Кабинет
AAU - Muslim Students Union

AAU - Muslim Students Union

This is the official channel of AAU-MSU. Group: @aaumsu_discussion Youtube: youtube.com/@aaumsu Twitter: x.com/aaumsu12 Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303 Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1 Email: [email protected]

Юзернейм
@aaumsu
Подписчики7 841
Просмотров на пост, 7 дн.432за 7 дней
ERR5,51 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
28 нояб. 2026 г.713
29 нояб. 2026 г.412

Самые просматриваемые за месяц

  1. 🌾 የብርሃን ዱካዎች ክፍል 15 " በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ" እስቲ አንድ ዓለም አስቡ፤ በከተማዋ ጎዳናዎችና መንደሮች ውስጥ አንድ አዋጅ ነጋሪ ከሙስሊሞች የግምጃ ቤት (በይቱል ማል) የተሞሉ የወርቅና የብር ከረጢቶችን ተሸክሞ እየዞረ በታላቅ ድምፅ ይጣራል፦ “ድሆች የት አላችሁ? ምስኪኖችስ የት ናችሁ? በዕዳ የተያዛችሁ ባለዕዳዎች የት አላችሁ? ማግባት እየፈለጋችሁ መህር (ጥሎሽ) ያጣችሁ ወጣቶችስ የት ናችሁ? ኑና ከአላህ ገንዘብ ውሰዱ!”... ነገር ግን የሚወስድ አንድም ሰው አልተገኘም! ይህ ትዕይንት በምናብ የተሳለ ሕልም ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ የኺላፋ ዘመን በሁለት ዓመት ከጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ በሙስሊሞች ምድር ላይ በገሃድ የታየ እውነታ ነበር::! ዑመር በየሀገሩ ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፈ ➤ ዕዳ ያለበት ሰው ሁሉ ዕዳው ከግምጃ ቤት እንዲከፈልለት ➤ ማግባት እየፈለገ አቅም ያጣ ወጣት ሁሉ መንግሥት እንዲድረው ➤ማረስ ወይም መነገድ ፈልጎ መነሻ ካፒታል ያጣ ሰው ከግምጃ ቤት እንዲሰጠው ➤እንዲያውም በእስልምና ጥላ ሥር የሚኖሩ (አህሉ ዚማ) ድሃና አቅመ ደካማ አይሁዶችና ክርስቲያኖች እንኳ ከግምጃ ቤት ቋሚ ደመወዝ እንዲቆረጥላቸው አደረገ ጥቂት ወራት እንኳ ሳያልፉ የመንግሥት ግምጃ ቤቶች በሐላል ገንዘብ ተትረፈረፉ፤ የአፍሪካ (ቱኒዚያ አካባቢ) ገዥ የነበረው የሕያ ኢብኑ ሰዒድ ለኸሊፋው የሚያስገርም ደብዳቤ ጻፈ፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! የዘካና የሰደቃ ገንዘቦችን ሰብስበን የሚሰጣቸው ድሆችን ብንፈልግ አንድም ድሃ አጣን! ታዲያ ገንዘቡን ምን እናድርገው?” ዑመርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በገንዘቡ ባሪያዎችን እየገዛችሁ ለአላህ ብላችሁ ነፃ አውጧቸው!” የዚህ ታላቅ ሰው ርኅራኄ ከሰው ልጆች አልፎ የምድር አራዊትንና የሰማይ አእዋፍን እስከመድረስ ደረሰ! ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን ያንን ዘመን ተሻጋሪ ቃል ተናገረ፦ ✨✨✨ “በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ!” ✨✨✨ በእነዚያ ብሩህ ቀናት ውስጥ፣ ወደ ደማስቆ ቤተ-መንግሥት ከንጉሥ ወይም ከሚኒስትር ያልተላከ አንድ ልዩ ደብዳቤ ደረሰ... ደብዳቤው በግብፅ ምድር ከምትኖር “ፈርቱና አል-ሰውዳእ” ከተባለች አንዲት ድሃ ሴት የተላከ ነበር እንዲህ ስትል ጻፈች፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! እኔ ምስኪን ሴት ነኝ፤ ሕይወቴን የምመራባቸው ጥቂት ዶሮዎች አሉኝ። ነገር ግን የቤቴ አጥር አጭር ስለሆነ ውሾችና ተኩላዎች እየዘለሉ ገብተው ዶሮዎቼን ይበሉብኛል... ስለዚህ ወይ አጥሬን አስረዝምልኝ፣ አለበለዚያ በቂያማ ቀን በአላህ ፊት እከስሃለሁ!” ኸሊፋው ደብዳቤውን ሲያነብ ሰውነቱ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ! ቅሬታዋን አልናቀውም ይልቁንም ወዲያውኑ ለግብፅ ገዥ (ለአዩብ ኢብኑ ሹረሕቢል) እንዲህ የሚል ትዕዛዝ ጻፈ፦ “ይህ ደብዳቤዬ እንደደረሰህ፣ ራስህ በአካል ወደ ፈርቱና ቤት ሄደህ ዶሮዎቿ ከአውሬ እስኪድኑ ድረስ አጥሯን በገዛ እጅህ ገንባላት!” በዚህም መሠረት ስለ አንዲት ዶሮ እንኳ አላህ ይጠይቀኛል ብሎ በሚፈራ ኸሊፋ ትዕዛዝ፣ የግብፅ ገዥ ራሱ ወጥቶ የድሃዋን ሴት አጥር ገነባላት! እንዴት ያለ ልብ ነው! እንዴት ያለ የአላህ ፍርሃት ነው! ሥልጣንን ለመግዛት ሳይሆን ለማገልገል፣ ሀብትን ለማከማቸት ሳይሆን የተቸገሩትን ለማስታገስ የተጠቀመ ታላቅ ሰው! የሰውን እንባ ብቻ ሳይሆን የአንዲትን ድሃ ሴት ዶሮዎች ጭምር በአደራነት የተመለከተ ኸሊፋ! ምንኛ ውብ አርአያ ነው! رحمه الله رحمة واسعة. #ሚሽካት የብርሃን ዱካዎች ይቀጥላል....⚖️✨ @aaumsu

    Текст
    Просмотры713
    Пересылки—
    Реакции10
    Комментарии—
  2. Просмотры504
    Пересылки—
    Реакции7
    Комментарии—
  3. Просмотры483
    Пересылки—
    Реакции13
    Комментарии—
  4. Просмотры450
    Пересылки—
    Реакции14
    Комментарии—

Новые посты

#7117Текст
Просмотры403−7%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#7115Фото
Просмотры4320%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#7114Фото
Просмотры4310%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#7112Фото
Просмотры411−5%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#7110Текст
Просмотры483+12%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#7109Фото
Просмотры450+4%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#7108Текст
Просмотры413−4%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—

Все посты