5ኪሎ ግቢ ምትማሩ ኒቃቢስት ተማሪዎች ጀምአው በአስቸኳይ ሊያናግራችሁ ስለሚፈልግ @Niqab_issueBot በውስጥ በኩል contact አድርጉን!! @aaumsu
Open in TelegramPosts of AAU - Muslim Students Union
«በየትኛውም የሕይወት ደረጃ ላይ ብትሆኑ፣ “ሙስሊሕ” (አስተካካይና ለውጥ አምጪ) ደረጃ ላይ መድረስ ይኖርባችኋል። ሙስሊሖች መሆን ትችላላችሁ፤ ለዚህ የሚበቃ ብዙ አቅምና ጸጋ አላችሁ!» — ሼኽ አዩብ ደርባቸው @aaumsu
Open in Telegram🎙 በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ ሼኽ አዩብ ደርባቸው በዳሩል-አርቀም 3ኛ ዙር የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ። @aaumsu
Open in Telegram🎙 «ዳሩል አርቀም» — ከመድረኩ የቀረበ ግጥም (በእስማኤል) ኢስላም የመጀመሪያውን ዩኒቨርሲቲ ሲመሰርት በትንሽ ቁስ በትንሽ ቤት በትልቅ ልብ ለግዙፍ fate እንዲህ ነበር የጀመረው የዲን ስፌት! ሄደ ተመመ ተመመ ምንጩ ውቅያኖስ ሆኖ አለምን አሰጠመ የጊዜው ሃያላን ጋራ ሰይፍ መዞ ገጠመ ጦር አንፈልግም ላሉትም ኪታብ ገልጦ አሰለመ ይህ ሁሉ ጁህድ ያ ሁሉ ማዕረካ ዳሩል አርቀም ነው ምንጩ ሲለካ በዚያች ጠባብ ቤት የቀሰሙት ደርስ መሪ አረጋቸው አለም ጫፍ ድረስ ያ ነቢ ነቢ አንተል ሙደሪስ ከይፈ ዩህዘሙ ማ ደረስተሁ ዳኢመን የፉዝ መን አቅወይተሁ! @aaumsu
Open in Telegram✨ የዳር አል-አርቀም 3ኛ ዙር (Cohort 3) ተመራጮች! ማሻአላህ! በዓላማ ለመማር፣ በስነ-ምግባር ለመምራት እና በኢኽላስ ለማገልገል የ6 ወራት ጉዟቸውን የጀመሩት የ3ኛ ዙር ተማሪዎች በከፊል እነሆ! አላህ ጉዟቸውን የተባረከና ለዲናቸውም ለኡማውም የሚተርፍ ያድርግላቸው! 🤲 🔥 ቀጣዩ ተራ የአንተ / የአንቺ ነው! @aaumsu
Open in Telegramየአላህን ቤት በመገንባት ጀነትዎን ይገንቡ! በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች አሚር አብዱልፈታህ ቃሲም፣ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርስቲው መስጂድ እንደሌለውና ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚሁ የጀመዓው ዓላማ ገቢ ማሰባሰቢያ ይሆን ዘንድ፣ ዐረብኛን በቀላሉ ለመማር የሚያስችል «ኑን — የዐረብኛ ቋንቋ ንባብና ጽሁፍ መማሪያ መጽሐፍ» ተዘጋጅቶ ቀርቧል። መጽሐፉን በመግዛትና የቻሉትን አስተዋጽኦ በማድረግ የዚህ ታላቅ ሰደቀቱል ጃሪያ ተካፋይ ይሁኑ! 🏦 CBE: 1000628156585 ፨Acc Name: Kotebe University Muslim Students Jemea @aaumsu
Open in TelegramየEMYC 3 ዋና ዋና ምሰሶዎች የEMYC የኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ጉዳዮች ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ሙሀመድአሚን ካሳው፣ ካውንስሉ የተመሰረተባቸውን ሦስት ዋና ዋና ምሰሶዎች በመድረኩ አብራርተዋል፦ 1. ወጣቶችን ማብቃት፦ ሙስሊም ወጣቶችን በእውቀት፣ በኢኮኖሚ እና በጠንካራ ትስስር ማጠናከር። 2. አንድነትን መገንባት፦ ወጣቶች ዲናቸውን፣ ማህበረሰባቸውን እና ሀገራቸውን ለማገልገል በአንድነት እንዲሰለፉ ማድረግ። 3. የትምህርት ልህቀት፦ ትምህርትን በንቃት በማሳደግ ብቁና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሙስሊም ወጣት ልሂቃንን ማፍራት። @aaumsu
