"ኢ-ፍትኃዊነት ፈጣሪን የመስደብ ያህል ታላቅ ኃጢአት ነው:: ምክንያቱም የተፈጥሮ ሕግ ምክንያታዊ ለሆኑ ፍጥረታት ይህንን ሥርዓት ሠርቷልና። ይኸውም እንደየባሕርያቸው እርስ በርስ ሊረዳዱ እንጂ ሊጎዳዱ አይደለም። ስለዚህም የተፈጥሮን ፈቃድ የሚተላለፍ ሰው አምላኩን ይሳደባል።" "ነገሮች እንዲሆኑ ወይም እንዳይሆኑ ከመጸለይ ይልቅ፣ ምንም ነገር ቢሆን እንዳትፈራ፣ እንዳትመኝ ወይም እንዳታዝን ለምን አትጸልይም? አምላክ ሰዎችን መርዳት የሚችል ከሆነ በዚህ መንገድ ሊረዳን አይችልምን? ምናልባት “እነዚህን ነገሮች አምላክ በእኔ ስልጣን - ስር አድርጓቸዋል” ትልም ይሆናል᎓᎓ ታዲያ በቁጥጥርህ ስር ያልሆነውን ነገር ለመለወጥ እንደ ባሪያ ወይም እንደ ለማኝ ከምትማጸን፣ በስልጣንህ ስር ያለውን በነጻነት መፈጸም አይሻልህምን?" “ይህ ነገር ሁሌም ይገርመኛል፦ ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ይልቅ አብልጠን እንደምንወድ የታወቀ ነው። ሆኖም ስለ ራሳችን ከምናስበው ይልቅ ሌሎች ስለ እኛ ስለሚያስቡት እንጨነቃለን። መልአከ ወይም ጠቢብ ሰው ተገልጦን በልብህ የምታስበውን አትደብቅ፤ ወዲያውኑ ጩኸሀ ተናገረው ቢለን፣ አንዲት ቀን እንኳ አንዘልቅም ነበር። ለራሳችን ካለን እወነታኝነት ይልቅ የሌሎች አስተያየት ያንን ያህል ይገዛናል።” “ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ለራስህ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ዛሬ የማገኛቸው ሰዎች ጣልቃ ገቦች፣ ምስጋና ቢሶች፣ ትዕቢተኞች፣ አታላዮች፣ ምቀኞችና ርሀራሄ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲህ የሆኑት መልካሙን ከክፉው መለያት ስለማይችሉ ነው። እኔ ግን የመልካምን ነገር ውበትና የክፉንም ነገር አስቀያሚነት አይቻለሁ፤ ስለዚህ አንዳቸውም ሊጎዱኝ አይችሉም።” "እውነተኛ እድለኛነት ማለት፣ ውሸትን፣ ግብዝነትን፣ ትዕቢትን ሳያውቁና ሳይቀምሱ ከዚህ ዓለም መሰናበት ነበር፡፡ ነገር ግን “ቀጣዩ ምርጥ ዕድል” እነዚህን ክፉ ነገሮች ከተጠየፍክ በኋላ መሞት ነው:: ወይስ ከክፋት ጋር ለመተኛት ወስነሃል? ልምድህ እንኳ እንደ ቸነፈር በሽታ እንድትሸሸው አላስተማረህምን? ምክንያቱም የአእምሮ ክፋት ከተበከለ አየር ከሚመጣ በሽታ ይልቅ እጅግ የከፋ ቸነፈር ነውና። የሥጋ በሽታ ሕይወትህን ብቻ ያጠፋል፤ ይህኛው ግን ሰውነትህንና ሰብአዊነትህን ይገድላል።" Marcus Aurelius 📖Meditation
Открыть в Telegram
ግጥም ፍቅር ቅኔ
ለማንኛዉም አስተያየት👉 @hollynba ግጥም ቃላትን በንዝረት በምትሃት በዉበት እና በእዉነት አበጃጅቶ እፈጥርልናል ቁስልን ማከም ተስፋን ማለምለም አቅም አለዉ ፍቅር ዉበት እንደ ተመልካቹ እንደሆነዉ ሁሉ ፍቅርም በዚዉ ሊገለፅ የሚችል በተለያየ አንደበት በተለያየ ትሩጋሜ ሊገለፅ የሚችል ረቂቅ የፈጣሪ ልግስና ነዉ ቅኔ ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ።
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 29 окт. 2026 г. | 489 |
| 30 окт. 2026 г. | 497 |
| 31 окт. 2026 г. | 455 |
| 2 нояб. 2026 г. | 468 |
| 3 нояб. 2026 г. | 510 |
| 6 нояб. 2026 г. | 578 |
| 7 нояб. 2026 г. | 607 |
| 12 нояб. 2026 г. | 476 |
| 14 нояб. 2026 г. | 427 |
| 15 нояб. 2026 г. | 399 |
| 17 нояб. 2026 г. | 327 |
| 18 нояб. 2026 г. | 310 |
| 21 нояб. 2026 г. | 208 |
| 22 нояб. 2026 г. | 181 |
| 23 нояб. 2026 г. | 139 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры607Пересылки—Реакции4Комментарии—
- 02Просмотры578Пересылки—Реакции4Комментарии—
- 03Просмотры510Пересылки—Реакции5Комментарии—
- 04Просмотры497Пересылки—Реакции1Комментарии—
