Account

Posts of አቤል ተፈራ በላይ

newest first

#772Audio
Views791+10%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#769Text
Views1,620+125%vs avg
Forwards—
Reactions39
Comments—
#768Text

አስፈሪው ቀን ደሴ ልትያዝ በዙሪያዋ አስፈሪ ጦርነት እየተደረገ ባለበት በዚያ አስጨናቂ ጊዜ ከባሕር ዳር ሆኜ ደሴ መናፈሻ ተርሚናል ኮንዶሚንየም ወደምትኖረው ታላቅ እህቴ ስልክ ደወልኩ። ድምጿ በከባድ ፍርሃት ተውጦ ነበር "ገብተዋል... ቤት ለቤት እያንኳኩ ነው... ወይኔ በቃ ሊገሉን ነው!" ስትለኝ ስልኩ ተቋረጠ። ያኔ ሰማይና ምድሩ ዞረብኝ። በዚያች ጠባብ ቤት ውስጥ ታናናሽ ወንድሞቼ የእህቴ ልጆች የእህቴ ባለቤት... በአጠቃላይ ስድስት የቤተሰቤ አባላት ነበሩ። "ይህንን መርዶ እናቴ እንዴት ልትቋቋመው ነው? ይሄንን ሁሉ ሐዘን እንዴት ልትሰማ ነው?" የሚለው ሀሳብ ሲመጣብኝ ፊቴ ምንም ሳይቀየር እንባዬ እንደ ጎርፍ ይፈስ ጀመር ሰማይና ምድሩ ተገላበጠብኝ። በጭንቀቴ መሃል ቀጥታ ተንበረከኩ። "አምላከ ኢየሱስ ሞዕ እርዳኝ! ቤተሰቦቼን ጠብቃቸው! አደራ በተወደደው ባለሟልህ በቅዱስ እስጢፋኖስ እለምንሃለሁ፤ ክፉ አታሳማኝ" ብዬ በጸሎት ተማጸንኩ። በመቀጠልም፣ "የክብርህን መግለጫ ስላደረክልኝ ነገር ለማመስገን፣ ከወልድያ እስከ ኃይቅ እስጢፋኖስ በእግሬ ተጉዤ እመጣለሁ" ብዬ ስዕለት ተሳልኩ፤ ተነስቼም እንባዬን ጠረግሁ። በተፈጥሮዬ ልመናዬን በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት አቀርባለሁ እንጂ፣ ስዕለት የመሳል ልምድ አልነበረኝም። ነገር ግን ያ አስጨናቂ ሰዓት ከአቅሜ በላይ ሲሆን ይህንን ታላቅ ቃል ለእግዚአብሔር ገባሁ። እዚህ ላይ ሁላችንም ልናስተውለው የሚገባ አንድ ትልቅ መንፈሳዊ እውነት አለ፤ ስዕለት ከመሳልህ በፊት ልትሳል ካሰብከው ነገር ነጻ ነህ፤ ከተሳልክ በኋላ ግን ለእግዚአብሔር ባለ ዕዳ ትሆናለህ። ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ በመክብብ 5፥4-5 ላይ በግልጽ ሲያስቀምጠው፣ "ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልክ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ በሰነፎች ደስ አይለውምና የተሳልኸውን ፈጽም። ተስለህ የማትፈጽም ከመሆንህ ባትሳል ይሻላል" በማለት የገባነውን ቃል ኪዳን መፈጸም ምን ያህል ክብደት እንዳለው ያስተምረናል። እንዲሁም በዘዳግም 23፥21 ላይ "ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልክ ጊዜ... አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፣ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈልን አትዘግይ" ይላል። እግዚአብሔር በዚያች አስፈሪ ቀን የቤተሰቦቼን ሕይወት በቸርነቱ ጠብቆልኛል። አሁን ደግሞ የገባሁትን ቃል፣ ያንን የተቀደሰ ዕዳ የመክፈል ግዴታ አለብኝ። ስዕለት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባው ውል በመሆኑ፣ በችግራችን ጊዜ በለቅሶ የገባነውን ቃል በደስታችን ጊዜ መርሳት የለብንም። እግዚአብሔር የገባነውን ቃል የምንፈጽምበትን ጸጋና ጤና ያድለን። እናንተስ በሕይወታችሁ በጭንቀት ሰዓት ገብታችሁት ገና ያልፈጸማችሁት ስዕለት ይኖር ይሆን?

Open in Telegram
Views1,730+140%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#767Text
Views1,440+100%vs avg
Forwards—
Reactions25
Comments—
#765Text

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦ የሰዎች ውድቀት፦ አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣ የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም

Open in Telegram
Views2,090+190%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#763Text

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት የሁለተኛው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። በክፍል 1 ትምህርታችን የላኩላችሁን PDF እንዳነበባችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት ክፍል 2 ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሁለት ሰነድ ውስጥ የሰውን ልጅ ውድቀትና የስደት ታሪክ ከመመልከታችን በፊት ፈጣሪ በጥንተ ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሰጠውን ወደር የለሽ ክብርና ልዕልና በ22ቱ ፍጥረታት አውድ ውስጥ እንመለከታለን። በመቀጠልም ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀጥተኛው ቃል ባይቀመጥም በባሕርዩ ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ውል የነበረውን የአዳምና የእግዚአብሔርን ግንኙነት የቃል ኪዳኑን አራት መሠረታዊ ዓምዶች (የቃል ኪዳን ሰጭ ተቀባይ ተስፋና ምልክት እንዲሁም የሚጸናበትን ሁኔታ) ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር እንመረምራለን። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይሀንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

Open in Telegram
Views2,260+213%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#761Photo
Views1,770+145%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#760Photo
Views1,550+115%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#759Photo
Views1,530+112%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#757Text

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምሀርት መርሐ-ግብር መሠረት የመጀመሪያው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን ጥልቅና መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሳምንት የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወልድያ ኢትዮጵያ

Open in Telegram
Views1,510+109%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—
#754Text
Views2,010+179%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#753Text
Views2,210+207%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#752Text
Views2,650+268%vs avg
Forwards—
Reactions43
Comments—
#750Photo
Views3,580+397%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—
#749Text
Views2,310+220%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—