Open in Telegram🎙 በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል (EMYC) የኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ጉዳዮች ምክትል ሥራ አስፈጻሚ እና የEHEMSU ፕሬዝዳንት ሙሀመድአሚን ካሳው እና በዳር አል-አርቀም 3ኛ ዙር የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ። @aaumsu
Open in Telegram«የምንሰጠው የምስክር ወረቀት ብቻ አይደለም!» የዳር አል-አርቀም ዋና ዳይሬክተር አረፋት በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከዚህ የ6 ወራት ሥልጠና በኋላ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ 20 ተጨባጭ ፕሮጀክቶች እንደሚጠበቁ ገልጸዋል። እውቀት ወደ ተግባር፣ ሥልጠና ወደ ተጨባጭ ለውጥ! @aaumsu
Open in Telegramየ6 ወራት የአመራር አካዳሚ — 180 ሰዓታት! ከዩኒቨርስቲ ትምህርት፣ ከረመዳንና ከሸዋል ጋር ተጣጥሞ በሳምንቱ መጨረሻ (ቅዳሜና እሁድ) የሚሰጠው የዳር አል-አርቀም 3ኛ ዙር 180 ሰዓታት በዚህ መልኩ ተከፋፍለዋል፦ 120 ሰዓት፦ ሴሚናሮችና የተግባር ልምምዶች 40 ሰዓት፦ በአማካሪ የታገዘ የማህበረሰብ የመስክ ሥራ 20 ሰዓት፦ የግል ንባብና Reflection @aaumsu
Open in Telegramከአንድ ካምፓስ ወደ ከተማ አቀፍ አካዳሚ! የዳር አል-አርቀም የዕድገት ጉዞ፦ • 1ኛ ዙር፦ 12 ተማሪዎች (ለ20 ሳምንታት) • 2ኛ ዙር፦ 40 ተማሪዎች • 3ኛ ዙር፦ 60 ተማሪዎች — ከAAU ብቻ ሳይሆን ከ18 የተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ! በ6 ኪሎ የተዘራው ዘር ዛሬ ከተማ አቀፍ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። አልሀምዱሊላህ! @aaumsu
Open in Telegramየኢስላም ብርሃን የተቀጣጠለው ነቢዩ (ﷺ) በዓላማ ትውልድን ከቀረጹባት ከትንሿ የአርቀም (ረ.ዐ) ቤት ነበር። ዛሬም ያንኑ አሻራ በመከተል፣ በAAU MSU እና EMYC ትብብር «በዓላማ መማር» በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የዳር አል-አርቀም 3ኛ ዙር (Cohort 3) የመክፈቻ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል! አላህ ጉዟችንን የተባረከና ፍሬያማ ያድርግልን! 🤲 @aaumsu
Open in Telegram📢 የዳር አል-አርቀም (Dar Al-Arqam) 3ኛ ዙር የመክፈቻ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል! በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (AAU MSU) እና በEMYC ትብብር «በዓላማ መማር» በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የዳር አል-አርቀም 3ኛ ዙር (Cohort 3) የመክፈቻ መርሐ ግብር አልሀምዱሊላህ በአላህ ፈቃድ በይፋ ተጀምሯል። አላህ መድረኩን የተባረከ፣ ጠቃሚ እውቀትና ኸይር የምንቀስምበት ያድርግልን! አሚን። 🤲 @aaumsu