Новые посты
ንስር አሞራ እና አንተ ... አንቺ ... እኔ ... 🌏 ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ... #የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ... #ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ... #ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል። እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። ♦ 1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ? ♦ 2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ? የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል። ፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። ፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡ ፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። ፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። 🔖 ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ 🔥 ወዳጄ ሆይ:- 🔥 ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል። ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ... በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ... 🍋 ፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ... ፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ... ••• ♦ አስተውል ... ♦••• ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ... ፩ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል። ፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ። ፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ። ፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ። ፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል። ሲጠቃለል ... 🔖🔖🔖 አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል። ♥ " . . " " 😉 @hollypoem 👕👉 @hollypoem 👖 @hollypoem
Открыть в TelegramEsubalew etayew #ትሁት #hopeentertainment #የ_ቦታ #ሙዚቃ https://youtube.com/shorts/C8UtgCca7WI?si=3NEbjvBIqlepAj92
Открыть в TelegramSuccess has 6 ingredients 1: Goal 2: discipline 3: consistency 4: focus 5: Patience 6: Never give up
Открыть в Telegramበመንገድ ያጋጠመን ታታሪዉ የልጅ ገበሬ🥰 #brave #ገበሬ #journey #nature #travel https://youtube.com/shorts/LBdCnLN5GE8?si=cP9EZPuvqCyO3W-S
Открыть в Telegramጥርስ አለኝ ተብሎ ሲሳቅ አይዋልም አይን እንባ ስላለዉ አይዘረገፍም ለሚሳቅለት ሰዉ ለእንባም ቦታ አለዉ ለመዉቀስም ጊዜ ለመልስም ቀን አለዉ አንዳንዴም…………. ፈገግ ተብሎ በጥርስ ይለቀሳል እንባ እያወጡ በአይንም ይሳቃል የሚያዉቁትን ሁሉ ……. የታዘቡት ሁሉ………. አፍ ስላለ ብቻ አይዘከዘክም የጭንቅ የምጥ ቀን ዘላለም አይዘልቅም አንዳንዴም………. በዝምታ ብቻ የልብ ይተረካል አዉቀነዋል ያልነዉ ስንተነፍሰዉ ቀን ቀንን ሲወርሰዉ እድሜያችን ሲያበስለዉ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ከገለባ ይቀላል ያለወቅቱ ሲሆን ያስተዛዝበናል። By ትዝታ ወልዴ @hollypoem
