በሮሜ መልእክት ጥናት ላይ ለተጠየቁ ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ 1) ምግብን በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ 2) <<ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።>> ሮሜ 5:14 ኃጢአት ባልሰሩት ላይ ለምን ሞት ነገሰ ? ኃጢአት ያልሰሩት የተባሉትስ እነማን ናቸው ? ከሙሴ በኋላስ ሞት መንገሱን አቁሟል ወይ ? 3) <<የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።>> ሮሜ 8:34 በዚህ ጥቅስ ላይ ሁለት ጥያቄ ተነስቷል። በአንዳንድ መጻሕፍት የሚማልደው የሚለውን የሚፈርደው ይለዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎሙን በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ 1ኛው ነው። ሌላው የሚማልደው የሚለው ቢብራራልን ለሚል ጥያቄዎች በዚህ ሪከርድ መልስ ተሰጥቷል። ሽር አድርጉ ለጓደኞቻችሁ https://t.me/Stpoulos
Open in Telegramአቤል ተፈራ በላይ
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 3, 2026 | 651 |
| Nov 10, 2026 | 791 |
Latest posts
ኢዮብን እንዴት ዋልክ ቢሉት በጤናም በህመምም እያለ በማግኘትም በማጣትም ሆኖ ሚስቱ ከድታው ልጆቹ ሞተውበት ዘመዶቹ ትተውት ሰውነቱ ቆስሎና ተልቶ በድንጋይ እያከከ መልሱ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ነበረ! ወዳጄ ሆይ እንደምን አመሸህ
Open in Telegramአለመጸለይ "አለመኖርና እየኖሩ አለመስራት ሁለቱም እኩል ናቸው"እንዳለው ፈላስፋው ካልጸለይክ እየኖርክ አይደለም። ወንድሜ እጅን ከኪስ ውስጥ ከቶ መሰላል መውጣት እንደማይቻል ሁሉ ያለ ጸሎትም መንፈሳዊ ሰው መሆን አትችልም። ስለዚህ እጅህን ለጸሎት ዘርጋው። በእርግጥ "ለጸሎት ጊዜ አጣሁ" ልትል ትችላለህ ግን እኮ ለመብላት ጊዜ አለህ። ሰው የቱንም ያክል ጊዜ ባይኖረው ለምግብ ግን ጊዜ አለው። ስለዚህ በምግብ ጊዜ እንኳ ጸልይ በቀን ሦስት ጊዜ ብትበላ የምግቡ መጀመሪያና መጨረሻ እንኳ ብጸልይ በቀን ስድስት ጊዜ ጸለይክ ማለት ነው። ሰው ሆነህ ካልጸለይክ እውነት እልሃለሁ እንደ እንሰሳ እየኖርክ እንደ ሰው እየተመገብክ ነው ማለት ነው። ጸሎት እኛ ለመዳን ፈቃዳችንን የምንገልጽበት መንገድ ነውና ጸልይ። ጸሎት ለመጀመር ፈልጋችሁ ከምን መጀመር ግራ ለገባችሁ በውስጥ መስመር አውሩኝ @Abellteferaaa የጽሑፉ ባለቤት በክርስቶስ ካሳ ዘኮንቦልቻ
Open in Telegramአስፈሪው ቀን ደሴ ልትያዝ በዙሪያዋ አስፈሪ ጦርነት እየተደረገ ባለበት በዚያ አስጨናቂ ጊዜ ከባሕር ዳር ሆኜ ደሴ መናፈሻ ተርሚናል ኮንዶሚንየም ወደምትኖረው ታላቅ እህቴ ስልክ ደወልኩ። ድምጿ በከባድ ፍርሃት ተውጦ ነበር "ገብተዋል... ቤት ለቤት እያንኳኩ ነው... ወይኔ በቃ ሊገሉን ነው!" ስትለኝ ስልኩ ተቋረጠ። ያኔ ሰማይና ምድሩ ዞረብኝ። በዚያች ጠባብ ቤት ውስጥ ታናናሽ ወንድሞቼ የእህቴ ልጆች የእህቴ ባለቤት... በአጠቃላይ ስድስት የቤተሰቤ አባላት ነበሩ። "ይህንን መርዶ እናቴ እንዴት ልትቋቋመው ነው? ይሄንን ሁሉ ሐዘን እንዴት ልትሰማ ነው?" የሚለው ሀሳብ ሲመጣብኝ ፊቴ ምንም ሳይቀየር እንባዬ እንደ ጎርፍ ይፈስ ጀመር ሰማይና ምድሩ ተገላበጠብኝ። በጭንቀቴ መሃል ቀጥታ ተንበረከኩ። "አምላከ ኢየሱስ ሞዕ እርዳኝ! ቤተሰቦቼን ጠብቃቸው! አደራ በተወደደው ባለሟልህ በቅዱስ እስጢፋኖስ እለምንሃለሁ፤ ክፉ አታሳማኝ" ብዬ በጸሎት ተማጸንኩ። በመቀጠልም፣ "የክብርህን መግለጫ ስላደረክልኝ ነገር ለማመስገን፣ ከወልድያ እስከ ኃይቅ እስጢፋኖስ በእግሬ ተጉዤ እመጣለሁ" ብዬ ስዕለት ተሳልኩ፤ ተነስቼም እንባዬን ጠረግሁ። በተፈጥሮዬ ልመናዬን በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት አቀርባለሁ እንጂ፣ ስዕለት የመሳል ልምድ አልነበረኝም። ነገር ግን ያ አስጨናቂ ሰዓት ከአቅሜ በላይ ሲሆን ይህንን ታላቅ ቃል ለእግዚአብሔር ገባሁ። እዚህ ላይ ሁላችንም ልናስተውለው የሚገባ አንድ ትልቅ መንፈሳዊ እውነት አለ፤ ስዕለት ከመሳልህ በፊት ልትሳል ካሰብከው ነገር ነጻ ነህ፤ ከተሳልክ በኋላ ግን ለእግዚአብሔር ባለ ዕዳ ትሆናለህ። ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ በመክብብ 5፥4-5 ላይ በግልጽ ሲያስቀምጠው፣ "ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልክ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ በሰነፎች ደስ አይለውምና የተሳልኸውን ፈጽም። ተስለህ የማትፈጽም ከመሆንህ ባትሳል ይሻላል" በማለት የገባነውን ቃል ኪዳን መፈጸም ምን ያህል ክብደት እንዳለው ያስተምረናል። እንዲሁም በዘዳግም 23፥21 ላይ "ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልክ ጊዜ... አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፣ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈልን አትዘግይ" ይላል። እግዚአብሔር በዚያች አስፈሪ ቀን የቤተሰቦቼን ሕይወት በቸርነቱ ጠብቆልኛል። አሁን ደግሞ የገባሁትን ቃል፣ ያንን የተቀደሰ ዕዳ የመክፈል ግዴታ አለብኝ። ስዕለት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባው ውል በመሆኑ፣ በችግራችን ጊዜ በለቅሶ የገባነውን ቃል በደስታችን ጊዜ መርሳት የለብንም። እግዚአብሔር የገባነውን ቃል የምንፈጽምበትን ጸጋና ጤና ያድለን። እናንተስ በሕይወታችሁ በጭንቀት ሰዓት ገብታችሁት ገና ያልፈጸማችሁት ስዕለት ይኖር ይሆን?
Open in Telegramእንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰዎት! አዲሱን ዓመት በበጎ ሥራ እና በበረከት እንጀምር። ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን አገልግሎት ለመደገፍ እና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የ 200 ብር ቻሌንጅ አዘጋጅቷል። እርስዎም አቅም በፈቀደ መጠን በዚህ ቻሌንጅ ላይ በመሳተፍ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት እንዳይቋረጥ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያድርጉ፤ የቅዱሳኑም በረከት ተካፋይ ይሁኑ! የማኅበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000764435617 ይህን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት አብሮነትዎን ያሳዩን። መልካም አዲስ ዓመት!
Open in Telegramበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦ የሰዎች ውድቀት፦ አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣ የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም
Open in Telegramታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቁልቢ ገብርኤል ከሐምሌ 17-20 ለአራት ተከታታይ ቀናት ትኬት ለመቁረጥ 0935256161 መሌ አርሴማ ጉንደር በር 0963678818 ጌጤ ጫማ ማደሻ አዳጎ 0967383005 ኤርምያስ ግእዝ ፎቶ ቤት ለበለጠ መረጃ 0909802404 0967522055
Open in Telegramበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት የሁለተኛው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። በክፍል 1 ትምህርታችን የላኩላችሁን PDF እንዳነበባችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት ክፍል 2 ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሁለት ሰነድ ውስጥ የሰውን ልጅ ውድቀትና የስደት ታሪክ ከመመልከታችን በፊት ፈጣሪ በጥንተ ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሰጠውን ወደር የለሽ ክብርና ልዕልና በ22ቱ ፍጥረታት አውድ ውስጥ እንመለከታለን። በመቀጠልም ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀጥተኛው ቃል ባይቀመጥም በባሕርዩ ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ውል የነበረውን የአዳምና የእግዚአብሔርን ግንኙነት የቃል ኪዳኑን አራት መሠረታዊ ዓምዶች (የቃል ኪዳን ሰጭ ተቀባይ ተስፋና ምልክት እንዲሁም የሚጸናበትን ሁኔታ) ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር እንመረምራለን። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይሀንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
Open in TelegramConnections
Similar channels
- Catholic Web News Network@catholicbReligion2.83K
- GRACE LIFE COMMUNITY CHURCH@gracelifecommunitychurchReligion2.82K
Fursaan Media@fursaan_mediaReligion2.81K
AL-RISALA HUMANITY CENTER@alrisala1Religion2.78K
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹@orthodox_tewahedo23Religion2.78K
የአንዋር መስጂድ ደርሶች@anwardersReligion2.98K
ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት@hiwotemenekosatReligion2.98K- ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን@yhbchawassaReligion2.99K