Open in Telegram🌾 የብርሃን ዱካዎች ክፍል 15 " በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ" እስቲ አንድ ዓለም አስቡ፤ በከተማዋ ጎዳናዎችና መንደሮች ውስጥ አንድ አዋጅ ነጋሪ ከሙስሊሞች የግምጃ ቤት (በይቱል ማል) የተሞሉ የወርቅና የብር ከረጢቶችን ተሸክሞ እየዞረ በታላቅ ድምፅ ይጣራል፦ “ድሆች የት አላችሁ? ምስኪኖችስ የት ናችሁ? በዕዳ የተያዛችሁ ባለዕዳዎች የት አላችሁ? ማግባት እየፈለጋችሁ መህር (ጥሎሽ) ያጣችሁ ወጣቶችስ የት ናችሁ? ኑና ከአላህ ገንዘብ ውሰዱ!”... ነገር ግን የሚወስድ አንድም ሰው አልተገኘም! ይህ ትዕይንት በምናብ የተሳለ ሕልም ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ የኺላፋ ዘመን በሁለት ዓመት ከጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ በሙስሊሞች ምድር ላይ በገሃድ የታየ እውነታ ነበር::! ዑመር በየሀገሩ ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፈ ➤ ዕዳ ያለበት ሰው ሁሉ ዕዳው ከግምጃ ቤት እንዲከፈልለት ➤ ማግባት እየፈለገ አቅም ያጣ ወጣት ሁሉ መንግሥት እንዲድረው ➤ማረስ ወይም መነገድ ፈልጎ መነሻ ካፒታል ያጣ ሰው ከግምጃ ቤት እንዲሰጠው ➤እንዲያውም በእስልምና ጥላ ሥር የሚኖሩ (አህሉ ዚማ) ድሃና አቅመ ደካማ አይሁዶችና ክርስቲያኖች እንኳ ከግምጃ ቤት ቋሚ ደመወዝ እንዲቆረጥላቸው አደረገ ጥቂት ወራት እንኳ ሳያልፉ የመንግሥት ግምጃ ቤቶች በሐላል ገንዘብ ተትረፈረፉ፤ የአፍሪካ (ቱኒዚያ አካባቢ) ገዥ የነበረው የሕያ ኢብኑ ሰዒድ ለኸሊፋው የሚያስገርም ደብዳቤ ጻፈ፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! የዘካና የሰደቃ ገንዘቦችን ሰብስበን የሚሰጣቸው ድሆችን ብንፈልግ አንድም ድሃ አጣን! ታዲያ ገንዘቡን ምን እናድርገው?” ዑመርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በገንዘቡ ባሪያዎችን እየገዛችሁ ለአላህ ብላችሁ ነፃ አውጧቸው!” የዚህ ታላቅ ሰው ርኅራኄ ከሰው ልጆች አልፎ የምድር አራዊትንና የሰማይ አእዋፍን እስከመድረስ ደረሰ! ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን ያንን ዘመን ተሻጋሪ ቃል ተናገረ፦ ✨✨✨ “በሙስሊሞች ምድር ላይ ወፍ ተራበች እንዳይባል እህልና ጥራጥሬን በተራሮች ጫፍ ላይ በትኑ!” ✨✨✨ በእነዚያ ብሩህ ቀናት ውስጥ፣ ወደ ደማስቆ ቤተ-መንግሥት ከንጉሥ ወይም ከሚኒስትር ያልተላከ አንድ ልዩ ደብዳቤ ደረሰ... ደብዳቤው በግብፅ ምድር ከምትኖር “ፈርቱና አል-ሰውዳእ” ከተባለች አንዲት ድሃ ሴት የተላከ ነበር እንዲህ ስትል ጻፈች፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! እኔ ምስኪን ሴት ነኝ፤ ሕይወቴን የምመራባቸው ጥቂት ዶሮዎች አሉኝ። ነገር ግን የቤቴ አጥር አጭር ስለሆነ ውሾችና ተኩላዎች እየዘለሉ ገብተው ዶሮዎቼን ይበሉብኛል... ስለዚህ ወይ አጥሬን አስረዝምልኝ፣ አለበለዚያ በቂያማ ቀን በአላህ ፊት እከስሃለሁ!” ኸሊፋው ደብዳቤውን ሲያነብ ሰውነቱ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ! ቅሬታዋን አልናቀውም ይልቁንም ወዲያውኑ ለግብፅ ገዥ (ለአዩብ ኢብኑ ሹረሕቢል) እንዲህ የሚል ትዕዛዝ ጻፈ፦ “ይህ ደብዳቤዬ እንደደረሰህ፣ ራስህ በአካል ወደ ፈርቱና ቤት ሄደህ ዶሮዎቿ ከአውሬ እስኪድኑ ድረስ አጥሯን በገዛ እጅህ ገንባላት!” በዚህም መሠረት ስለ አንዲት ዶሮ እንኳ አላህ ይጠይቀኛል ብሎ በሚፈራ ኸሊፋ ትዕዛዝ፣ የግብፅ ገዥ ራሱ ወጥቶ የድሃዋን ሴት አጥር ገነባላት! እንዴት ያለ ልብ ነው! እንዴት ያለ የአላህ ፍርሃት ነው! ሥልጣንን ለመግዛት ሳይሆን ለማገልገል፣ ሀብትን ለማከማቸት ሳይሆን የተቸገሩትን ለማስታገስ የተጠቀመ ታላቅ ሰው! የሰውን እንባ ብቻ ሳይሆን የአንዲትን ድሃ ሴት ዶሮዎች ጭምር በአደራነት የተመለከተ ኸሊፋ! ምንኛ ውብ አርአያ ነው! رحمه الله رحمة واسعة. #ሚሽካት የብርሃን ዱካዎች ይቀጥላል....⚖️✨ @aaumsu
Open in Telegram