መስማማት አለበት። · He plays cricket. · They play cricket. · Each student has a book. · The list of items is on the table. · Neither answer is correct. · በቀላል የአሁን ጊዜ (simple present tense)፣ የሦስተኛ ሰው ነጠላ ርዕሰ ጉዳይ (third-person singular subject) በአጠቃላይ በ -s ወይም -es የሚጨርስ የግስ ቅጥያ ይወስዳል። 10. የተለመዱ የግስ ህጎች (Common Verb Rules): 1. ከ did/does/did በኋላ ሁልጊዜ V1 ይጠቀሙ። (ምሳሌ፦ Did he go?) 2. ከሞዳል ግሶች በኋላ ሁልጊዜ V1 ይጠቀሙ። (ምሳሌ፦ She can sing.) 3. ከ have/has/had በኋላ ሁልጊዜ V3 ይጠቀሙ። (ምሳሌ፦ He has written a letter.) 4. ቀጣይ ጊዜ (Present continuous) ለመፍጠር am/is/are + V-ing ይጠቀሙ። 5. ተገብሮ ድምጽ (Passive voice) ለመፍጠር be + V3 ይጠቀሙ። 6. ከ to በኋላ (infinitive) V1 ይጠቀሙ። (ምሳሌ፦ I want to learn.) 7. ከቅድመ-ግስ (preposition) በኋላ አብዛኛውን ጊዜ V-ing ይጠቀሙ። (ምሳሌ፦ He is interested in learning.) 11. የተለመዱ ስህተቶች (Common Errors):

Open in Telegram
Views10,500+145%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—