Кабинет
የፊሊሞን ደብዳቤዎች 🧣

የፊሊሞን ደብዳቤዎች 🧣

. የሆነ ቀን እንሄዳለን…ባንፈልገውም እና ምርጫችን ባይሆንም መሄዳችን የግድ ነው…ሁሉን ነገር እዚሁ ትተን ነው እምንሄደው…አንብበን ያልጠገብናቸውን መፅሐፍቶቻችንን ፣ አውረተን ያልጠገብናቸውን ጓደኞቻችንን ፣ አደምጠን ያልጠገብናቸውን ሙዚቃዋቻችንን ፣ የኖርንላቸው እና የኖሩንን ቤተሰቦቻችንን ትተን የሆነ ቀን እንሄዳለን…በቃ እንዲሁ ሁሉን ነገር ትተን እንሄዳለን… Cross👉 @itsmehappy

Юзернейм
@filimonhappy
Категория
Искусство
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики2 540+1 за 1 день
Просмотров на пост, 7 дн.414−56,1% к пред. 7 дн.
ERR16,30 %за 7 дней

Подписчики, 30 дней

28 нояб. – 29 нояб.+1 (0%)

Показать таблицей
ДатаПодписчики
28 нояб. 2026 г.2 539
29 нояб. 2026 г.2 540

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
8 нояб. 2026 г.1 660
15 нояб. 2026 г.1 170
16 нояб. 2026 г.1 030
18 нояб. 2026 г.935
21 нояб. 2026 г.633
22 нояб. 2026 г.646
26 нояб. 2026 г.228
28 нояб. 2026 г.137

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры1,66 тыс.
    Пересылки—
    Реакции33
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры1,17 тыс.
    Пересылки—
    Реакции14
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры1,03 тыс.
    Пересылки—
    Реакции21
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры935
    Пересылки—
    Реакции18
    Комментарии—

