Account

AAU - Muslim Students Union

This is the official channel of AAU-MSU. Group: @aaumsu_discussion Youtube: youtube.com/@aaumsu Twitter: x.com/aaumsu12 Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303 Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1 Email: [email protected]

Username
@aaumsu
Subscribers7,841
Avg views per post, 7d432last 7 days
ERR5.51%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 28, 2026713
Nov 29, 2026412

Most viewed this month

  1. 01

    🌾 የብርሃን ዱካዎች ክፍል 15 " በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ" እስቲ አንድ ዓለም አስቡ፤ በከተማዋ ጎዳናዎችና መንደሮች ውስጥ አንድ አዋጅ ነጋሪ ከሙስሊሞች የግምጃ ቤት (በይቱል ማል) የተሞሉ የወርቅና የብር ከረጢቶችን ተሸክሞ እየዞረ በታላቅ ድምፅ ይጣራል፦ “ድሆች የት አላችሁ? ምስኪኖችስ የት ናችሁ? በዕዳ የተያዛችሁ ባለዕዳዎች የት አላችሁ? ማግባት እየፈለጋችሁ መህር (ጥሎሽ) ያጣችሁ ወጣቶችስ የት ናችሁ? ኑና ከአላህ ገንዘብ ውሰዱ!”... ነገር ግን የሚወስድ አንድም ሰው አልተገኘም! ይህ ትዕይንት በምናብ የተሳለ ሕልም ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ የኺላፋ ዘመን በሁለት ዓመት ከጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ በሙስሊሞች ምድር ላይ በገሃድ የታየ እውነታ ነበር::! ዑመር በየሀገሩ ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፈ ➤ ዕዳ ያለበት ሰው ሁሉ ዕዳው ከግምጃ ቤት እንዲከፈልለት ➤ ማግባት እየፈለገ አቅም ያጣ ወጣት ሁሉ መንግሥት እንዲድረው ➤ማረስ ወይም መነገድ ፈልጎ መነሻ ካፒታል ያጣ ሰው ከግምጃ ቤት እንዲሰጠው ➤እንዲያውም በእስልምና ጥላ ሥር የሚኖሩ (አህሉ ዚማ) ድሃና አቅመ ደካማ አይሁዶችና ክርስቲያኖች እንኳ ከግምጃ ቤት ቋሚ ደመወዝ እንዲቆረጥላቸው አደረገ ጥቂት ወራት እንኳ ሳያልፉ የመንግሥት ግምጃ ቤቶች በሐላል ገንዘብ ተትረፈረፉ፤ የአፍሪካ (ቱኒዚያ አካባቢ) ገዥ የነበረው የሕያ ኢብኑ ሰዒድ ለኸሊፋው የሚያስገርም ደብዳቤ ጻፈ፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! የዘካና የሰደቃ ገንዘቦችን ሰብስበን የሚሰጣቸው ድሆችን ብንፈልግ አንድም ድሃ አጣን! ታዲያ ገንዘቡን ምን እናድርገው?” ዑመርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በገንዘቡ ባሪያዎችን እየገዛችሁ ለአላህ ብላችሁ ነፃ አውጧቸው!” የዚህ ታላቅ ሰው ርኅራኄ ከሰው ልጆች አልፎ የምድር አራዊትንና የሰማይ አእዋፍን እስከመድረስ ደረሰ! ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን ያንን ዘመን ተሻጋሪ ቃል ተናገረ፦ ✨✨✨ “በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ!” ✨✨✨ በእነዚያ ብሩህ ቀናት ውስጥ፣ ወደ ደማስቆ ቤተ-መንግሥት ከንጉሥ ወይም ከሚኒስትር ያልተላከ አንድ ልዩ ደብዳቤ ደረሰ... ደብዳቤው በግብፅ ምድር ከምትኖር “ፈርቱና አል-ሰውዳእ” ከተባለች አንዲት ድሃ ሴት የተላከ ነበር እንዲህ ስትል ጻፈች፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! እኔ ምስኪን ሴት ነኝ፤ ሕይወቴን የምመራባቸው ጥቂት ዶሮዎች አሉኝ። ነገር ግን የቤቴ አጥር አጭር ስለሆነ ውሾችና ተኩላዎች እየዘለሉ ገብተው ዶሮዎቼን ይበሉብኛል... ስለዚህ ወይ አጥሬን አስረዝምልኝ፣ አለበለዚያ በቂያማ ቀን በአላህ ፊት እከስሃለሁ!” ኸሊፋው ደብዳቤውን ሲያነብ ሰውነቱ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ! ቅሬታዋን አልናቀውም ይልቁንም ወዲያውኑ ለግብፅ ገዥ (ለአዩብ ኢብኑ ሹረሕቢል) እንዲህ የሚል ትዕዛዝ ጻፈ፦ “ይህ ደብዳቤዬ እንደደረሰህ፣ ራስህ በአካል ወደ ፈርቱና ቤት ሄደህ ዶሮዎቿ ከአውሬ እስኪድኑ ድረስ አጥሯን በገዛ እጅህ ገንባላት!” በዚህም መሠረት ስለ አንዲት ዶሮ እንኳ አላህ ይጠይቀኛል ብሎ በሚፈራ ኸሊፋ ትዕዛዝ፣ የግብፅ ገዥ ራሱ ወጥቶ የድሃዋን ሴት አጥር ገነባላት! እንዴት ያለ ልብ ነው! እንዴት ያለ የአላህ ፍርሃት ነው! ሥልጣንን ለመግዛት ሳይሆን ለማገልገል፣ ሀብትን ለማከማቸት ሳይሆን የተቸገሩትን ለማስታገስ የተጠቀመ ታላቅ ሰው! የሰውን እንባ ብቻ ሳይሆን የአንዲትን ድሃ ሴት ዶሮዎች ጭምር በአደራነት የተመለከተ ኸሊፋ! ምንኛ ውብ አርአያ ነው! رحمه الله رحمة واسعة. #ሚሽካት የብርሃን ዱካዎች ይቀጥላል....⚖️✨ @aaumsu

    Text
    Views713
    Forwards—
    Reactions10
    Comments—
  2. 02
    Views504
    Forwards—
    Reactions7
    Comments—
  3. 03
    Views483
    Forwards—
    Reactions13
    Comments—
  4. 04
    Views450
    Forwards—
    Reactions14
    Comments—

Latest posts

#7115Photo
Views4320%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#7114Photo
Views4310%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#7112Photo
Views411−5%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#7110Text
Views483+12%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#7108Text
Views413−4%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—

All posts