ያልሄድንባቸዉ መንገዶች ያላወቅናቸዉ እዉነቶች መኖር ስንጀምር ያላየችን እናት ደርሰንለት ያልመረቀን አባት ከኛ አልፈን የምናተርፋቸዉ ነፍሶች ሳቃችንን ማየት ያለባቸዉ ምቀኛዎች……… ገና አሉ……….. በኛ ፈጣሪ ሲመሰገን ድንቅ እኮነዉ ቆመዉ ሲሉ እንዴት ሆነላት ሲባባሉ እግዚአብሔር የሚጠራበት ስሙ የሚከብርበት ጐጆ ቀልሰን እኔ ና አንተ የምንኖረዉ የምናየዉ ህይወት አለን……….. ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в Telegram
የትዝታ ወልዴ ግጥሞች
የምወዳችሁ ይሄ ''የትዝታ ወልዴ ግጥሞች channel ነዉ'' ሀሳብ፣ አስተያት እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ @TIZITA21 Tiktok 👇 https://www.tiktok.com/@tizu422?_t=8sNmoeHUwqA&_r=1 youTube👇 https://www.youtube.com/channel/UC_EVyfbdSLjfKkMWZ4XGxeQ Instagram https://www.instagram.com/p/CZRrvITIgLR/?
Подписчики, 30 дней
28 нояб. – 29 нояб.+7 (+0,1%)
Показать таблицей
| Дата | Подписчики |
|---|---|
| 28 нояб. 2026 г. | 6 634 |
| 29 нояб. 2026 г. | 6 641 |
Новые посты
አስሬ ሰአቴን እያየዉ እረፍዶብኝ ስጠዳደፍ እግሮቹን ወደኃላ አመሳቅሎ ፍልስስ ብሎ መሀል ቦሌ አስፓልቱ ላይ ሽር ብትን የሚሉትን መኪኖች ወይ ደሞ ህይወቱን ያያል (ልጅነት በራሱ ሙሉነት ነዉ አደል?) የኔ ልዑል ነፃነቱ ኡፍ🥹🥹🥹 ለዚ ፎቶ ወይ ግጥም ወይ ስም ስጡት ❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в Telegramጥርስ አለኝ ተብሎ ሲሳቅ አይዋልም አይን እንባ ስላለዉ አይዘረገፍም ለሚሳቅለት ሰዉ ለእንባም ቦታ አለዉ ለመዉቀስም ጊዜ ለመልስም ቀን አለዉ አንዳንዴም…………. ፈገግ ተብሎ በጥርስ ይለቀሳል እንባ እያወጡ በአይንም ይሳቃል የሚያዉቁትን ሁሉ ……. የታዘቡት ሁሉ………. አፍ ስላለ ብቻ አይዘከዘክም የጭንቅ የምጥ ቀን ዘላለም አይዘልቅም አንዳንዴም………. በዝምታ ብቻ የልብ ይተረካል አዉቀነዋል ያልነዉ ስንተነፍሰዉ ቀን ቀንን ሲወርሰዉ እድሜያችን ሲያበስለዉ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ከገለባ ይቀላል ያለወቅቱ ሲሆን ያስተዛዝበናል። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в Telegramየናቴ መቀነት አደናቅፎኝ የአስቴር ዘፈኗ አሳስቶኝ እንጂ እሮጬ የመጣሁ ናፍቀሀኝ አደለም ስርህ የተገኘዉ ሀጥያቴነህ አንተ ሳግኝ ሳቅፍህ ሳይህ ሀሴት አደርጋለሁ ትንሽ እቆይና ደሞ እፀፀታለሁ መጥፎ ሱስ……. ናፍቆት ሀጥያተኛ ደሞ ፅድቄ እኮነህ …… ጭልምልም ያለብኝ ዙርያዉ ገደል ሆኖ ሀጥያት አደል ታዲያ መጨላለም ደምኖ ሲያጡህ መኮስመን ሲያግኙህ መግነን ናፍቆት ፃድቅ…….. ለክፋም ለደጉም ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ሳያዩ ከመዋል ሳይሻል አይቀርም የት ነህ? ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в Telegramትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Открыть в Telegramአንተና እኔ የአሁን እድሜ ላይ ኗሪዎች ዛሬን አጥተን አሁን ነጥተን ለነገ አሳ አስጋሪዎች በደጉ ቀን ሳሉ ለክፉ ቀን ብሎ ስንቅን መለቃቀም ፍቅርን መጠርቀም። ደሞ………. ተፈቃቅረን ተፈላልገን ተብሰልስለን ………ደሞ ተፈራርተን ምናባቱን ፍርሀት ከሞት መቼ ይበልጣል አሁን ላይ ተዋዶ አሁን እንደሚ’ኖር እራሱስ መች ያዉቃል እዚሁ ላይ ተፋቅረን …………. አሁን እንደሚሞት ለነገ ሳናስቀር ……………ትእቢታችን ሰብረን ና እንታረቅና ነገ በኛ ይቅና ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в Telegramከልቤ ላይ አንተን ማዉጣት ማለት…… ገቢዎች ሰምተዉኝ ያላመንኩበትን ጉዳዬን መቀልበስ ቀበሌ ገብቼ በደስታ መመለስ መርጌታ ከሚል ቻናሎች ላይ መዉጣት የተበደርኩትን ስመልስ በብቃት ከ crash ኤ ጋራ እራት እንደመዉጣት ለእናቴ በአደራ ሚስጢር እንደማዉራት አንተን መርሳት ለኔ…… አለቃዬን መዉደድ እብድ ሰዉ ማሳበድ ዛፍና ፓል መግጨት ተምሬ በድፍረት ያልፍልኛል ማለት እርሺኝ ብሎ ማሰብ……… ወፍ በእግሯ ስትሳብ ተኩላ በዉበት ሲሳብ ቴሌ በትክክል ሲያመጣልኝ ሂሳብ እኒህ ሁሉ ተቀይረዉ ምድር ቀዉጢ እስካልሆነች- አንተን መርሳት ዉዴ የሚቻል አደለም። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄@semetnbegtmИскусство6,05 тыс.
ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)@huluezihИскусство7,49 тыс.
Riyaad Raayyaa@dhangaa_walalooИскусство4,66 тыс.
የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች@eliasshitahunИскусство11,3 тыс.
የሄኖክ አሸብር ግጥሞች እና ወጎች@henokashebirИскусство3,88 тыс.
ግጥም 🇪🇹@kidapoimИскусство3,8 тыс.
ግጥምና ወግ Eyob Z Mariam@poeteyobzmariamИскусство3,02 тыс.
የፊሊሞን ደብዳቤዎች 🧣@filimonhappyИскусство2,54 тыс.