Новые посты

#532Текст

Переслано из ቅዳጅ ገፆች📜

ርዕስ አልተገኘለትም(ርዕሱ ነው) ነጭ ግድግዳ የተባለ ነገር እያስጠላት መጥቷል።ሞት ሞት የሚሸት ክፍል መታጎሯ ለማን ጥቅም እንደሆነ አይገባትም ፤ለእርሷ ወይስ ለእነሱ?ሁሌ ወደ ክፍሏ ሱክ ሱክ እያሉ ወጣ ገባ የሚሉት ሰዎች ነጭ የለበሱ አውሬዎች ይመስሏታል፤ልክ እንደዛች ሴት... ዛሬም እንደ ትናንቱ ሁሉ አንድ ነጭ ለባሽ ፍጥረት ፊት ለፊቷ ተቀምጧል። "እስኪ ስለቀንሽ ነገሪኝ።" መነፅሩን ገፋ እያደረገ ጠየቃት። "ቀኔ...ቀኔ...ቆንጆ ስጋ በስሱ የተቆረጠ..." ለራሷ በሚመስል ድምፅ ዝም ብላ ታወራለች።ዶክተሩ አንዳች ነገር ቸከቸከ እና በድጋሚ ቀና አለ "አሌክሳንድራ! እባክሽ ከእኔ ጋር ሁኝ" ትዕዛዝ ይሁን ልምምጥ ባልገባው ድምፅ ተናገረ።እርሷም ቀና ብላ አየችው።ጭንቅላቷን በእሺታ አወዛውዛ ዞር ልትል ስትል መልክ አየች፤የሰው ሊያውም የሴት፤ሌላ የትም አደለም እዚያው መነፅሩ ውስጥ።የት እንደምታውቃት ለማስታወስ ሞከረች።ፀጉሯ ሊተኮስ እንደተሰየመ ደረቅ ሳር ቆም ቆም ያለ፤ፊቷ ከአዲስ ወረቀት የነጣ ሴት ፊት።የት ነበር ምታውቃት...?ዶክተሩ በፅሞና ሲያያት ቆየና "ምን እያሰብሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፤የምርም ጓግቶ ነበር። "መነፅርህ ውስጥ ሴት አየሁ።ማን ናት እያልኩ ነበር።ዶክተርዬ አቃታለሁ መሰል..."ምታስብ መስላ ዝም አለች።ከአፍታ በኋላ ፍለጋው ቀንቷት ይሆን አድክሟት ቀና ብላ እርሱኑ ማየት ጀመረች።እርሱም ምናልባት ከወራት በኋላ የተለወጠ ነገር ያለ ስለመሰለው መናገር ቀጠለ። "እርሷ አሌክሳንድራ ስቲቨንስ ትባላለች።ሀርላንድ የሚባል ባል እና ክርስቲ ምትባል ቆንጅዬ ልጅ ነበረቻት።ባሏ የሚሰራው በቤት ሽያጭ ጉዳዮች ነበር።እርሷ ደግሞ አራሷን ክርስቲን ይዛ የቤት እመቤት፤ውብ ወይዘሮ ነበረች። እጅግ ደስተኞች ነበሩ።ከአመት አመት በፍቅር እንደ አዲስ እፍ የሚሉ ቤተሰቦች..."ፊቷን አስተዋላት።ጉንጯን እጆቿ ላይ አስደግፋ በተመስጦ ነበር ምታዳምጠው።ቀልቡ ጥሩ ነጥብ ላይ እንደደረሰ ሹክ አለው።ቀጠለ "...የሆነ ቀን ላይ ተነስታ ማንም ያላሰበውን አደረገች።ባሏን፤ የልጀነት ምኞቷን፤ስለ ፍቅሩ የመነነችለትን አዳሟን...ገደለችው።ቆራርጣ ማቀዝቀዣ ውስጥ አስቀመጠችው።...ትንሿ ክርስቲ ነገሩ ሳይገባት ከማልቀስ በቀር ምንም አላለችም።አሌክሳንድራም ልጇን አንስታ..."ይሄን እንዳለ አቆመና ለደቂቃዎች ሁኔታዋን አጤነ።ፊቷ ከበፊቱም ይባስ ነጥቶ እና ገርጥቶ ነበር።ጥርሷን ምታኝከው ይመስል አስሬ ሰቅጣጭ ድምፅ ያወጣል።ከእግሯ እንቅጥቃጤና ከክፍሉ ዝምታ ጋር ተዳምሮ ክፍሉ አንዳች ደመናን ያረገዘ መሰለ።ያቋረጠውን አስታውሳ ቀዝቃዛ ንግግር ከፈተች። "...ካሪን አንስታ አይዞሽ የስጋ መረቅ ልሰራልሽ ነው አለቻት።...ፖሊሶች ከሰዓታት በኋላ ስለ ባሏ መሰወር ከጎረቤት ሰምተው ለፍለጋ በራቸውን አንኳኩ..."ማልቀስ ጀመረች።ከእምባዋ ጋር የፀፀት፤የብቸኝነት፤የበደል ስሜቷን አብራ አነባችው።ዶክተሩ ወራት የለፋበትን ውጤት በማግኘቱ ውስጥ ውስጡን ደስ ቢለውም የአሌክሳንድራ ሁኔታ ግን ወደ ጥልቅ ሀዘን ልቡን ለመክተት ብዙ አልፈጀበትም።ስለማፅናናት ቢያስብም ከግል ስሜቱ ስራውን አስቀደመ። "ምክንያቷ ምን ነበር ብለሽ ታስቢያለሽ አሌክሳንድራ? ጥርጣሬ፣ጥላቻ፣ቅናት፣ቂም ወይስ ንዴት ነበር በአንዲያ ፍቅሯ ላይ ጨክና ቢላ እንድታሳርፍ ያረጋት?" ምንም አላለችም ከልቧ አነባች ልቧ ደምን አነባ።የምድር ጫፍ ላይ ብቻዋን ያለች መሰላት።በድኗ ቀረ።ልቧ ሞተ። ለሰዓታት ተንሰቀሰቀች።ዶክተሩ ከነበረበት ሳይነሳ እስከምትጨርስ አብሯት ነበር።ከጎኗ መለየት አልቻለም ነበር።ድንገት"ወደ ክፍሌ እንዲወስዱኝ ንገራቸው" ለመቃወም ድፍረት አልነበረውም።ነርሷ እና አንዲት ፖሊስ መጥተው ወሰዷት። ከቀናት በኋላ ራሷን ማጥፍቷን ሰማ።የአልጋዋን ብረት ነቃቅላ ራሷን ልክ እንደ ባሏ ቆራርጣ ተገኘች።በባሏ ያረፉት እጆቿ ለእራሷም መጥፊያ አረገቻቸው። ከአመታት በኋላ ዲያሪዋ ተገኘ።ሙሉ ህይወቷ ነበር የተተየበበት።ከባሏ ሞት በፊት ከባድ ድብርት ውስጥ መግባቷን ፅፋ ነበር።ስለ መሞት ማስቧም ተገልጿል።የገደለችው ለት የፃፈችው ገፅ አጭር ነበር። "ውድ ማስታወሻዬ ዛሬ በስሱ የተቆራረጠ የስጋ መረቅ አምሮኝ ነበር።ሀርሊ እንዲገዛልኝ ስጠይቀው ስለ ገንዘብ ችግር አውርቶ ተጣላን እና መታኝ።እኔም ጭንቅላቱን በጠርሙስ ብዬው ወደቀ።ከዛም ያማረኝን ስጋ በላሁ።ካሪም ጠጥታለች ግን አልወደደችውም መሰል ካጠጣኋት በኋላ ተኛች፤አልተነፍስ አለች ደግሞ.....ሰው እያንኳኳ ነው መጣሁ..." ይል ነበር ልጇንም የገደለቻት እርሷ ነበረች? ለዚ ርዕስ ይሰጣል?ምንስ ተብሎ? ✍️🏼ቃል https://t.me/Piece_of_pages1 https://t.me/Piece_of_pages1