Открыть в Telegram( ሠርግና ሞት ) ========== ይኸው ሆይሆይታ ነው ይኸው እስክስታ ነው ዳንኪራው ደማምቋል ዛሬ እናንተ መንደር አንቺ ስትዳሪ .. የእኔ ልብ ያለ አዛኝ ያለ አልቃሽ ሊቀበር እሰይ ያለም ይሁን ኑሮሽ በሳቅ ይሙላ የኔም ዕምባ አይጉደል ሠርግና ሞት ወትሮስ አይለዩም አይደል ! by kiyorna @hollypoem
Открыть в Telegram"ዱርየ" የሚለውን ማዕረግ like እንደ "ሎሬት" ቆጥሮ በኩራት አፉን አጣሞ የሚያወራ generation ተፈጥሯል! Smoking cigarettes እና ጭስ በገመድ መሳብ, or ቅጠል መበጠስ is not nuclear physics bro. it's literally just basic self-destruction packaged as "gangster aesthetics." ገራሚው ነገር፤ ትክክለኛውን Hard work እና real knowledgeን ትቶ፣ እነዚህን tivial and basic bad habits እንደ "cool lifestyle" ማየት ፍጹም የmindset ኪሳራ ነው። ማዕረጉም አያኮራም ...✌️
Открыть в Telegramቃሌን አልሰጠሁም በትንሿ ጎጆ ፍቅርን ብንቀልስም ልባችን ተዋዶ ፍቅራችን ቢበዛም ጨለማን ለማጥፋት ሻማ ብናበራም ቃሌን አልሠጠሁም ቃሌን አልሰጠሁም አረሳህም ብየ ያንተን ስም አንስቼ መሀላንም ምየ ፍቅራችን ቢበዛም ከሰማይ ቢገዝፍ እምነት ከሌለው ግን ፍቅር ይሆናል ትርፍ አዎ ልድገምልህ ቃሌን አልሰጠሁም ፍቅራችንን ብየ ምየ አልተገዘትኩም እናም የኔ አበባ የልቤ አንድ አካል ለፍቅራችን ስትል እምነትን ይዘህ ዋል ግን እስከዚያው ቃሌን አልሰጠሁም ያንተን ስም አንስቼ መሀላም አልገባም 💔💔💔💔💔 ✍️ሀዩ
Открыть в Telegramያ...ወጣት ከጉባኤው መሃል.. ከአዳራሹ ጥግ ከምዕመኑ ጀርባ አንድ ወጣት ይታያል ከራሱ ያደባ ነፍስ አልባ ገላ መንፈስ እየጠማው ከህዝቡ ነጠላ እግዚያር አልባ በድን ገላን ይዞ የሚፍጨረጨረው ከምዕመኑ ጋራ ስሜት ለመጋራት፣ በራሱ ዓለም ነው ወኔን የሚጭረው በድን ይዞ አካል ስጋ የእግዚያር ዓለም ለሱ መቼ ነጋ አ..ል..ነ..ጋ..ም። እዚያ ከመቅደሱ ስግዱ ሲል ድንገት፣ ዲያቋኑ ተነስቶ ሁሉም ሰው ሲያለቅስ፣ ለነፍሱ ተደፍቶ የመንፈሱ ሙላት፣ በቅጡ ያልገባው እንዴት? ለምን? የሚል ለነፍስ የሚነባው አንድ ወጣት ይታያል፣ ከምዕመኑ ጀርባ ሃሳብ የሚንጠው፣ ከራሱ ያደባ። ትላንት የነበረው... ሁሉም እልል ሲል፣ ታሪኩን እያወሳ ትላንቱ የጠፋው፣ እራሱን የረሳ አምላኩን እንኳን ማወደሻ ሽርፍራፊ ትላንት፣ ታሪክ ማስታወሻ ከልቡ ከረጢት፣ ፈትቶ ሚበረብር አንድ ወጣት ይታያል ማነኝ በሚል ጭጋግ፣ ነፍሱ ምትሸበር። እዚያ ከመቅደሱ ቅዱስ መንፈስ መጥቶ ሲያርፍ በነፍስ አካል ሲርከፈከፍ ህዝቡ ሃሴት ሲጭር፣ ሰማይ ሲሄድ በመንፈሱ አንድ ወጣት ይታያል ብቻውን የቀረ፣ እዚያው ከመቅደሱ። እራሱን የታዘበ አካል ስጋው የለዘበ ማነኝ ያለ ገላ፣ ያዘነ ከነፍሱ መንፈሱን የገፋ፣ የቀረ ከራሱ ከመስኮቱ ታክኮ፣ መገኘቱን ያጣ አንድ ወጣት ይታያል መሄድ የሚቃጣ። ¶ መሽቶ ነግቶ፣ በሳምንቱ የሱ ስፍራ ከመስኮቱ አካል ስጋው እያነባ ሰውነቱ' ከሰው ጀርባ አንድ ወጣት ይታያል፣ እግዚያሩን ሚጠብቅ እስከ በደል ጉድፉ ሙት አካል ነኝ ያለ እስኪጎድል ሰልፉ " እስከመቼ ሲሉት እስካገኘው ያለ አንድ ጭፍርር ወጣት መስኮቱ ጋር አለ። እስከ መች? እስካገኘው By semere @hollypoem
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ግጥም የልብ ድምፅ@yenegitiem21Искусство2,2 тыс.
Sona walaloo@bashannanuufИскусство1,87 тыс.
ግጥም 🇪🇹@kidapoimИскусство3,81 тыс.
🕯️የህላዌ ብዕር✍️@poem_hiweИскусство1,25 тыс.
የሶላ ደብዳቤ@ammelakulettersИскусство1,12 тыс.
Walaloon Jaalala@walaloon_jaalalaИскусство35,9 тыс.
альфия творит | Художник Шайхулова Альфия@alfiatvoritИскусство2,26 тыс.
комикс "чудо"@komixchudoИскусство2,26 тыс.