Открыть в Telegram
Просмотры137−83%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#526Фото

. ምን ሆነ መሰለሽ… አጫጭር ቀሚስ…ለእርቃን ምንም ያልቀረው የለበሱ…እንኳን ለመንካት ለማየት የሚያሳሱ እንስቶች ቤቱን ሞልተውታል…እኔም ያዛዝኩት ሳያልቅ በናት ባናቱ ይህን አልኮል እጠጣዋለው…ካጠገቤም ያለ ዛሬ አይቻቸው እማላውቃቸው ሴቶች ተቀምጠዋል…ከምን ተነስተን እዚህ እንደደረስን ባላውቅም ስለ አንቺ እያወራን ነው… እናማ ምን ሆነ መሰለሽ… እንደ ሰዉ እኮ ጭዋታ እጀምራለው…ስለ ብዙ ነገር ማውራት እና ስሜቴን መግለፁ ፈልጌ ንግግሬን እጀምራለው ....ከዛ እንዴት እንዳሆነ ሳላውቀው ወሬ ሁሉ ስለ አንቺ ይሆናል…ምን አገናኘው ከማወራው ጋር?…እኔጃ! …እንቺን እዚህ ላይ ምን አመጣሽ…እኔጃልሽ !… እና ምን ሆነ መስለሽ… ያ ድሮ የምታውቂው ልቤ…አሁን ላይ ደንዳኖል…ምንም የማያስከፋው እና እማያስደነግጠው አልት ሆኖል…የሰው መሄድ እና መምጣት እማይደንቀው…ብቻ ምን ሆነ መሰለሽ…አንቺ ፍለጋ የወጣው ልቤ የትም ነው የቀረው…የትም !… ብቻ ምን ሆን መሰለሽ …………………   ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🤍 Telegram @filimonhappy 🤍

Открыть в Telegram
Просмотры621−21%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#523Голосовое
Просмотры935+19%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#515Фото
Просмотры1 170+49%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#514Фото
Просмотры1 660+111%к среднему
Пересылки—
Реакции33
Комментарии—
#513Текст

.      " አ ት ወ ደ ኝ ም …ግን አደል ? "    ሁሉም ስሜቶች ፊትዋ ላይ ይነበባሉ…ተስፋ መቁረጥ፣ አለመፈለግ፣መረሳት እና አለመወደድ…ያ የማይለያት ሳቋም የለም…ይህን ያህል ባዶ እንደደረኳት ግን አለወኩም ነበር…ከቆመችበት እጅዋን ይዤ አስቀመጥኳት…ግራ እጅዎንም እ ና ቱ ገበያ ስትሄድ ግጥም አደርጐ እንደሚይዝ ህፃን ይዤ አወራት ጀመር…       " ቃላቶቼን ለማይገባቸው ሰዎች ሰጥቼ ከጨረስኳቸው ቡኋላ መጠተሽ እኮ ነው…እራሴን ድጋሜ ለአዲስ ሰው ማስተዋወቅ አሁን ላይ ዳገት ስለሚሆንብኝ እኮ ነው ስለ እኔ ማላወራሽ…ከሄዱት ጋር የሄደ ልቤ እኮ ነውም ጠላቴ…እንጂ እንቺ እሚገባሽ ከዚህ በላይ …ትናንት ላይ ያልሆንኩትን መሆኔ ነው እኮ አሁን ላይ የነበርኩትን እንዳልሆን ሚያደርገኝ…መንገድ ዳር እንደተሰጠ ሽሮ ሁሉም እየዘገነ እንደሚያልፈው ልክ እንደዚያ ልቤን ብዙዎች ዘግነው ልብ አልባ አድርገውኝ እንጂማ አ ን ቺ እሚገባሽ ብዙ ነው…እ ወ ድ ሻ ለ ው  ብልሽ ልብሽ አይደግጥም ብዬ ነው እንጂማ የምር ነው ምወድሽ…ተዝግኖ በተረፈኝ ልቤ እወድሻለው…ንፋስ ሰማይ ላይ ወስዶ እንደሚያንከራትተው ሚስኪን ፌስታል ነው የኔ ልብ ለአንቺ…"       ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ      telegram @itsmehappy

Открыть в Telegram
Просмотры2 880+266%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—

Все посты

Связи